Development Bank of Ethiopia (DBE)
23.3K subscribers
2.11K photos
76 videos
4 files
581 links
The development bank of Ethiopia (DBE) is one of the financial institutions engaged in providing short, medium and long term development credits.
Download Telegram
በኮርፖሬት ገቨርናንስና ፋይናንስ ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫና የውይይት መድረክ ተካሔደ፡፡

የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ለኢትዮጵያ ልማት ባንክ የቦርድ አመራሮችና የማኔጅመንት አባላት በኮርፖሬት ገቨርናንስና ፋይናንስ ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናና ውይይት አካሔዷል፡፡

የግንዛቤ ማስጨበጫና የውይይት መድረኩን በይፋ ያስጀመሩት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር የሥርዓት ግንባታ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዝናቡ ይርጋ ሲሆኑ፣ መድረኩ አስተዳደሩ የተሰጠውን በመንግሥት የልማት ድርጅቶች የዘመናዊ ኩባንያ አስተዳደር የመዘርጋትና የልማት ድርጅቶችን ዓለማቀፍ ተወዳዳሪና ውጤታማ የማድረግ ተግባርን መሰረት አድርጎ የተካሔደ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ የልማት ባንክ በተካሔደ የለውጥ እንቅስቃሴ ወደትርፋማነት የመጣና በጥሩ አመራሮችና ሠራተኞች እጅ ያለ ተቋም እንደሆነ የገለጹት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ የዘመናዊ ኩባንያ አሰራርን መዘርጋትና ለበለጠ ውጤታማነት አሰራርን በጥናት እያዳበሩ መሄድ ትኩረት የሚሰጠው ተግባር ነው ብለዋል፡፡

በግንዛቤ ማስጨበጫና የውይይት መድረኩ የኮርፖሬት ገቨርናንስና ፋይናንስ መሪ ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ መጠሪያሽ ኃይለጊዮርጊስ የኮርፖሬት ገቨርናንስን በተመለከተ እንዲሁም የትራንስፎርሜሽንና አቅም ግንባታ መሪ ሥራአስፈጻሚ አቶ ሰይፉ ዋሼ ደግሞ ኮርፖሬት ፋይናንስን በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነድ አቅርበዋል፡፡

የኮርፖሬት ገቨርናንስና ፋይናንስ ሥርዓት በዕቅድ ተካቶ፣ 13 መመሪያዎች ተዘጋጅተውለትና ክትትልና ድጋፍ እየተደረገ በትኩረት ከሚሰራባቸው ቀዳሚ ሀገራዊ ተቋማት አንዱ የሆነው የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ሲሆን፣ በዚህ ሂደትም አብዛኛዎቹን የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ከኪሳራ ወጥተው ወደትርፋማነት እንዲሸጋገሩ ማድረግ ችሏል፡፡
❤16👍15👏1🤝1
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ተልዕኮውን ለማሳካት የመንግስትን የልማትና የትኩረት አቅጣጫ መሰረት በማድረግ፣ ከሀገር ውስጥና ከውጭ የብድር ገንዘብ በማሰባሰብ አዋጭ ለሆኑና ለተመረጡ የልማት ፕሮጀክቶች የፋይናንስና የቴክኒክ ድጋፍ የሚያደርግ የገንዘብ ተቋም ነው፡፡
ባንኩ በአሁኑ ጊዜ የሚሰጠውን ድጋፍ በማስፋፋት በልዩ ልዩ የኢንቨስትመንት መስኮች ለመሳተፍ ፍላጎት፣ እውቀት እና ሙያ ኖሯቸው በካፒታል እጥረት ምክነያት መንቀሳቀስ ላልቻሉ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የካፒታል ዕቃ ኪራይ/ሊዝ ፋይናንሲንግ አገልግሎት በመስጠት የአገሪቱን ኢኮኖሚያዊ እድገት ለመደገፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
👍50❤12👏3
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ አደረሳችሁ!

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
👍23❤3🤝1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ልዩ የፋናንስ ተቋም ሆኖ፣ የመንግሥት የልማት አቅጣጫን መሠረት በማድረግ አዋጪ ለሆኑ የልማት ፕሮጀክቶች ከሀገር ውስጥና ከውጪ የብድር ገንዘብ በማሰባሰብ የፋይናንስና የቴክኒክ ድጋፍ በመስጠት የተሰጠውን አገራዊ ኃላፊነት እየተወጣ ያለ የፖሊሲ ባንክ ነው፡፡ ባንኩ ከጊዜ ወደ ጊዜ ተደራሽነቱን እያሰፋ ይገኛል፡፡
በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሊዝ ፋይናንስ የብድር አገልግሎት ተጠቃሚ ከሆኑን ከራሰቸው አልፈው አካባቢያቸውን መቀየር የቻሉ በርካታ ሰዎችን ታሪካቸው መማሪያ ይሆን ዘንድ በቴሌቭዥን ፕሮግራማችን እያቀረብን መሆኑ ይታወቃል፡፡ ዛሬ ደግሞ ወደ ቦንጋ ተጉዘን የባንካችን ደንበኛ የሆነ ወጣት ታሪክ ይዘን ቀርበናል ተከታተሉ፡፡
👍24❤10
የግብርና ግብዓቶች ላይ ያለንን አቅም ማጎልበት፤ በአርብቶ አደርና ቆላማ አካባቢዎች ያለውን ልማት ማፋጠን የትኩረት አቅጣጫችን ነው

ለኢንቨስትመንት መሠረቱ መሬት፣ ካፒታል እና የሰው ኃይል እንዲሁም ቴክኖሎጂ ናቸው፡፡ መሬት ለማምረቻ ኢንዱስትሪም ሆነ በግብርና ዘርፍ ለሚደረግ ኢንቨስትመንት ቁልፉ ግብዓት ነው፡፡ አንድ ኢንዱስትሪ ለመትከል መሬት፤ የግብርና ምርት ለማምረትም የሚታረሰው መሬት መኖር ግድ ይላል፡፡

መሬት በሌለበት ግብርናም ፋብሪካም አይታሰብም፡፡ ከዚህ አኳያ አገራችን ለኢንዱስትሪም ሆነ ለግብርና መሰረታዊ የሆነው ግብዓት ያላት አገር መሆኗ በተደጋጋሚ ይጠቀሳል፡፡ በመሆኑም አንድ ሰው ወደ ኢንቨስትመንት ለመግባት በየአካባቢው ያለውን ይህን የግብዓት አቅም ማየት እና መጠቀም ይገባዋል ማለት ነው፡፡

የሰው ኃይልም ለአንድ ኢኮኖሚ ግንባታ ወሳኝ ነው፡፡ በአንድ ሀገር ውስጥ የሚኖር እውቀት እና የመስራት አቅም ያለው ሕዝብ ለኢኮኖሚው መሰረት ነው፡፡ በሰው ኃይል አቅም ያደገ አገር አገራዊ ኢኮኖሚውን ውጤታማ በማድረግ በኩል የተሻለ እድል እንዳለው እሙን ነው፡፡

ሌላው ለኢንቨስትመንት መሰረት የሚሆነው ካፒታል ነው፡፡ ካፒታል ጥሬ ገንዘብ ማለት ብቻ ሳይሆን ጥሬ ገንዘቡ ለምርት ግብዓት በሚውሉ ማሽኖች ሲመነዘር ማለት ነው፡፡ በመሆኑም ካፒታል ማለት በኢኮኖሚ ውስጥ ተመንዝሮ ትርፍ ሊያመጣ የሚችል የሥራ መሳሪያ እንደማለት ነው፡፡ በመሆኑም የሰው ኃይል፣ መሬት እና ካፒታል እንዲሁም ቴክኖሎጂን አቀናጅቶ በመጠቀም ለገበያ የሚያስፈልገውን ምርትም ሆነ አገልግሎት ማቅረብ መቻል ከራስ አልፎ በአገር ደረጃ ኢኮኖሚያዊ ለውጥ ለማምጣት ወሳኝ ነው፡፡ በአጠቃላይ መሬት፤ የሰው ኃይል እና ካፒታል ከቴክኖሎጂ ጋር ተደምሮ ምርታማነትን በማሳደግ ለኢኮኖሚያዊ እድገት መሰረት ነው፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከላይ የተጠቀሱት አገራዊ አቅሞችን አቀናጅቶ ወደ ምርት ለመግባት የተዘጋጀ ኃይልን የምርታማነት መሰረት የሆነውን የፋይናንስ ችግር በመቅረፍ ላለፉት ዓመታት በአጋርነት መቆም የቻለ አስተማማኝ የልማት አጋር ነው፡፡ ባንኩ በተለያዩ ጊዜያት ሀገራዊ ፋይዳቸው ከፍ ያሉ ሁነቶችን ስፖንሰር በማድረግ የአምራች ዘርፉን ለማበረታታት እና በዘርፉ ያሉ ተግዳሮቶች ላይ ውይይት በማድረግ ማነቆች እንዲፈቱ እያደረገ ይገኛል፡፡

እንደሚታወቀው በአገራችን ከትላልቅ እስከ መካከለኛ እርሻዎችን ለማልማት መስኖ ጥቅም ላይ ሲውል ቆይቷል። የተፈጥሮ ሀብትና የመስኖ ቴክኖሎጂን በአግባቡ መጠቀም በአገራችን የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ እንደሚያስችል ይታመናል፡፡ የኢትዮጵያ ቆላማና አርብቶ አደር አካባቢዎች ከዚህ አኳያ ሊሰጡ የሚችሉት ጥቅምና ዕድሎች በመመዘን በእነዚህ አካባቢዎች የሚደረግ ኢንቨስትመንት ባንኩ ያበረታታል፤ ድጋፍም ያደርጋል፡፡ በኢትዮጵያ ቆላማ አካባቢዎች የሚገኘውን ሰፊ መሬት፣ ውሃ፣ እንስሳትና የሰው ሀብት በመጠቀም አገሪቱ የልማት ተልዕኮዋን እንድታሳካ ባንኩ የመስኖና ቆላማ አካባቢ የልማት እንቅስቃሴዎችን ለመደገፍ የራሱን ድርሻ እየተወጣ ይገኛል፡፡

ከሰሞኑ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር በሚሊኒየም አዳራሽ እንዲሁም የግብርና ሚኒስቴር በኤግዚቢሽን ማዕከል ያዘጋጁትን ኤግዚቢሽን ባንካችን አጋር የሆነው በግብርና ግብዓቶች እና በአርብቶ አደርና ቆላማ አካባቢዎች ባሉ የልማት አቅሞች ላይ ግንዛቤ እንዲያዝ ካለው መሠረታዊ ፍላጎት በመነጨ ነው፡፡

የምስራቅ አፍሪካ አርብቶ አደሮች ኤክስፖ "አርብቶ አደርነት የምስራቅ አፍሪካ ኅብረቀለም" በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ሲሆን የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ኤክስፖው አርብቶ አደሩ ለአገራዊ ኢኮኖሚ ዕድገት ጉልህ ድርሻ እንዳለው በመገንዘብ ነው ኤክስፖውን በአጋርነት ያዘጋጀው፡፡ በአርብቶ አደሩ አካባቢ ያለውን እምቅ ጸጋ በመጠቀም የአገርን ልማት ማረጋገጥ እንደሚገባ በማመን ባንካችን በአካባቢው የሚደረጉ የልማት እንቅስቃሴዎችን በሙሉ አቅሙ ለማገዝም ዝግጁ መሆኑን አረጋግጧል፡፡

በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በግብርና ዘርፍ ላይ የወለድ ተመን በማሻሻል ዘርፉን ከመደገፍ ባሻገር የግብርና ሚኒስቴር የግብርና ዘርፉን ለማበረታታት የፋይናንስ አቅርቦትን ማሳደግ ወሳኝ መሆኑን ለማሳየት እንዲሁም አምራቹ እና ሸማቹን ለማገናኘት ያዘጋጀው ባዛር አጋር በመሆኑ ባንኩ ለአገር ልማት እያደረገ ያለውን አበርክቶት በተግባር ማረጋገጥ ችሏል፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
👍29❤3
የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲዊ ሪፐብሊክ መንግሥት በዐሥር ዓመት የኢኮኖሚ ልማት መሪ ዕቅዱ ዋነኛ የትኵረት አቅጣጫ አድርጎ ከያዛቸው ጉዳዮች አንዱ የመስኖ እና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ነው፡፡

ይህን ግብ እውን ለማድረግ የፋይናንስ አቅርቦት ወሳኝ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ እንደ አንድ የመንግስትን የልማት እቅድ ለማሳለጥ የሚሰራ የፋይይናንስ ተቋም የግብርና ዘርፍ አገልግሎት ባንኩ አገልግሎት ከሚሰጥባቸው ዋነኛውና ቁልፉ የኢኮኖሚ ዘርፍ ነው፡፡

ባንኩ ዘመናዊ ግብርናን በከፍተኛ የፋይናንስ አቅርቦት በተከታታይ በመደገፍ ይታወቃል፡፡ በፕሮጀክት ፋይናንሲንግ የብድር አቅርቦት አሰራር በመስኖ ሊለሙ የሚችሉ ሜካናይዝድ ዘመናዊ የግብርና ፕሮጄክቶችን፣ ዘመናዊ እንስሳት እርባታ ፕሮጀክቶችን፣ ዘመናዊ የዶሮ እርባታ ፕሮጀክቶችን በዋናነት ፋይናንስ ያደርጋል፡፡ በተጨማሪም ከላይ የተጠቀሱትን ዓይነት ፕሮጀክቶች ለመደገፍ ሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት የሚያቀርቡትን ፈንድ በማስተዳደርም የኢትዮጵያ ልማት በሀገሪቱ እንዲስፋፋ ይሠራል፡፡

አርብቶ አደርና ቆላማ አካባቢዎች ላይ ባንኩ የሚያረቧቸውን እንስሳት እንደ ማስያዣ ተጠቅሞ በዘመናዊ እርባታ ሥራ ለሚኖራቸው ተሳትፎ አጋር ለመሆን እየተንቀሳቀሰ ነው፡፡ እንስሳት እርባታን በተለይም ከብቶችንና በጎችን ፍየሎችን (Livestock) በዘመናዊ መንገድ የማርባት ፕሮጀክቶችን ከዘመናዊ መኖ (feed) ዝግጅት (ምርት) ጋር አዛምደው ለሚሠሩ አርብቶ አደሮችና ቆላማ አካባቢ ባለሀብቶች ተመራጭ አገልግሎት ይዞ ቀርቧል፡፡

መስኖን ለሚጠቀሙ ዘመናዊ እርሻዎች (ሰብል እና ፍራፍሬ ልማት) ላይ ለሚሰማሩም ከፍተኛ አገልግሎት ይሰጣል፡፡ ቆላማ አካባቢዎች ለዶሮ እርባታ ተስማሚ በመሆናቸው በዚህ ረገድ ያለውንም የባንኩን አገልግሎት በስፋት መጠቀም ይችላሉ፡፡ አርብቶ አደሮች በሚገኙባቸውና ቆላማ በሆኑ አካባባዎች የሚገኙ የባንኩ ዲስትሪክቶችና ቅርንጫፎችም በፕሮጀክት ፋይናንሲንግ አገልግሎት ማኅበረሰቡን ለመደገፍ እየተንቀሳቀሱ ነው፡፡

አዋሽ አካባቢ የሚገኙ በመስኖ የሚለሙ እርሻዎች ለዚህ እንደ ምሳሌ ይጠቀሳሉ፡፡ በሊዝ ፋይናንሲንግ ለግብርና ልማት በተለይ በሰብል ምርት፣ በእንስሳት እርባታ፣ በመኖ ዝግጅትና በመሳሰሉ ዘርፎች (cultivating land, raising and harvesting crops, and feeding, breeding, and raising livestock) የሚጠቅሙ ማሽነሪዎችን፣ ልዩ ልዩ መሣሪያዎችን፣ አስፈላጊ ዕቃዎችን በኪራይ አገልግሎት (Lease Financing) ለደንበኞች ያቀርባል፡፡ በዚህ ረገድ በእነዚህ አርብቶ አደርና ቆላማ አካባቢዎችን የሚሸፍኑ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዲስትሪክትና ቅርንጫፎች እስከ አሁን በግብርና ሜካናይዜሽን የእርሻ ትራክተርና ኮምባይን ሃርቨስተሮችን፣ ውሃ ፓምፖችን፣ የወተት ሀብትን የማቀነባበር ሥራ የሚሠራባቸውን መሣሪያዎች፣ የዳቦ መጋጋሪያ ማሽኖችን፣ ዱቄት ማምረቻዎችን፣ ፕላስቲክ ማዳበሪያ ማምረቻዎችን እና ሌሎችንም ማሽነሪዎች በባንኩ እቃ ኪራይ አገልግሎት ለቆላማ አካባቢዎች የሚጠቅሙ መሣሪያዎችን እያቀረበ ነው፡፡

የመስኖ እርሻን ለጥቅም ከማዋል አንጻርም ባንኩ ከአገልግሎት አቅራቢዎች (Service Providers) ጋር በመሥራት የውሃ ቁፋሮ ከሚያካሂዱና የለማውን ውሃ ለቆላማ አካባቢ ለሚገኙ ገበሬዎች በመስኖ ውሃውን በማቅረብ እርሻ ሥራዎችን በመደገፍ ላይ ነው፡፡
👍28❤4
የገጠር ፋይናንስ አቅርቦት ማሻሻያ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በ306 ሚሊዮን ዶላር ገንዘብ የገጠር ፋይናንስ አቅርቦት ማሻሻያ ፕሮግራም(RUFIP)ን ተግባራዊ እያደረገ ነው፡፡ ፕሮግራሙ በገጠር ያሉ በርካታ ቤተሰቦችን ኖሮአቸውን የሚያሻሽል፣ ድህነትን የሚቀንስ በገቢና ንብረት በማፍራት በኩል አቅም የማጠናከር ሥራ የሚሠራ ሲሆን፣ እስከ 11,000 በሚደርሱ የማኅብራት ኅብረትና በገጠር አነስተኛ የፋይናነስ ተቋማት(RFIs) ሀገር አቀፍ ኔትዎርክ በኩል ተደራሽ የሚሆን አገልግሎት ነው፡፡ የገጠር የፋይናንስ አቅርቦት ማሻሻያ ፕሮግራም (RUFIP) አሁን ባለው ሶስተኛ ዙር ፕሮግራሙ (2020-2026) አርብቶ አደሮችን የፋይናንስ አገልግሎት ተካታችነት የበለጠ የሚያረጋግጥ ሆኖ እየተሠራ ነው፡፡

በተለይም በአፋር እና ሶማሌ ክልሎች ያሉ አርብቶ አደር ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበራት በኢትዮጵያ አነስተኛና የፋይናንስ አገልግሎት ተቋማት ማኅበር እና በክልሎች የኅብረት ሥራ ማስፋፋያ ቢሮዎች በኩል የዚህ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየተሠራ ነው፡፡ ባንኩ የአሠልጣኞች ሥልጠናን፣ ተቋማዊ አቅም ግንባታን፣ የአቅም ግንባታ የጉብኝት መርሐ ግብሮችን፣ የቴክኒክ ባለሙያዎችን የማብቃት ሥራን፣ የገጠር የቁጠባና ብድር ማኅበራት ኅብረት ኮሚቴ አባላትን የማነቃቃት፣ ለኅብረቶቹ የማስፋፋያ፣ ኦዲተርና የሒሳብ ባለሙያዎችን በኮንትራት መቅጠርን፣ ተሸከርካሪዎች ግዢ የመሳሰሉትን አቅም ግንባታ ሥራዎች በቀጥታ ይሠራል፡፡

የአደጋ ስጋት ቅነሳና አካታች የአርብቶ አደር ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮጀክት (DRIVE) የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አርብቶ አደር ማኅበረሰቡን ለማገልገል በቅርቡ ለመተግበር እየተንቀሳቀሰባቸው ካሉ ፕሮጀክቶች አንዱ የአርብቶ አደር ኢኮኖሚ አደጋ ተጋላጭነት ቅነሳና የፋይናነስ አካታችነት ፕሮጀክት (DRIVE) ነው፡፡ ይህ ፕሮጀክት የሚተገበረው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከንግድ ሚኒስቴር፣ ከግብርና ሚኒስቴር ጋር በመሆን በፈጸመው የሦስትዮሽ ስምምነት ነው፡፡ የሚተገበረውም በአፋር፣ ሶማሊ፣ ኦሮሚያ፣ ደቡብ ኢትዮጵያ፣ ደቡብ ምዕራብ ክልሎች ነው፡፡ ይህም አርብቶ አደሮች የፋይናንስ አገልግሎት ተደራሽነታቸውን ለማሳደግና የቁም ከብት ንግድ በአፍሪካ ቀንድ እንዲስፋፋ የሚግዝ ነው፡፡ የሚያተኩረውም በእንስሳት ሀብት ልማት (Livestock) ላይ ሲሆን ቁም ከብቶችን በኤክስፖርት ደረጃ ለማርባት ከዓለም ባንክ በተገኘ 20,000,000 USD ድጋፍ የሚተገበር ነው፡፡

ይህ አገልግሎትም መስፈርቱን አሟልተው ለሚቀርቡ የግል ባለሀብቶች እና መስፈርቱን አሟልተው ለሚቀርቡ አርብቶ አደር ወጣቶችና ሴቶች ኅብረት ስራ ማኅበራት በሚሰጥ የፋይናነስ አገልግሎት ይሆናል፡፡ ለዚህ አገልግሎትም ባንኩ ቁም ከብትን ጨምሮ ተገቢ ያላቸውን ተንቀሳቃሽ ማስያዣዎች የሚጠይቅ ይሆናል፡፡
👍29❤5🤝3
👍23❤1