Development Bank of Ethiopia (DBE)
23.3K subscribers
2.1K photos
76 videos
4 files
579 links
The development bank of Ethiopia (DBE) is one of the financial institutions engaged in providing short, medium and long term development credits.
Download Telegram
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሊዝ ፋይናንሲንግ አገልግሎት ከነበረበት 2 ቢሊየን ብር ወደ 11 ቢሊየን ብር አደገ፡፡

ከሰሞኑ በግብርና ዘርፍ ለተሰማሩ ደንበኞቹ 15 ትራክተርና 10 ኮምባይን ሀርቨስተር እንዲሁም በማዕድን ዘርፍ ለተሰማሩ ደንበኞቹ 14 ኤክስካቫተር በሊዝ ፋይናንሲንግ አገልግሎት ዘርፍ አቅርቧል።

የኮምባይን ሀርቨስተር መሳሪያዎቹ 72 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚገመቱ ሲሆን፤ ትራክተሮቹ ከ43 ሚሊዮን ብር በላይ እንዲሁም ኤክስካቫተሮቹ  áЍ87 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ መሆናቸው ነው በርክክብ ስርዓቱ ላይ የተገለጸው።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ዶክተር ዮሐንስ አያሌው፤ ባንኩ ላለፉት አምስት ዓመታት የተለያዩ የሪፎርም ሥራዎችን አከናውኖ በኢትዮጵያ ካሉ ባንኮች ሁለተኛውን ከፍተኛ ካፒታል ማስመዝገብ መቻሉን በርክክቡ ወቅት ገልጸዋል።

በግብርና፣ በኢንዱስትሪ፣ በማዕድን፣ አገልግሎትና ሌሎችም ዘርፎች  ለተሰማሩ ዜጎች የሚያደርገው ድጋፍ በየጊዜው እድገት እያሳየ መሆኑንም አንስተዋል።

በተያዘው በጀት ዓመት ባንኩ ለደንበኞች ለማቅረብ ካቀደው 51 ቢሊዮን ብር ውስጥ 15 ቢሊዮን ብር የሚሆነውን ለግብርና ዘርፉ የተመደበ መሆኑንም ገልፀዋል።

በግብርናው ዘርፍ የተደረገው ግብርና ማሽነሪዎች ርክክብ የግብርና ሜካናይዜሽንን በማጠናከር የምርት ብክነትን ለመቀነስ የሚያስችል ከመሆኑም ባሻገር የአርሶ አደሩን ጊዜና ጉልበት ለመቆጠብ አስተዋፅዖ የሚኖረው መሆኑንም አስረድተዋል።
የግብርና ዘርፉን ማዘመንና ምርታማነቱን ማሳደግ ኢንዱስትሪዎች በቂ ጥሬ ዕቃ አግኝተው በሙሉ አቅማቸው እንዲያመርቱ እገዛ ያደርጋልም ተብሏል።

በማዕድን ዘርፉ የተሰጡ መሳሪያዎችም አገሪቱ በዘርፉ ያላትን ሰፊ ዕድል እንድትጠቀም የሚያስችል መሆኑን ጠቅሰው፤ በሊዝ ፋይናንሲንግ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ባንኩ በትኩረት እየሰራ መሆኑም ነው የተገለጸው።

ባንኩ ለ486 ደንበኞች ከ580 በላይ ለግብርና አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዘመናዊ ማሽነሪዎችን ከ100 በላይ የሚሆኑ ለማዕድን ዘርፉ የሚያግዙ  ኤክስካቫተሮችን ለደንበኞቹ ማቅረቡንም ተናግረዋል።

አቶ እንዳለ መኩሪያ እና አቶ ፈይሳ  ቡታ፤ የተረከቧቸው መሳሪያዎች ሥራቸውን የሚያዘምኑ ከመሆናቸው ባሻገር ገቢ ምርቶችን ለመተካትና ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶችን ለማሳደግ የሚያስችሉ መሆኑን ገልፀዋል።

ሌላኛው ተረካቢ አቶ ዳንኤል ወልደሰንበት፤ የተረከቡት ኤክስካቫተር በተሰማሩበት የማዕድን ዘርፉ የላቀ ጠቀሜታ የሚሰጣቸው መሆኑን ተናግረዋል ።
👍41❤7
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የቴክኖሎጂ አቅሙን በማሳደግ በዘመናዊ ቴክኖሎጅ የታገዙ አገልግሎቶችን ለመስጠት የሚያስችለውን ስራ እየሰራ እንደሚገኝ አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት (ዩኒዶ) ጋር በመተባበር በቴክኖሎጂ መተግበሪያዎች ዙሪያ ስልጠና ለአመራሮች ሰጥቷል፡፡

በስልጠናው የመክፈቻ ፕሮግራም ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የባንኩ የኮርፖሬት አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው በላይ ባለቤትነቱ የዩኒዶ የሆነው ኮንፋር የተሰኘው መተግበሪያ በአለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያለው የፕሮጀክት ብድር ጥናትና ትንተና  መተግበሪያ ነው፡፡  የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዋነኛ ስራም የፕሮጀክት ብድር አቅርቦት መሆኑን ያመላከቱት አቶ ጌታቸው በዘመናዊ ቴክኖሎጅ የተደገፈ ፈጣንና አስተማማኝ አገልግሎት ለመስጠት ከዮኒዶ ጋር እየተሰራ እንደሚገኝ እና ባንኩ መተግበሪያዉን መጠቀም የሚያስችለውን 100 ላይሰንስ ከዩኒዶ መግዛቱንም ገልጸዋል፡፡

መተግበሪያው ከዚህ ቀደም ብድር ለማጽደቅ የሚፈጀውን ጊዜ እንደሚያሳጥር እና ከባለሙያ ስህተት በጸዳ መልኩ ሙሉ በሙሉ በዘመናዊ ቴክኖሎጅ የሚሰራ መሆኑን የገለጹት ም/ል ፕሬዝዳንቱ በቴክኖሎጅው ለመጠቀም ለባንኩ የስራ ሀላፊዎች ከዩኒዶ በመጡ አስልጣኞች እንዲሰለጥኑ መደረጉን  ጠቁመዋል፡፡

ባንኩ ትልቅ የቴክኖሎጅ አቅም እየፈጠረ ነው ያሉት አቶ ጌታቸው ይህም ባንኩ በ5 ዓመት የስትራቴጅክ ዕቅዱ አካቶ እየፈጸመው እንደሚገኝም ገልጸዋል፡፡

በሁለት ዙሮች ተከፍሎ የሚሰጠው ስልጠና ለ15 ቀን የሚቆይ ሲሆን ከሁሉም ዲስትሪክቶች እና ከዋናው መስሪያ ቤት ለተመረጡ የስራ ሀላፊዎች የሚሰጥ ስልጠና ነው፡፡
👍43❤9