Development Bank of Ethiopia (DBE)
23.3K subscribers
2.1K photos
76 videos
4 files
578 links
The development bank of Ethiopia (DBE) is one of the financial institutions engaged in providing short, medium and long term development credits.
Download Telegram
❤28👍10👏2
❤24👍15
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
እንኳን ለ2016 ዓ.ም ኢሬቻ በዓል አደረሳችሁ እያለ
በዓሉ የሰላም፣ የፍቅርና የደስታ እንዲሆን ይመኛል፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚለቃቸውን ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ዌብሳይት፡- www.dbe.com.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/dbethiopia
ቴሌግራም፦ https://t.me/DBE1900
ትዊተር፡- https://twitter.com/DBE_Ethiopia
ሊንክድኢን፡- https://www.linkedin.com/in/dbe1900/ በመወዳጀት፣ ለሌሎች በማጋራትና ገንቢ አስተያየትዎን በመስጠት ቤተሰብ ይሁኑ፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
❤37👍26🤝4
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በሰሜን አሜሪካ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሚሰጣቸውን የባንክ አገልግሎቶች አስተዋወቀ።

ባንኩ ይህንን የማስተዋወቅ ተግባር ያከናወነው በቨርጂኒያ እና ሲያትል ግዛቶች ነው።

በዚህም የባንኩን ታሪክ፣ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች እንዲሁም ያደረጋቸውን ማሻሻያዎች የተመለከቱ በራሪ ወረቀቶችን የማድረስ እና ገለጻ የማድረግ ስራ ተከናውኗል።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በሁለቱ ግዛቶች ላይ በተካሄደው የቴስት ኦፍ አፍሪካ እና የኢትዮጵያ ቀን ፌስቲቫሎች ላይ የተሳተፈውን እና ከኢትዮጵያ የተጓዘውን የባህል ቡድን ስፖንሰር በማድረግ ነው በመድረኮቹ የተሳተፈው።

በፌስቲቫሎቹ የታደሙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ባንኩ ስለሚሰጣቸው አገልግሎቶች እንዲሁም ከሌሎች የንግድ ባንኮች ምን ይለየዋል የሚለውን መረዳታቸውን ተናግረዋል።

በቀጣይ በሀገር ቤት በሚኖራቸው ቆይታም ከባንኩ ጋር ለመስራት መነሳሳትን የፈጠረላቸውን ግንዛቤ ማግኘታቸውንም ነው የገለጹት።

ባንኩ ኤምጂ ኮርፖሬት አሶሴት እና የአዲስ አበባ ባህል ኪነጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመተባበር ያሰናዱትን ዝግጅት ስፖንሰር አድርጓል።
👍58👏9🤝2❤1
👍34❤9🤝6
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚለቃቸውን ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ዌብሳይት፡- www.dbe.com.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/dbethiopia
ቴሌግራም፦ https://t.me/DBE1900
ትዊተር፡- https://twitter.com/DBE_Ethiopia
ሊንክድኢን፡- https://www.linkedin.com/in/dbe1900/ በመወዳጀት፣ ለሌሎች በማጋራትና ገንቢ አስተያየትዎን በመስጠት ቤተሰብ ይሁኑ፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
❤34👍28👏2
👍10❤4
ቃል በተግባር

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ባለፉት አራት የለውጥ ዓመታት የተሰጠውን ተልዕኮ በአግባቡ በመወጣት በየዓመቱ እደርስበታለሁ ብሎ ያስቀመጠውን ግብ እያሳካ የሚገኝ የፖሊሲ ባንክ ነው፡፡ ባንኩ ከዛሬ አራት አመታት በፊት የመበተን አደጋ ውስጥ የነበረ እዳ እንጂ ትርፍ የሌለው፤ እንደአንድ የመንግስት የፖሊሲ ባንክ የገበያ ጉድለትን በመሙላት የኢኮኖሚ ስብራቶችን መጠገን ሲገባው ራሱን በራሱ እየገዘገዘ የነበረ ባንክ መሆኑ የአደባባይ ሃቅ ነው፡፡

ባንኩ ይህንን ታሪኩን ከመሰረቱ ለመለወጥ በቁርጠኝነት የተነሳው የስራ አመራር ቦርድና እና ማኔጅመንት መላው የባንኩን ሰራተኛ ውጤት ተኮር ስራ እንዲሰራ በማስተባበር ቃሉን በተግባር ለውጦ ባንኩን ከነበረበት የቁልቁለት ጉዞ መንጥቆ በማውጣት ስኬታማ ማድረግ ችሏል፡፡ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አንጋፋነቱን የሚመጥን የተቋም ቁመና እንዲላበስ የባንኩ የሥራ አመራር ኃላፊነቱን በመወጣት የላቀ አበርክቶት ነበረው፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚወጥናቸው ተግባራት እንዲሳኩ በማድረግ በየምዕራፉ የሚያስመዘግባቸው ስኬቶች ጤናማነቱ የተጠበቀ የፋይናንስ ተቋም እንዲሆን አስችሎታል፡፡ ባንኩ እንደ አንድ የፖሊሲ ባንክ ለበለጠ ስኬት እንዲበቃም የስራ አመራሩ አሁንም ጥረቱን ቀጥሏል፡፡

ባንኩ ቃሉን እንደጠበቀ ለደንበኞች ጥያቄ ምላሽ የሚሰጥ አገልግሎት ይፋ አድርጓል፡፡ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን በይፋ አሳውቋል፡፡ የሸሪዓ ሕግን ተከትሎ ከባንኩ አገልግሎት መጠቀም የሚፈልጉ ሙስሊም ደንበኞቹን ዲቢኢ-ተዐውን ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎትን ይፋ በማድረግ ባንኩ ለህዝቡ የተጠጋ፤ ዓላማውም በሁሉም የአገሪቱ አቅጣጫ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን አገራችን ያላትን እምቅ ሃብት በመጠቀም ለአገርና ለህዝብ ለውጥ የሚያመጡ ተቋም መገንባት የሚችሉበትን እድል እያሰፋ ይገኛል፡፡

ዲቢኢ-ተዐውን የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት በይፋ መጀመሩ የተበሰረ በመሆኑ አገልግሎቱን መጠቀም የሚሻ ሁሉ ወደባንኩ በመምጣት ተጠቃሚ መሆን እንደሚችል እናሳውቃለን፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
👍56❤17🤝8
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በሀገር አቀፍ ደረጃ ባሉት 24 ዲስትሪክቶች፣ 100 ቅርንጫፎች እና በዋና መስሪያ ቤት ውስጥ የዲቢኢ-ተዐውን ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎቱን በተሳለጠ ሁኔታ ለመስጠት ዝግጅት ደንበኞችን መቀበል ጀምሯል፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የዲቢኢ-ተዐውን አገልግሎት ወደ ትግበራ ከገባ በኋላ በሚኖሩ ጥቂት ዓመታት ውስጥ በርካታ በሸሪዓው የተፈቀዱ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ተከፍተው ለሚሊዮኖች የስራ እድል ይፈጥራሉ ተብሎ ይታሰባል፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚለቃቸውን ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ዌብሳይት፡- www.dbe.com.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/dbethiopia
ቴሌግራም፦ https://t.me/DBE1900
ትዊተር፡- https://twitter.com/DBE_Ethiopia
ሊንክድኢን፡- https://www.linkedin.com/in/dbe1900/ በመወዳጀት፣ ለሌሎች በማጋራትና ገንቢ አስተያየትዎን በመስጠት ቤተሰብ ይሁኑ፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
👍69❤24👏3
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በግብርና ዘርፍ የሚመጡ ፕሮጀክቶችን ፋይናንስ ማድረግን እንደሚያበረታታ በተደጋጋሚ አሳውቋል፡፡ በግብርና ዘርፍ የሚደረጉ ኢንቨስትመንቶች ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸውና ለኢንዱስትሪ ማበብ የራሳቸውን ድርሻ የሚወጡ ናቸው፡፡

አገራችን ያላትን ለግብርና አጋዥ የሆኑ ምቹ ሁኔታዎች እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም በሁሉም የአገራችን አካባቢዎች ያሉትን አቅሞች አቀናጅቶ የግብርና ዘርፍ ላይ በትኩረት መሥራት፣ ከግብርና ልማታችን ጋር ተመጋጋቢ የሆኑ ኢንዱስትሪዎችን በመትከልና በማስፋፋት የውጭ ምንዛሬን የሚተኩ ምርቶችን ለማምረት ያስችለናል፡፡

ያለንን የሰው ሃይልና የመሬት ሃብት እንደ መልካም እድል ተጠቅሞ አገራችንን ከጥገኝነት የሚያላቅቅ፤ የህዝባችንን የምግብ ዋስትናውን ማረጋገጥ የሚቻልበት ሁኔት ለመፍጠር በግብርና ዘርፍ ልማት ላይ መረባረብ ያስፈልጋል፡፡ ጉልበት፣ መሬት፣ ፋይናንስና ቴክኖሎጂ አቀናጅቶ ተግባር ላይ በማዋልና በጎደለን ጉዳይ ላይ በመረባረብ ልማታችንን ማፋጠን ይገባል፡፡

በመሆኑም በየትኛውም የአገራቸን አካባቢ የሚገኙ ዜጎቻችን በግብርና ዘርፍ ላይ እንዲሰማሩ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፍላጎት ያለው ሲሆን፣ በዚህም መስክ ለሚመጡ ዘመናዊ የግብርና የፕሮጀክትና ሊዝ ፋይናንሲንግ ጥያቄዎችን ምላሽ በመስጠት ለአገራችን እድገት በትጋት እንደሚሠራ ያረጋግጣል፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚለቃቸውን ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ዌብሳይት፡- www.dbe.com.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/dbethiopia
ቴሌግራም፦ https://t.me/DBE1900
ትዊተር፡- https://twitter.com/DBE_Ethiopia
ሊንክድኢን፡- https://www.linkedin.com/in/dbe1900/ በመወዳጀት፣ ለሌሎች በማጋራትና ገንቢ አስተያየትዎን በመስጠት ቤተሰብ ይሁኑ፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
👍37❤7👏1
👍18❤11🤝2
የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች በኢኮኖሚ እድገት እና ዘላቂ ልማት ውስጥ ያላቸውን ሚና በመገንዘብ በገበያ ውስጥ የኢንተርፕራይዞችን ቁጥር ለማስፋት የኢትዮጵያ ልማት ወደስራ ለመሰማራት የሚያበቃቸውን የቢዝነስ ክህሎት ስልጠና በመስጠት የፋይናንስ ድጋፍ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ዛሬ ላይ በኢኮኖሚ እድገታቸው አለምን እየመሩ ያሉ አገራት የለውጥ መሰረቶቻቸው በመሆን እያገለገሉ ያሉት በርካታ የሰው ኃይል በማቀፍ እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ማዕከል በመሆን የሚታወቁት የአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክም ኢንተርፕራይዞች ያላቸውን አገራዊ ፋይዳ በመገንዘብ ከፍተኛ በጀት በመመደብ ለአራት ተካታታይ ዙሮች ለአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ስልጠና መስጠቱ ይታወሳል፡፡ በእነዚህ ዙሮች ስልጠና የወሰዱ አንቀሳቃሾች የቢዝነስ እቅዳቸውን ለባንኩ በማስገባት በሊዝ ፋይናንሲንግ የብድር ሞዳሊቲ ተጠቃሚ እየሆኑ ይገኛሉ፡፡ እነዚህን ስኬታማ ባለታሪኮች የስራ ጥረት የሚያትት ዘገባ ወደእናንተ በቅርቡ የምናደርሰ መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ለመግለጽ እንወዳለን፡፡

እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሊዝ ፋይናንስ የብድር አሰጠጥ ፕሮግራም አሁን ባለው የፋይናንስ ገበያ ውስጥ የስራ ሃሳብ ኖሯቸው ነገር ግን ዋስትና አስይዞ ብድር መበደር አዳጋች ለሆነባቸው ዜጎች ሰፊ እድል የሚሰጥ ነው፡፡ በመሆኑም ባንኩ ከፍተኛ መዋለ ነዋይ አፍስሶ ያሰለጠናቸው የአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች በአገር ኢኮኖሚ ውስጥ ትርጉም ያለው ለውጥ እንዲያመጡ ይጠበቃል፡፡

አገራችን ያላትን እምቅ አቅም ወደ ስራ በመለወጥ ሃብት መፍጠር የሚችል በርካት ኢንቨስተር ትፈልጋለች፡፡ በመሆኑም ስልጠና የወሰደው ኃይል እርስ በእርስ በመተሳሰር የገበያ ክፍተቱን የሚሞሉ የስራ ሃሳቦችን በማመንጨት እና ፕሮጀክት ፕሮፖዛል በማዘጋጀት ከባንካችን ጋር አብሮ መስራት ይችላል፡፡

ባንካችን በአራተኛ ዙር በመጀመሪያ ምዕራፍ ስልጠና የወሰዱትን ጨምሮ ከዚህ ቀደም በነበሩ ሶስት ዙሮች ስልጠና ወስደው የስራ ሃሳብ ያላቸው ሰልጣኞች የስራ ሃሳባቸውን አቅርበው ባንኩ ባስቀመጠው አሰራር መሰረት ሂደቱን ጠብቆ መስተናገድ እንደሚችሉ በዚህ አጋጣሚ ማስታወስ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የ4ኛ ዙር ስልጠና ወስዳችሁ ሰርተፊኬት ባትወስዱም ባንኩ ስልጠና መከታተላችሁን የሚያረጋግጥ መረጃ በማዕከል ደረጃ ያደራጀ በመሆኑ ሰርተፉኬቱን ሳትጠብቁ የፕሮጀክት ፕሮፖዛል በአቅራቢያችሁ በሚገኝ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ቅርንጫፍ ወይም ዲስትሪክት እንድታመልክቱ እንጋብዛለን፡፡

በተጨማሪም ባንካችን ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት መስጠት የጀመረ በመሆኑ የእስልምና ሐይማኖት ተከታይ ሰልጣኞችም ባንካችን መሰጠት በጀመረው ኢጃራ (ሊዝ) ፋይናንሲንግ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት መጠቀም የምትችሉ መሆኑን እናስገነዝባለን፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚለቃቸውን ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ዌብሳይት፡- www.dbe.com.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/dbethiopia
ቴሌግራም፦ https://t.me/DBE1900
ትዊተር፡- https://twitter.com/DBE_Ethiopia
ሊንክድኢን፡- https://www.linkedin.com/in/dbe1900/ በመወዳጀት፣ ለሌሎች በማጋራትና ገንቢ አስተያየትዎን በመስጠት ቤተሰብ ይሁኑ፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
👍98❤24
👍19❤9
❤9👍5
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች ምንድን ናቸው
 
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በሊዝ ፋይናንሲንግ እና ፕሮጀክት ፋይናንሲንግ የብድር ሞዳሊቲ ያለ ተጨማሪ ብድር ማስያዣ (ዋስትና) ፕሮጅከቱን ብቻ ዋስትና በመያዝ ለደንበኞች አገልግሎት እየሰጠ ያለ ብቸኛው የፖሊሲ ባንክ ነው፡፡

ባንኩ በፕሮጀክት ፋይናንሲንግ ዘርፍ የግብርና á•áˆŽáŒ€áŠ­á‰śá‰˝áĽ የግብርና áˆáˆ­á‰ľ áˆ›á‰€áŠá‰Łá‰ áˆŞá‹Ť áŠ˘áŠ•á‹ąáˆľá‰ľáˆŞá‹Žá‰˝áĽ የማምረቻ áŠ˘áŠ•á‹ąáˆľá‰ľáˆŞá‹Žá‰˝áĽ የማዕድን áˆáˆ›á‰ľ áŠ˘áŠ•á‹ąáˆľá‰ľáˆŞá‹Žá‰˝ እንዲሁም በሊዝ á‹á‹­áŠ“áŠ•áˆ˛áŠ•áŒ á‹˜áˆ­á á‹¨áŒá‰Ľáˆ­áŠ“ ፕሮጀክቶች፥ የግብርና ምርት ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎች፥ የማምረቻ ኢንዱስትሪዎች፥ የቱሪዝም ኢንዱስትሪ፥ የግንባታ ዕቃዎች አምራች ኢንዱስትሪዎች፥ የማዕድን ልማት ኢንዱስትሪዎች፥ የግብርና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ንዑስ ዘርፎች ብድር እያቀረበ ይገኛል፡፡

በተጨማሪም በቅርቡ ዲቢኢ-ተዐውን የኢትዮጵያ ልማት ባንክ- ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ለመሰጠት የሚያስችሉ ዝግጅቶችን በማጠናቀቅ ደንበኞች ወደተግባር የሚገቡበትን እድል እያሰፋ ይገኛል፡፡ በተደጋጋሚ ደንበኞች ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ባንኩ በይፋ መስጠት የሚጀምርበትን ቀን ሲጠባበቁ መቆየታቸው ይታወሳል፡፡ በዚህም ባንኩ ለደንበኞች ጥያቄ ምላሽ በመስጠት á‰ á‹˛á‰˘áŠ˘-ተዐውን áˆĽáˆ­ ከሚሰጡ áŠ áŒˆáˆáŒáˆŽá‰śá‰˝ áˆ˜áŠŤáŠ¨áˆ á‰ áˆ€á‰Ľá‰ľ áˆ›áˆ°á‰Łáˆ°á‰Ľ áˆ‹á‹­ á‰ľáŠľáˆ¨á‰ľ ያደረጉ áˆąáŠŠáŠ­áŠ“ áˆ™á‹łáˆ¨á‰Ł á‹¨á‰°áˆ°áŠ™ አዲስ አገልግሎቶች á‹¨á‰€áˆ¨á‰Ą áˆ˛áˆ†áŠ•áŁ á‰ á‹á‹­áŠ“áŠ•áˆ˛áŠ•áŒ áˆ‹á‹­ á‹°áŒáˆž áŠ˘áŒƒáˆŤ (ሊዝ ፋይናንሲንግ) áŠĽáŠ“ áˆ™áˆŤá‰Łáˆ€ (ፕሮጀክት ፋይናንሲንግ) ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎቶችን ለመስጠት ደንበኞችን መቀበል ጀምሯል፡፡
 
ከቅርብ ጌዜያት ወዲህ ደግሞ የስራ ፈጠራ ሐሳብ ፋይናንሲንግ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል አሰራር ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል።

ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ ብድር ለመውሰድ ደንበኞች መከተል የሚገባቸው ሂደቶች ምንድን ናቸው
 
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ብድር ለመስጠት በዘረዘራቸው ንዑስ ዘርፎች ላይ መሰማራት የሚፈልግ ማንኛውም ደንበኛ ምክር ሃሳብ ማዘጋጀት እና ህጋዊ መረጃዎችን አደራጅቶ መያዝ ያስፈልጋል፡፡ ከዚህ ቀደም በዚህ ገጽ ላይ በለቀቅነው ቼክ ሊስት ላይ የተጠቀሱትን መረጃዎች አሟልቶ መምጣት ይገባል፡፡ በመሆኑም መረጃዎቹን በተሟላ መልኩ አዘጋጅቶ አቅራቢያ ወዳለ የባንኩ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ማስገባት አለበት፡፡ በቅርንጫፍ ጽ/ቤት እና በዲስትሪክት ደረጃ ማለቅ ያለበት ሂደት ካለቀ በኋላ ወደ ዋና መስሪያ ቤት ለውሳኔ የሚመጣ ሲሆን በዋና መስሪያ ቤት ደረጃ á•áˆŽáŒ€áŠ­á‰ąáŠ• በመመዘን ውሳኔ ይተላለፋል፡፡ ፕሮጀክቶቹ ማሟላት የሚገባቸው ቀሪ የሰነድ ጉዳዮች ካሉ እንዲሟሉ የሚደረገ ሲሆን አዋጭ ያልሆኑ ፕሮጀክቶች ደግሞ ውድቅ ይደረጋሉ፡፡ አዋጭነታቸው የታመነባቸው ፕሮጀክቶች ደግሞ እንዲጸድቁ በማድረግ ቀሪ ስራዎች ይፈጸማሉ፡፡
 
በአጠቃላይ እነዚህ ሂደቶች ጊዜ የሚጠይቁ የባንክ አሰራርን ተከትለው የሚፈጸሙ በመሆኑ ደንበኞች የሚጠበቅባቸውን ኃለፊነት በመወጣትና ሂደቱ የሚጠይቀውን ጊዜ ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት መጠበቅ ይገባቸዋል፡፡
 
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!   

 
👍53❤14🤝2
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጋር በመተባበር አፍላገ ልማት የተሰኘ ሳምንታዊ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ማዘጋጀት ከጀመረ ከዓመት በላይ አስቆጥሯል፡፡ በዚህ በባንኩ በሊዝ ፋይናንስ እና ፕሮጀክት ፋይናንስ የብድር አቅርቦት ስርዓት ተጠቃሚ የሆኑ ተበዳሪዎችን የስኬት ታሪክ በማቅረብ ልምድ እንዲቀሰምበት እያደረገ ይገኛል፡፡ የሳምንታዊ ፕሮግራማችን አካል በሆነው አዝናኝ እና አስተማሪ የሆነ ድርማ፣ የአገር ውስጥ እና የውጭ የልማት ባንኮችን የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎችን ለተመለካቾች በማድረስ ላይ ይገኛል፡፡

ከስኬት በስተጀርባ በተሰኘው ፕሮግራማችን የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚሰጠውን የኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ስልጠና ወስደው ከባንኩ በሊዝ ፋይናንስ የብድር ሞዳሊት ብድር ወስደው ተጠቃሚ የሆኑ ባለታሪኮችን ጨምሮ ሌሎች በባንኩ የብድር አቅርቦት ተጠቃሚ የሆኑ ባለታሪኮችን ተሞክሮ በማስተላለፍ ልምድ እንዲቀሰምበት እየተደረገ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ እንደ አገር እያደረገ ያለውን አስተዋጽዖ በቀጣይ ክፍሎች አሰናድቶ በማቅረብ ተጨማሪ አቅም ለመፍጠር የተለያዩ መሰናዶዎችን በየሳንቱ ያቀርባል ከነዚህም

· ወቅታዊና ምጥን መረጃ
· ከስኬት በስተጀርባ
· ወቅታዊ መሰናዶዎች
· ዓለም አቀፍ የልማት ባንኮች ተሞክሮ
· እንግዳ
· ዘጋቢ ፊልሞች እና ድራማ

አፍላገ ልማት ፕሮግራምን መከታተል ለምትሹ ሁሉ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በኢቲቪ ዜና ቻናል ዘወትር እሁድ ከምሽቱ 2፡50- 3፡30 በድጋሚ ማክሰኞ ከ10፡00 እስከ 10፡40 እንዲሁም በኢትዮጵያ ሬዲዮ ዘወትር ሰኞ ረፋድ ከ3፡20 – 4፡00 በመከታተል ስለ ባንካችን የበለጠ ማወቅ እና የበለጠ መጠቀም የምትችሉበት መረጃ እንድትወስዱ ተጋብዛችኋል፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚለቃቸውን ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ዌብሳይት፡- www.dbe.com.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/dbethiopia
ቴሌግራም፦ https://t.me/DBE1900
ትዊተር፡- https://twitter.com/DBE_Ethiopia
ሊንክድኢን፡- https://www.linkedin.com/in/dbe1900/ በመወዳጀት፣ ለሌሎች በማጋራትና ገንቢ አስተያየትዎን በመስጠት ቤተሰብ ይሁኑ፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
👍30❤7