Development Bank of Ethiopia (DBE)
23.3K subscribers
2.1K photos
76 videos
4 files
579 links
The development bank of Ethiopia (DBE) is one of the financial institutions engaged in providing short, medium and long term development credits.
Download Telegram
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሊዝ ፋይናንሲንግ አገልግሎት ከነበረበት 2 ቢሊየን ብር ወደ 11 ቢሊየን ብር አደገ፡፡

ከሰሞኑ በግብርና ዘርፍ ለተሰማሩ ደንበኞቹ 15 ትራክተርና 10 ኮምባይን ሀርቨስተር እንዲሁም በማዕድን ዘርፍ ለተሰማሩ ደንበኞቹ 14 ኤክስካቫተር በሊዝ ፋይናንሲንግ አገልግሎት ዘርፍ አቅርቧል።

የኮምባይን ሀርቨስተር መሳሪያዎቹ 72 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚገመቱ ሲሆን፤ ትራክተሮቹ ከ43 ሚሊዮን ብር በላይ እንዲሁም ኤክስካቫተሮቹ  áЍ87 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ መሆናቸው ነው በርክክብ ስርዓቱ ላይ የተገለጸው።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ዶክተር ዮሐንስ አያሌው፤ ባንኩ ላለፉት አምስት ዓመታት የተለያዩ የሪፎርም ሥራዎችን አከናውኖ በኢትዮጵያ ካሉ ባንኮች ሁለተኛውን ከፍተኛ ካፒታል ማስመዝገብ መቻሉን በርክክቡ ወቅት ገልጸዋል።

በግብርና፣ በኢንዱስትሪ፣ በማዕድን፣ አገልግሎትና ሌሎችም ዘርፎች  ለተሰማሩ ዜጎች የሚያደርገው ድጋፍ በየጊዜው እድገት እያሳየ መሆኑንም አንስተዋል።

በተያዘው በጀት ዓመት ባንኩ ለደንበኞች ለማቅረብ ካቀደው 51 ቢሊዮን ብር ውስጥ 15 ቢሊዮን ብር የሚሆነውን ለግብርና ዘርፉ የተመደበ መሆኑንም ገልፀዋል።

በግብርናው ዘርፍ የተደረገው ግብርና ማሽነሪዎች ርክክብ የግብርና ሜካናይዜሽንን በማጠናከር የምርት ብክነትን ለመቀነስ የሚያስችል ከመሆኑም ባሻገር የአርሶ አደሩን ጊዜና ጉልበት ለመቆጠብ አስተዋፅዖ የሚኖረው መሆኑንም አስረድተዋል።
የግብርና ዘርፉን ማዘመንና ምርታማነቱን ማሳደግ ኢንዱስትሪዎች በቂ ጥሬ ዕቃ አግኝተው በሙሉ አቅማቸው እንዲያመርቱ እገዛ ያደርጋልም ተብሏል።

በማዕድን ዘርፉ የተሰጡ መሳሪያዎችም አገሪቱ በዘርፉ ያላትን ሰፊ ዕድል እንድትጠቀም የሚያስችል መሆኑን ጠቅሰው፤ በሊዝ ፋይናንሲንግ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ባንኩ በትኩረት እየሰራ መሆኑም ነው የተገለጸው።

ባንኩ ለ486 ደንበኞች ከ580 በላይ ለግብርና አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዘመናዊ ማሽነሪዎችን ከ100 በላይ የሚሆኑ ለማዕድን ዘርፉ የሚያግዙ  ኤክስካቫተሮችን ለደንበኞቹ ማቅረቡንም ተናግረዋል።

አቶ እንዳለ መኩሪያ እና አቶ ፈይሳ  ቡታ፤ የተረከቧቸው መሳሪያዎች ሥራቸውን የሚያዘምኑ ከመሆናቸው ባሻገር ገቢ ምርቶችን ለመተካትና ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶችን ለማሳደግ የሚያስችሉ መሆኑን ገልፀዋል።

ሌላኛው ተረካቢ አቶ ዳንኤል ወልደሰንበት፤ የተረከቡት ኤክስካቫተር በተሰማሩበት የማዕድን ዘርፉ የላቀ ጠቀሜታ የሚሰጣቸው መሆኑን ተናግረዋል ።
👍41❤7
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የቴክኖሎጂ አቅሙን በማሳደግ በዘመናዊ ቴክኖሎጅ የታገዙ አገልግሎቶችን ለመስጠት የሚያስችለውን ስራ እየሰራ እንደሚገኝ አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት (ዩኒዶ) ጋር በመተባበር በቴክኖሎጂ መተግበሪያዎች ዙሪያ ስልጠና ለአመራሮች ሰጥቷል፡፡

በስልጠናው የመክፈቻ ፕሮግራም ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የባንኩ የኮርፖሬት አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው በላይ ባለቤትነቱ የዩኒዶ የሆነው ኮንፋር የተሰኘው መተግበሪያ በአለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያለው የፕሮጀክት ብድር ጥናትና ትንተና  መተግበሪያ ነው፡፡  የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዋነኛ ስራም የፕሮጀክት ብድር አቅርቦት መሆኑን ያመላከቱት አቶ ጌታቸው በዘመናዊ ቴክኖሎጅ የተደገፈ ፈጣንና አስተማማኝ አገልግሎት ለመስጠት ከዮኒዶ ጋር እየተሰራ እንደሚገኝ እና ባንኩ መተግበሪያዉን መጠቀም የሚያስችለውን 100 ላይሰንስ ከዩኒዶ መግዛቱንም ገልጸዋል፡፡

መተግበሪያው ከዚህ ቀደም ብድር ለማጽደቅ የሚፈጀውን ጊዜ እንደሚያሳጥር እና ከባለሙያ ስህተት በጸዳ መልኩ ሙሉ በሙሉ በዘመናዊ ቴክኖሎጅ የሚሰራ መሆኑን የገለጹት ም/ል ፕሬዝዳንቱ በቴክኖሎጅው ለመጠቀም ለባንኩ የስራ ሀላፊዎች ከዩኒዶ በመጡ አስልጣኞች እንዲሰለጥኑ መደረጉን  ጠቁመዋል፡፡

ባንኩ ትልቅ የቴክኖሎጅ አቅም እየፈጠረ ነው ያሉት አቶ ጌታቸው ይህም ባንኩ በ5 ዓመት የስትራቴጅክ ዕቅዱ አካቶ እየፈጸመው እንደሚገኝም ገልጸዋል፡፡

በሁለት ዙሮች ተከፍሎ የሚሰጠው ስልጠና ለ15 ቀን የሚቆይ ሲሆን ከሁሉም ዲስትሪክቶች እና ከዋናው መስሪያ ቤት ለተመረጡ የስራ ሀላፊዎች የሚሰጥ ስልጠና ነው፡፡
👍43❤9
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የአምራች ኢንዱስትሪውን ዘርፍ ለማበረታታት ከመቼውም ጊዜ በላይ በትኩረት እንደሚሰራ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ባዘጋጀው "የኛ ምርት" ኤግዚቢሽንና ባዛር ላይ አሳውቋል፡፡

ባንኩ በስካይ ላይት ሆቴል ከታህሳስ 3 እስከ 7 ቀን 2016 ዓ.ም የተካሄደውን ኤግዚቢሽንና ባዛር ስፖንሰር በማድርግ አምራች እና ሸማቹ እንዲገናኝ የራሱን አስተዋጽዖ አበርክቷል፡፡ ኤግዚቢሽንና ባዛሩን ያዘጋጀው የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዞች ልማት አምራቹ ያለበትን የፋይናንስ ችግር ለመፍታት መወሰድ በሚገባቸው እርምጃዎች እና በአጠቃላይ የአምራቹን ዘርፍ የሚያበረታቱ አገራዊ አቅሞችን በተመለከተ በቂ ግንዛቤ እንዲያዝ በማድረግ በኩል ላቅ ያለ አበርክቶት እንደሚኖረው የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አለባቸው ንጉሴ ተናግረዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ እንደገለፁት እንደሀገር በዘርፋ በስፋት ለመሰማራት የሚያስችል ሰፊ የሰው ኃይል፣ የግብርናና የተፈጥሮ ሀብት እንዲሁም ሰፊ የገበያ ዕድል ያለ በመሆኑ ይህን አስተባባሮ በመምራትና በመደገፍ መንቀሳቀስ ይገባል፡፡ በአነስተኛና መካከለኛ አምራች ዘርፍ እንደሀገር መሰረት መሆን የሚችሉ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ያብራሩት ዶ/ር አለባቸው ሀገራዊ አቅማችንን በማጠናከር ተጨማሪ ጥረቶችን ማድረግ እንደሚጠበቅ አስገንዝበዋል፡፡

"ኢትዮጵያ ታምርት፤ እኛም እንሸምት" በሚል መሪ ሃሳብ በተካሄደው የፖናል ውይይት ላይ የሀገር ውስጥ ምርቶችን የመጠቀም ልማድና የማሻሻያ ሃሳቦች፣ ኢንዱስትሪያላይዜሽንን በመገንባት ሂደት የመንግስት ሚና፣ ለአምራች ኢንተርፕራይዞች ልማት የፋይናንስ ተቋማት ሚና በሚሉ ርዕሶች ሰፊና ገንቢ ውይይቶች ተደርገዋል፡፡

ከኤግዚቢሽንና ባዛሩ ጎን ለጎን በተካሄደው የፓናል ውይይት የአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች ለኢንዱስትሪ ልማትና ግንባታ ያላቸው ሚናና ዘርፉ በኢኮኖሚው ውስጥ የሚኖረውን ድርሻ በላቀ ደረጃ ለማሳደግ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችና ምቹ ሁኔታና ተግዳሮች ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት ተደርጓል፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው፣ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አለባቸው ንጉሴ፣ በአምራች ኢንተርፕራይዝ ዘርፍ ረጅም ልምድ ያላቸው ዶ/ር ንግስት ሐይሌ እና የኢንተርፕራይዝ ባለቤት ኢንጅነር አይሸሽም ጥላሁን የተሳተፉበት የፓናል ውይይት የተካሄደ ሲሆን፣ ውይይቱን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል መርተውታል፡፡

አቶ መላኩ አለበል የአምራች ኢንተርፕራይዞች ልማት ለሀገራችን አማራጭ ሳይሆን ዋነኛ የኢኮኖሚ ግንባታ ትኩረት መሆኑን ገልጸው፣ ይህን ታሳቢ ያደረጉ ድጋፎችን በማቅረብ የሀገር ውስጥ አምራቾችን ማበራከት፣ ማጠናከርና የገበያ ድርሻቸውንም ማሻሻል ይገባል ብለዋል።

ሚኒስትሩ አያይዘውም በዘርፉ ተኪ ምርትን ማስፋትና ኤክስፖርትን ማበረታታት እንዲቻል በትኩረት እየተሰራ በመሆኑ ተቋማት ተቀናጅተው መስራት ይኖርባቸዋል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው በበኩላቸው የአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዝ ዘርፍ በዓለም አቀፍ ደረጃ የስራ እድል በመፍጠር፣ አዳዲስና የፈጠራ ሀሳቦች በማመንጨትና ኢኮኖሚያዊ አቅምን በማጠናከር በኩል ጉልህ ድርሻ ያላቸው መሆኑን ያነሱ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ይህን ታሳቢ ያደረገ ስራ እየሰራ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

ባንኩ ለአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ስልጠና ከመስጠት ጀምሮ ኢንተርፕራይዞቹ በፋይናንስ እንዲደገፉ ከፍተኛ ገንዘብ መድቦና በዚህ ላይ የሚሰራ ሰፊ የሰው ኃይል አሰማርቶ እየሰራ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

በተመሳሳይ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለአምራች ኢንተርፕራይዞች እየቀረቡ ባሉ የፋይናንስ አቅርቦቶችና በዚህ ሂደት ውስጥ በሚገኙ የፋይናንስ ተቋማት ሚና ዙሪያ በተደረገው የፓናል ውይይት ላይ የተሳተፉት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ፋይናንሲንግ ም/ፕሬዚዳንት አቶ አስፋው አበራ እንዳሉት የፋይናንስ አቅርቦቱን ለማሻሻል ባንኩ ልዩ መስኮቶችን በመክፈትና ከልዩ ልዩ የፋይናንስ ተቋማት ጋር በመቀናጀት እየሠራ ከመሆኑም በላይ የዘርፉን ልዩ ባህርይ ታሳቢ ያደረጉ አዳዲስ አሠራሮችን በመተግበር ላይ ነው፡፡

በመጨረሻም "ኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት" በሚል መሪ ሃሳብ በኢትዮጵያ ስካይ ላይት ሆቴል የተከፈተውና "የኛ ምርት" የተሰኘው የአምራች ኢንተርፕራይዞች ኤግዚቢሽንና ባዛር የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል እና ሌሎች ሚኒስትሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንዲሁም የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንትና የማኔጅመንት አባላት ባዛሩን የጎበኙ ሲሆን ባዛሩ ኢትዮጵያ የደረሰችበትን የአምራች ኢንተርፕራይዞች ቴክኖሎጂና የምርት እድገት ለመረዳት የሚያስችልና ከኤግዚቢሽንና ባዛሩ በሚገኘው ልምድ የአምራች ኢንተርፕራይዞችን አቅም ለማሳደግና ለማሻሻል የሚረዱ የድጋፍ ማዕቀፎች ለማዘጋጀት የጎላ ሚና እንደሚኖረው ተመላክቷል፡፡

"የኛ ምርት" ኤግዚቢሽንና ባዛር በቀጣይ በየዓመቱ በተመሳሳይ ወቅት ለማካሄድ እቅድ እንደተያዘም ተመላክቷል፡፡

የአምራች ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች በበኩላቸው የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የአገር ውስጥ አምራች ኢንተርፕራይዞች የተሻለ ምርት እንዲያመርቱ ከሚሰጠው ሁሉን አቀፍ ድጋፍ በተጨማሪ ምርቶቻቸው እንዲተዋወቁ ኤግዚቢሽንና ባዛር ማዘጋጀቱን በማመስገን ድጋፉ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው አስገንዝበዋል፡፡ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚለቃቸውን ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ዌብሳይት፡- www.dbe.com.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/dbethiopia
ቴሌግራም፦ https://t.me/DBE1900
ትዊተር፡- https://twitter.com/DBE_Ethiopia
ሊንክድኢን፡- https://www.linkedin.com/in/dbe1900/
ዩቱብ:- https://www.youtube.com/@developmentbankofethiopia

በመወዳጀት፣ ለሌሎች በማጋራትና ገንቢ አስተያየትዎን በመስጠት ቤተሰብ ይሁኑ፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
👍37❤4
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለሊዝ ፋይናንስ ደንበኞች የትራክተር፣ ኮምባይን ሐርቨስተር እና የኤክስካቫተር ማሽነሪዎችን አስረክቧል፡፡ ይህን አስመልክቶ የደንበኞችን አስተያየት እና የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው መልዕክት የተካተተበትን ፕሮግራም መስፈንጠሪያውን በመጫን እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡

https://www.youtube.com/watch?v=C8JfqegidHg

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚለቃቸውን ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ዌብሳይት፡- www.dbe.com.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/dbethiopia
ቴሌግራም፦ https://t.me/DBE1900
ትዊተር፡- https://twitter.com/DBE_Ethiopia
ሊንክድኢን፡- https://www.linkedin.com/in/dbe1900/
ዩቱብ:- https://www.youtube.com/@developmentbankofethiopia

በመወዳጀት፣ ለሌሎች በማጋራትና ገንቢ አስተያየትዎን በመስጠት ቤተሰብ ይሁኑ፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
👍26❤7🤝2