Development Bank of Ethiopia (DBE)
23.3K subscribers
2.11K photos
76 videos
4 files
580 links
The development bank of Ethiopia (DBE) is one of the financial institutions engaged in providing short, medium and long term development credits.
Download Telegram
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዲስትሪክትን የመስክ ምልከታ በማድረግ የስራ እንቅስቃሴውን ጎበኙ::

የቋሚ ኮሚቴው ቡድን አስተባባሪ የተከበሩ አቶ እያሱ ዛላ እንዳሉት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በክልሉ የሰራው ሥራ አድንቀው ለፕሮጀክቶቹ መፋጠን እና ለስራው ውጤታማነት የተበዳሪዎች የስልጠና ቀድሞ መውሰድ ውጤቱን ከፍ አድርጎታል፡፡

አስተባባሪው አያይዘውም ባንኩ ሲሰጥ የነበረው የአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተር ፕራይዝ አንቀሳቃሾች ስልጠና ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል::

ቋሚ ኮሚቴው በባንኩ ብድር ተመቻችቶላቸው ምርት የጀመሩ የተለያዩ አምራች ተቋማትን በአካል ተገኝተው ምልከታ አድርገዋል::

በሌላ በኩል ባንኩ በደንበኝነት የሚያውቃቸው ተበዳሪዎች ቋሚ ኮሚቴው ባንኩ የሰጠውን ብድር የት እንደደረሰ ለመመልከት በጠየቀበት ጊዜ ድርጅታቸውን ማስጎብኘታቸው ባለሀብቱ እና ባንኩ ያላቸውን መደጋገፍ የሚያሳይ መሆኑንም በምልከታቸው ወቅት መታዘባቸውን ገልጸዋል፡፡

በአከባቢው ከሚለማው ፕሮጀክት ቀዳሚ የሆነውን የቡና ልማት ፕሮጀክትን ቋሚ ኮሚቴው በተመለከተበት ወቅት በዘርፉ ለሚታየው የቡና ገበያ መቀዛቀዝ መንግስት መፍትሔ እንዲሰጣችው አልሚዎች ጠይቀዋል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው ለኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሚዛን ቅርንጫፍ ምርታማነትን ለማረጋገጥ እና ለሚፈለገው የሥራ መስክ የሚያደርገው ድጋፍ ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ጠቁሞ፣ በቡና ልማቱ ዙሪያ የገበያ ትስስሩ ድጋፍ ማጠናከር እንደሚገባም አስገንዝቧል::

በመጨረሻም የቋሚ ኮሚቴው አስተባባሪ አቶ እያሱ ባንኩ ከነበረበት ችግር ተላቆ በሀገር ደረጃ እያበረከተ ያለው አስተዋጽጾ የሚደነቅ መሆኑን ገልጸው ፣ባለድርሻ አካላት ድጋፍ ማድርግ ከቻሉ በባንኩ እየተመዘገበ ያለው ለውጥ እና እድገት ከዚህም ሊልቅ የሚችል ነው ሲሉ በመስክ ተገኝተው ምልከታና ጉብኝት ለተሳተፉ የቋሚ ኮሚቴ አባላት እና ለባንኩ አመራሮች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚለቃቸውን ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ዌብሳይት፡- www.dbe.com.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/dbethiopia
ቴሌግራም፦ https://t.me/DBE1900
ትዊተር፡- https://twitter.com/DBE_Ethiopia
ሊንክድኢን፡- https://www.linkedin.com/in/dbe1900/
ዩቱብ:- https://www.youtube.com/@developmentbankofethiopia

በመወዳጀት፣ ለሌሎች በማጋራትና ገንቢ አስተያየትዎን በመስጠት ቤተሰብ ይሁኑ፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
👍35❤4👏1
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ባለፉት ጥቂት ዓመታት እያስመዘገባቸው ያሉ ስኬቶች ባንኩ በለውጥ ጎዳና ላይ እንዳለ የሚያረጋግጡ ናቸው፡፡ ባንኩ ትናንትን ተሻግሮ ዛሬ ላይ ለውጥ እያመጣ ያለ ባንክ ሲሆን የልማት አጋርነቱን በተጨባጭ ማሳየት የቻለ እና ለሀገራችን ልማት መፋጠን እየተጋ ያለ ባንክ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በሌሎች ሀገራት እንደሚገኙ ውጤታማ የልማት ባንኮች በሀገራችን ኢኮኖሚያዊ እድገትና ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ ግልጽ ተልዕኮ በማስቀመጥ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡

ባንኩ እቅዶቹን፣ በተጨባጭ እያስመዘገባቸው ያሉ ለውጦችን፣ በባንኩ እገዛ አገር መጥቀም የቻሉ ፕሮጀክቶችን ለመከታተልና አጠቃላይ ከባንካችን የሚለቀቁ ማናቸውንም መረጃዎች ለማግኘት የማህበራዊ ትስስር ገጾቻችንን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡

ዌብሳይት፡- www.dbe.com.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/dbethiopia
ቴሌግራም፦ https://t.me/DBE1900
ትዊተር፡- https://twitter.com/DBE_Ethiopia
ሊንክድኢን፡- https://www.linkedin.com/in/dbe1900/
ዩቱብ:- https://www.youtube.com/@developmentbankofethiopia

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
👍22❤5🤝3
የአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ለአንድ አገር እድገት ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ፡፡ በተለይ ከፍተኛ የሆነ የስራ እድል በመፍጠር፣ የውጭ ምንዛሬ በማስገኘት፣ ከውጭ የሚገቡ ምርቶች በአገር ውስጥ አንዲተኩ በማድረግ እና የቴክኖሎጂ ሽግግርን በማምጣት በኩል ላቅ ያለ ፋይዳ አላቸው፡፡
የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች አገራችን ወደ ኢንዱስትሪ የምታደርገውን መዋቅራዊ ሽግግር የሚያፋጥኑ በመሆኑ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ኢንተርፕራይዞቹ ከልማዳዊ አሰራር ተላቀው የንግድ ስራቸው ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ እንዲመራ የአቅም ግንባታ ስልጠና በመስጠት ይደግፋል፡፡
ዌብሳይት፡- www.dbe.com.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/dbethiopia
ቴሌግራም፦ https://t.me/DBE1900
ትዊተር፡- https://twitter.com/DBE_Ethiopia
ሊንክድኢን፡- https://www.linkedin.com/in/dbe1900/
ዩቱብ:- https://www.youtube.com/@developmentbankofethiopia
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
👍32❤11
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የግብርና ሜካናዬዝሽንን በመደገፍ የግብርና ስራውን ማዘመን ላይ ትኩረት አድርጎ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ በዚህም በግብርና ስራ ላይ የሚወጣውን ጉልበት በመቆጠብ እና ምርታማነትን በመጨመር የጎላ ድርሻ እየተወጣ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው፡፡
👍41❤9🤝1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ተጠቃሚ ካደረጋቸው የሊዝ ፋይናንስ ደንበኞች መካከል የቦንጋ ዲስትሪክት ደንበኛችን አቶ አሸናፊ ዳመታ አንዱ ናቸው፡፡ የዛሬው የስኬት በስተጀርባ አሹ የቤትና የቢሮ እቃዎች ማምረቻ ድርጅት የስራ እንቅስቃሴን ይዳስሳል፡፡
👍17❤7
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓልን ምክንያት በማድረግ ልዩ የበዓል ዝግጅት አሰናድቶ ታህሳስ 28 በኢቲቪ ዜና ቻናል ከ8 እስከ 10 ሰዓት ይጠብቃችኋል፡፡

እየተዝናኑ በጎ መስራትን የሚመለከቱበት፣ በሰዎች ደስታ ውስጥ የሚገኝ ልዩ ደስታን የሚያጣጥሙበት፣ አገር በሰው ልብ እንደሚሰራ የሚማሩበት ልዩ የበዓል ዝግጅት አሰናድቶ ይጠብቃችኋል፡፡ እንዳያመልጣችሁ፡፡

መልካም በዓል፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
👍36❤2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ለመላው የክርስትና እምነት ተካታዮች
እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
❤28👍7
❤17👍10
❤31👍9
በኮርፖሬት ገቨርናንስና ፋይናንስ ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫና የውይይት መድረክ ተካሔደ፡፡

የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ለኢትዮጵያ ልማት ባንክ የቦርድ አመራሮችና የማኔጅመንት አባላት በኮርፖሬት ገቨርናንስና ፋይናንስ ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናና ውይይት አካሔዷል፡፡

የግንዛቤ ማስጨበጫና የውይይት መድረኩን በይፋ ያስጀመሩት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር የሥርዓት ግንባታ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዝናቡ ይርጋ ሲሆኑ፣ መድረኩ አስተዳደሩ የተሰጠውን በመንግሥት የልማት ድርጅቶች የዘመናዊ ኩባንያ አስተዳደር የመዘርጋትና የልማት ድርጅቶችን ዓለማቀፍ ተወዳዳሪና ውጤታማ የማድረግ ተግባርን መሰረት አድርጎ የተካሔደ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ የልማት ባንክ በተካሔደ የለውጥ እንቅስቃሴ ወደትርፋማነት የመጣና በጥሩ አመራሮችና ሠራተኞች እጅ ያለ ተቋም እንደሆነ የገለጹት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ የዘመናዊ ኩባንያ አሰራርን መዘርጋትና ለበለጠ ውጤታማነት አሰራርን በጥናት እያዳበሩ መሄድ ትኩረት የሚሰጠው ተግባር ነው ብለዋል፡፡

በግንዛቤ ማስጨበጫና የውይይት መድረኩ የኮርፖሬት ገቨርናንስና ፋይናንስ መሪ ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ መጠሪያሽ ኃይለጊዮርጊስ የኮርፖሬት ገቨርናንስን በተመለከተ እንዲሁም የትራንስፎርሜሽንና አቅም ግንባታ መሪ ሥራአስፈጻሚ አቶ ሰይፉ ዋሼ ደግሞ ኮርፖሬት ፋይናንስን በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነድ አቅርበዋል፡፡

የኮርፖሬት ገቨርናንስና ፋይናንስ ሥርዓት በዕቅድ ተካቶ፣ 13 መመሪያዎች ተዘጋጅተውለትና ክትትልና ድጋፍ እየተደረገ በትኩረት ከሚሰራባቸው ቀዳሚ ሀገራዊ ተቋማት አንዱ የሆነው የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ሲሆን፣ በዚህ ሂደትም አብዛኛዎቹን የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ከኪሳራ ወጥተው ወደትርፋማነት እንዲሸጋገሩ ማድረግ ችሏል፡፡
❤16👍15👏1🤝1
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ተልዕኮውን ለማሳካት የመንግስትን የልማትና የትኩረት አቅጣጫ መሰረት በማድረግ፣ ከሀገር ውስጥና ከውጭ የብድር ገንዘብ በማሰባሰብ አዋጭ ለሆኑና ለተመረጡ የልማት ፕሮጀክቶች የፋይናንስና የቴክኒክ ድጋፍ የሚያደርግ የገንዘብ ተቋም ነው፡፡
ባንኩ በአሁኑ ጊዜ የሚሰጠውን ድጋፍ በማስፋፋት በልዩ ልዩ የኢንቨስትመንት መስኮች ለመሳተፍ ፍላጎት፣ እውቀት እና ሙያ ኖሯቸው በካፒታል እጥረት ምክነያት መንቀሳቀስ ላልቻሉ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የካፒታል ዕቃ ኪራይ/ሊዝ ፋይናንሲንግ አገልግሎት በመስጠት የአገሪቱን ኢኮኖሚያዊ እድገት ለመደገፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
👍50❤12👏3