የክርስትና እምነት ተከታይ የማህበራችን አባላት በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው አደረሳችሁ !
መልካም የትንሳዔ በዓል እንዲሆንላችሁ መልካም ምኞታችንን እየገለፅን በዓሉን በግቢ ውስጥ የምታከብሩ አባላቶቻችን ፍፁም ሀላፊነት በተሞላበት መንገድ እንድታከብሩ እናሳስባለን።
መልካም የትንሳዔ በዓል ይሁንላችሁ!!!
የደ/ብ/ዩ የህግ ተማሪዎች ማህበር ፅ/ቤት
@DBULSA

❤4
ውድ ተማሪዎቻችን፤
የሀበሻ የአረጋውያንና ምስኪኖች መርጃ ልማት ድርጅት የተጣለበትን ማህበራዊ ኃላፊነት እንዲወጣና ለወገኖቻችን መጠለያ የሚሆን የህንፃ ግንባታ እንዲያከናውን ላደረጋችሁት ከፍተኛ ድጋፍ ድርጅቱ የላቀ ምስጋናውን አቅርቧል።
የዩኒቨርሲቲያችን ተማሪዎቻች ከምግብ ፍጆታቸው ላይ የሥጋ ወጪን በመቀነስ፣ በአጠቃላይ ብር 2,512,345.16 (ሁለት ሚሊዮን አምስት መቶ አስራ ሁለት ሺህ ሦስት መቶ አርባ አምስት ከ16 ሳንቲም) በማሰባሰብ ለድርጅቱ ገቢ አድርገዋል።
በዚህ የተቀደሰ የበጎ አድራጎት ስራ ላይ የማህበራችን ስራ አስፈፃሚ አባላት ከፍተኛ የሆነ የማስተባበር ስራ ሰርተዋል።
ማህበራችን እንደ በጎ ስራው ተሳታፊ የተሰማውን ከፍተኛ ደስታ እየገለፀ በቀጣይም በተዩኒቨርሲቲው ውስጥ በሚካሄዱ የበጎ አድራጎት ስራዎች ላይ በንቃት እንደሚሳተፍ እንገልፃለን።
ክብር ለደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች
የደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ የህግ ተማሪዎች ማህበር ፅህፈት ቤት

❤3
ለሶስተኛ ዓመት የህግ ተማሪዎች
የደ/ብ/ዩ የህግ ተማሪዎች ማህበር በሶስተኛ ዓመት ተማሪዎች መካከል የመድረክ ላይ ክርክር(Debate) ማድረግ ይፈልጋል።የመድረክ ላይ ክርክርሩ(debate) በኢትዬጵያ ፌደራሊዝም ስርዓት ላይ ትኩረት የሚያደር ሲሆን ከ ሁለቱም ክፍሎች ከእያንዳንዳቸው 3 ተማሪዎች ይወዳደራሉ።
በመሆኑም በመድረክ ክርክሩ ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ ተማሪዎች እስከ ዛሬ ምሽት 3:00 ድረስ በክፍል ተወካዮቻችሁ አማካኝነት እንድትመዘገቡ እናሳስባለን።

❤2
ለሁሉም የደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች
በነገው እለት በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የህግ ተማሪዎች መካከል የወቅቱን የኢትዮጵያ የፌደራሊዝም ስርዓት መሰረት ያደረገ የመድረክ ላይ ክርክር ይካሄዳል።
በመድረክ ላይ ክርክሩ ሀገራችን ኢትዮጵያ ስለምትከተለው የፌደራሊዝም ስርዓት አንኳር ነጥቦች ክርክር ይደረግባቸዋል።
በህግ መምህሩ ዶ/ር ያሬድ አማካሪነት እና በደ/ብ/ዩ የህግ ተማሪዎች ማህበር አዘጋጅነት በዩኒቨርሲቲው ህግ ኮሌጅ ድጋፍ የተዘጋጀው የመድረክ ላይ ክርክሩ ነገ ጠዋት ማለትም በ 8/09/2018 ከ ጠዋቱ 3:00 በ PR አዳራሽ ይካሄዳል።
በመሆኑም ተማሪዎች በመድረኩ ተገኝታችሁ የፕሮግራሙ ተካፋይ እንድትሆኑ ተጋብዛችሗል።
የደ/ብ/ዩ የህግ ተማሪዎች ማህበር
@dbulsa

👍1
የደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ የህግ ተማሪዎች ማህበር ከዩኒቨርሲቲው ህግ ኮሌጅ ጋር በትብብር ያዘጋጀው የመድረክ ላይ ክርክር ዛሬ ጠዋት ተካሂዷል።
የመድረክ ክርክሩ በኢትዮጵያ ፌደራሊዝም ስርዓት ላይ ትኩረት ያደረገ ሲሆን ተከራካሪ ተማሪዎች የኢትዮጵያን ነባራዊ የታሪክ,የፖለቲካ,የህግ ሁኔታ ከአለም አቀፍ ልምዶች ጋር አጣምረው ሞግተዋል።
በፕሮግራሙ የህግ ኮሌጅ ዲን ዶክተር ሆነልኝ ተማሪዎቻቸው በክፍል ውስጥ የተማሩትን ፅንሰ ሀሳብ የተግባር ልምምድ እያደረጉ ብቃታቸውን እንዲያሳድጉ መሰል መድረኮች በቀጣይነት እንዲዘጋጁ ብርቱ ጥረት እንደሚያደርጉ ገልፀው የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ህግ ተማሪዎች ቡድን ለሀገር አቀፍ የ Moot court ውድድር በማለፉ ዩኒቨርሲቲውን ወክሎ አርባ ምንጭ ለውድድር እንዳቀና ተናግረዋል።
ዶር ሆነልኝ የመድረክ ክርክሮች እና moot court ለህግ ተማሪ ትክክለኛ የህግ ሰው ሆኖ እንዲገኝ ሚናው ትልቅ እንደሆነ የተናገሩ ሲሆን በቀጣይነት ከህግ ተማሪዎች ማህበራችን ጋር ኮሌጁ በጥብቅ እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።

Debre Berhan University law students association
Photo
በመድረኩ ተጋባዥ እንግዳ የነበሩት የፖለቲካ ሳይንስ ምሁሩ ረዳት ፕሮፌሰር አያሌው በርካታ ሀሳቦችን የተናገሩ ሲሆን መሰል የመድረክ ፕሮግራሞች መዘጋጀታቸው ተማሪዎች የተሻለ በራስ መተማመን እንደዚሁም እውቀት እንዲገነቡ ሚናቸው ከፍተኛ መሆኑን ገልፀዋል።
ረዳት ፕሮፌሰር አያሌው በማንኛውም ጊዜ ተማሪዎች ለሚያደርጉት የመድረግ ክርክሮች እርዳታቸውን ከጠየቁ በሙያቸው ለማገዝ ዝግጅ መሆናቸውን እንደዚሁም ገልፀዋል።ፕሮፌሰሩ በቅርብ በፌደራሊዝም ላይ ብቻ ትኩረት አድርጎ የሚሰራ ክበብ ለማቋቋም ፕሮፖዛል ለዩኒቨርሲቲው እንደገባና ክበቡ ሙሉ በሙሉ ፈቃድ አግኝቶ ወደ ስራ ሲገባ የህግ ተማሪዎች በግንባር ቀደምትነት ሊሳተፉበት እንደሚገባ አሳስበዋል።
ማህበራችን ይኸ የክርክር ፕሮግራም ተጀምሮ እስኪያልቅ በማማከር ድጋፍ ሲያደርጉ ለነበሩት የህግ ትምህርት ቤታችን አንጋፋ መምህር ዶ/ር ያሬድ,የህግ ትምህርት ቤቱ እና ሌሎችም ድጋፍ ላደረጉ አካላት ምስጋናውን እያቀረበ በቀጣይ ከህግ ኮሌጃችን ጋር በመሆን የተማሪዎችን ብቃት ከፍ ሊያደርጉ የሚችሉ የተግባር ስራዎችን እንደሚያከናውን ቁርጠኝነቱን ይገልፃል።
የደ/ብ/ዩ የህግ ተማሪዎች ማህበር ፕሬዝዳንት ፅ/ቤት

የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት
ለደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ማህበረሰብ፤ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም በዓለም ዙሪያ ለምትገኙ ሙስሊሞች በሙሉ፡ እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የደስታና የመተሳሰብ እንዲሆንላችሁ ዩኒቨርሲቲያችን ልባዊ ምኞቱን ይገልጻል።
የዘንድሮው የዒድ አል-አድሃ በዓል የእርስ በእርስ አንድነታችንን የምናጠናክርበት፣ የተቸገሩትን በመርዳት የምንደጋገፍበትና ለአገራችን ሰላምና እድገት በጋራ የምንቆምበት ይሆን ዘንድ እንመኛለን።
ዒድ ሙባረክ! መልካም የአረፋ በዓል!
ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ
On behalf of Debre Berhan University (DBU), we extend our warmest and most heartfelt greetings to the DBU Muslim community, to all Ethiopian Muslims, and to all Muslims across the globe on the sacred occasion of the 1447th Eid al-Adha. Wishing You a Blessed 1447th Eid al-Adha (Arafa)!
May this auspicious festival bring peace, harmony, prosperity, and immense joy to your homes. As we celebrate the values of sacrifice, devotion, and compassion, let us also renew our commitment to unity, mutual support, and the pursuit of knowledge. Wishing you a safe, blessed, and joyous celebration.

❤1
ማህበራችን ለእስልምና እምነት ተከታይ የደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች,መምህራን እና ሰራተኞች በሙሉ እንኳን ለ 1447ኛው የዒድ አል አድሃ በዓል አደረሳችሁ ማለት ይወዳል።
በዓሉ የሰላም,የደስታ እና የአብሮነት እንዲሆንላችሁ ይመኛል።
🌙🌙🌙ኢድ ሙባረክ 🌙🌙🌙
@dbulsa
በዓሉ የሰላም,የደስታ እና የአብሮነት እንዲሆንላችሁ ይመኛል።
🌙🌙🌙ኢድ ሙባረክ 🌙🌙🌙
@dbulsa
❤2
👍5❤3
Debre Berhan University law students association
Photo
ነሃሴ 13/2018
ለቀድሞው ዲናችን ለመምህር ሆነልኝ ሀይሉ የተበረከተ የላቀ ምስጋና
መምህር ሆነልኝ ሀይሉ በዲንነት ቆይታቸው ወቅት ለሕግ ትምህርት ቤታችን እና ለተማሪዎቻችን ላበረከቱት ሁለገብና የማይተካ አስተዋፅኦ ማኅበራችን በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የሕግ ማኅበረሰብ ስም የላቀ ምስጋናውን ያቀርባል።
መምህር ሆነልኝ ለኮሌጃችን ተማሪዎች ከዲንነት ኃላፊነት ባሻገር ለተማሪዎች እንደ አባትና ታላቅ ወንድም በመሆን በመካሪነታቸው፣ በቅንነታቸውና በአጋዥነታቸው በተማሪዎች ዘንድ እጅግ የተወደዱ የኮሌጃችን አብሪ ኮከብ ሆነው በቅንነት አገልግለዋል። ተማሪዎቻችን በዕውቀትና በውጤት የበለጡ ሆነው እንዲወጡ ሌት ተቀን ያደረጉት ጥረት፣ በተማሪዎችና በመምህራን ዘንድ ከፍተኛ መነቃቃትንና የጥንካሬ መንፈስን ፈጥሯል።
በተለይም ማኅበራችን እንደ ማኅበር ተጠናክሮ እንዲቀጥልና ዓላማውን እንዲያሳካ ላደረጉልን ያልተገደበ ድጋፍና እግዛ ትልቅ አክብሮት አለን። መ/ር ሆነልኝ ሀይሉ ላበረከቱት ቀጣይነት ያለው አወንታዊ አስተዋፅኦ እያመሰገንን፣ በቀጣዩ የሕይወትና የሙያ ጉዟቸው ስኬት፣ ጤና እና ሰላም እንዲገጥማቸው መልካም ምኞታችንን እንገልጻለን።
ለአዲሱ የኮሌጃችን ዲን ለዶክተር ያሬድ ሀይለማርያም የእንኳን ደስ አለዎት እና የመልካም የስራ ዘመን ምኞት
የሕግ ኮሌጃችን ዲን ሆነው ለተሾሙት ለአንጋፋው መምህራችን ለዶ/ር ያሬድ ሀይለማርያም እንኳን ለዚህ ከፍተኛ የአመራር ኃላፊነት በደህና መጡ እያልን፣ አዲሱ የሥራ ዘመናቸው የስኬት፣ የጤና እና የውጤታማነት እንዲሆንላቸው መልካም ምኞታችንን እንገልፃለን።
ማኅበራችን ከዶክተር ያሬድ ጋር በቅርበትና በትክክለኛ አጋርነት በመስራት፦
የሕግ ትምህርት ቤቱ የትምህርትና የመማር-ማስተማር አካባቢ ለተማሪዎች የበለጠ ምቹ፣ ፍሬያማና ተስማሚ እንዲሆን፣
ተማሪዎችን በከፍተኛ ዕውቀት፣ ክህሎትና በብቃት የማዘጋጀት ሂደቱን በጋራ ለማጠናከር፣
ከቀጥተኛ አካዳሚክ ዘርፍ ውጭ ማኅበራችን ለሚያካሂዳቸው የተማሪዎች ተሳትፎ፣ ልማትና ማኅበራዊ እንቅስቃሴዎች ላይ አብረን ለመስራት ትልቅ ተስፋ እና ዝግጁነት ያለን መሆኑን እያረጋገጥን አዲሱ የኮሌጃችን ዲን ዶ/ር ያሬድ ጠንካራ ድጋፋቸውን እንደሚጠሱን ተስፋችን የለመለመ ነው።
የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የሕግ ተማሪዎች ማኅበር