Development Bank of Ethiopia (DBE)
23.3K subscribers
2.1K photos
76 videos
4 files
578 links
The development bank of Ethiopia (DBE) is one of the financial institutions engaged in providing short, medium and long term development credits.
Download Telegram
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕጻናት መርጃ የ31 ሚሊዮን ብር ዋጋ ያላቸው ለቀዶ ሕክምና የሚያገለግሉ የተለያዩ ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕጻናት መርጃ የ31 ሚሊዮን ብር ዋጋ ያላቸው ለቀዶ ሕክምና የሚያገለግሉ የተለያዩ ቁሳቁሶች ሕዳር 07 ቀን 2016 ዓ.ም በኢትዮጵያ የልብ ህሙማን መርጃ ውስጥ በተዘጋጀ የርክክብ መርሐ ግብር ላይ ተከናውኗል።

በርክክብ መርሐ ግብሩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕጻናት መርጃ ስራ አስፈጻሚ አቶ ኅሩይ አሊ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው በሕዳር 2015 ዓ/ም ወደ ማዕከሉ በመምጣት ባደረጉት ጉብኝት፣ ከጤና ባለሞያዎች እና የአስተዳደር ሰራተኞች ጋር ባደረጉት ውይይት መሠረት ማዕከሉ የቀዶ ህክምናውን ለመስጠት እንዳይችል ያደረጉትን ችግሮች በመረዳት ባንኩ ድጋፍ ለማድረግ መወሰኑን በማስታወስ ባንኩ ቃሉን ጠብቆ ድጋፍ በማድረጉ አመስግነዋል፡፡

የኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕጻናት መርጃ ብቁ የህክምና ባለሙያዎች እያሉት ከአቅም በታች እንዲሰራ ያደረጉት የህክምና ቁሳቁስ እጥረት መሆኑን ያወሱት የኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕጻናት መርጃ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሳልሀዲን ከሊፋ በበኩላቸው ባንኩ ያለባቸውን ክፍተት ተረድቶ ድጋፍ በማድረግ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ተወጥቷል ብለዋል፡፡ ሰብሳቢው አያይዘውም ድጋፉ ቀጣይነት እንዲኖረው አሳስበዋል፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዝደንት ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው ለቁሳቁሶቹ ርክክብ መብቃት አስተዋጽኦ ያደረጉ አካላትን አመስግነውና የባንኩም ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ቃል ገብተው በዶ/ር በላይ አበጋዝ ጥረት ተከፍቶና በመልካም አመራሮችና ባለሙያዎች ተጠናክሮ በሰብአዊነት ላይ የተመሰረተ ቅዱስ ተግባር የሚከናወንበትን ይህንን ማዕከል ሌሎች ተቋማትም እንዲደግፉት ከአደራ ጋር ጥሪዬን አስተላልፋለሁ ብለዋል።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የገባውን ቃል መሰረት አድርጎ ለኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕጻናት መርጃ የ31 ሚሊዮን ብር ዋጋ ያላቸው የልብ ቀዶ ሕክምና አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ የሕክምና ግብዓቶችን ድጋፍ ማድረጉ የበርካታ ህጻናቶችን ልብ የሚጠግንና የብዙ እናቶችን እምባ የሚያብስ ነው ያለቸው የኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕጻናት መርጃ በጎ ፈቃድ አምባሳደር እና የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የብራንድ አምባሳደር አርቲስት መሰረት መብራቴ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የህጻናቱን ልብ በመጠገን እንዲረባረብ ጥሪ አቅርባለች፡፡

ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ የተገኘው ድጋፍ ከ250 በላይ የልብ ቀዶ ሕክምናዎች ለመስጠት የሚያስችል ድጋፍ መሆኑን ያብራሩት የማዕከሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር ሚክሎል መንግስቴ   በድጋፉ በልብ ሕመም የሚሰቃዩ ወረፋ የሚጠብቁ በርካታ ታካሚዎችን እንግልት የሚቀንስ እና ለሁላችንም እፎይታን የሚሰጥ ድጋፍ ነው ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ብቸኛው የሀገራችን የፖሊሲ ባንክ እንደመሆኑ የሀገራዊ ልማቶች ሁሉ መሰረት ሰዋዊ ልማት እንደሆነ በመገንዘብ ማህበረሰብ ተኮር በሆኑ ሰብዓዊ ተግባራት ላይ የሚሳተፍ ተቋም እንደሆነ ይታወቃል፡፡
👍50❤25👏1
የልብ ሕክምና ግብአቶችን በሀገር ውስጥ በማምረት ላይ ለሚሳተፉ ባለሃብቶች የፋይናንስ ብድር እንደሚመቻች ተገለፀ

በሀገራችን ብቸኛ የፖሊሲ ባንክ የሆነው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የልብ ሕክምና ግብአቶችን በሀገር ውስጥ ማምረት ለሚፈልጉ ባለሃብቶች የፋይናንስ ብድር እንደሚያመቻች ለኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕጻናት መርጃ ማዕከል 31 ሚሊዮን ብር ዋጋ ያላቸው የሕክምና ግብአቶች ርክክብ መርሐግብር ላይ ነው።

በርክክብ መርሐግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው በሀገር ውስጥ የሕክምና ግብአቶችን በማምረት ከውጭ ሀገር በግዢ የሚመጣውን ማስቀረት እንደሚገባ ጠቁመዋል። ለዚህም የሕክምና ግብአቶችን በሀገር ውስጥ ለማምረት ለሚፈልጉ ባለሃብቶች የልማት ባንክ ብድር እንደሚያመቻች ተናግረዋል።

በማዕከሉ በተደረገው የርክክብ መርሐግብር ላይ ከ250 በላይ ለሆኑ ሕጻናት የልብ ቀዶ ሕክምና ለማድረግ የሚያስችሉ የሕክምና ግብአቶች ድጋፍ ተደርገዋል።
👍39❤23
ልማት ባንኮች በአነስተኛ የብድር ተቋማት እና በግል የፋይናንስ ተቋማት የሚታየውን ከፍተኛ የሆነ የፋይናንስ አቅርቦት ችግር በመፍታት በኩል ጉልህ ሚና ይጫወታሉ፡፡ ለመካከለኛም ሆነ ግዙፍ ኢንዱስትሪዎች መስፋፋት የፋይናንስ አቅርቦትን ማሳለጥ ይገባል፡፡ ለግብርና፣ ለኢንዱስትሪ፣ ለቴክኖሎጂ እና ስራ ፈጠራ መበራከት የፋይናንስ ተቋማት ድርሻ የላቀ ነው፡፡

ኢንቨስትመንትን ለማሳለጥ፥ መካከለኛ እና ግዙፍ ኢንዱስትሪዎች ያሉባቸውን የፋይናንስ አቅርቦት ችግር በመፍታት ኢኮኖሚያዊ ለውጥ እንዲመጣ በማድረግ በኩል ልማት ባንኮች አቅም አላቸው፡፡ በረጅም ጊዜ ተከፍሎ የሚያልቅ የብድር አገልግሎት በመስጠት ኢንቨስትመንትን ለማስፋፋት እና አነስተኛ ብድር የሚያቀርቡ የፋይናንስ ተቋማት እንዲሁም የግል የፋይናንስ ተቋማት መድረስ የማይችሉትን የኢንቨስትመነት መስኮችን በመሸፈን ለኢኮኖሚ ለውጥ መሰረት በመሆን የሚያገለግሉ ናቸው ልማት ባንኮች፡፡

በአገራት የልማት ግቦች ስኬት ውስጥ የልማት ባንኮች ድርሻ የላቀ እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ኢኮኖሚያዊ ለውጥ ለማምጣት ኢንቨስትመንትን ማስፋፋት፤ ለኢንቨስትመንት መስፋፋት ደግሞ የፋይናንስ አቅረቦትን ማስፋት አስፈላጊ በመሆኑ በዚሁ መንገድ የልማት ባንኮቻቸውን በማጠናከር አቅም መፍጠር የቻሉ አገራት የአገራቸውን ኢኮኖሚያዊ ለውጥ ባጠረ ጊዜ ማረጋገጥ ችለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በሊዝ ፋይናንሲንግ እና ፕሮጀክት ፋይናንሲንግ የብድር ሞዳሊት የረጅም እና አጭር ጊዜ ብድር በማቅረብ ለኢንዱስትሪ ማበብ የራሱን ድርሻ እየተወጣ ይገኛል፡፡ ባንኩ ራሱን እያሳደገ ያላካተታቸውን ዘርፎች ጭምር በቀጣይ እያካተተ በአለማችን አሉ ከሚባሉ ስኬታማ ልማት ባንኮች ተርታ ለመሰለፍ አልሞ እየሰራ ያለ ባንክ ነው፡፡

መንግስት ይህንን ባንክ ከውድቀት በመታደግ ወደ ስኬት እንዲመጣ በማድረግ እና እንደ አንድ ብቸኛ የፖሊሲ ባንክ ፕሮጀክቶችን ብቻ እንደ ብድር ማስያዣነት በመጠቀም እንዲሁም የገበያ ክፍተትን ሊሞሉ የሚችሉ ግዙፍ አገራዊ ፕሮጀክቶችን ፋይናንስ በማድረግ ኃላፊነቱን በመወጣት ላይ ይገኛል፡፡

በአገራችን ያለውን የተፈጥሮ ጸጋ ተጠቅሞ፤ ሁሉም በየአካባቢው ያለው ጸጋ ላይ ተረባርቦ መስራት ከቻለ አንደ አገር ትልቅ ለውጥ ማምጣት ይቻላል፡፡ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሃብቱ ህዝብ ነው፡፡ መንግስት፣ የባንኩ ተበዳሪዎች፣ የባንኩ ሰራተኞች አና መላው የአገራችን ህዝብ ለልማት ባንክ ማደግ ትልቅ ዋጋ አላቸው፡፡ በመሆኑም እነዚህ አካላት እንደየኃላፊነታቸው የሚገባቸውን ከተወጡ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚፈልገው አይነት ልማት የሚገኝባትና ያደገች አገር መገንባት ይቻላል፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚለቃቸውን ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ዌብሳይት፡- www.dbe.com.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/dbethiopia
ቴሌግራም፦ https://t.me/DBE1900
ትዊተር፡- https://twitter.com/DBE_Ethiopia
ሊንክድኢን፡- https://www.linkedin.com/in/dbe1900/ በመወዳጀት፣ ለሌሎች በማጋራትና ገንቢ አስተያየትዎን በመስጠት ቤተሰብ ይሁኑ፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
👍31❤8👏1
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከሰሞኑ ለመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር የበጀት ዓመቱን የሩብ ዓመት አፈጻጸም በተመለከተ ሪፖርት ማድረጉን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

በውይይቱ በኢትዮጵያ ልማት ባንክ የተነሱ አንኳር ነጥቦች፡-

1.      በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ከ4 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር መሰብሰብ መቻሉ፣

2.      ከ 8.9 ቢሊዮን ብር ብድር ማጽደቁን፣

3.      በዲስትሪክትና በቅርንጫፍ ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ከቀረበው ብድር ውስጥ በግብርናው ዘርፍ የቀረበው ብድር ከፍተኛ መሆኑ፣

እንዲሁም የባንኩ የአምስት ዓመት ስትራቴጅክ ዕቅድ አራተኛ ዓመቱን ጨርሶ አምስተኛ ዓመቱን መጀመሩን ያብራሩት በውይይቱ ሪፖርቱን ያቀረቡት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው ናቸው፡፡

በተመሳሳይ በመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር የተነሱ አንኳር ነጥቦች፡-

1.      የኢትዮጵያ ልማት ባንክ 158 ሚሊዮን ብር የመንግስት ትርፍ ድርሻ መክፈሉ፣

2.      ባንኩ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ማስጀመሩ፣

3.      የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የብድር ተከፋይ አፈጻጸም ከፍተኛ መሆኑን፣

4.      የባንኩ የሀብት መጠን መጨመሩን

5.      የተበላሸ ብድር ከ4 ዓመት በፊት ከ40 በመቶ በላይ ከነበረበት ወደ 7 በመቶ ማውረድ መቻሉን የመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ሐ/ሚካኤል አንስተዋል፡፡
👍48🤝6❤3
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በአገራችን መሰረታዊ የኢኮኖሚ ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉ ፕሮጀክቶችን ፋይናንስ እያደረገ ይገኛል፡፡ ባንኩ በተለይ ያለንን እምቅ አገራዊ አቅም ተጠቅመን በአጭር ጊዜ ማደግ የምንችልባቸውን እድሎች መጠቀም እንደሚገባ የፋይናንስ አቅርቦት ከማመቻቸት በተጨማሪ ስልጠና በመስጠት ጭምር አገራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል፡፡

ባንኩ ከ115 ዓመታት በፊት በግብርና ዘርፍ በሬ በብድር በማቅረብ ግብርናውን ሲደግፍ የነበረና ዛሬ ላይም ዘመናዊ የግብርና መሳሪያዎችን ትራክተሮችን፣ የትራክተር ተቀጽላዎችን፣ ኮምባይን ሃርቨስተሮችን፣ የግብርና መለዋወጫዎችንና፣ ሌሎች ግብዓቶችን በማቅረብ ለግብርናው መዘመን የራሱን አስተዋጽዖ እያበረከተ የሚገኝ የፖሊሲ ባንክ ነው፡፡

የግብርና ዘርፍ መዘመንና መስፋት የግብርን ምርት ግብዓቶችን በመጠቀም እሴት ጨምረው ለአገር ውስጥ እና ለውጭ ገበያ መቅረብ የሚችሉ ምርቶችን የሚያቀርቡ አምራች ኢንዱስትሪዎችን በስፋት ለመትከል የሚያስችል ነው፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ባለፉት ዓመታት የአምራች ኢንዱስትሪውን ዘርፍ ጥቅል የሀገር ውስጥ ምርት ድርሻ ለማሳደግና የአስር ዓመት መሪ የኢንዱስትሪ የልማት ግብን ለማሳካት ባንኩ በትኩረት እየሰራ መሆኑን መገለጹ የሚታወስ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚለቃቸውን ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ዌብሳይት፡- www.dbe.com.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/dbethiopia
ቴሌግራም፦ https://t.me/DBE1900
ትዊተር፡- https://twitter.com/DBE_Ethiopia
ሊንክድኢን፡- https://www.linkedin.com/in/dbe1900/
ዩቱብ:- https://www.youtube.com/channel/UC_Rd6GxGVezCISTX7quEDJw

በመወዳጀት፣ ለሌሎች በማጋራትና ገንቢ አስተያየትዎን በመስጠት ቤተሰብ ይሁኑ፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
👍26❤7
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚለቃቸውን ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ዌብሳይት፡- www.dbe.com.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/dbethiopia
ቴሌግራም፦ https://t.me/DBE1900
ትዊተር፡- https://twitter.com/DBE_Ethiopia
ሊንክድኢን፡- https://www.linkedin.com/in/dbe1900/
ዩቱብ:- https://www.youtube.com/@developmentbankofethiopia

በመወዳጀት፣ ለሌሎች በማጋራትና ገንቢ አስተያየትዎን በመስጠት ቤተሰብ ይሁኑ፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
👍30❤3👏3🤝1
ፕሬስ መግለጫ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የግብርና ዘርፉን በስፋት ለመደገፍ የሚያስችል የወለድ ተመን ማሻሻያ አደረገ።

ማሻሻያው ባንኩ በሊዝ ፋይናንስ እና በፕሮጀክት ፋይናንስ የብድር ሞዳሊቲ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች አካቷል።

ህዳር 20 ቀን፣2016 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በግብርና ዘርፍ ላይ መንግስት እየወሰደ ያለውን እርምጃ ማሳካት እንዲቻልና የግብርና ዘርፍ ኢንቨስትመንትን ለማስፋፋት የወለድ ተመን ማሻሻያ አደረገ፡፡

ባንኩ ዛሬ በላከው የፕሬስ መግለጫ እንዳመላከተው ከምስረታው ጀምሮ ለግብርና ዘርፉ ትኩረት በመስጠት ሲደግፍ የቆየ የፖሊሲ ባንክ መሆኑን በመጥቀስ ግብርናውን ለማሻሻል መንግስት እየወሰደ ያለውን እርምጃ ማሳካት እንዲቻልና የግብርና ሴክተሩን በማነቃቃት በዘርፉ የግል ኢንቨስትመንትን ለማበረታታት እና ለመሳብ የባንኩ የሥራ አመራር ቦርድ የወለድ ተመን ማሻሻያ ማድረጉን አሳውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ባለፉት ዓመታት ባካሄደው ሪፎርም የነበሩበትን ተግዳሮቶች እየቀረፈና አዳዲስ አገልግሎቶችን ለደንበኞች እያቀረበ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ በመግለጫው የተመላከተ ሲሆን ይህ የወለድ ተመን ማሻሻያም ወቅቱን የጠበቀ እና በአገራችን ያለውን ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ማዕከል ያደረገ መሆኑን አብራርቷል፡፡

ባንኩ የወለድ ተመን ማሻሻያ ማድረጉን አስመልክቶ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው እንዳሉት፣ “የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ኢትዮጵያ ያላትን ከፍተኛ የሆነ ያልታረሰ የመሬት ሀብት ወደ ስራ ለማስገባት፤ ባለሀብቶች፣ አርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች የበለጠ እንዲበረታቱ ለማድረግ በግብርና ዘርፍ በአነስተኛ፣ መካከለኛና የኮርፖሬት ፕሮጀክት ብድር ለሚጠይቁ ይጠበቅ የነበረው የ11.5 በመቶ የማበደሪያ የወለድ ተመን ወደ 7 በመቶ ዝቅ አድርጓል።” ፕሬዚዳንቱ አክለውም ባንኩ ስራ ላይ ያዋለው ይህ ማሻሻያ ዘርፉን ለማሳደግ ያቀደው ስትራቴጅያዊ ሪፎርም አካል ሲሆን፣ መንግስት የግብርና ዘርፉን ለማሳደግ እየሰራ ያለውን ስራ የበለጠ የሚያግዝ መሆኑንም ገልፀዋል።

ባንኩ የወለድ ተመን ማሻሻያ ማድረጉ በአምራች ዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶች በጥሬ እቃ አቅርቦት እጥረት ምክንያት የነበረባቸውን ዝቅተኛ የማምረት አቅም በማሻሻልና በውጭ ምንዛሬ የሚገቡ ምርቶችን ለመቀነስ ከመርዳቱም በላይ ሀገራችን በዘርፉ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እንድታገኝ የሚያግዝ መሆኑም ተብራርቷል።

በተጨማሪም የተደረገው የወለድ ተመን ማሻሻያ የምግብና የኢንዱስትሪ ሰብሎች ላይ ያተኮረ ሥራ በኢንቨስተሩ እንዲሰራ የሚያበረታታ ሲሆን፣ የምግብ ፍላጎትንና ለኢንዱስትሪ የሚሆኑ የጥሬ ዕቃዎች አቅርቦት ሙሉ በሙሉ በአገር ውስጥ ምርቶች ከማሟላት ጎን ለጎን፣ የምግብ ዋጋ ንረትን ለማረጋጋትና የውጭ ምንዛሬ አቅምን ለማሳደግ እንደ መንግስት እየተሰራ ያለውን ስራ እንደሚያጠናክር ይጠበቃል።

ለከፍተኛ፣ ለአነስተኛና መካከለኛ የግብርና ፕሮጀክቶች የተደረገው የማበደሪያ ወለድ ምጣኔ ማሻሻያ ባንኩ ለዘርፉ ዕድገት ያለውን ቁርጠኛ አቋም ያሳየበት መሆኑም በመግለጫው ተመላክቷል።

በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሀገራችንን ኢኮኖሚያዊ ልማት በተሻለ ደረጃ እንዲረጋገጡ አሁን በገበያው ውስጥ ካለው ነባራዊ ሁኔታ በመነሳት በተመረጡ ዘርፎች ለተሰማሩ እና ግዙፍ ፕሮጀክቶችን ለሚያነቀሳቅሱ ተበዳሪዎች በሌሎች አገልግሎቶች ላይ መጠነኛ የወለድ ተመን ማሻሻያ ማድረጉ ተጠቁሟል።
👍56❤14👏1🤝1
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በግብርና ዘርፍ በአነስተኛ፣ መካከለኛና የኮርፖሬት ፕሮጀክት ብድር ለሚጠይቁ ይጠበቅ የነበረው የ11.5 በመቶ የማበደሪያ የወለድ ተመን ወደ 7 በመቶ ዝቅ እንዲል አድርጓል። ይህ ማሻሻያ በግብርና ዘርፍ የሚደረገውን ኢንቨስትመንት የሚያበረታታ ሲሆን እንደ አገር ያሉንን አቅሞች አሟጦ በመጠቀም ኢኮኖሚያዊ ለውጥ ለማምጣት የሚያስችል ነው፡፡ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በግብርና ዘርፍ በአነስተኛ፣ መካከለኛና የኮርፖሬት ፕሮጀክት ብድር ለሚጠይቁ ይጠበቅ የነበረው የ11.5 በመቶ የማበደሪያ የወለድ ተመን ወደ 7 በመቶ ዝቅ እንዲል አድርጓል። ይህ ማሻሻያ በግብርና ዘርፍ የሚደረገውን ኢንቨስትመንት የሚያበረታታ ሲሆን እንደ አገር ያሉንን አቅሞች አሟጦ በመጠቀም ኢኮኖሚያዊ ለውጥ ለማምጣት መሰረት ነው፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
👍44👏29❤10🤝4