DBU የተማሪዎች ህብረት!!
2.82K subscribers
616 photos
9 videos
103 files
146 links
የደ/ብ/ዩ የተማሪዎች ህብረት የመረጃ አውታር !!!
Download Telegram
ማሳሰቢያ
ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ እና በቀን 18-19/03/2017 ዓ.ም ለተጠራችሁ አዲስ ተማሪዎች በሙሉ ዩኒቨርስቲዉ ከዚህ በፊት ሲያደርግ የነበረዉ መነሀሪያ እና ጠባሴ ላይ የነበረ የመኪና ምደባ ባሁኑ ወቅት ባለመመደቡ ሁሉም አዲስ ገቢ ተማሪዎች ዩኒቨርሰቲው ቅጥር ግቢ እስከምትገቡ ድረስ ምንም አይነት የተመደበ እና ሀላፊነቱን የሚወስድ አካል እንደሌለ ተገንዝባችሁ እራሳችሁን እንዲሁም ንብረታችሁን እንድትጠብቁ ለማሳወቅ እንወዳለን።
የተማሪዎች ህብረት ጽ/ቤት
ለመላው የደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በሙሉ በቤተ-መፃህፍት (library) ዙሪያ ከሚመለከታቸዉ የሁሉም ቤተ-መፃህፍት ሀላፊዎች እና አስተባባሪዎች ጋር በቀን 12/03/2017 ዓ.ም ባደረግነው ስብሰባ እስካሁን ድረስ በተማሪም ሆነ በሰራተኛ ሲፈጠሩ የነበሩ የቤተ-መፃህፍት ህግና ደንብ የጣሱ ክፍቶች በያዝነው የትምህርት ዘመን እንደማይኖሩ እንዲሁም ለመማር ማስተማር ሂደቱ ሁላችንም የበኩላችንን ድርሻ እንደምንወጣ ስምምነት ላይ ደርሰናል ።

የተማሪ ህብረት ጽ/ቤት
እንዴት አመሻችሁ ዉድ ተማሪዎቻችን ዛሬ በግቢያችን የተፈጠረዉን የመብራት መቆራረጥ በሀገር ደረጃ መሆኑን ተገንዝባችሁ የግቢው ጀኔሬተር የሚበራዉ ዶርም ላይ ስለሆነ እራሳችሁን ከተለያዩ ነገሮች ለመጠበቅ በጊዜ ወደ ዶርም እንድትገቡ እናሳስባለን ።

የተማሪዎች ህብረት ጽ/ቤት
https://t.me/DBUstudent
https://t.me/DBUstudent
ውድ ተማሪዎቻችን ከላይ በተጠቀሱት የውድድር ዘርፎች ላይ መወዳደር እችላለው የምትሉ በተጠቀሰዉ ቀን ቢሮ በአካል በመገኘት እየመጣችሁ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን።

የተማሪዎች ህብረት ጽ/ቤት
ይህ ከላይ የምትመለከቱት ምስል በማህበራዊ ድህረገጾች ላይ እየተሰራጨ የሚገኝ ሀሰተኛ መረጃ መሆኑን አውቃችሁ እራሳችሁን ከእንግልት እንድትጠብቁ እናሳስባለን።

የአቅም ማሻሻያ(Remidial) ተማሪዎች ትክክለኛ የመግቢያ ቀን ሲታወቅ የምናሳውቃችሁ ይሆናል።
+ለበለጠ መረጃ የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ትክክለኛውን የፌስ ቡክ ድህረገጽ ተከታተሉ !
https://www.facebook.com/dbu.edu.et

የተማሪዎች ህብረት ጽ/ቤት
እንኳን ደስ አላችሁ

በዛሬው ዕለት የጂሲ ሰለብሬሽን (GC celebration ) የምታከብሩ የዩኒቨርስቲያችን ተማሪዎች በሙሉ እንኳን አደረሳችሁ ።

ከምንም በላይ ከፊታችሁ እየተቃረበ ያለውን የመውጫ ፈተና (Exit Exam) በተሻለ ውጤት ለማምጣት ከወዲሁ ሳትዘናጉ እየተዘጋጃችሁ እንድትቆዩ ስንል ቤተሰባዊ ምክራችንን ለማስተላለፍ እንወዳለን።

የተማሪዎች ህብረት ጽ/ቤት
https://t.me/DBUstudent
አስቸኳይ ማስታወቂያ
በሰዐቱ ስትገኙ ማስረጃ መያዛችሁን እንዳትረሱ።

የተማሪዎች ህብረት ጽ/ቤት
"ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።" ሉቃ 2:11
ለመላው የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት(ለገና) በዓል በሰላምና በጤና  አደረሳችሁ አደረሰን!!!
በዓሉ የሰላም የፍቅር የመተሳሰብ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን።
       
ውድ ተማሪዎቻችን በዓሉን ስታከብሩ በፍቅርና በመተሳሰብ እንዲሁም እራሳችሁን ከተለያዩ ጎጂ ነገሮች እየጠበቃችሁ እንድታከብሩ እናሳስባለን።


             መልካም በዓል!!!🙏🙏



                    የተማሪዎች ህብረት
Midterm exam schedule for freshman students👇
ለሁሉም የአንደኛ አመት ተማሪዎች በሙሉ የፈተና ፕሮግራማችሁ ይህን ይመስላል ስለዝህ በሰአቱ በመገኘት ፈተናችሁን ውሰዱ ምንም የሚያስፈራ ነገር የለውም ድሮ ታች ክላስ ስትፈተኑ እንደነበረው አድርጋችሁ ውሰዱት እንዳትደናገጡ በርቱ በተረፈ መልካም ፈተና!!!
ክፍት የስራ ማስታወቂያ!!! ለሚመለከታችሁ የስራ ፈላጊዎች በሙሉ እነሆ የስራ እድል ተመቻችቶሎታ ይመዝገቡና እድሎን ይሞክሩ አስራት ወልደየስ ጤና ስይንስ ኮሌጅ