Development Bank of Ethiopia (DBE)
23.3K subscribers
2.1K photos
76 videos
4 files
578 links
The development bank of Ethiopia (DBE) is one of the financial institutions engaged in providing short, medium and long term development credits.
Download Telegram
👍31❤17
👍23❤17
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በቱሪዝምና ጤና መስኮች ብድር በማቅረብ አገልግሎቱን እያሰፋፋ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ መንግሥት ትኩረት በሚሰጣቸው ዘርፈች ላይ ብድር በማቅረብና የቴክኒክ ድጋፍ በመስጠት የልማት አጋርነቱን በማረጋገጥ ዛሬ ላይ ደርሷል፡፡ ባንኩ በፕሮጀክትና ሊዝ ፋይናንሲንግ አገልግሎቱ እስካሁን ዘመናዊ የእርሻ ልማቶችን፣ የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ እና የማምረቻ ኢንዱስትሪዎችን ፋይናንስ በማድረግ ለሀገር ልማት አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ እያደረገ ይገኛል፡፡

ባንኩ ባለፉት አራት ዓመታት ባከናወነው ሪፎርም አገልግሎቱን ለማስፋት እየተንቀሳቀሰ ሲሆን ከግብርናና ኢንዱስትሪ ዘርፎች በተጨማሪ በአገልግሎት ዘርፍ ደግሞ የውጪ ምንዛሪ በሚያስገኙና ከፍተኛ ማኅበራዊ ፋይዳ ባላቸው የቱሪዝምና የጤና መስኮችም ብድር በማቅረብ አገልግሎቱን እያስፋፋ ይገኛል፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚለቃቸውን ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ዌብሳይት፡- www.dbe.com.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/dbethiopia
ቴሌግራም፦ https://t.me/DBE1900
ትዊተር፡- https://twitter.com/DBE_Ethiopia
ሊንክድኢን፡- https://www.linkedin.com/in/dbe1900/ በመወዳጀት፣ ለሌሎች በማጋራትና ገንቢ አስተያየትዎን በመስጠት ቤተሰብ ይሁኑ፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
👍44❤3👏3
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የጤናውን ሴክተር ፋይናንስ ማድረግ ያስፈለገበት ምክነያት፡-
-በሀገሪቱ የጤና አገልግሎት ሽፋን እንዲስፋፋ ያግዛል፤
-ዓለም አቀፍ ደረጃ የጠበቁ፣ እጅግ በጣም ዘመናዊ (Tertiary) ሆስፒታሎች፣ ንዑስ የህክምና (sub-specialty) አገልግሎት
-መስጫዎችን በማስፋፋት ከውጪ ወደ ሀገር ውስጥ የሚመጡ ታካሚዎችን ቁጥር ማሳደግና ውጭ ምንዛሪን ማስገኘት፤
-ሴክተሩን ማዘመንና ወደ ውጪ ሄደው የሚታከሙ ዜጎችን ቁጥር በመቀነስ የውጭ ምንዛሪ ፍጆታን መቀነስ ያስችላል፤
-በጤና ዘርፍ ያለውን የባለሙያዎች ሥራ ዕድል እንዲሰፋ፣ በመስኩ የሚሠለጥኑ ቁጥራቸው እንዲበራከት ያስችላል፤
-የግሉ ሴክተር በጤናው ዘርፍ ሚናው እንዲጎላ ማድረግ ያስችላል፤
-በተለይም በማደግ ላይ ያሉ፣ ገጠራማ፣ በረሃማ አካባቢዎች ያለውን ጤና አገልግሎት ሽፋን ማሳደግ ያስችላል፤
-የጤና አገልግሎቱን ጥራት ማሻሻል ያስችላል፤
-በሕክምና መሣሪያዎች እጥረት ምክንያት ሊፈጠሩ የሚችሉ የአገልግሎት አሰጣጥ ውስንነትን ያሻሽላል።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚለቃቸውን ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ዌብሳይት፡- www.dbe.com.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/dbethiopia
ቴሌግራም፦ https://t.me/DBE1900
ትዊተር፡- https://twitter.com/DBE_Ethiopia
ሊንክድኢን፡- https://www.linkedin.com/in/dbe1900/ በመወዳጀት፣ ለሌሎች በማጋራትና ገንቢ አስተያየትዎን በመስጠት ቤተሰብ ይሁኑ፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
👍45❤3
የጤናው ሴክተር በፕሮጀክት ፋይናንሲንግ አገልግሎት ሥርዓት/ዘዴ

ባንኩ በዚህ የአገልግሎት ሥርዓት በገበያ አዋጪ የሆኑ እጅግ በጣም ዘመናዊ ሆስፒታሎችን ፋይናንስ ያደርጋል፡፡ እነዚህ ሆስፒታሎች የሜዲካል ቱሪዝምን የማስፋፋት አቅም የሚኖራቸው፣ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ አገልግሎቶችን የሚያቀርቡ፣ አገልግሎት በሚሰጥባቸው የሕክምና ዘርፎች እጅግ ብቁ የሆኑ ጤና ባለሙያዎችን የያዙ፣ በሚያቀርቡት ልዩ የሕክምና (highly specialized medical care) አገልግሎቱ የተሻለ፣ ተመራጭ፣ ተፈላጊ የሕክምና አገልግሎት መስጠት ላይ ትኩረት ያደርጋሉ፡፡

እነዚህ በባንኩ ፋይናንስ ለመደረግ የሚቀርቡ እጅግ በጣም ዘመናዊ ሆስፒታሎች እና የግል ሪፈራል ሆስፒታሎች በሚመለከተው የመንግሥት አካልና በባንኩ የሚጠበቅባቸውን ዝቅተኛ መመዘኛዎች ያሟሉ ሆነው መቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

አዋጪ የግል ሪፈራል ሆስፒታሎች ድንገተኛና ድንገተኛ ያልሆኑ ታካሚዎች ከመጀመሪያ ደረጃ ጤና ክብካቤ(ሕክምና) ሲመሩ፣ ሲተላለፉ፣ ሪፈር ሲባሉ ለመቀበል የሚያበቃ በቂ ሀብት(አቅም) ያላቸው ናቸው፡፡ በቂ ሀብት (አቅም) ሲባል ሦስት የሙሉ ሰዓት ሐኪሞች፣ እንዲሁም እንደ አጠቃላይ ሆስፒታል ሥራ ፈቃድ ይዞ የሚገኝ ማለት ነው፡፡

ሆስፒታሎቹ ገና በማደግ ላይ ባሉ ክልሎች ማለትም ቤኒሻንጉል ጉምዝ፣ ጋምቤላ፣ አፋር፣ ሶማሌ፣ ደቡብ ምዕራብ እና ሲዳማ ክልልን በመሳሰሉ አካባቢዎች የሚገነቡ መሆን አለባቸው፡፡

ከዚህ ባሻገር ባንኩ በፕሮጀክት ፋይናንሲንግ አገልግሎት በስፋትና በጥናት የገባበት የምድኃኒት ፋብሪካ (ኢንደስትሪ) ነው። እስከ አሁን ባንኩ ያቋቋማቸው አሉ። አሁን ግን በስፋት በኢንዱስትሪ ፓርኮች ጭምር በስፋት እንዲቋቋሙ ማገዝ ነው።

የጤናው ሴክተር በሊዝ ፋይናንስ አገልግሎት ሥርዓት

ባንኩ ፋይናንስ የሚያደርጋቸው ልዩ ልዩ የሕክምና መስጫ መሣሪያዎች ማለትም የሕክምና ላብራቶሪ መሣሪያዎች (laboratory equipment)፣ የምርመራ መሣሪያዎች (diagnostic equipment) ፣ የሕክምና ንጽህና መጠበቂያ መሣሪያዎች (medical sanitation equipment) እና ሌሎች የሕክምና መሣሪያዎችን ነው፡፡

በሊዝ ፋይናንሲንግ አገልግሎት ከሕክምና መሣሪያዎች አቅርቦት ባሻገር የሕክምና መሣሪያዎችን ማምረትንም ያበረታታል። ስለዚህ በዚህ ረገድ ባንኩ ሰፊ ሥራ እየሠራ ነው።

መሠረታዊ የብቃት መስፍርቶች (Eligibility Criteria)

1. አመልካቾች በጤናና ተያያዥ ሙያዎች ከታወቁ ወይም እውቅና ካላቸው ተቋማት የሠለጠኑ መሆን ይጠበቅባቸዋል።

2.አገልግሎት ሰጪው/ተከራዩ አስፈላጊውን ሙያዊ ፈቃድ ከሚመለከተው የመንግሥት አካል ማግኘት አለበት፡፡ ይሁን እንጂ አዲስ የሊዝ አገልግሎት አመልካች አገልግሎት ለማግኘት ማመልከቻውን ባቀረበበት ወቅት የሙያ ፈቃዱን ይዞ መገኘት አስገዳጅ ላይሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን በማስፋፊያ የሊዝ አገልግሎት ጥያቄ አቅራቢ ማመልከቻውን ሲያቀርብ የሙያ ፈቀድ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡

3.አመልካቹ ከቀረጥ ነጻ አገልግሎት ተጠቃሚ ለመሆኑም ከሚመለከተው የመንግሥት አካል የድጋፍ ድብዳቤ ማስገባት ይኖርበታል፡፡

በጤና ክብካቤና ንጽህና አጠባበቅ ለሚሰጡ አገልግሎቶች ዋነኛ ዘርፎች የሚባሉት፡-

• በሕክምና አገልግሎት (Medical services)፦ የሕክምና ላብራቶሪ መሣሪያዎችን ፣ የምርመራ መሣሪያዎችን፣ ሌሎች የሕክምና ቁሳቁስ

• በህክምና መስክ የቆሻሻ ማስወገጃ አገልግሎት (Waste Disposal services) ፦ በሕክምና አገልግሎት ሂደት በቆሻሻ ማስወገድ አገልግሎቶች ላይ ጥቅም የሚሰጡ የንጽህና አጠባበቅ መሣሪያዎች ናቸው፡፡

የባንኩ ማበረታቻዎች

አንደኛ፦ ባንኩ ማስያዣ አይጠይቅም። ማስያዣው የሚሆነው ፕሮጀክቱ ራሱ ነው። ነገር ግን በዘርፉ ለመሰማራት የሚፈልግ አካል 25 በመቶ መዋጮ ማምጣት ይኖርበታል። 75 በመቶውን ባንኩ ፋይናንስ ያቀርባል።

ሁለተኛ፦ ማበረታቻ ወለድ ነው። የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፋይናንስ የሚያቀርበው በዝቅተኛ ወለድ ነው፡፡ ባንኩ እስከ 20 ዓመታት የሚያበድር ሆኖ የሚያስከፍለው ወለድ11 ነጥብ አምስት በመቶ ነው። ይሄ ዝቅተኛ የሚባል ወለድ ነው። ዋናው ዓላማ የግል ሴክተሩ አትራፊ ሆኖ ገበያ ክፍተት በሚሞሉ ሥራዎች እንዲገባ እንዲሁም ኢንቨስትመንት እንዲስብም ለማድረግ ስለሆነ ወለዱ ዝቅተኛ ነው፡፡

ሦስተኛ፦ ሰፊ ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል። ክፍተቶች በሚታዩበት ቦታ ላይ ቴክኒካዊ ድጋፍ ይሰጣል። ምክርና ሥልጠና ይሰጣል።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ፋይናንሲንግ የቱሪዝም ጤናና ሌሎች ክትትል ዳይሬክቶሬት

ስልክ: +251 115549746 የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚለቃቸውን ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ዌብሳይት፡- www.dbe.com.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/dbethiopia
ቴሌግራም፦ https://t.me/DBE1900
ትዊተር፡- https://twitter.com/DBE_Ethiopia
ሊንክድኢን፡- https://www.linkedin.com/in/dbe1900/ በመወዳጀት፣ ለሌሎች በማጋራትና ገንቢ አስተያየትዎን በመስጠት ቤተሰብ ይሁኑ፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
👍43❤7👏2
👍19❤5
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለማዕድን አልሚ ደንበኞች ለማዕድን እና ኮንስትራክሽን ግብዓት ስራ ማሳለጫ የሚያገለግሉ ሎደር ማሽነሪዎችን አስረከበ፡፡

ብዛታቸው 15 የሚሆኑ ሎደሮችና ሌሎች ማሽነሪዎች በ44 ሚሊዮን ብር በባንኩ ወጪ ተደርጎ የተገዙ ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሀገራችን ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት የሆነውን ግብርናን ለማዘመን የተለያዩ የግብርና ማሽነሪዎችን በማስመጣት ለደንበኞቹ በማቅረብ ላይ ከመሆኑም በላይ በአምራች ኢንዱትሪው እና በአግሮ ፕሮሰሲንግ ዘርፉ የተሰማሩ አልሚዎችን ከመደገፍ በተጨማሪ በማዕድን ዘርፉም ይህንን አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡

ባንኩ በዚህ ዘርፍ ለተሰማሩ ከ110 በላይ ደንበኞች ከ1.4 ቢሊዮን ብር በላይ ፋይናንስ በማድረግ ለማዕድን ልማት ዘርፉ ማደግ እየሰራ መሆኑም በርክክብ መርሃ ግብሩ ወቅት ተገልጿል።

በእለቱ ማሽነሪዎችን ያስረከቡት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ፋይናንሲንግ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አስፋው አበራ ባንኩ የማዕድን ዘርፍ ልማትን በመደገፍ ለሀገራዊ ዕድገት የበኩሉን አስተዋጽኦ እየተወጣ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

መንግስት የዘርፉን ኢንቨስትመንት ለማሳደግ ትኩረት ሰጥቶ የተለያዩ ተግባራትን በማከናወን ላይ ይገኛል ያሉት አቶ አስፋው በተለይም ወርቅ፣እምነበረድና የተለያዩ ማዕድናትን ለውጭ ገበያ በማቅረብ አበረታች ውጤቶች መታየታቸው በማዕድን ዘርፉ ጠንክረን ብንሰራ በኢኮኖሚያችን ላይ አዎንታዊ ለውጥ ማምጣት እንደምንችል አመላካች ነው ብለዋል፡፡

ለማዕድን ልማት የሚያግዙ ማሽነሪ አቅራቢ የሆኑት  አቶ አብይ አበበ በበኩላቸው ሀገራችን እምቅ የማዕድን ሀብት ያላት በመሆኑ በዘርፉ ተጠቃሚ ለመሆን ባንኩ ዘመናዊ ማሽነሪዎችን ለደንበኞቹ ማቅረቡ ኢኮኖሚው እንዲያድግ የበኩሉን ለመወጣት ከማገዙም በላይ  ለሾል እድል ፈጠራ ፋይዳው የጎላ ነው ብለዋል።

ባንኩ ያቀረባቸውን ሎደር ማሽኖችን ለመረከብ ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የመጡ ደንበኞች በበኩላቸው በየአካባቢያቸው የሚገኙ ማዕድናትን ለማልማት የማሽኖቹ መኖር ወሳኝ መሆኑን ጠቁመው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በአጭር ጊዜ ማሽነሪዎቹን ማስረከቡ እንዳስደሰታቸው ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የመንግስት የልማት ትኩረት የሆኑ የኢኮኖሚ ዘርፎችን ፋይናንስ የሚያደርግ ተቋም እንደመሆኑ የማዕድን ዘርፍ ልማትን በፋይናንስ በመደገፍ ለሀገራዊ ዕድገት የበኩሉን አስተዋጽኦ እየተወጣ ይገኛል፡፡
👍35❤7🤝3👏1
❤28👍10👏2
❤24👍15
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
እንኳን ለ2016 ዓ.ም ኢሬቻ በዓል አደረሳችሁ እያለ
በዓሉ የሰላም፣ የፍቅርና የደስታ እንዲሆን ይመኛል፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚለቃቸውን ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ዌብሳይት፡- www.dbe.com.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/dbethiopia
ቴሌግራም፦ https://t.me/DBE1900
ትዊተር፡- https://twitter.com/DBE_Ethiopia
ሊንክድኢን፡- https://www.linkedin.com/in/dbe1900/ በመወዳጀት፣ ለሌሎች በማጋራትና ገንቢ አስተያየትዎን በመስጠት ቤተሰብ ይሁኑ፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
❤37👍26🤝4
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በሰሜን አሜሪካ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሚሰጣቸውን የባንክ አገልግሎቶች አስተዋወቀ።

ባንኩ ይህንን የማስተዋወቅ ተግባር ያከናወነው በቨርጂኒያ እና ሲያትል ግዛቶች ነው።

በዚህም የባንኩን ታሪክ፣ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች እንዲሁም ያደረጋቸውን ማሻሻያዎች የተመለከቱ በራሪ ወረቀቶችን የማድረስ እና ገለጻ የማድረግ ስራ ተከናውኗል።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በሁለቱ ግዛቶች ላይ በተካሄደው የቴስት ኦፍ አፍሪካ እና የኢትዮጵያ ቀን ፌስቲቫሎች ላይ የተሳተፈውን እና ከኢትዮጵያ የተጓዘውን የባህል ቡድን ስፖንሰር በማድረግ ነው በመድረኮቹ የተሳተፈው።

በፌስቲቫሎቹ የታደሙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ባንኩ ስለሚሰጣቸው አገልግሎቶች እንዲሁም ከሌሎች የንግድ ባንኮች ምን ይለየዋል የሚለውን መረዳታቸውን ተናግረዋል።

በቀጣይ በሀገር ቤት በሚኖራቸው ቆይታም ከባንኩ ጋር ለመስራት መነሳሳትን የፈጠረላቸውን ግንዛቤ ማግኘታቸውንም ነው የገለጹት።

ባንኩ ኤምጂ ኮርፖሬት አሶሴት እና የአዲስ አበባ ባህል ኪነጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመተባበር ያሰናዱትን ዝግጅት ስፖንሰር አድርጓል።
👍58👏9🤝2❤1
👍34❤9🤝6
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚለቃቸውን ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ዌብሳይት፡- www.dbe.com.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/dbethiopia
ቴሌግራም፦ https://t.me/DBE1900
ትዊተር፡- https://twitter.com/DBE_Ethiopia
ሊንክድኢን፡- https://www.linkedin.com/in/dbe1900/ በመወዳጀት፣ ለሌሎች በማጋራትና ገንቢ አስተያየትዎን በመስጠት ቤተሰብ ይሁኑ፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
❤34👍28👏2
👍10❤4
ቃል በተግባር

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ባለፉት አራት የለውጥ ዓመታት የተሰጠውን ተልዕኮ በአግባቡ በመወጣት በየዓመቱ እደርስበታለሁ ብሎ ያስቀመጠውን ግብ እያሳካ የሚገኝ የፖሊሲ ባንክ ነው፡፡ ባንኩ ከዛሬ አራት አመታት በፊት የመበተን አደጋ ውስጥ የነበረ እዳ እንጂ ትርፍ የሌለው፤ እንደአንድ የመንግስት የፖሊሲ ባንክ የገበያ ጉድለትን በመሙላት የኢኮኖሚ ስብራቶችን መጠገን ሲገባው ራሱን በራሱ እየገዘገዘ የነበረ ባንክ መሆኑ የአደባባይ ሃቅ ነው፡፡

ባንኩ ይህንን ታሪኩን ከመሰረቱ ለመለወጥ በቁርጠኝነት የተነሳው የስራ አመራር ቦርድና እና ማኔጅመንት መላው የባንኩን ሰራተኛ ውጤት ተኮር ስራ እንዲሰራ በማስተባበር ቃሉን በተግባር ለውጦ ባንኩን ከነበረበት የቁልቁለት ጉዞ መንጥቆ በማውጣት ስኬታማ ማድረግ ችሏል፡፡ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አንጋፋነቱን የሚመጥን የተቋም ቁመና እንዲላበስ የባንኩ የሥራ አመራር ኃላፊነቱን በመወጣት የላቀ አበርክቶት ነበረው፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚወጥናቸው ተግባራት እንዲሳኩ በማድረግ በየምዕራፉ የሚያስመዘግባቸው ስኬቶች ጤናማነቱ የተጠበቀ የፋይናንስ ተቋም እንዲሆን አስችሎታል፡፡ ባንኩ እንደ አንድ የፖሊሲ ባንክ ለበለጠ ስኬት እንዲበቃም የስራ አመራሩ አሁንም ጥረቱን ቀጥሏል፡፡

ባንኩ ቃሉን እንደጠበቀ ለደንበኞች ጥያቄ ምላሽ የሚሰጥ አገልግሎት ይፋ አድርጓል፡፡ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን በይፋ አሳውቋል፡፡ የሸሪዓ ሕግን ተከትሎ ከባንኩ አገልግሎት መጠቀም የሚፈልጉ ሙስሊም ደንበኞቹን ዲቢኢ-ተዐውን ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎትን ይፋ በማድረግ ባንኩ ለህዝቡ የተጠጋ፤ ዓላማውም በሁሉም የአገሪቱ አቅጣጫ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን አገራችን ያላትን እምቅ ሃብት በመጠቀም ለአገርና ለህዝብ ለውጥ የሚያመጡ ተቋም መገንባት የሚችሉበትን እድል እያሰፋ ይገኛል፡፡

ዲቢኢ-ተዐውን የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት በይፋ መጀመሩ የተበሰረ በመሆኑ አገልግሎቱን መጠቀም የሚሻ ሁሉ ወደባንኩ በመምጣት ተጠቃሚ መሆን እንደሚችል እናሳውቃለን፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
👍56❤17🤝8
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በሀገር አቀፍ ደረጃ ባሉት 24 ዲስትሪክቶች፣ 100 ቅርንጫፎች እና በዋና መስሪያ ቤት ውስጥ የዲቢኢ-ተዐውን ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎቱን በተሳለጠ ሁኔታ ለመስጠት ዝግጅት ደንበኞችን መቀበል ጀምሯል፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የዲቢኢ-ተዐውን አገልግሎት ወደ ትግበራ ከገባ በኋላ በሚኖሩ ጥቂት ዓመታት ውስጥ በርካታ በሸሪዓው የተፈቀዱ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ተከፍተው ለሚሊዮኖች የስራ እድል ይፈጥራሉ ተብሎ ይታሰባል፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚለቃቸውን ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ዌብሳይት፡- www.dbe.com.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/dbethiopia
ቴሌግራም፦ https://t.me/DBE1900
ትዊተር፡- https://twitter.com/DBE_Ethiopia
ሊንክድኢን፡- https://www.linkedin.com/in/dbe1900/ በመወዳጀት፣ ለሌሎች በማጋራትና ገንቢ አስተያየትዎን በመስጠት ቤተሰብ ይሁኑ፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
👍69❤24👏3