Dilla Don Bosco ICT Center Digital Library 2
299 subscribers
233 photos
3 videos
28 files
11 links
Download Telegram
‎ማስታወቂያ

‎ለኮዲንግ ስልጠና ፈላጊዎች

‎የዲላ ዶን ቦስኮ ካቶሊክ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ማዕከል ለ8ኛ ዙር የኮዲንግ ሰልጣኞችን ተቀብሎ ማሰልጠን ይፈልጋል።

▶️ የክፍል ደረጃ: ከ6ኛ እስከ 10 ኛ ክፍል
▶️ የምዝገባ ቀናት: ከሰኛ ጥቅምት 24 ጀምሮ
▶️ የምዝገባ ቦታ: በት/ቤቱ ኢኮቴ ማዕከል እና ኦንላይን
▶️ ስልጠናው የሚሰጠው: ዘወትር ቅዳሜ ጠዋት
▶️ ስልጠናው የሚወስደው ጊዜ :አምስት ወራት

‎ያለን ቦታ ውስን ስለሆነ ፈጥነው ይመዝገቡ


‎ለበለጠ መረጃ: 0911984389
‎ቴሌግራም: @anduict
‎ኢሜል: andutsega@gmail.com

‎ስልጠናው ቅዳሜ ህዳር 6/2018 ዓ.ም ይጀምራል

‎የዲላ ዶን ቦስኮ ካቶሊክ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ማዕከል ።

‎በሚከተለው የጎጉል ፎርም በኦላይን መመዝገብ ይቻላል

https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSez0eOwB7nMFVbuBmf59Olv4p5PnYxQgztdss3KRZibW0jyXw/viewform?usp=header
ማስታወቂያ

‎ለ8ኛ ዙር የኮዲንግ ስልጠና የተመዘገባችሁ ተማሪዎች ከዚህ በፊት ቅዳሜ ሕዳር 6/2018 ዓ.ም ይጀምራል የተባለው ስልጠና በሚድ ተርም ፈተና ምክንያት ወደ ቅዳሜ ሕዳር 13/2018 ዓ.ም የተሸጋገረ መሆኑን እንገልፃለን።

‎እስከ አሁን ያልተመዘገባችሁ ተማሪዎች ውስን ቦታ ስላለ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

‎የዲላ ዶን ቦስኮ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ማዕከል።

በኦንላይን ለመመዝገብ የጎጉል ፎርሙን ተጠቀሙ
https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSez0eOwB7nMFVbuBmf59Olv4p5PnYxQgztdss3KRZibW0jyXw/viewform?usp=header
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ኢቲቪ የልጆች አለም ቻናል በዲላ ዶን ቦስኮ ት/ቤቶች ያደረገው ቆይታ። ቅዳሜ ከ8:00 ጀምሮ ይተላለፉል።

#እንዳያመልጣችሁ

የትጉህ መምህራን እና ተማሪዎች ስራ ለእይታ ይበቃል
1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በ2017 ዓ.ም 6ኛው ዙር የህፃናት ኮዲንግ ሰልጣኝ የነበሩ ተማሪዎች የሰሩት #የኢትዮጵያ_ባህላዊ_ሙዚቃ_መሳሪያን ለተማሪዎች የሚያስተዋውቅ አፕሊኬሽን አሰራር በኢትቪ የልጆች አለም ቲቪ ቻናል #ተማሪ_የማሪያም አቅርባለች። ሙሉውን ቃለ መጠይቅ ተጋበዙልን።

ስራውን በቡድን የሰሩት

1. ተማሪ ቃልኪዳን አማረ
2. ተማሪ የማሪያም ም/ፀሐይ
3. ተማሪ ኤልዳና ጌትነት
4. ተማሪ ዳግማዊ አማረ ናቸው
1
የ2018 ዓ.ም 8ኛ ዙር የህፃናት ኮዲንግ ስልጠና በምስል
ማስታወቂያ

‌‎ለ2018 ዓ.ም 8ኛ ዙር ኮዲንግ ሰልጣኞች

‌‎ከጥር 2/2018 ዓ.ም ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ የስልጠና ፕሮግራሙ ከሰዓት ወደ 8:00 ሰዓት የተለወጠ መሆኑን እንገልፃለን።

‎ቦስኮ ኮዲንግ አካዳሚ
2
ብዙዎቻችን ልጆቻችንን "ስንተኛ ወጣህ?" ብለን ስንጠይቅ፣ ሳናውቀው የልጆቻችንን የፈጠራ ብቃትና የነፃነት መንፈስ እየገደልን መሆኑን እናውቃለን?

1. ከዓለም አቀፍ ትምህርት ቤቶች (International Schools) የምንማረው ትልቅ ሚስጥር፦

እንደ IB (International Baccalaureate) ያሉ ስመ-ጥሩ የትምህርት ስርአቶች "ደረጃ" (Rank) የሚባል ነገር አይጠቀሙም። ይልቁንም ልጆችን በደረጃ (Levels/Grades - A, B, C) ይመዝናሉ።

ምክንያቱም፦ በአንድ ክፍል ውስጥ 95 ያመጣ ልጅ 1ኛ፣ 94 ያመጣ ደግሞ 2ኛ ቢባል፣ በሁለቱ ልጆች መካከል ያለው የ1 ነጥብ ልዩነት የብቃት ልዩነት ሳይሆን የፉክክር ጫና ብቻ ስለሚፈጥር ነው።

2. "መብለጥ" ወይስ "ማወቅ"?

ዓለም አቀፍ ጥናቶች እንደሚያሳዩት፣ በፉክክር (Competition) ላይ ብቻ ያደጉ ልጆች ነገ ለስራ አለም ሲሰማሩ "የትም ፍጭው ዱቄቱን አምጭው" በሚል ስሌት ለጥቅማቸው ሲሉ ሌላውን ከመጉዳት አይመለሱም። ይልቁንም በትብብር (Collaboration) ላይ ያተኮረ ትምህርት ለስኬታማ ህይወት ወሳኝ ነው።

3. እውነተኛው መመዘኛ "ራስን መብለጥ" ነው!

ልጃችን ዛሬ 80 ካመጣ፣ ነገ 85 እንዲያመጣ ማበረታታት እንጂ፣ ከጓደኛው ጋር ማወዳደር የለብንም። የፈረንሳይና የፊንላንድ የትምህርት ስርአቶች ውጤታማ የሆኑት ልጆችን እርስ በእርስ ማወዳደር ስላቆሙ ነው።

#ለወላጆች የቀረበ ምክር፦

• ልጃችሁን "ስንተኛ ወጣህ/ሽ?" ሳይሆን "ዛሬ ምን አዲስ ነገር ተማርክ/ሽ?" ብላችሁ ጠይቁ።
• ውጤቱን በደረጃ ሳይሆን በብቃቱ (Criteria) መዝኑት። 90 አምጥቶ 3ኛ ቢወጣ እንኳ፣ ያ ውጤት የእሱ ድንቅ ስኬት መሆኑን ንገሩት።

ታታሪና በራሱ የሚተማመን ትውልድ መፍጠር እንጂ፣ በደረጃ የተገደበ ፉክክር ውስጥ የሰጠመ ትውልድ መፈጠር የለበትም!
1