Development Bank of Ethiopia (DBE)
23.3K subscribers
2.11K photos
76 videos
4 files
580 links
The development bank of Ethiopia (DBE) is one of the financial institutions engaged in providing short, medium and long term development credits.
Download Telegram
በኮርፖሬት ገቨርናንስና ፋይናንስ ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫና የውይይት መድረክ ተካሔደ፡፡

የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ለኢትዮጵያ ልማት ባንክ የቦርድ አመራሮችና የማኔጅመንት አባላት በኮርፖሬት ገቨርናንስና ፋይናንስ ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናና ውይይት አካሔዷል፡፡

የግንዛቤ ማስጨበጫና የውይይት መድረኩን በይፋ ያስጀመሩት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር የሥርዓት ግንባታ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዝናቡ ይርጋ ሲሆኑ፣ መድረኩ አስተዳደሩ የተሰጠውን በመንግሥት የልማት ድርጅቶች የዘመናዊ ኩባንያ አስተዳደር የመዘርጋትና የልማት ድርጅቶችን ዓለማቀፍ ተወዳዳሪና ውጤታማ የማድረግ ተግባርን መሰረት አድርጎ የተካሔደ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ የልማት ባንክ በተካሔደ የለውጥ እንቅስቃሴ ወደትርፋማነት የመጣና በጥሩ አመራሮችና ሠራተኞች እጅ ያለ ተቋም እንደሆነ የገለጹት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ የዘመናዊ ኩባንያ አሰራርን መዘርጋትና ለበለጠ ውጤታማነት አሰራርን በጥናት እያዳበሩ መሄድ ትኩረት የሚሰጠው ተግባር ነው ብለዋል፡፡

በግንዛቤ ማስጨበጫና የውይይት መድረኩ የኮርፖሬት ገቨርናንስና ፋይናንስ መሪ ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ መጠሪያሽ ኃይለጊዮርጊስ የኮርፖሬት ገቨርናንስን በተመለከተ እንዲሁም የትራንስፎርሜሽንና አቅም ግንባታ መሪ ሥራአስፈጻሚ አቶ ሰይፉ ዋሼ ደግሞ ኮርፖሬት ፋይናንስን በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነድ አቅርበዋል፡፡

የኮርፖሬት ገቨርናንስና ፋይናንስ ሥርዓት በዕቅድ ተካቶ፣ 13 መመሪያዎች ተዘጋጅተውለትና ክትትልና ድጋፍ እየተደረገ በትኩረት ከሚሰራባቸው ቀዳሚ ሀገራዊ ተቋማት አንዱ የሆነው የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ሲሆን፣ በዚህ ሂደትም አብዛኛዎቹን የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ከኪሳራ ወጥተው ወደትርፋማነት እንዲሸጋገሩ ማድረግ ችሏል፡፡
❤16👍15👏1🤝1
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ተልዕኮውን ለማሳካት የመንግስትን የልማትና የትኩረት አቅጣጫ መሰረት በማድረግ፣ ከሀገር ውስጥና ከውጭ የብድር ገንዘብ በማሰባሰብ አዋጭ ለሆኑና ለተመረጡ የልማት ፕሮጀክቶች የፋይናንስና የቴክኒክ ድጋፍ የሚያደርግ የገንዘብ ተቋም ነው፡፡
ባንኩ በአሁኑ ጊዜ የሚሰጠውን ድጋፍ በማስፋፋት በልዩ ልዩ የኢንቨስትመንት መስኮች ለመሳተፍ ፍላጎት፣ እውቀት እና ሙያ ኖሯቸው በካፒታል እጥረት ምክነያት መንቀሳቀስ ላልቻሉ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የካፒታል ዕቃ ኪራይ/ሊዝ ፋይናንሲንግ አገልግሎት በመስጠት የአገሪቱን ኢኮኖሚያዊ እድገት ለመደገፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
👍50❤12👏3
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ አደረሳችሁ!

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
👍23❤3🤝1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ልዩ የፋናንስ ተቋም ሆኖ፣ የመንግሥት የልማት አቅጣጫን መሠረት በማድረግ አዋጪ ለሆኑ የልማት ፕሮጀክቶች ከሀገር ውስጥና ከውጪ የብድር ገንዘብ በማሰባሰብ የፋይናንስና የቴክኒክ ድጋፍ በመስጠት የተሰጠውን አገራዊ ኃላፊነት እየተወጣ ያለ የፖሊሲ ባንክ ነው፡፡ ባንኩ ከጊዜ ወደ ጊዜ ተደራሽነቱን እያሰፋ ይገኛል፡፡
በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሊዝ ፋይናንስ የብድር አገልግሎት ተጠቃሚ ከሆኑን ከራሰቸው አልፈው አካባቢያቸውን መቀየር የቻሉ በርካታ ሰዎችን ታሪካቸው መማሪያ ይሆን ዘንድ በቴሌቭዥን ፕሮግራማችን እያቀረብን መሆኑ ይታወቃል፡፡ ዛሬ ደግሞ ወደ ቦንጋ ተጉዘን የባንካችን ደንበኛ የሆነ ወጣት ታሪክ ይዘን ቀርበናል ተከታተሉ፡፡
👍24❤10
የግብርና ግብዓቶች ላይ ያለንን አቅም ማጎልበት፤ በአርብቶ አደርና ቆላማ አካባቢዎች ያለውን ልማት ማፋጠን የትኩረት አቅጣጫችን ነው

ለኢንቨስትመንት መሠረቱ መሬት፣ ካፒታል እና የሰው ኃይል እንዲሁም ቴክኖሎጂ ናቸው፡፡ መሬት ለማምረቻ ኢንዱስትሪም ሆነ በግብርና ዘርፍ ለሚደረግ ኢንቨስትመንት ቁልፉ ግብዓት ነው፡፡ አንድ ኢንዱስትሪ ለመትከል መሬት፤ የግብርና ምርት ለማምረትም የሚታረሰው መሬት መኖር ግድ ይላል፡፡

መሬት በሌለበት ግብርናም ፋብሪካም አይታሰብም፡፡ ከዚህ አኳያ አገራችን ለኢንዱስትሪም ሆነ ለግብርና መሰረታዊ የሆነው ግብዓት ያላት አገር መሆኗ በተደጋጋሚ ይጠቀሳል፡፡ በመሆኑም አንድ ሰው ወደ ኢንቨስትመንት ለመግባት በየአካባቢው ያለውን ይህን የግብዓት አቅም ማየት እና መጠቀም ይገባዋል ማለት ነው፡፡

የሰው ኃይልም ለአንድ ኢኮኖሚ ግንባታ ወሳኝ ነው፡፡ በአንድ ሀገር ውስጥ የሚኖር እውቀት እና የመስራት አቅም ያለው ሕዝብ ለኢኮኖሚው መሰረት ነው፡፡ በሰው ኃይል አቅም ያደገ አገር አገራዊ ኢኮኖሚውን ውጤታማ በማድረግ በኩል የተሻለ እድል እንዳለው እሙን ነው፡፡

ሌላው ለኢንቨስትመንት መሰረት የሚሆነው ካፒታል ነው፡፡ ካፒታል ጥሬ ገንዘብ ማለት ብቻ ሳይሆን ጥሬ ገንዘቡ ለምርት ግብዓት በሚውሉ ማሽኖች ሲመነዘር ማለት ነው፡፡ በመሆኑም ካፒታል ማለት በኢኮኖሚ ውስጥ ተመንዝሮ ትርፍ ሊያመጣ የሚችል የሥራ መሳሪያ እንደማለት ነው፡፡ በመሆኑም የሰው ኃይል፣ መሬት እና ካፒታል እንዲሁም ቴክኖሎጂን አቀናጅቶ በመጠቀም ለገበያ የሚያስፈልገውን ምርትም ሆነ አገልግሎት ማቅረብ መቻል ከራስ አልፎ በአገር ደረጃ ኢኮኖሚያዊ ለውጥ ለማምጣት ወሳኝ ነው፡፡ በአጠቃላይ መሬት፤ የሰው ኃይል እና ካፒታል ከቴክኖሎጂ ጋር ተደምሮ ምርታማነትን በማሳደግ ለኢኮኖሚያዊ እድገት መሰረት ነው፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከላይ የተጠቀሱት አገራዊ አቅሞችን አቀናጅቶ ወደ ምርት ለመግባት የተዘጋጀ ኃይልን የምርታማነት መሰረት የሆነውን የፋይናንስ ችግር በመቅረፍ ላለፉት ዓመታት በአጋርነት መቆም የቻለ አስተማማኝ የልማት አጋር ነው፡፡ ባንኩ በተለያዩ ጊዜያት ሀገራዊ ፋይዳቸው ከፍ ያሉ ሁነቶችን ስፖንሰር በማድረግ የአምራች ዘርፉን ለማበረታታት እና በዘርፉ ያሉ ተግዳሮቶች ላይ ውይይት በማድረግ ማነቆች እንዲፈቱ እያደረገ ይገኛል፡፡

እንደሚታወቀው በአገራችን ከትላልቅ እስከ መካከለኛ እርሻዎችን ለማልማት መስኖ ጥቅም ላይ ሲውል ቆይቷል። የተፈጥሮ ሀብትና የመስኖ ቴክኖሎጂን በአግባቡ መጠቀም በአገራችን የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ እንደሚያስችል ይታመናል፡፡ የኢትዮጵያ ቆላማና አርብቶ አደር አካባቢዎች ከዚህ አኳያ ሊሰጡ የሚችሉት ጥቅምና ዕድሎች በመመዘን በእነዚህ አካባቢዎች የሚደረግ ኢንቨስትመንት ባንኩ ያበረታታል፤ ድጋፍም ያደርጋል፡፡ በኢትዮጵያ ቆላማ አካባቢዎች የሚገኘውን ሰፊ መሬት፣ ውሃ፣ እንስሳትና የሰው ሀብት በመጠቀም አገሪቱ የልማት ተልዕኮዋን እንድታሳካ ባንኩ የመስኖና ቆላማ አካባቢ የልማት እንቅስቃሴዎችን ለመደገፍ የራሱን ድርሻ እየተወጣ ይገኛል፡፡

ከሰሞኑ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር በሚሊኒየም አዳራሽ እንዲሁም የግብርና ሚኒስቴር በኤግዚቢሽን ማዕከል ያዘጋጁትን ኤግዚቢሽን ባንካችን አጋር የሆነው በግብርና ግብዓቶች እና በአርብቶ አደርና ቆላማ አካባቢዎች ባሉ የልማት አቅሞች ላይ ግንዛቤ እንዲያዝ ካለው መሠረታዊ ፍላጎት በመነጨ ነው፡፡

የምስራቅ አፍሪካ አርብቶ አደሮች ኤክስፖ "አርብቶ አደርነት የምስራቅ አፍሪካ ኅብረቀለም" በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ሲሆን የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ኤክስፖው አርብቶ አደሩ ለአገራዊ ኢኮኖሚ ዕድገት ጉልህ ድርሻ እንዳለው በመገንዘብ ነው ኤክስፖውን በአጋርነት ያዘጋጀው፡፡ በአርብቶ አደሩ አካባቢ ያለውን እምቅ ጸጋ በመጠቀም የአገርን ልማት ማረጋገጥ እንደሚገባ በማመን ባንካችን በአካባቢው የሚደረጉ የልማት እንቅስቃሴዎችን በሙሉ አቅሙ ለማገዝም ዝግጁ መሆኑን አረጋግጧል፡፡

በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በግብርና ዘርፍ ላይ የወለድ ተመን በማሻሻል ዘርፉን ከመደገፍ ባሻገር የግብርና ሚኒስቴር የግብርና ዘርፉን ለማበረታታት የፋይናንስ አቅርቦትን ማሳደግ ወሳኝ መሆኑን ለማሳየት እንዲሁም አምራቹ እና ሸማቹን ለማገናኘት ያዘጋጀው ባዛር አጋር በመሆኑ ባንኩ ለአገር ልማት እያደረገ ያለውን አበርክቶት በተግባር ማረጋገጥ ችሏል፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
👍29❤3