Development Bank of Ethiopia (DBE)
23.3K subscribers
2.1K photos
76 videos
4 files
578 links
The development bank of Ethiopia (DBE) is one of the financial institutions engaged in providing short, medium and long term development credits.
Download Telegram
ፕሬስ መግለጫ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የግብርና ዘርፉን በስፋት ለመደገፍ የሚያስችል የወለድ ተመን ማሻሻያ አደረገ።

ማሻሻያው ባንኩ በሊዝ ፋይናንስ እና በፕሮጀክት ፋይናንስ የብድር ሞዳሊቲ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች አካቷል።

ህዳር 20 ቀን፣2016 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በግብርና ዘርፍ ላይ መንግስት እየወሰደ ያለውን እርምጃ ማሳካት እንዲቻልና የግብርና ዘርፍ ኢንቨስትመንትን ለማስፋፋት የወለድ ተመን ማሻሻያ አደረገ፡፡

ባንኩ ዛሬ በላከው የፕሬስ መግለጫ እንዳመላከተው ከምስረታው ጀምሮ ለግብርና ዘርፉ ትኩረት በመስጠት ሲደግፍ የቆየ የፖሊሲ ባንክ መሆኑን በመጥቀስ ግብርናውን ለማሻሻል መንግስት እየወሰደ ያለውን እርምጃ ማሳካት እንዲቻልና የግብርና ሴክተሩን በማነቃቃት በዘርፉ የግል ኢንቨስትመንትን ለማበረታታት እና ለመሳብ የባንኩ የሥራ አመራር ቦርድ የወለድ ተመን ማሻሻያ ማድረጉን አሳውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ባለፉት ዓመታት ባካሄደው ሪፎርም የነበሩበትን ተግዳሮቶች እየቀረፈና አዳዲስ አገልግሎቶችን ለደንበኞች እያቀረበ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ በመግለጫው የተመላከተ ሲሆን ይህ የወለድ ተመን ማሻሻያም ወቅቱን የጠበቀ እና በአገራችን ያለውን ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ማዕከል ያደረገ መሆኑን አብራርቷል፡፡

ባንኩ የወለድ ተመን ማሻሻያ ማድረጉን አስመልክቶ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው እንዳሉት፣ “የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ኢትዮጵያ ያላትን ከፍተኛ የሆነ ያልታረሰ የመሬት ሀብት ወደ ስራ ለማስገባት፤ ባለሀብቶች፣ አርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች የበለጠ እንዲበረታቱ ለማድረግ በግብርና ዘርፍ በአነስተኛ፣ መካከለኛና የኮርፖሬት ፕሮጀክት ብድር ለሚጠይቁ ይጠበቅ የነበረው የ11.5 በመቶ የማበደሪያ የወለድ ተመን ወደ 7 በመቶ ዝቅ አድርጓል።” ፕሬዚዳንቱ አክለውም ባንኩ ስራ ላይ ያዋለው ይህ ማሻሻያ ዘርፉን ለማሳደግ ያቀደው ስትራቴጅያዊ ሪፎርም አካል ሲሆን፣ መንግስት የግብርና ዘርፉን ለማሳደግ እየሰራ ያለውን ስራ የበለጠ የሚያግዝ መሆኑንም ገልፀዋል።

ባንኩ የወለድ ተመን ማሻሻያ ማድረጉ በአምራች ዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶች በጥሬ እቃ አቅርቦት እጥረት ምክንያት የነበረባቸውን ዝቅተኛ የማምረት አቅም በማሻሻልና በውጭ ምንዛሬ የሚገቡ ምርቶችን ለመቀነስ ከመርዳቱም በላይ ሀገራችን በዘርፉ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እንድታገኝ የሚያግዝ መሆኑም ተብራርቷል።

በተጨማሪም የተደረገው የወለድ ተመን ማሻሻያ የምግብና የኢንዱስትሪ ሰብሎች ላይ ያተኮረ ሥራ በኢንቨስተሩ እንዲሰራ የሚያበረታታ ሲሆን፣ የምግብ ፍላጎትንና ለኢንዱስትሪ የሚሆኑ የጥሬ ዕቃዎች አቅርቦት ሙሉ በሙሉ በአገር ውስጥ ምርቶች ከማሟላት ጎን ለጎን፣ የምግብ ዋጋ ንረትን ለማረጋጋትና የውጭ ምንዛሬ አቅምን ለማሳደግ እንደ መንግስት እየተሰራ ያለውን ስራ እንደሚያጠናክር ይጠበቃል።

ለከፍተኛ፣ ለአነስተኛና መካከለኛ የግብርና ፕሮጀክቶች የተደረገው የማበደሪያ ወለድ ምጣኔ ማሻሻያ ባንኩ ለዘርፉ ዕድገት ያለውን ቁርጠኛ አቋም ያሳየበት መሆኑም በመግለጫው ተመላክቷል።

በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሀገራችንን ኢኮኖሚያዊ ልማት በተሻለ ደረጃ እንዲረጋገጡ አሁን በገበያው ውስጥ ካለው ነባራዊ ሁኔታ በመነሳት በተመረጡ ዘርፎች ለተሰማሩ እና ግዙፍ ፕሮጀክቶችን ለሚያነቀሳቅሱ ተበዳሪዎች በሌሎች አገልግሎቶች ላይ መጠነኛ የወለድ ተመን ማሻሻያ ማድረጉ ተጠቁሟል።
👍5614👏1🤝1
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በግብርና ዘርፍ በአነስተኛ፣ መካከለኛና የኮርፖሬት ፕሮጀክት ብድር ለሚጠይቁ ይጠበቅ የነበረው የ11.5 በመቶ የማበደሪያ የወለድ ተመን ወደ 7 በመቶ ዝቅ እንዲል አድርጓል። ይህ ማሻሻያ በግብርና ዘርፍ የሚደረገውን ኢንቨስትመንት የሚያበረታታ ሲሆን እንደ አገር ያሉንን አቅሞች አሟጦ በመጠቀም ኢኮኖሚያዊ ለውጥ ለማምጣት የሚያስችል ነው፡፡ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በግብርና ዘርፍ በአነስተኛ፣ መካከለኛና የኮርፖሬት ፕሮጀክት ብድር ለሚጠይቁ ይጠበቅ የነበረው የ11.5 በመቶ የማበደሪያ የወለድ ተመን ወደ 7 በመቶ ዝቅ እንዲል አድርጓል። ይህ ማሻሻያ በግብርና ዘርፍ የሚደረገውን ኢንቨስትመንት የሚያበረታታ ሲሆን እንደ አገር ያሉንን አቅሞች አሟጦ በመጠቀም ኢኮኖሚያዊ ለውጥ ለማምጣት መሰረት ነው፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
👍44👏2910🤝4
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ "አፍላገ ልማት" የቴሌቪዥን ፕሮግራም በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን እሁድ 2፡50 እስከ 3፡30 የሚተላለፍ ሳምንታዊ ፕሮግራም፡፡

#ከስኬት በስተጀርባ
#የዓለምአቀፍ የልማት ባንኮች ተሞክሮ
#ድራማ

https://youtu.be/HS1ta5eHEpE

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚለቃቸውን ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ዌብሳይት፡- www.dbe.com.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/dbethiopia
ቴሌግራም፦ https://t.me/DBE1900
ትዊተር፡- https://twitter.com/DBE_Ethiopia
ሊንክድኢን፡- https://www.linkedin.com/in/dbe1900/
ዩቱብ:- https://www.youtube.com/@developmentbankofethiopia

በመወዳጀት፣ ለሌሎች በማጋራትና ገንቢ አስተያየትዎን በመስጠት ቤተሰብ ይሁኑ፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
15👍14👏1🤝1
በትጋት የተገኘ ውጤት
ዜማ ያሬድ

ወደ ንግድ አለም የገቡት ገና በልጅነታቸው ነው፡፡ ገጠር ውስጥ በንግድ ላይ ከተሰማሩ ባለሃብት ጋር በመጠጋት ንግድን እንደተለማመዱ ይናገራሉ የዛሬው ባለታሪካችን አቶ ታምራት አንጋሳ፡፡ አቶ ታምራት ንግድን አንድ ብለው የጀመሩት በየከፍለ አገሩ ረጅም ጉዞ በእግራቸው በመጓዝ ቡና በብቅሎ ጭነው በማከፋፈል ነበር፡፡ ታዲያ የአሰሪዎቻቸውን ቡና ጭነው ሩቅ ሄደው በማከፋፈል የጫኑትን አንድ አራተኛ ለጉልበታቸው ዋጋ በመቀበል ቀስ በቀስ የራሳቸውን ስራ ወደመስራት እንደተሸጋገሩ አጫውተውናል፡፡

ታታሪው አቶ ታምራት ከብዙ ልፋት በኋላ የራሳቸውን ጭነት ማጓጓዣ በቅሎ በመግዛት ከአሰሪያቸው በተጨማሪ የራሳቸውን ጭነት ይዘው በማከፋፈል ካፒታላቸውን ማሳደግ ቀጠሉ፡፡ እንዲህ እያሉ ቀስ በቀስ ለሌላ ስራ ማስጀመሪያ የሚሆን ገንዘብ ካጠራቀሙ ሙሉ በሙሉ የእህል ንግድ ጀመሩ፡፡

በመስራት ውስጥ በመልፋት ውስጥ ስኬት እንዳለ የሚያምኑት አቶ ታምራት ከብዙ ጥረት በኋላ ወዳሰቡት መንገድ መድረስ መቻላቸውን ይናገራሉ፡፡ "ስኬታማ የሚያደርገው መስራት ነው፡፡ እኔ ሁሌም ቢሆን ወደኋላ ተመልሼ የወደኩበትን ሳይሆን ወደፊት ማድረግ የምችለውን ብቻ ነው የማስበው ለዛም ነው በብዙ ችግር ውስጥ አልፌ ስኬታማ መሆን የቻልኩት" ይላሉ፡፡

አቶ ታምራት በአንድ በቅሎ የጀመሩትን ስራ እያሳደጉ የስራ መኪና ወደመግዛት ተሸጋገሩ፡፡ ጥረታቸውን በመቀጠልም ስራቸውን እያሰፉ ተጨማሪ መኪኖችን በመግዛት የካፒታል አቅማቸውን ማጠናከር ችለዋል፡፡

በዚህ ሁኔታ ላይ እያሉ ህልማቸውን እውን የሚያደርግ ዜና ሰሙ፡፡ አቶ ታምራት ፋብሪካ መትከል እቅዳቸው ነበርና ወሊሶ ውስጥ አንድ የዱቄት ፋብሪካ እንደሚሸጥ ይፋ ይሆናል፡፡ በባለቤትነት የያዙት ዱቄት ፋብሪካ ለሽያጭ ቀረበ፡፡ ይህን መልካም አጋጣሚ በመጠቀም አቶ ታምራት እጃቸው ላይ ያለውን መኪና በመሸጥ በ2006 ለሽያጭ የቀረበውን የዱቄት ፋብሪካ ገዙ፡፡

አቶ ታምራት የወሊሶ የዱቄት ፋብሪካን እንዳሰቡት ገዝተው ወደስራ ከገቡ በኋላ ግን ማሽኑ አሮጌ በመሆኑ ለስራ አስቸጋሪ ሆነባቸው፡፡ በተደጋጋሚ እየተበላሸ ያስቸገራቸውን ማሽን ለማስጠገን የመንቀሳቀሻ መኪና ሳይቀር በመሸጥ ፋብሪካው የመክሰር አደጋ ውስጥ እያለ ነው ልማት ባንክ በ2010 ዓ.ም ፋብሪካቸውን የታደገላቸው፡፡

"ልማት ባንክ በጣም አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ሆኜ የደረሰልኝ፡፡ ልማት ባንክ ለእኔ ችግሬን ያቃለለልኝ ባንክ ነው" የሚሉት አቶ ታምራት በ2010 ዓ.ም በሊዝ ፋይናንስ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የስንዴ ዱቄት መፍጫ ማሽን አቅርቦላቸዋል፡፡ አቶ ታምራት ለአምስት ተከታታይ ዓመታት ብድራቸውን ሳያዛንፉ በመከፈል ፋብሪካው በእግሩ እንዲቆም ማድረግ የቻሉ ታታሪ ናቸው፡፡ አቶ ታምራት ተጨማሪ የበቆሎ ዱቄት መፍጫ ማሽን በሊዝ ፋይናንስ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ በመውሰድ የተከሉ ሲሆን በራሳቸው ወጪ ደግሞ ሁለት የዳቦ ማሽኖች እና የከብቶች መኖ ማቀነባበሪያ እውን ማድረግ ችለዋል፡፡

በወሊሶ የዱቄት ፋብሪካ 72 ጊዜያውና ቋሚ ሰራተኞች ተቀጥረው የሚሰሩ ሲሆን በቀጣይ የመኮረኒ እና የፓስታ ፋብሪካም ለመትከል እቅድ እንደያዙ አጫውተውናል፡፡ "ለእኔ ስኬት መስራት ነው፡፡ ሰው ከሰራ ይለወጣል፡፡ እኔ በብዙ ድካም ውስጥ ነው እዚህ የደረስኩት፡፡" ያሉት አቶ ታምራት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሰራተኞች ያላቸው መተባበር እና የሚሰጡት ምክር አዳዲስ ስራዎችን እንዲያስቡ እንደረዳቸው በመግለጽ በችግሬ ጊዜ የደረሰልኝ ባንክ ላመሰግን እፈልጋለሁ ብለዋል፡፡

በትጋት፣ በትዕግስት መስራት ከራስ አልፎ ማህበረሰብን ብሎም አገርን መለወጥ የሚያስችል ኢኮኖሚያዊ አቅም ለመፍጠር ያሳችላል፡፡ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዓላማ በጋራ ጥረት አገር ለማሻገር የቆረጡ እጆችን ማገዝ ነው፡፡ በዚህም ባለፉት ዓመታት በፈጸማቸው ተግባራት በርካቶችን መጥቀም የቻለ የፖለሲ ባንክ ነው፡፡
👍4214
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በግብርና ሜካናይዜሽን ስራ ላይ ለተሰማሩ የባንኩ ደንበኞች ትራክተሮችንና የኮምባይነር ሀርቨስተር ማሽኖችን በካፒታል ዕቃ ኪራይ የፋይናንስ ሞዳሊቲ በማቅረብ የእርሻውን ክፍለ ኢኮኖሚ እየደገፈ ይገኛል፡፡

ባንካችን ባለፉት ጥቂት ዓመታት ብቻ የግብርና ስራውን ማቀላጠፍ የሚችሉ የትራክተር እና ኮምባይነር ሀርቨስተር ማሽኖችን ለደንበኞች በሊዝ ፋይናንሲንግ አገልግሎት በማቅረብ የራሱን ድርሻ እየተወጣ ይገኛል፡፡

በተመሳሳይ በማዕድን ዘርፍ ለተሰማሩ የኤክስካቫተር እንዲሁም በማስጎብኘት ስራ ላይ ለተሰማሩ ደንበኞች ደግሞ የተለያዩ ዓይነት መኪኖችን በማቅረብ አገልግሎቱን ለደንበኞች ተደራሽ እያደረገ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
👍4619🤝3