Development Bank of Ethiopia (DBE)
23.3K subscribers
2.11K photos
76 videos
4 files
581 links
The development bank of Ethiopia (DBE) is one of the financial institutions engaged in providing short, medium and long term development credits.
Download Telegram
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ አደረሳችሁ!

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
👍233🤝1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ልዩ የፋናንስ ተቋም ሆኖ፣ የመንግሥት የልማት አቅጣጫን መሠረት በማድረግ አዋጪ ለሆኑ የልማት ፕሮጀክቶች ከሀገር ውስጥና ከውጪ የብድር ገንዘብ በማሰባሰብ የፋይናንስና የቴክኒክ ድጋፍ በመስጠት የተሰጠውን አገራዊ ኃላፊነት እየተወጣ ያለ የፖሊሲ ባንክ ነው፡፡ ባንኩ ከጊዜ ወደ ጊዜ ተደራሽነቱን እያሰፋ ይገኛል፡፡
በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሊዝ ፋይናንስ የብድር አገልግሎት ተጠቃሚ ከሆኑን ከራሰቸው አልፈው አካባቢያቸውን መቀየር የቻሉ በርካታ ሰዎችን ታሪካቸው መማሪያ ይሆን ዘንድ በቴሌቭዥን ፕሮግራማችን እያቀረብን መሆኑ ይታወቃል፡፡ ዛሬ ደግሞ ወደ ቦንጋ ተጉዘን የባንካችን ደንበኛ የሆነ ወጣት ታሪክ ይዘን ቀርበናል ተከታተሉ፡፡
👍2410
የግብርና ግብዓቶች ላይ ያለንን አቅም ማጎልበት፤ በአርብቶ አደርና ቆላማ አካባቢዎች ያለውን ልማት ማፋጠን የትኩረት አቅጣጫችን ነው

ለኢንቨስትመንት መሠረቱ መሬት፣ ካፒታል እና የሰው ኃይል እንዲሁም ቴክኖሎጂ ናቸው፡፡ መሬት ለማምረቻ ኢንዱስትሪም ሆነ በግብርና ዘርፍ ለሚደረግ ኢንቨስትመንት ቁልፉ ግብዓት ነው፡፡ አንድ ኢንዱስትሪ ለመትከል መሬት፤ የግብርና ምርት ለማምረትም የሚታረሰው መሬት መኖር ግድ ይላል፡፡

መሬት በሌለበት ግብርናም ፋብሪካም አይታሰብም፡፡ ከዚህ አኳያ አገራችን ለኢንዱስትሪም ሆነ ለግብርና መሰረታዊ የሆነው ግብዓት ያላት አገር መሆኗ በተደጋጋሚ ይጠቀሳል፡፡ በመሆኑም አንድ ሰው ወደ ኢንቨስትመንት ለመግባት በየአካባቢው ያለውን ይህን የግብዓት አቅም ማየት እና መጠቀም ይገባዋል ማለት ነው፡፡

የሰው ኃይልም ለአንድ ኢኮኖሚ ግንባታ ወሳኝ ነው፡፡ በአንድ ሀገር ውስጥ የሚኖር እውቀት እና የመስራት አቅም ያለው ሕዝብ ለኢኮኖሚው መሰረት ነው፡፡ በሰው ኃይል አቅም ያደገ አገር አገራዊ ኢኮኖሚውን ውጤታማ በማድረግ በኩል የተሻለ እድል እንዳለው እሙን ነው፡፡

ሌላው ለኢንቨስትመንት መሰረት የሚሆነው ካፒታል ነው፡፡ ካፒታል ጥሬ ገንዘብ ማለት ብቻ ሳይሆን ጥሬ ገንዘቡ ለምርት ግብዓት በሚውሉ ማሽኖች ሲመነዘር ማለት ነው፡፡ በመሆኑም ካፒታል ማለት በኢኮኖሚ ውስጥ ተመንዝሮ ትርፍ ሊያመጣ የሚችል የሥራ መሳሪያ እንደማለት ነው፡፡ በመሆኑም የሰው ኃይል፣ መሬት እና ካፒታል እንዲሁም ቴክኖሎጂን አቀናጅቶ በመጠቀም ለገበያ የሚያስፈልገውን ምርትም ሆነ አገልግሎት ማቅረብ መቻል ከራስ አልፎ በአገር ደረጃ ኢኮኖሚያዊ ለውጥ ለማምጣት ወሳኝ ነው፡፡ በአጠቃላይ መሬት፤ የሰው ኃይል እና ካፒታል ከቴክኖሎጂ ጋር ተደምሮ ምርታማነትን በማሳደግ ለኢኮኖሚያዊ እድገት መሰረት ነው፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከላይ የተጠቀሱት አገራዊ አቅሞችን አቀናጅቶ ወደ ምርት ለመግባት የተዘጋጀ ኃይልን የምርታማነት መሰረት የሆነውን የፋይናንስ ችግር በመቅረፍ ላለፉት ዓመታት በአጋርነት መቆም የቻለ አስተማማኝ የልማት አጋር ነው፡፡ ባንኩ በተለያዩ ጊዜያት ሀገራዊ ፋይዳቸው ከፍ ያሉ ሁነቶችን ስፖንሰር በማድረግ የአምራች ዘርፉን ለማበረታታት እና በዘርፉ ያሉ ተግዳሮቶች ላይ ውይይት በማድረግ ማነቆች እንዲፈቱ እያደረገ ይገኛል፡፡

እንደሚታወቀው በአገራችን ከትላልቅ እስከ መካከለኛ እርሻዎችን ለማልማት መስኖ ጥቅም ላይ ሲውል ቆይቷል። የተፈጥሮ ሀብትና የመስኖ ቴክኖሎጂን በአግባቡ መጠቀም በአገራችን የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ እንደሚያስችል ይታመናል፡፡ የኢትዮጵያ ቆላማና አርብቶ አደር አካባቢዎች ከዚህ አኳያ ሊሰጡ የሚችሉት ጥቅምና ዕድሎች በመመዘን በእነዚህ አካባቢዎች የሚደረግ ኢንቨስትመንት ባንኩ ያበረታታል፤ ድጋፍም ያደርጋል፡፡ በኢትዮጵያ ቆላማ አካባቢዎች የሚገኘውን ሰፊ መሬት፣ ውሃ፣ እንስሳትና የሰው ሀብት በመጠቀም አገሪቱ የልማት ተልዕኮዋን እንድታሳካ ባንኩ የመስኖና ቆላማ አካባቢ የልማት እንቅስቃሴዎችን ለመደገፍ የራሱን ድርሻ እየተወጣ ይገኛል፡፡

ከሰሞኑ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር በሚሊኒየም አዳራሽ እንዲሁም የግብርና ሚኒስቴር በኤግዚቢሽን ማዕከል ያዘጋጁትን ኤግዚቢሽን ባንካችን አጋር የሆነው በግብርና ግብዓቶች እና በአርብቶ አደርና ቆላማ አካባቢዎች ባሉ የልማት አቅሞች ላይ ግንዛቤ እንዲያዝ ካለው መሠረታዊ ፍላጎት በመነጨ ነው፡፡

የምስራቅ አፍሪካ አርብቶ አደሮች ኤክስፖ "አርብቶ አደርነት የምስራቅ አፍሪካ ኅብረቀለም" በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ሲሆን የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ኤክስፖው አርብቶ አደሩ ለአገራዊ ኢኮኖሚ ዕድገት ጉልህ ድርሻ እንዳለው በመገንዘብ ነው ኤክስፖውን በአጋርነት ያዘጋጀው፡፡ በአርብቶ አደሩ አካባቢ ያለውን እምቅ ጸጋ በመጠቀም የአገርን ልማት ማረጋገጥ እንደሚገባ በማመን ባንካችን በአካባቢው የሚደረጉ የልማት እንቅስቃሴዎችን በሙሉ አቅሙ ለማገዝም ዝግጁ መሆኑን አረጋግጧል፡፡

በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በግብርና ዘርፍ ላይ የወለድ ተመን በማሻሻል ዘርፉን ከመደገፍ ባሻገር የግብርና ሚኒስቴር የግብርና ዘርፉን ለማበረታታት የፋይናንስ አቅርቦትን ማሳደግ ወሳኝ መሆኑን ለማሳየት እንዲሁም አምራቹ እና ሸማቹን ለማገናኘት ያዘጋጀው ባዛር አጋር በመሆኑ ባንኩ ለአገር ልማት እያደረገ ያለውን አበርክቶት በተግባር ማረጋገጥ ችሏል፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
👍293
የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲዊ ሪፐብሊክ መንግሥት በዐሥር ዓመት የኢኮኖሚ ልማት መሪ ዕቅዱ ዋነኛ የትኵረት አቅጣጫ አድርጎ ከያዛቸው ጉዳዮች አንዱ የመስኖ እና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ነው፡፡

ይህን ግብ እውን ለማድረግ የፋይናንስ አቅርቦት ወሳኝ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ እንደ አንድ የመንግስትን የልማት እቅድ ለማሳለጥ የሚሰራ የፋይይናንስ ተቋም የግብርና ዘርፍ አገልግሎት ባንኩ አገልግሎት ከሚሰጥባቸው ዋነኛውና ቁልፉ የኢኮኖሚ ዘርፍ ነው፡፡

ባንኩ ዘመናዊ ግብርናን በከፍተኛ የፋይናንስ አቅርቦት በተከታታይ በመደገፍ ይታወቃል፡፡ በፕሮጀክት ፋይናንሲንግ የብድር አቅርቦት አሰራር በመስኖ ሊለሙ የሚችሉ ሜካናይዝድ ዘመናዊ የግብርና ፕሮጄክቶችን፣ ዘመናዊ እንስሳት እርባታ ፕሮጀክቶችን፣ ዘመናዊ የዶሮ እርባታ ፕሮጀክቶችን በዋናነት ፋይናንስ ያደርጋል፡፡ በተጨማሪም ከላይ የተጠቀሱትን ዓይነት ፕሮጀክቶች ለመደገፍ ሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት የሚያቀርቡትን ፈንድ በማስተዳደርም የኢትዮጵያ ልማት በሀገሪቱ እንዲስፋፋ ይሠራል፡፡

አርብቶ አደርና ቆላማ አካባቢዎች ላይ ባንኩ የሚያረቧቸውን እንስሳት እንደ ማስያዣ ተጠቅሞ በዘመናዊ እርባታ ሥራ ለሚኖራቸው ተሳትፎ አጋር ለመሆን እየተንቀሳቀሰ ነው፡፡ እንስሳት እርባታን በተለይም ከብቶችንና በጎችን ፍየሎችን (Livestock) በዘመናዊ መንገድ የማርባት ፕሮጀክቶችን ከዘመናዊ መኖ (feed) ዝግጅት (ምርት) ጋር አዛምደው ለሚሠሩ አርብቶ አደሮችና ቆላማ አካባቢ ባለሀብቶች ተመራጭ አገልግሎት ይዞ ቀርቧል፡፡

መስኖን ለሚጠቀሙ ዘመናዊ እርሻዎች (ሰብል እና ፍራፍሬ ልማት) ላይ ለሚሰማሩም ከፍተኛ አገልግሎት ይሰጣል፡፡ ቆላማ አካባቢዎች ለዶሮ እርባታ ተስማሚ በመሆናቸው በዚህ ረገድ ያለውንም የባንኩን አገልግሎት በስፋት መጠቀም ይችላሉ፡፡ አርብቶ አደሮች በሚገኙባቸውና ቆላማ በሆኑ አካባባዎች የሚገኙ የባንኩ ዲስትሪክቶችና ቅርንጫፎችም በፕሮጀክት ፋይናንሲንግ አገልግሎት ማኅበረሰቡን ለመደገፍ እየተንቀሳቀሱ ነው፡፡

አዋሽ አካባቢ የሚገኙ በመስኖ የሚለሙ እርሻዎች ለዚህ እንደ ምሳሌ ይጠቀሳሉ፡፡ በሊዝ ፋይናንሲንግ ለግብርና ልማት በተለይ በሰብል ምርት፣ በእንስሳት እርባታ፣ በመኖ ዝግጅትና በመሳሰሉ ዘርፎች (cultivating land, raising and harvesting crops, and feeding, breeding, and raising livestock) የሚጠቅሙ ማሽነሪዎችን፣ ልዩ ልዩ መሣሪያዎችን፣ አስፈላጊ ዕቃዎችን በኪራይ አገልግሎት (Lease Financing) ለደንበኞች ያቀርባል፡፡ በዚህ ረገድ በእነዚህ አርብቶ አደርና ቆላማ አካባቢዎችን የሚሸፍኑ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዲስትሪክትና ቅርንጫፎች እስከ አሁን በግብርና ሜካናይዜሽን የእርሻ ትራክተርና ኮምባይን ሃርቨስተሮችን፣ ውሃ ፓምፖችን፣ የወተት ሀብትን የማቀነባበር ሥራ የሚሠራባቸውን መሣሪያዎች፣ የዳቦ መጋጋሪያ ማሽኖችን፣ ዱቄት ማምረቻዎችን፣ ፕላስቲክ ማዳበሪያ ማምረቻዎችን እና ሌሎችንም ማሽነሪዎች በባንኩ እቃ ኪራይ አገልግሎት ለቆላማ አካባቢዎች የሚጠቅሙ መሣሪያዎችን እያቀረበ ነው፡፡

የመስኖ እርሻን ለጥቅም ከማዋል አንጻርም ባንኩ ከአገልግሎት አቅራቢዎች (Service Providers) ጋር በመሥራት የውሃ ቁፋሮ ከሚያካሂዱና የለማውን ውሃ ለቆላማ አካባቢ ለሚገኙ ገበሬዎች በመስኖ ውሃውን በማቅረብ እርሻ ሥራዎችን በመደገፍ ላይ ነው፡፡
👍284
የገጠር ፋይናንስ አቅርቦት ማሻሻያ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በ306 ሚሊዮን ዶላር ገንዘብ የገጠር ፋይናንስ አቅርቦት ማሻሻያ ፕሮግራም(RUFIP)ን ተግባራዊ እያደረገ ነው፡፡ ፕሮግራሙ በገጠር ያሉ በርካታ ቤተሰቦችን ኖሮአቸውን የሚያሻሽል፣ ድህነትን የሚቀንስ በገቢና ንብረት በማፍራት በኩል አቅም የማጠናከር ሥራ የሚሠራ ሲሆን፣ እስከ 11,000 በሚደርሱ የማኅብራት ኅብረትና በገጠር አነስተኛ የፋይናነስ ተቋማት(RFIs) ሀገር አቀፍ ኔትዎርክ በኩል ተደራሽ የሚሆን አገልግሎት ነው፡፡ የገጠር የፋይናንስ አቅርቦት ማሻሻያ ፕሮግራም (RUFIP) አሁን ባለው ሶስተኛ ዙር ፕሮግራሙ (2020-2026) አርብቶ አደሮችን የፋይናንስ አገልግሎት ተካታችነት የበለጠ የሚያረጋግጥ ሆኖ እየተሠራ ነው፡፡

በተለይም በአፋር እና ሶማሌ ክልሎች ያሉ አርብቶ አደር ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበራት በኢትዮጵያ አነስተኛና የፋይናንስ አገልግሎት ተቋማት ማኅበር እና በክልሎች የኅብረት ሥራ ማስፋፋያ ቢሮዎች በኩል የዚህ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየተሠራ ነው፡፡ ባንኩ የአሠልጣኞች ሥልጠናን፣ ተቋማዊ አቅም ግንባታን፣ የአቅም ግንባታ የጉብኝት መርሐ ግብሮችን፣ የቴክኒክ ባለሙያዎችን የማብቃት ሥራን፣ የገጠር የቁጠባና ብድር ማኅበራት ኅብረት ኮሚቴ አባላትን የማነቃቃት፣ ለኅብረቶቹ የማስፋፋያ፣ ኦዲተርና የሒሳብ ባለሙያዎችን በኮንትራት መቅጠርን፣ ተሸከርካሪዎች ግዢ የመሳሰሉትን አቅም ግንባታ ሥራዎች በቀጥታ ይሠራል፡፡

የአደጋ ስጋት ቅነሳና አካታች የአርብቶ አደር ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮጀክት (DRIVE) የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አርብቶ አደር ማኅበረሰቡን ለማገልገል በቅርቡ ለመተግበር እየተንቀሳቀሰባቸው ካሉ ፕሮጀክቶች አንዱ የአርብቶ አደር ኢኮኖሚ አደጋ ተጋላጭነት ቅነሳና የፋይናነስ አካታችነት ፕሮጀክት (DRIVE) ነው፡፡ ይህ ፕሮጀክት የሚተገበረው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከንግድ ሚኒስቴር፣ ከግብርና ሚኒስቴር ጋር በመሆን በፈጸመው የሦስትዮሽ ስምምነት ነው፡፡ የሚተገበረውም በአፋር፣ ሶማሊ፣ ኦሮሚያ፣ ደቡብ ኢትዮጵያ፣ ደቡብ ምዕራብ ክልሎች ነው፡፡ ይህም አርብቶ አደሮች የፋይናንስ አገልግሎት ተደራሽነታቸውን ለማሳደግና የቁም ከብት ንግድ በአፍሪካ ቀንድ እንዲስፋፋ የሚግዝ ነው፡፡ የሚያተኩረውም በእንስሳት ሀብት ልማት (Livestock) ላይ ሲሆን ቁም ከብቶችን በኤክስፖርት ደረጃ ለማርባት ከዓለም ባንክ በተገኘ 20,000,000 USD ድጋፍ የሚተገበር ነው፡፡

ይህ አገልግሎትም መስፈርቱን አሟልተው ለሚቀርቡ የግል ባለሀብቶች እና መስፈርቱን አሟልተው ለሚቀርቡ አርብቶ አደር ወጣቶችና ሴቶች ኅብረት ስራ ማኅበራት በሚሰጥ የፋይናነስ አገልግሎት ይሆናል፡፡ ለዚህ አገልግሎትም ባንኩ ቁም ከብትን ጨምሮ ተገቢ ያላቸውን ተንቀሳቃሽ ማስያዣዎች የሚጠይቅ ይሆናል፡፡
👍295🤝3
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ራሱን ከአደጋ ከማውጣት ተሻግሮ በተበላሸ ብድር ውስጥ የሚገኙ ግዙፍ ድርጅቶች ወደ ምርት እንዲገቡ በትኩረት እየሰራ መሆኑ ተገለፀ።

ይህ የተገለፀው የመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር የኤም.ኤን.ኤስ ማኑፋክቸሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ቴክስታይል ኢንዱስትሪ በባንኩ መተዳደር ከጀመረ በኋላ እያመጣ ያለውን ለውጥ በአካል ተገኝቶ በተመለከተበት ወቅት ነው።

የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር እና የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከፍተኛ አመራሮች የኤም.ኤን.ኤስ ማኑፋክቸሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ቴክስታይል ከፍተኛ ውጤት እያስመዘገበ እንዲመጣ ባንኩ የቅርብ ክትትልና ድጋፍ ማድረጉና ፋብሪካው ዘመናዊ የአመራረት አካሄድን እንዲከተል በመደረጉ መሆኑም ነው የተገለፀው።

ኤም.ኤን.ኤስ ማኑፋክቸሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ 1.4 ቢሊዮን ብር  በላይ ብድር በመውሰድ ስራ የጀመረ የጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ሲሆን፣ ፕሮጀከቱ ማበርከት የሚገባውን ዘርፈ ብዙ ፋይዳዎች እውን እንዲሆኑ ባንኩ የተለያዩ ድጋፎችን ያደረገለት ቢሆንም ማህበሩ የክፍያ ግዴታውን መወጣት ባለመቻሉ እና የማምረት አቅሙ በመዳከሙ ባንኩ ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ ተረክቦ እያስተዳደረው የሚገኝ ግዙፍ የጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ነው፡፡

የመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ኃ/ሚካኤል እንዳሉት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ባለፉት ዓመታት ራሱን በከፍተኛ ሪፎርም ውስጥ አስገብቶ መስራቱ በርካታ ለውጦችን እንዲያስመዘግብ ከመቻሉም በላይ በርካቶች  ከባንኩ ጋር አብረው እንዲሰሩ እያደረገ ነው። ባንኩ ራሱን እንደ ተቋም ከማስተካከል ተሻግሮ ብድር ለመክፈል ተቸግረው ተዘግተው የቆዩ ፕሮጀክቶችን ራሱ ተረክቦ ማስተዳደር በመጀመሩ  ውጤቶች መመዝገባቸውን ነው ዋና ዳይሬክተሩ የገለፁት።

የኤምኤንኤስ ፋብሪካ  ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ደሳለኝ ፍሬው  ስለፋብሪካው ከምስረታው ጀምሮ ስለነበረበትረና አሁን ስለደረሰበት የገለፁ ሲሆን፣ በተለይ ፋብሪካው ኪሳራ ማስመዝገቡን፣ የኢትዮጵ የልማት ባንክ አብዛኛዎቹ አገልግሎት መስጠት ያቆሙ ማሽኖች ያሉት ድርጅት መረከቡንና በፋብሪካው የነበረው የሰው ኃይል ወደሌላ ተቋም እየለቀቀ እንደነበር ገልፀዋል፡፡ ባንኩ ያበደረው ሃብት ባክኖ እንዳይቀር ባደረገው ጥናት መሰረት በሽርክና አብረው ሊሰሩ የሚችሉ ተቋማት ስላልነበሩ ማኔጅመንቱን እራሱ ተረክቦ ድርጅቱን ውጤታማ ለማድረግ በመወሰን ወደተግባር መገባቱም ነው የተገለፀው፡፡

ባንኩ ፋብሪካውን ከተረከበ በኋላ የመደባቸው የራሱ ሠራተኞች የድርጅቱን መሰረታዊ ክፍተቶች በመለየትና ስትራቴጂያዊ ዕቅድ በማዘጋጀት ወደተግባር መገባቱና በርካታ  ማሽኖች ተጠግነው ማምረት እንዲጀምሩ መደረጉ፣ ከዚህ በፊት ፋብሪካው 400  ሠራተኞች ብቻ የነበሩት ሲሆን፣በአሁኑ ወቅት ከ1050 በላይ ሠራተኞችን ቀጥሮ እየሠራ መገኘቱ፣ አሁን ላይ ከ1.7 ቢሊዮን ጠቅላላ ዓመታዊ ሽያጭ መፈፀም የሚያስችል አቅም የፈጠረ  ሲሆን፣ በበጀት ዓመቱ መጨረሻ 189 ሚሊዮን ብር በላይ ትርፍ ለማስመዝገብ አቅዶ  መስራቱ ባንኩ በፋብሪካው ውስጥ መሰረታዊ ለውጥ እንዲፈጠር ያሳለፈው ውሳኔ ማሳያ ነውም ተብሏል፡፡

በተመሳሳይ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር የሥርዓት ግንባታ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዝናቡ ይርጋ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የህዝብን ሀብት በመጠበቅና የሰጠው ብድር መልሶ እንዲያገግም እየሰራው ያለው ተግባር የሚበረታታ እና እውቅና ሊሰጠው የሚገባ መሆኑን ነው የገለፁት።

የአስተዳደሩ የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ትዕግስቱ አምሳሉ በበኩላቸው ባንኩ የፖሊሲ ባንክ በመሆኑ ሀገሪቱ የምታዎጣቸውን የልማት ፖሊሲን በፋይናንስ የመደገፍ ተግባር ነው የሚሰራው፤ አሁን ግን ተቋማትን በመደገፍና ውጤታማ እንዲሆኑ እያደረገ ያለው ተግባር አዲስ ተሞክሮ ሊሆን የሚችል እና መተዋወቅ የሚገባው ተግባር ነው ብለዋል፡፡

የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አቶ ኃብታሙ ኃይለሚካኤል በጉብኝቱ ማጠቃለያ ወቅት እንዳሉት ድርጅቱ በእውቀት እየተመራ መሆኑን መመልከታቸውን፤ ከዓመታ ስራ ማቆም በኋላ በባንኩ ስትራቴጂካዊ ድጋፍና ክትትል ከፍተኛ ለውጥ ማስመዝገብ የቻለው ቀን ከሌት በመስራት ያመጣ በመሆኑ በአስተዳደሩ ስም ማመስገን ይገባል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም አሁን ካየናቸውና ከተመዘገቡ መልካም ውጤቶች በተጨማሪ ቀጣይ ስኬቶችን ለማስመዝገብ የገበያ ትስስርና መፍጠር፣ ምርቶቹን በስፋት ማስተዋወቅ፣ስትራቴጂውን እንደገና መከለስ፣የምርት አማራጮችን ማስፋት፣ከወጪ ንግድ ጋር የተገናኙ ተግባራትን  ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው የመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር በኤምኤንኤስ ቴክስታይል ፋብሪካ ተገኝቶ ክትትልና ድጋፍ ማድረጉ፣ባንኩ ፋብሪካውን ተረክቦ ማስተዳደር ከጀመረ በኋላ ያስመዘገባቸውን ውጤቶች መመልከቱና በቀጣይ በሚኖሩ ድጋፎች ዙሪያ እና ፋብሪካውን የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ ከባንኩ ጎን መሆኑን አመስግነው ፣ትኩረት ያስፈልጋቸዋል ተብለው በአስተዳደሩ የተሰጡ አስተያይቶችን መነሻ በማድረግ ባንኩ እንደሚሰራ ነው   ፕሬዚዳንቱ ያስታወቁት።
👍373