DBU የተማሪዎች ህብረት!!
2.81K subscribers
620 photos
9 videos
103 files
148 links
የደ/ብ/ዩ የተማሪዎች ህብረት የመረጃ አውታር !!!
Download Telegram
ውድ ተማሪዎቻችን ዲኤስ ቲቪው መስተካከሉ የታወቀ ነገር ነው ። በመሆኑም ዛሬ 7:00 ላይ ኳስ ጨዋታ መኖሩን እንገልፃለን።

የተማሪዎች ሕብረት !!!
Forwarded from D@W D@W
አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ
👇👇👇👇
ማንኛውንም የዩኒቨርሲቲያችንን መረጃ ለተማሪዎች ለማድረስ የዩኒቨርሲቲያችን ትክክለኛ የ tgm እና የ fb ገፅ ተከፍቷል።

የ telegramገፃችን
👇👇 https://t.me/asratwoldeyeshealthsciencecampus

የ facebookገፃችን
👇👇👇
https://www.facebook.com/profile.php?id=100087595710493

በመሆኑም ከላይ ያለውን የfb እና የtgm ገፅ በሁሉም ት/ት ክፍል እንዲሁም አዲስ ወደ ግቢያችን ለገቡት ተማሪዎችም የዩኒቨርስቲያችን ትክክለኛው የfb እና የtgm ድህረ ገፅ ለሁሉም እንዲደርስ በየክላሳችሁ በተከፈተው የtgm ግሩፕ ላይ ሼር በማድረግ ሁሉም የግቢያችን ተማሪዎች አባል ሆነው መረጃውን በቀላሉ እንዲያገኙ ሼር አድርጉ።
ማስታወቂያ

ሁላችሁም የክላስ ተወካዮች ከዚህ ቀደም ክትትል እንድታደርጉበት የተሰጣችሁን የመከታተያ ቅፅ (educational assessment ) እስከ ዕሮብ 21/03/2015 ዓ.ም ድረስ ከተማሪዎች ኅብረት ቢሮ እየመጣችሁ እንድታስገቡ!!!

የተማሪዎች ኅብረት
ማስታወቂያ
ለስፖርት አፍቃሪያን በሙሉ ተቋርጦ የነበረው DSTV ዛሬ 5/05/2015 ዓ/ም ከ 9:00 ሰአት ጀምሮ አገልግሎት ስለሚሠጥ በሠአቱና በቦታውና ተገኝታችሁ ተሳታፊ እንድትሆኑ እያልን እናሳስባለን ።
መልካም እድል
ማስታወቃያ
የተማሪ ህብረት፥ የተማሪ ፖሊስ ፥ የድስፕሊን ኮምቴ ሰኞ የምክክር መድረክ ከፕሬዚዳንት ፅ/ቤት ጋር በመመረቂያ አዳራሽ ይኖራል ስለተባለ ከወዲሁ እየተዘጋጃችሁ ቆዪ መቅረት ፈፅሞ አይቻልም ።
ሰዓት ከቀኑ 8:00
መሳሰቢ ፦ ተለዋጭ ሀሳብ ካለ እናሳውቃለን
ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ት/ት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት የተሰጠ መግለጫ!

በቅድሚያ በዩኒቨርሲቲ ቆይታችሁ ማሟላት የሚጠበቅባችሁን አሟልታችሁ ለዚህ ለበቃችሁ ውድ እጩ ምሩቃን እና ክቡራን የምሩቃን ቤተሰቦች እንኳን ደስ አላችሁ እያልን በዚህ አመት በሁሉም የትምህርት ክፍሎች የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና፤ ተመራቂ ተማሪዎች ያላቸውን ብቃት ለመለካት የተዘጋጀ እና ለት/ት ጥራት የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ ቢሆንም የነበሩ ክፍተቶችን እና በቅድሚያ መሟላት የነበረባቸው ሁኔታዎችን በዝርዝር በማስቀመጥ ቢያንስ ቁጥራቸው በዛ ያሉ ተመራቂዎች በሚገኙባቸው የት/ት ፕሮግራሞች በዚህ አመት እንዲጀመር አልያም በሙከራ ደረጃ እንዲሰጥ ያላሳለሰ ጥረት አድርገናል።

ሆኖም የት/ት ጥራትን ለማምጣት በሁሉም የት/ት ክፍሎች እንዲጀመር በመወሰኑ፤ ያሉ ነባራዊ ሁኔታዎችን ከግምት በማስገባት በትግበራው ተማሪው ተጎጂ እንዳይሆን እያደረግን ቆይተናል። በቅርቡ በተሰጡት የመለማመጃ እና የሙከራ ፈተናዎች ወቅት የነበሩ ክፍተቶችን ከየዩኒቨርሲቲው የተማሪ ህብረቶች በመሰብሰብ እና በዋናው ፈተና ወቅት ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን በመለየት እንዲስተካከሉ ለት/ት ሚኒስቴር ከወዲሁ አሳውቀናል።

በተጨማሪም ምርቃት እና የመውጫ ፈተናን በተመለከተ ከት/ት ሚኒስቴር ጋር በነበረን ቅድመ ውይይት የምረቃ መርሀ-ግብር ላይ የሚሳተፉ ተማሪዎችን በተመለከት ዩኒቨርሲቲዎች የቀደመ አሰራራቸውን መከተል እንደሚችሉ ስምምነት ላይ ደርሰን የነበረ ቢሆንም፤ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ “የመውጫ ፈተናን ያላለፉ ተማሪዎች የምርቃት ፕሮግራም ላይ አይሳተፉም” በማለት በድንገት አሳውቆ የነበረ መሆኑ ይታወቃል።

ውሳኔው ከተገለፀበት እለት ጀምሮ እንደ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ት/ት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት ጉዳዩ አግባብነት የሌለው፣ በህግ ለተቋማት ሴኔት በተሰጠ ስልጣን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያለ አግባብ ጣልቃ መግባቱን እንዲሁም ውሳኔው ከ4-7 አመታት የተማረው ተማሪን ብቻ ሳይሆን የሀገር መሰረት የሆነውን ቤተሰብንም ጭምር የሚጎዳ፤ ለት/ት ጥራቱም ምንም ፋይዳ የሌለው መሆኑን በመግለፅ በተደጋጋሚ ውይይት ያደረግን ሲሆን በዚህም መሰረት ት/ት ሚኒስቴር በግብታዊነት ያስተላለፈውን ውሳኔ በማሻሻል ወደቀድሞ ሀሳብ ተመልሷል። ለዚህም በተመራቂ ተማሪዎች ስም ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ምስጋናችንን እናቀርባለን።

በዚህም መሰረት በሀገራችን የሚገኙ ሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አንድ/ሁለት ያልተሟላ ውጤት ኖሯቸው ከግማሽ በላይ ጠቅላላ ድምር ውጤት(CGPA>=2.00) ያላቸውን ተማሪዎች የምርቃት መርሀ-ግብር እንዲሳተፉ አድርገው ሲያሟሉ ዲግሪ የሚሰጡ ሲሆን አሁንም በተመሳሳይ የመውጫ ፈተናውን የማያልፍ ተማሪ ካለ የምርቃት መርሀ-ግብር ላይ በመሳተፍ ለምዘናው ብቁ በሆነ ጊዜ በየሶስት ወሩ በሚሰጠው ፈተና ያለገደብ መመዘን ብሎም ድጋሚ የመፈተን ፍላጎት የሌለው እጩ ምሩቅ በደረጃ ዝቅ ያለ የት/ት ማስረጃ መውሰድ እንደሚችል በመመሪያ ተቀምጧል።

በመሆኑም ውድ እጩ ምሩቃን በምርቃት መርሀ-ግብር ዙሪያ ሲነሱ የነበሩ ነገሮችን ታግሳችሁ ከሚመለከታቸው አካላት መልስ እስኪሰጥ በትግስት ስለጠበቃችሁ ምስጋናችንን እያቀረብን፤ ጥያቄያችን መልስ አግኝቶ ሁሉም ተመራቂ ተማሪ የምርቃት መርሀ-ግብር ላይ የሚሳተፍ በመሆኑን እንገልፃለን።

በተያያዘም የመውጫ ፈተናውን ያለፉ ተማሪዎች በትምህርት ማስረጃቸው ላይ ከ100 ያመጡት ውጤት የሚገለፀው በጊዜያዊው ማስረጃቸው(Tempo) ላይ ሳይሆን በትራንስክሪፕት ማለትም የወጪ መጋራታቸውን ከፍለው ሲያጠናቅቁ በሚሰጣቸው፤ የወሰዱትን የት/ት አይነቶች ከነውጤታቸው በሚያሳየው ማስረጃ ላይ መሆኑን እየገለፅን መንግስት አዲስ ቅጥር ማቆሙን ካሳወቀ 2 አመታት ያለፉ ቢሆንም በግሉ ዘርፍ ብቻ ሳይሆን በመንግስት መስሪያ ቤቶችም የተለያዩ አዲስ ቅጥሮች ሲፈፀሙ የቆዩ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን።

በመጨረሻም ክቡራን እጩ ምሩቃን፦
1) የምትፈተኑበት ኮምፒውተር ፈተና ከመጀመሩ በፊት ሙሉ አገልግሎት እንደሚሰጥ ፈትሻችሁ እንድትቀመጡ፤
2) ፈተናውን በምትሰሩበት ወቅት የኮምፒውተር ገመዶች በሰውነታችሁም ሆነ በሌላ ነገሮች እንዳይነኩ እና እንዳይቋረጡ ጥንቃቄ እንድታደርጉ፤
3) ወደ መፈተኛ ክፍሎች ስትገቡ እና ፈተናው በሚሰጥበት ጊዜ መመሪያዎችን እንድታከብሩ፤
4) ምዘናው በበይነመረብ የሚሰጥ እንደመሆኑ በፈተናው ወቅት ችግሮች ካጋጠሙም ወድያው መፍታት ስለሚቻል እንከን ሲያጋጥማችሁ በየመፈተኛ አዳራሹ ለተመደቡ የአይሲቲ ባለሙያዎች በፍጥነት እንድታሳውቁ እንዲሁም የሚያጋጥሟችሁን የትኛውም ተግዳሮቶች በግቢያቹ ላለው ህብረታችሁ በማመልከት ከግቢው ከአቅም በላይ ከሆነ በእኛ በኩል በሚመለከተው አካል እንዲፈታ የምናደርግ መሆኑን እየገለፅን በቅርቡ በተሰጠው የሙከራ ፈተና ልክ በመዘጋጀት ያለምንም ፍርሀት እና ጭንቀት የፈተና ስነ-ምግባርን በጠበቀ መልኩ እንድትፈተኑ አደራ እያልን መልካም ፈተና እንዲሆንላችሁ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ት/ት ተቋማት ተማሪዎች ስም አብዝተን እንመኛለን።


መልካም እድል!

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ት/ት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት



@EHEISUOfficialChannell
ሰላም ውድ ተመራቂ ተማሪዎች ፈተና እደት ነበር ?
የመመረቂያ ቀን መቸ ነው እያላችሁ ለጠየቃችሁን ልጆች ሀምሌ 13 ነው።
እንኳን ደስ አላችሁ!!
Congratulations!!🎓🎓🎓
ሁሉም የ2015 ዓ.ም የደ/ብ/ዩ ተመራቂ ተማሪዎች ሀምሌ 13 በደመቀ ሁኔታ ይመረቃሉ።
ሰላም ውድ የ2013 እና 2014 ባች  የDBU ተማሪዎች ሰሜታችሁ ይገባናል የሁላችንም ስሜት ነው ቢሆንም ባሁኑ ሰዓት ምንም አይነት ስለ ጥሪ ቀን የተወሰነ ነገር ስለሌለ ጥሪው እንደተወሰነ እናሳውቃለን እስከዛው በትዕግስት ጠብቁን፡፡
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ🌷🌹💒
በዓሉን የሰላም የፍቅርና የአድነት ያድርግልን!!!🙏🙏🐓🐑🐐🌈🌈🌈
የወንዶች ዶርም ድልድል