Development Bank of Ethiopia (DBE)
22.9K subscribers
2.23K photos
83 videos
4 files
631 links
The development bank of Ethiopia (DBE) is one of the financial institutions engaged in providing short, medium and long term development credits.
Download Telegram
Development Bank of Ethiopia
Exchange rate, Applicable Tuesday, July 14, 2026

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚሰጣቸውን እለታዊ የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት ለማግኘት ካዛንችስ ጆሴፍ ብሮዝ ቲቶ መንገድ በሚገኘው የዋና መስሪያ ቤት ኮርፖሬት ቅርንጫፍ ጎራ ይበሉ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፡-

ዘወትር በስራ ሰዓት በስልክ ቁጥር 0115546495 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

ከባንካችን የሚለቀቁ ማናቸውንም መረጃዎች ለማግኘት የማህበራዊ ትስስር ገጾቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን::

ዌብሳይት፡- www.dbe.com.et
ፌስቡክ፡- https://web.facebook.com/dbethiopia

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!

#exchangerate #DBE #Ethiopia
6
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የኢኮኖሚ ዕድገትን እና የዘርፍ አፈጻጸምን ገምግሟል
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ 7ኛ መደበኛ ስብሰባውን በማካሄድ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ዕድገት፣ የዋጋ ግሽበት፣ የበጀት ጉድለት እና የውጭ ኢኮኖሚ ሁኔታን በዝርዝር ገምግሟል።
እንደ ኮሚቴው መግለጫ፣ የሀገሪቱ የውስጥ ኢኮኖሚ ዕድገት ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን፣ ባለፈው በጀት ዓመት 9.2 በመቶ አማካይ ዕድገት መመዝገቡ ተረጋግጧል። ይህ አፈጻጸም ባለፉት ስምንት ዓመታት በአማካይ ተመዝግቦ ከነበረው 7.5 በመቶ ዕድገት የላቀ መሆኑን ኮሚቴው ጠቅሷል። ዕድገቱ በተለይ በግብርና እና በኢንዱስትሪ ዘርፎች ከፍተኛ አስተዋጽኦ የተመዘገበበት ሲሆን፣ የኢንዱስትሪው ዘርፍ 3.7 በመቶ፣ የግብርናው ዘርፍ ደግሞ 2.3 በመቶ ድርሻ አበርክተዋል። ይህ ውጤት የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙ ተስፋ ሰጪ በሆነ አቅጣጫ ላይ መሆኑን የሚያሳይ ነው። በኢንዱስትሪው ዘርፍ እየታየ ያለው የማኑፋክቸሪንግ መስፋፋት፣ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት፣ የሲሚንቶ፣ የብረት እና የብረት ውጤቶች ምርት መጨመር ለቀጣዩ በጀት ዓመት ከዚህ የተሻለ ውጤት እንደሚመዘገብ አመላካች መሆኑን ኮሚቴው ገምግሟል።
በመጨረሻም ኮሚቴው ለወደፊት ኢኮኖሚያዊ መረጋጋት እና የዋጋ ግሽበትን ለመቀነስ የሚያግዙ የፖሊሲ ምክረ-ሃሳቦችን አቅርቧል፤ እነዚህም የብድር ጣሪያን ተግባራዊ ማድረግ፣ የባንኮችን የብድርና ተቀማጭ ገንዘብ ምጣኔ ማስተካከል፣ የውጭ ምንዛሬ የመጠባበቂያ ግዴታን ዝቅ ማድረግ እና የወለድ ምጣኔን መሠረት ያደረገ የገንዘብ ፖሊሲን ማጠናከር ላይ ያነጣጠሩ ናቸው።
👍41
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
Follow , like and share our social media pages!
................................
Development Bank of Ethiopia!

Your development partner!
👍102👏2
የማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችንን ይወዳጁ፤ ያጋሩ!
👍3
Development Bank of Ethiopia
Exchange rate, Applicable Wednesday, July 15, 2026

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚሰጣቸውን እለታዊ የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት ለማግኘት ካዛንችስ ጆሴፍ ብሮዝ ቲቶ መንገድ በሚገኘው የዋና መስሪያ ቤት ኮርፖሬት ቅርንጫፍ ጎራ ይበሉ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፡-

ዘወትር በስራ ሰዓት በስልክ ቁጥር 0115546495 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

ከባንካችን የሚለቀቁ ማናቸውንም መረጃዎች ለማግኘት የማህበራዊ ትስስር ገጾቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን::

ዌብሳይት፡- www.dbe.com.et
ፌስቡክ፡- https://web.facebook.com/dbethiopia

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!

#exchangerate #DBE #Ethiopia
👍42
5
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሥርዓተ-ፆታ እኩልነትና ማህበራዊ አካታችነት (GESI) ክፍል የባንኩን የፋይናንስ አገልግሎቶች የአገሪቱን ህጎች መሰረት በማድረግ ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ፍትሃዊ፣ አካታችና ውጤታማ በሆነ መልኩ ተደራሽ ለማድረግ የተዋቀረ ክፍል ነው።
ክፍሉ በሕገ-መንግስቱ የተረጋገጡ መብቶችን በማክበር፣ ታሪካዊና መዋቅራዊ ክፍተቶችን ለመቅረፍ እንዲሁም ሴቶችና ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎች በውሳኔ ሰጪነት እንዲሁም የፋይናንስ ዘርፍ ያላቸውን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማሳደግ ይሰራል።
ግልጽነት፣ ተጠያቂነት እና በመረጃ ላይ የተመሰረተ አሰራርን እንደ መርህ በመያዝ፣ አድሎአዊ አሰራሮችን በማስወገድ ዘላቂ የልማት ግቦችን ለማሳካት ሴት የባንኩ ሰራተኞች ባንኩ የያዘውን እቅድ ከግብ እንዲመታ በትጋት እንዲሰሩ በማስተባበር የሚተጋ ይሆናል።
ሙሉውን የሥርዓተ-ፆታ ፖሊሲያችንን ለማንበብ ድረ-ገጻችንን ይጎብኙ።


The Development Bank of Ethiopia’s (DBE) Gender Equality and Social Inclusion (GESI) Department is dedicated to ensuring that the Bank’s financial services are equitable, inclusive, and effective for all Ethiopians, in full alignment with national laws. Guided by the constitutional rights of all citizens, the department works to bridge historical and structural gaps, aiming to enhance the participation and benefit of women and marginalized groups in both financial inclusion and decision-making roles. By upholding principles of transparency, accountability, and evidence-based practice, the department strive to eliminate discriminatory practices and achieve sustainable development goals, while coordinating with dedicated female staff to ensure the Bank’s strategic objectives are successfully realized. For further information and to read our full policy, please visit the bank website. #DBE #GESI #GenderEquality #InclusiveFinance #Ethiopia
9
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
👍7
Development Bank of Ethiopia
Exchange rate, Applicable Thursday, July 16, 2026

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚሰጣቸውን እለታዊ የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት ለማግኘት ካዛንችስ ጆሴፍ ብሮዝ ቲቶ መንገድ በሚገኘው የዋና መስሪያ ቤት ኮርፖሬት ቅርንጫፍ ጎራ ይበሉ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፡-

ዘወትር በስራ ሰዓት በስልክ ቁጥር 0115546495 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

ከባንካችን የሚለቀቁ ማናቸውንም መረጃዎች ለማግኘት የማህበራዊ ትስስር ገጾቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን::

ዌብሳይት፡- www.dbe.com.et
ፌስቡክ፡- https://web.facebook.com/dbethiopia

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!

#exchangerate #DBE #Ethiopia
2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
Follow , like and share our social media pages!
................................
Development Bank of Ethiopia!

Your development partner!
3
ለምን ገዘፈ?
በአፍሪካ ስመ-ጥር የፖሊሲ ባንኮች ይሰደሩ ቢባል፣ ከቀዳሚዎቹ ረድፍ ላይ ስሙ ይነበባል።
አርማውን በግብሩ የኳለው ይህ ባንክ፣ የቁጭት ታሪኮችን በልማት ትርክት ተክቷል።
ሀገር በድንግል መሬቷ ፀጋ እንድትለማ፣ ከውድ ማዕድናቶቿ በረከት እንድትቋደስ፣ የጎጆ ኢንዱስትሪ እንዲዘምንና የውጪ ንግድ እንዲስፋፋ አስችሏል።
ማምረት ብቻ ሳይሆን እሴትን ጨምሮ ማቀነባበር፣ ለጥራት ብቻ ሳይሆን ለላቀ ጥራት፣ የሐሳብ እና የልማት ውጥኖች ግዘፍ ይነሱ ዘንድ ለ117 ዓመታት ያለማቋረጥ ሰርቷል።
ይህ፣ ከብዙ የስኬት ታሪኮች በጥቂቱ የተዘገነ የአንጋፋው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ታሪክ ነው።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አሁን ላይ በግዝፈቱና ባለው አጠቃላይ ሀብት ከአፍሪካ የፖሊሲ ባንኮች ቀዳሚዎች ተርታ ውስጥ ገብቷል።
ጥያቄው፣ "የዚህ ግዝፈት ምንጭ ምንድን ነው?" የሚለው ነው። ውሃን ከጥሩው እንዲሉ፣ ርዕይ እና ተልዕኮ ቀዳሚው ሆኖ እናገኘዋለን።
ባንኩ "የግብርና እና የንግድ የኢትዮጵያ ማህበር" በሚል ስያሜ በ1901 ዓ.ም ልዩ የፋይናንስ ተቋም ሆኖ ተመሰረተ።
የመንግሥት የልማት ውጥኖችን መሠረት አድርጎ፣ አዋጭ ለሆኑ ፕሮጀክቶች ፈጣን፣ አስተማማኝ እና ቀጣይነት ያለው የፋይናንስ እና የቴክኒክ ድጋፍ ማቅረቡ ደግሞ "ልዩ" የመባሉ መገለጫ ነው።
ይህ፣ ቀጣዩን ትውልድ ታሳቢ ያደረገ: ሀገር የማሻገር የጠራ ርዕይ ባንኩ አሁን ላለበት ግዝፈት መሠረቱን በአለት ላይ አድርጎታል ።
የዘርፍ ልየታ ደግሞ ሁለተኛው ምክንያት ነው። የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ግዙፍ ኢንቨስትመንቶችን ፋይናንስ ያደርጋል። እርሻ፣ የመስኖ ግብርና፣ የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ፣ የመፈብረኪያ ተቋማት (Manufacturing)፣ የከበሩ ማዕድናት ኢንዱስትሪዎች፣ የኃይል ማመንጫ፣ የጤና ዘርፍ እና የውጭ ምንዛሬ የሚያስገኙ ፕሮጀክቶች ተጠቃሾች ናቸው።
እነዚህ ዘርፎች እንደ ኢንቨስትመንታቸው ሁሉ የገዘፈ ሀብት የሚፈጥሩ፣ ኢኮኖሚውን በሰፊና ቀጣይነት ባለው የሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በቴክኖሎጂ ማላመድና ሽግግር፣ ብሎም በውጭ ምንዛሬ ግኝት የሚደግፉ ናቸው።
ያ ማለት፣ የፖሊሲ ባንኩ እንደ በንግድ ላይ እንደተሰማሩ ባንኮች ከፍተኛ ትርፍ ለማስመዝገብ (Profit Maximization) ሳይሆን፣ በከፍተኛ ደረጃ የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ለውጥ በሚያመጡ ፕሮጀክቶች ላይ በማተኮር የትርፍ ፍልስፍናውን ትርክት እንዲለይ ያስቻለ ነው።
ሌላኛው ነጥብ የብድር ዘመን እና የጊዜ ርዝማኔ (Loan Maturity) ነው።
የፖሊሲ ባንኮች የመካከለኛ እና የረጅም ጊዜ (Medium to Long-term) ብድር ይሰጣሉ።ይህ አልሚዎች ፋብሪካዎችን ጨምሮ ግዙፍ ኢንቨስትመንቶቻቸው ሥራ ጀምረው ገቢ እስኪያመነጩ ድረስ የሚኖረውን የሀብት ፈጠራ ጊዜ የሚሸፍንላቸው ነው።
አደጋ የመጋፈጥ ፍላጎት (Risk Tolerance) ደግሞ ሌላኛው የባንኩ ግዝፈት ምንጭ ነው።
የንግድ ባንኮች ከፍተኛ ስጋት (Risk) ያለባቸውን አዳዲስ የፈጠራ ሥራዎች፣ ትላልቅ የኢንዱስትሪ ግንባታዎችን ወይም ገና ያልተሞከሩ የግብርና ሥራዎችን የመርዳት ፍላጎታቸው አነስተኛ ከመሆኑ ባሻገር፣ በዋስትና ረገድ በጣም ጥብቅ ናቸው።
የፖሊሲ ባንኮች ግን አገራዊ ፋይዳቸው ከፍተኛ ለሆኑ ነገር ግን ስጋት ላለባቸው ፕሮጀክቶች ብድር ለመስጠት ፈቃደኛ ናቸው። ፕሮጀክቱ ሊያመጣ የሚችለው አገራዊ ጥቅም (Social and Economic Return) ከፋይናንስ ስጋቱ በላይ ተመዝኖ ድጋፍ ያደርጋሉ።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከውጭ ሀገርና ዓለም አቀፍ ተቋማት ጭምር የፋይናንስ ምንጭ (Sources of Fund) መሆኑ፣ የብድር ወለድ መጠንን ዝቅተኛ ማድረጉ (Concessional/Subsidized) እና ተያያዥ የመስኩን ሳይንሳዊ እሳቤዎች የምስረታው አምዶች ማድረጉ አሁን ላለበት ከፍታ ትልቅ አበርክቶ አላቸው።
አደረጃጀቱም ቢሆን የግዝፈቱ ምንጭ ነው። ባንኩ አሁን ላይ በመላ ሀገሪቱ በ24 ዲስትሪክቶችና በ100 ቅርንጫፎቹ ልማትና አልሚዎችን ከመቼውም ጊዜ በላይ በቅርበት እያገለገለ ይገኛል። ልማት ባንክ የእድገት ደረጃውን ተከትሎ ራሱን ከየዘመኑ የአሰራር ስርዓት እና ቴክኖሎጂ ጋር ማዘመኑ ተጠቃሽ የከፍታው ምስጢር ነው።
ከቴክኖሎጂ አንፃር ብቻ ብናይ፣ በባንክ ኢንዱስትሪው ከሚጠቀሱት ሥርዓቶች ውስጥ የኮር ባንኪንግ (Core Banking System) አንዱ ነው። ይህ ሥርዓት ባንኩ የውስጥ አሠራሩን፣ የሂሳብ አያያዙንና የሪፖርት አቀራረቡን ዘመናዊና ማዕከላዊ በሆነ የቴክኖሎጂ መዋቅር ላይ እንዲመሰርት አድርጎታል።
ልማት ባንክ ከሀገራት እና ከዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ጋር በትብብር መስራቱ በግዝፈት ታሪኩ ላይ የሚጻፍ ልምድ ነው። ባንኩ ከዓለም የገንዘብ ድርጅት (IMF) እና ከዓለም ባንክ ጨምሮ፣ ከቻይና፣ ጀርመንና ብራዚል ልማት ባንኮች፣ ከብሪታንያ የውጭ ጉዳይ፣ የኮመንዌልዝ እና የልማት ቢሮ (FCDO)፣ ከተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) እና ከመሳሰሉት ጋር በቅርበት መስራቱ ከተቋሙ ድንበር ዘለል ግንኙነት በተጨማሪ ለሀገር መልካም ገጽታ ግንባታ የጎላ ሚና ተጫውቷል።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለዘመናት ዓላማና ግብሩን በአግባቡ ማሰናሰልና መፈጸም መቻሉ ተደምሮ፣ አጠቃላይ የፈጠረው ሀብት በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ የመጀመሪያ ደረጃ ተርታ ካሉ የፖሊሲ ባንኮች ውስጥ እንዲሰለፍ አስችሎታል። ይህ ደግሞ የአንድ ባንክ ስኬት ብቻ ሳይሆን፣ የሀገር ኩራትና ጌጥነት መገለጫ ጭምር የሆነ የድል ታሪክ ነው።
#DBE#Ethiopia#FinanceNews#Bank
15
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
#DBE#mining#Ethiopia#GoldMarket
Development Bank of Ethiopia
Exchange rate, Applicable Friday, July 17, 2026

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚሰጣቸውን እለታዊ የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት ለማግኘት ካዛንችስ ጆሴፍ ብሮዝ ቲቶ መንገድ በሚገኘው የዋና መስሪያ ቤት ኮርፖሬት ቅርንጫፍ ጎራ ይበሉ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፡-

ዘወትር በስራ ሰዓት በስልክ ቁጥር 0115546495 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

ከባንካችን የሚለቀቁ ማናቸውንም መረጃዎች ለማግኘት የማህበራዊ ትስስር ገጾቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን::

ዌብሳይት፡- www.dbe.com.et
ፌስቡክ፡- https://web.facebook.com/dbethiopia

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!

#exchangerate #DBE #Ethiopia
5
ኢጃራ (ሊዝ) ፋይናንሲንግ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በኢጃራ ፋይናንስ የሚያደርጋቸው የኢኮኖሚ ዘርፎች:-
7👍2