Development Bank of Ethiopia (DBE)
23.3K subscribers
2.1K photos
76 videos
4 files
578 links
The development bank of Ethiopia (DBE) is one of the financial institutions engaged in providing short, medium and long term development credits.
Download Telegram
የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች በኢኮኖሚ እድገት እና ዘላቂ ልማት ውስጥ ያላቸውን ሚና በመገንዘብ በገበያ ውስጥ የኢንተርፕራይዞችን ቁጥር ለማስፋት የኢትዮጵያ ልማት ወደስራ ለመሰማራት የሚያበቃቸውን የቢዝነስ ክህሎት ስልጠና በመስጠት የፋይናንስ ድጋፍ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ዛሬ ላይ በኢኮኖሚ እድገታቸው አለምን እየመሩ ያሉ አገራት የለውጥ መሰረቶቻቸው በመሆን እያገለገሉ ያሉት በርካታ የሰው ኃይል በማቀፍ እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ማዕከል በመሆን የሚታወቁት የአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክም ኢንተርፕራይዞች ያላቸውን አገራዊ ፋይዳ በመገንዘብ ከፍተኛ በጀት በመመደብ ለአራት ተካታታይ ዙሮች ለአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ስልጠና መስጠቱ ይታወሳል፡፡ በእነዚህ ዙሮች ስልጠና የወሰዱ አንቀሳቃሾች የቢዝነስ እቅዳቸውን ለባንኩ በማስገባት በሊዝ ፋይናንሲንግ የብድር ሞዳሊቲ ተጠቃሚ እየሆኑ ይገኛሉ፡፡ እነዚህን ስኬታማ ባለታሪኮች የስራ ጥረት የሚያትት ዘገባ ወደእናንተ በቅርቡ የምናደርሰ መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ለመግለጽ እንወዳለን፡፡

እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሊዝ ፋይናንስ የብድር አሰጠጥ ፕሮግራም አሁን ባለው የፋይናንስ ገበያ ውስጥ የስራ ሃሳብ ኖሯቸው ነገር ግን ዋስትና አስይዞ ብድር መበደር አዳጋች ለሆነባቸው ዜጎች ሰፊ እድል የሚሰጥ ነው፡፡ በመሆኑም ባንኩ ከፍተኛ መዋለ ነዋይ አፍስሶ ያሰለጠናቸው የአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች በአገር ኢኮኖሚ ውስጥ ትርጉም ያለው ለውጥ እንዲያመጡ ይጠበቃል፡፡

አገራችን ያላትን እምቅ አቅም ወደ ስራ በመለወጥ ሃብት መፍጠር የሚችል በርካት ኢንቨስተር ትፈልጋለች፡፡ በመሆኑም ስልጠና የወሰደው ኃይል እርስ በእርስ በመተሳሰር የገበያ ክፍተቱን የሚሞሉ የስራ ሃሳቦችን በማመንጨት እና ፕሮጀክት ፕሮፖዛል በማዘጋጀት ከባንካችን ጋር አብሮ መስራት ይችላል፡፡

ባንካችን በአራተኛ ዙር በመጀመሪያ ምዕራፍ ስልጠና የወሰዱትን ጨምሮ ከዚህ ቀደም በነበሩ ሶስት ዙሮች ስልጠና ወስደው የስራ ሃሳብ ያላቸው ሰልጣኞች የስራ ሃሳባቸውን አቅርበው ባንኩ ባስቀመጠው አሰራር መሰረት ሂደቱን ጠብቆ መስተናገድ እንደሚችሉ በዚህ አጋጣሚ ማስታወስ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የ4ኛ ዙር ስልጠና ወስዳችሁ ሰርተፊኬት ባትወስዱም ባንኩ ስልጠና መከታተላችሁን የሚያረጋግጥ መረጃ በማዕከል ደረጃ ያደራጀ በመሆኑ ሰርተፉኬቱን ሳትጠብቁ የፕሮጀክት ፕሮፖዛል በአቅራቢያችሁ በሚገኝ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ቅርንጫፍ ወይም ዲስትሪክት እንድታመልክቱ እንጋብዛለን፡፡

በተጨማሪም ባንካችን ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት መስጠት የጀመረ በመሆኑ የእስልምና ሐይማኖት ተከታይ ሰልጣኞችም ባንካችን መሰጠት በጀመረው ኢጃራ (ሊዝ) ፋይናንሲንግ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት መጠቀም የምትችሉ መሆኑን እናስገነዝባለን፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚለቃቸውን ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ዌብሳይት፡- www.dbe.com.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/dbethiopia
ቴሌግራም፦ https://t.me/DBE1900
ትዊተር፡- https://twitter.com/DBE_Ethiopia
ሊንክድኢን፡- https://www.linkedin.com/in/dbe1900/ በመወዳጀት፣ ለሌሎች በማጋራትና ገንቢ አስተያየትዎን በመስጠት ቤተሰብ ይሁኑ፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
👍9824
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች ምንድን ናቸው
 
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በሊዝ ፋይናንሲንግ እና ፕሮጀክት ፋይናንሲንግ የብድር ሞዳሊቲ ያለ ተጨማሪ ብድር ማስያዣ (ዋስትና) ፕሮጅከቱን ብቻ ዋስትና በመያዝ ለደንበኞች አገልግሎት እየሰጠ ያለ ብቸኛው የፖሊሲ ባንክ ነው፡፡

ባንኩ በፕሮጀክት ፋይናንሲንግ ዘርፍ የግብርና ፕሮጀክቶች፥ የግብርና ምርት ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎች፥ የማምረቻ ኢንዱስትሪዎች፥ የማዕድን ልማት ኢንዱስትሪዎች እንዲሁም በሊዝ ፋይናንሲንግ ዘርፍ የግብርና ፕሮጀክቶች፥ የግብርና ምርት ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎች፥ የማምረቻ ኢንዱስትሪዎች፥ የቱሪዝም ኢንዱስትሪ፥ የግንባታ ዕቃዎች አምራች ኢንዱስትሪዎች፥ የማዕድን ልማት ኢንዱስትሪዎች፥ የግብርና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ንዑስ ዘርፎች ብድር እያቀረበ ይገኛል፡፡

በተጨማሪም በቅርቡ ዲቢኢ-ተዐውን የኢትዮጵያ ልማት ባንክ- ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ለመሰጠት የሚያስችሉ ዝግጅቶችን በማጠናቀቅ ደንበኞች ወደተግባር የሚገቡበትን እድል እያሰፋ ይገኛል፡፡ በተደጋጋሚ ደንበኞች ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ባንኩ በይፋ መስጠት የሚጀምርበትን ቀን ሲጠባበቁ መቆየታቸው ይታወሳል፡፡ በዚህም ባንኩ ለደንበኞች ጥያቄ ምላሽ በመስጠት በዲቢኢ-ተዐውን ሥር ከሚሰጡ አገልግሎቶች መካከል በሀብት ማሰባሰብ ላይ ትኵረት ያደረጉ ሱኩክና ሙዳረባ የተሰኙ አዲስ አገልግሎቶች የቀረቡ ሲሆን፣ በፋይናንሲንግ ላይ ደግሞ ኢጃራ (ሊዝ ፋይናንሲንግ) እና ሙራባሀ (ፕሮጀክት ፋይናንሲንግ) ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎቶችን ለመስጠት ደንበኞችን መቀበል ጀምሯል፡፡
 
ከቅርብ ጌዜያት ወዲህ ደግሞ የስራ ፈጠራ ሐሳብ ፋይናንሲንግ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል አሰራር ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል።

ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ ብድር ለመውሰድ ደንበኞች መከተል የሚገባቸው ሂደቶች ምንድን ናቸው
 
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ብድር ለመስጠት በዘረዘራቸው ንዑስ ዘርፎች ላይ መሰማራት የሚፈልግ ማንኛውም ደንበኛ ምክር ሃሳብ ማዘጋጀት እና ህጋዊ መረጃዎችን አደራጅቶ መያዝ ያስፈልጋል፡፡ ከዚህ ቀደም በዚህ ገጽ ላይ በለቀቅነው ቼክ ሊስት ላይ የተጠቀሱትን መረጃዎች አሟልቶ መምጣት ይገባል፡፡ በመሆኑም መረጃዎቹን በተሟላ መልኩ አዘጋጅቶ አቅራቢያ ወዳለ የባንኩ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ማስገባት አለበት፡፡ በቅርንጫፍ ጽ/ቤት እና በዲስትሪክት ደረጃ ማለቅ ያለበት ሂደት ካለቀ በኋላ ወደ ዋና መስሪያ ቤት ለውሳኔ የሚመጣ ሲሆን በዋና መስሪያ ቤት ደረጃ ፕሮጀክቱን በመመዘን ውሳኔ ይተላለፋል፡፡ ፕሮጀክቶቹ ማሟላት የሚገባቸው ቀሪ የሰነድ ጉዳዮች ካሉ እንዲሟሉ የሚደረገ ሲሆን አዋጭ ያልሆኑ ፕሮጀክቶች ደግሞ ውድቅ ይደረጋሉ፡፡ አዋጭነታቸው የታመነባቸው ፕሮጀክቶች ደግሞ እንዲጸድቁ በማድረግ ቀሪ ስራዎች ይፈጸማሉ፡፡
 
በአጠቃላይ እነዚህ ሂደቶች ጊዜ የሚጠይቁ የባንክ አሰራርን ተከትለው የሚፈጸሙ በመሆኑ ደንበኞች የሚጠበቅባቸውን ኃለፊነት በመወጣትና ሂደቱ የሚጠይቀውን ጊዜ ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት መጠበቅ ይገባቸዋል፡፡
 
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!   

 
👍5314🤝2
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጋር በመተባበር አፍላገ ልማት የተሰኘ ሳምንታዊ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ማዘጋጀት ከጀመረ ከዓመት በላይ አስቆጥሯል፡፡ በዚህ በባንኩ በሊዝ ፋይናንስ እና ፕሮጀክት ፋይናንስ የብድር አቅርቦት ስርዓት ተጠቃሚ የሆኑ ተበዳሪዎችን የስኬት ታሪክ በማቅረብ ልምድ እንዲቀሰምበት እያደረገ ይገኛል፡፡ የሳምንታዊ ፕሮግራማችን አካል በሆነው አዝናኝ እና አስተማሪ የሆነ ድርማ፣ የአገር ውስጥ እና የውጭ የልማት ባንኮችን የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎችን ለተመለካቾች በማድረስ ላይ ይገኛል፡፡

ከስኬት በስተጀርባ በተሰኘው ፕሮግራማችን የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚሰጠውን የኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ስልጠና ወስደው ከባንኩ በሊዝ ፋይናንስ የብድር ሞዳሊት ብድር ወስደው ተጠቃሚ የሆኑ ባለታሪኮችን ጨምሮ ሌሎች በባንኩ የብድር አቅርቦት ተጠቃሚ የሆኑ ባለታሪኮችን ተሞክሮ በማስተላለፍ ልምድ እንዲቀሰምበት እየተደረገ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ እንደ አገር እያደረገ ያለውን አስተዋጽዖ በቀጣይ ክፍሎች አሰናድቶ በማቅረብ ተጨማሪ አቅም ለመፍጠር የተለያዩ መሰናዶዎችን በየሳንቱ ያቀርባል ከነዚህም

· ወቅታዊና ምጥን መረጃ
· ከስኬት በስተጀርባ
· ወቅታዊ መሰናዶዎች
· ዓለም አቀፍ የልማት ባንኮች ተሞክሮ
· እንግዳ
· ዘጋቢ ፊልሞች እና ድራማ

አፍላገ ልማት ፕሮግራምን መከታተል ለምትሹ ሁሉ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በኢቲቪ ዜና ቻናል ዘወትር እሁድ ከምሽቱ 2፡50- 3፡30 በድጋሚ ማክሰኞ ከ10፡00 እስከ 10፡40 እንዲሁም በኢትዮጵያ ሬዲዮ ዘወትር ሰኞ ረፋድ ከ3፡20 – 4፡00 በመከታተል ስለ ባንካችን የበለጠ ማወቅ እና የበለጠ መጠቀም የምትችሉበት መረጃ እንድትወስዱ ተጋብዛችኋል፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚለቃቸውን ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ዌብሳይት፡- www.dbe.com.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/dbethiopia
ቴሌግራም፦ https://t.me/DBE1900
ትዊተር፡- https://twitter.com/DBE_Ethiopia
ሊንክድኢን፡- https://www.linkedin.com/in/dbe1900/ በመወዳጀት፣ ለሌሎች በማጋራትና ገንቢ አስተያየትዎን በመስጠት ቤተሰብ ይሁኑ፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
👍307
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕጻናት መርጃ የ31 ሚሊዮን ብር ዋጋ ያላቸው ለቀዶ ሕክምና የሚያገለግሉ የተለያዩ ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕጻናት መርጃ የ31 ሚሊዮን ብር ዋጋ ያላቸው ለቀዶ ሕክምና የሚያገለግሉ የተለያዩ ቁሳቁሶች ሕዳር 07 ቀን 2016 ዓ.ም በኢትዮጵያ የልብ ህሙማን መርጃ ውስጥ በተዘጋጀ የርክክብ መርሐ ግብር ላይ ተከናውኗል።

በርክክብ መርሐ ግብሩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕጻናት መርጃ ስራ አስፈጻሚ አቶ ኅሩይ አሊ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው በሕዳር 2015 ዓ/ም ወደ ማዕከሉ በመምጣት ባደረጉት ጉብኝት፣ ከጤና ባለሞያዎች እና የአስተዳደር ሰራተኞች ጋር ባደረጉት ውይይት መሠረት ማዕከሉ የቀዶ ህክምናውን ለመስጠት እንዳይችል ያደረጉትን ችግሮች በመረዳት ባንኩ ድጋፍ ለማድረግ መወሰኑን በማስታወስ ባንኩ ቃሉን ጠብቆ ድጋፍ በማድረጉ አመስግነዋል፡፡

የኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕጻናት መርጃ ብቁ የህክምና ባለሙያዎች እያሉት ከአቅም በታች እንዲሰራ ያደረጉት የህክምና ቁሳቁስ እጥረት መሆኑን ያወሱት የኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕጻናት መርጃ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሳልሀዲን ከሊፋ በበኩላቸው ባንኩ ያለባቸውን ክፍተት ተረድቶ ድጋፍ በማድረግ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ተወጥቷል ብለዋል፡፡ ሰብሳቢው አያይዘውም ድጋፉ ቀጣይነት እንዲኖረው አሳስበዋል፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዝደንት ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው ለቁሳቁሶቹ ርክክብ መብቃት አስተዋጽኦ ያደረጉ አካላትን አመስግነውና የባንኩም ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ቃል ገብተው በዶ/ር በላይ አበጋዝ ጥረት ተከፍቶና በመልካም አመራሮችና ባለሙያዎች ተጠናክሮ በሰብአዊነት ላይ የተመሰረተ ቅዱስ ተግባር የሚከናወንበትን ይህንን ማዕከል ሌሎች ተቋማትም እንዲደግፉት ከአደራ ጋር ጥሪዬን አስተላልፋለሁ ብለዋል።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የገባውን ቃል መሰረት አድርጎ ለኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕጻናት መርጃ የ31 ሚሊዮን ብር ዋጋ ያላቸው የልብ ቀዶ ሕክምና አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ የሕክምና ግብዓቶችን ድጋፍ ማድረጉ የበርካታ ህጻናቶችን ልብ የሚጠግንና የብዙ እናቶችን እምባ የሚያብስ ነው ያለቸው የኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕጻናት መርጃ በጎ ፈቃድ አምባሳደር እና የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የብራንድ አምባሳደር አርቲስት መሰረት መብራቴ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የህጻናቱን ልብ በመጠገን እንዲረባረብ ጥሪ አቅርባለች፡፡

ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ የተገኘው ድጋፍ ከ250 በላይ የልብ ቀዶ ሕክምናዎች ለመስጠት የሚያስችል ድጋፍ መሆኑን ያብራሩት የማዕከሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር ሚክሎል መንግስቴ   በድጋፉ በልብ ሕመም የሚሰቃዩ ወረፋ የሚጠብቁ በርካታ ታካሚዎችን እንግልት የሚቀንስ እና ለሁላችንም እፎይታን የሚሰጥ ድጋፍ ነው ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ብቸኛው የሀገራችን የፖሊሲ ባንክ እንደመሆኑ የሀገራዊ ልማቶች ሁሉ መሰረት ሰዋዊ ልማት እንደሆነ በመገንዘብ ማህበረሰብ ተኮር በሆኑ ሰብዓዊ ተግባራት ላይ የሚሳተፍ ተቋም እንደሆነ ይታወቃል፡፡
👍5025👏1
የልብ ሕክምና ግብአቶችን በሀገር ውስጥ በማምረት ላይ ለሚሳተፉ ባለሃብቶች የፋይናንስ ብድር እንደሚመቻች ተገለፀ

በሀገራችን ብቸኛ የፖሊሲ ባንክ የሆነው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የልብ ሕክምና ግብአቶችን በሀገር ውስጥ ማምረት ለሚፈልጉ ባለሃብቶች የፋይናንስ ብድር እንደሚያመቻች ለኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን ሕጻናት መርጃ ማዕከል 31 ሚሊዮን ብር ዋጋ ያላቸው የሕክምና ግብአቶች ርክክብ መርሐግብር ላይ ነው።

በርክክብ መርሐግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው በሀገር ውስጥ የሕክምና ግብአቶችን በማምረት ከውጭ ሀገር በግዢ የሚመጣውን ማስቀረት እንደሚገባ ጠቁመዋል። ለዚህም የሕክምና ግብአቶችን በሀገር ውስጥ ለማምረት ለሚፈልጉ ባለሃብቶች የልማት ባንክ ብድር እንደሚያመቻች ተናግረዋል።

በማዕከሉ በተደረገው የርክክብ መርሐግብር ላይ ከ250 በላይ ለሆኑ ሕጻናት የልብ ቀዶ ሕክምና ለማድረግ የሚያስችሉ የሕክምና ግብአቶች ድጋፍ ተደርገዋል።
👍3923
ልማት ባንኮች በአነስተኛ የብድር ተቋማት እና በግል የፋይናንስ ተቋማት የሚታየውን ከፍተኛ የሆነ የፋይናንስ አቅርቦት ችግር በመፍታት በኩል ጉልህ ሚና ይጫወታሉ፡፡ ለመካከለኛም ሆነ ግዙፍ ኢንዱስትሪዎች መስፋፋት የፋይናንስ አቅርቦትን ማሳለጥ ይገባል፡፡ ለግብርና፣ ለኢንዱስትሪ፣ ለቴክኖሎጂ እና ስራ ፈጠራ መበራከት የፋይናንስ ተቋማት ድርሻ የላቀ ነው፡፡

ኢንቨስትመንትን ለማሳለጥ፥ መካከለኛ እና ግዙፍ ኢንዱስትሪዎች ያሉባቸውን የፋይናንስ አቅርቦት ችግር በመፍታት ኢኮኖሚያዊ ለውጥ እንዲመጣ በማድረግ በኩል ልማት ባንኮች አቅም አላቸው፡፡ በረጅም ጊዜ ተከፍሎ የሚያልቅ የብድር አገልግሎት በመስጠት ኢንቨስትመንትን ለማስፋፋት እና አነስተኛ ብድር የሚያቀርቡ የፋይናንስ ተቋማት እንዲሁም የግል የፋይናንስ ተቋማት መድረስ የማይችሉትን የኢንቨስትመነት መስኮችን በመሸፈን ለኢኮኖሚ ለውጥ መሰረት በመሆን የሚያገለግሉ ናቸው ልማት ባንኮች፡፡

በአገራት የልማት ግቦች ስኬት ውስጥ የልማት ባንኮች ድርሻ የላቀ እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ኢኮኖሚያዊ ለውጥ ለማምጣት ኢንቨስትመንትን ማስፋፋት፤ ለኢንቨስትመንት መስፋፋት ደግሞ የፋይናንስ አቅረቦትን ማስፋት አስፈላጊ በመሆኑ በዚሁ መንገድ የልማት ባንኮቻቸውን በማጠናከር አቅም መፍጠር የቻሉ አገራት የአገራቸውን ኢኮኖሚያዊ ለውጥ ባጠረ ጊዜ ማረጋገጥ ችለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በሊዝ ፋይናንሲንግ እና ፕሮጀክት ፋይናንሲንግ የብድር ሞዳሊት የረጅም እና አጭር ጊዜ ብድር በማቅረብ ለኢንዱስትሪ ማበብ የራሱን ድርሻ እየተወጣ ይገኛል፡፡ ባንኩ ራሱን እያሳደገ ያላካተታቸውን ዘርፎች ጭምር በቀጣይ እያካተተ በአለማችን አሉ ከሚባሉ ስኬታማ ልማት ባንኮች ተርታ ለመሰለፍ አልሞ እየሰራ ያለ ባንክ ነው፡፡

መንግስት ይህንን ባንክ ከውድቀት በመታደግ ወደ ስኬት እንዲመጣ በማድረግ እና እንደ አንድ ብቸኛ የፖሊሲ ባንክ ፕሮጀክቶችን ብቻ እንደ ብድር ማስያዣነት በመጠቀም እንዲሁም የገበያ ክፍተትን ሊሞሉ የሚችሉ ግዙፍ አገራዊ ፕሮጀክቶችን ፋይናንስ በማድረግ ኃላፊነቱን በመወጣት ላይ ይገኛል፡፡

በአገራችን ያለውን የተፈጥሮ ጸጋ ተጠቅሞ፤ ሁሉም በየአካባቢው ያለው ጸጋ ላይ ተረባርቦ መስራት ከቻለ አንደ አገር ትልቅ ለውጥ ማምጣት ይቻላል፡፡ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሃብቱ ህዝብ ነው፡፡ መንግስት፣ የባንኩ ተበዳሪዎች፣ የባንኩ ሰራተኞች አና መላው የአገራችን ህዝብ ለልማት ባንክ ማደግ ትልቅ ዋጋ አላቸው፡፡ በመሆኑም እነዚህ አካላት እንደየኃላፊነታቸው የሚገባቸውን ከተወጡ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚፈልገው አይነት ልማት የሚገኝባትና ያደገች አገር መገንባት ይቻላል፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚለቃቸውን ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ዌብሳይት፡- www.dbe.com.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/dbethiopia
ቴሌግራም፦ https://t.me/DBE1900
ትዊተር፡- https://twitter.com/DBE_Ethiopia
ሊንክድኢን፡- https://www.linkedin.com/in/dbe1900/ በመወዳጀት፣ ለሌሎች በማጋራትና ገንቢ አስተያየትዎን በመስጠት ቤተሰብ ይሁኑ፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
👍318👏1
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከሰሞኑ ለመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር የበጀት ዓመቱን የሩብ ዓመት አፈጻጸም በተመለከተ ሪፖርት ማድረጉን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

በውይይቱ በኢትዮጵያ ልማት ባንክ የተነሱ አንኳር ነጥቦች፡-

1.      በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ከ4 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር መሰብሰብ መቻሉ፣

2.      ከ 8.9 ቢሊዮን ብር ብድር ማጽደቁን፣

3.      በዲስትሪክትና በቅርንጫፍ ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ከቀረበው ብድር ውስጥ በግብርናው ዘርፍ የቀረበው ብድር ከፍተኛ መሆኑ፣

እንዲሁም የባንኩ የአምስት ዓመት ስትራቴጅክ ዕቅድ አራተኛ ዓመቱን ጨርሶ አምስተኛ ዓመቱን መጀመሩን ያብራሩት በውይይቱ ሪፖርቱን ያቀረቡት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው ናቸው፡፡

በተመሳሳይ በመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር የተነሱ አንኳር ነጥቦች፡-

1.      የኢትዮጵያ ልማት ባንክ 158 ሚሊዮን ብር የመንግስት ትርፍ ድርሻ መክፈሉ፣

2.      ባንኩ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ማስጀመሩ፣

3.      የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የብድር ተከፋይ አፈጻጸም ከፍተኛ መሆኑን፣

4.      የባንኩ የሀብት መጠን መጨመሩን

5.      የተበላሸ ብድር ከ4 ዓመት በፊት ከ40 በመቶ በላይ ከነበረበት ወደ 7 በመቶ ማውረድ መቻሉን የመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ሐ/ሚካኤል አንስተዋል፡፡
👍48🤝63