የመንግሰት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የ2022/2023 ዓ.ም የስራ አፈጻጸምን በዛሬው እለት የገመገመ ሲሆን በቀጣይ እቅዶች ላይም ውይይት በማድረግ መሻሻል የሚገባቸው ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡
በውይይቱ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ያለፈው በጀት ዓመት አፈጻጸምን በተመለከተ ሪፖርት ያቀረቡት የባንኩ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው ባንኩ በሪፎርሙ እተገብራቸዋለሁ ብሎ ካስቀመጣቸው ሰባት ምሰሶች አኳያ በበጀት ዓመቱ በሁሉም መለኪያ የተሻለ የሚባል አፈጸጸም ማስመዝገቡን ተናግረዋል፡፡
የመንግሰት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አቶ ሃብታሙ ኃ/ሚካኤል በበኩላቸው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በጥሩ መሰረት ላይ እየተገነባ የሚገኝ ባንክ መሆኑን በመግለጽ የባንኩ ቦርድ፣ ማኔጅመነት እና ሰራተኞች በተቀናጀ መልኩ በመስራት የመበተን አደጋ ውስጥ የነበረን ባንክ እንዲያንሰራራ በማድረግ ትርፋማ እንዲሆን በማድረጋቸው ሊመሰገኑ ይገባል ብለዋል፡፡
በመንግሰት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር የቀረቡ ዝርዝር ግምገማዎችን በዝርዝር የምንመለስበት ይሆናል፡፡

👍65👏15❤10
በኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሊዝ ፋይናንሲንግ አገልግሎት ለማግኘት መሟላት ያለባቸዉ መስፈርቶችን በሚመለከት ዝርዝር መረጃ በዚህ የፌስ ቡክ ገጻችን ላይ ማጋራታችን ይታወሳል፡፡ ሆኖም በተደጋጋሚ መስፈረቱ ምን እንደሆነ መረጃ እንድናጋራችሁ በጠየቃችሁት መሰረት መረጃውን አጋርተናል፡፡ ለበለጠ መረጃ በአቅራቢያችሁ ወደሚገኝ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዲስትሪክት እና ቅርንጫፎች እንዲሁም በዋና መስሪያ ቤት በመምጣት መረጃ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡
👍70❤45👏5🤝2
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በ115 ዓመታት የአገልግሎት ዘመኑ ለአገር ልማት የሚጠቅሙ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን ፋይናንስ በማድረግ አገራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ የሚገኝ የፖሊሲ ባንክ ነው፡፡ ባንኩ በእነዚህ ዓመታት ውስጥ በርካታ ተግዳሮቶች የገጠሙት ቢሆንም ዛሬ ላይ አገራዊ ኃላፊነቱን መወጣት የሚያስችለውን ሁለንተናዊ ብቃት በመላበስ ስኬታማ መሆን የቻለ ባንክ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በያዝነው በጀት ዓመት ብቻ ቆጥሮ ያስቀመጣቸውን እቅዶች ሳያዛንፍ በተሟላ መልኩ መፈጸም መቻሉ ቦርዱ፣ ማኔጅመንቱና ሰራተኛው በተናበበ መልኩ ተግባራትም ለመፈጸማቸውን ማረጋገጫ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ በተጨማሪ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ባንኩ በለውጥ ጎዳና ውስጥ መሆኑን እውቅና በመስጠት በተለይ በበጀት ዓመቱ ላስመዘገበው ስኬት እውቅና በመስጠት አገራዊ የልማት እቅዶችን በማፋጠን በኩል ገንቢ ሚና የሚጫወትና ተስፋ የሚጣልበት ባንክ መሆኑን በቅርቡ ባደረገው የአፈጻጸም ግምገማ ላይ ማረጋገጡ ይታወሳል፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከአመሠራረቱ ጀምሮ በተለይ ለአርሶ አደሩ ቅርብ በመሆን የገበሬን ሥራ በሚያቀሉና ምርታማነትን በሚያፋጥኑ መላዎች ላይ አተኩሮ ሲሠራ የቆየ ነው፤ በዚህም ውጤት ማስመዝገብ የቻለ ባንክ እንደሆነ ከታሪኩ መረዳት ይቻላል፡፡
ባንኩ ባለፉት አራት የለውጥ ዓመታት ውጫዊና ውስጣዊ ተግዳሮቶችን መፍታት የሚችል ሁሉን አቀፍ የሆነ የሪፎርም ስትራቴጂ በመንደፍ አንጋፋነቱን ወደሚመጥን ለውጥ እየተሸጋገረ ይገኛል፡፡ በዚህም ከዓመት ዓመት ትርፋማ እየሆነ፣ ተደራሽነቱንም እያሰፋ የገበያ ክፍተት ባለባቸው መስኮች ላይ የሚመጡ የፋይናንስ ድጋፎችን አሠራሩን በጠበቀ መንገድ ምላሽ እየሰጠ ይገኛል፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወደፊትም አገራችን በአራቱም ማዕዘን ያሏትን እምቅ አቅሞች በመጠቀም፣ ልማታችንን በማፋጠን ለአገራዊ እድገት የላቀ ፋይዳ ባላቸው ዘርፎች ላይ በትኩረት መሥራቱን ይቀጥላል፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!

👍75❤18
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ያሳለፍነውን የ2015 በጀት ዓመት ያቀዳቸውን ከግብ በማድረስ በውጤት አጠናቋል፡፡ ለዚህም የቦርድ አመራር አባላት፣ የማኔጅመንት አባላት እና ሰራተኞች ከፍ ያለ አበርክቶት ነበራቸው፡፡
ባንካችን 2016 ዓ.ም በአገራችን በግብርናውም ሆነ በኢንዱስትሪ መስክ የተሻለ እምርታ የሚያመጡ ፕሮጀክቶች ፋይናንስ በማድረግ በሙሉ ኃላፊነት እና ቁርጠኝነት ለመስራት ዝግጅቱን አጠናቆ ወደ ትግበራ ገብቷል፡፡
ከባንካችን ጋር ለመስራት ለተዘጋጁ ሁሉ ያለውን የገበያ ክፍተት የሚሞላ፣ አገራችንን ያላትን አቅም መጠቀም የሚያስችል፣ አዳዲስና የስራ እድሎችን የሚፈጥር የስራ ሃሳብ ይዞ ለመጣ በአዳዲስ አገልግሎቶች እና በተሻለ ቅልጥፍና ደንበኞች የሚፈልጉትን አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ መሆናችንን በድጋሚ ያረጋግጣል፡፡
ኑ አብረን እንስራ፤ ልማታችንን በማፋጠን አገራችንን እናሻግር፡፡

👍66❤18👏7
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ባሰለፍነው በጀት ዓመት 241,272,016 ብር በዓይነትና በጥሬ ገንዘብ ለተቋማትና ለግለሰቦች በማበርከት ማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ መሆኑን አስታወቀ፡፡
የ2016 አዲስ አመት አስመልክቶም ባንኩ ለአቅመ ደካሞችና ለችግር ለተጋለጡ ወገኖች ከ23 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡
ከዚህ በፊት የኢትዮጵያ የሕጻናት የልብ ህሙማን መርጃ ማዕከል ለመቄዶንያ የበጎ አድራጎት ድርጅት፣ ለሰሊሆም የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ ድርጅት፣ ለዲቦራ ፋውንዴሽንና በቦረና ዞን በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ጨምሮ ነው ድጋፉን ያደረገው፡፡
በተለይም የሀገር ባለውለታዎችን ለሀገር ለአበረከቱት ሀገራዊ አስተዋጽዖ በምስጋና መልክ ላሉባቸው ጊዜያዊ ችግሮች ማቃለያ የተለያዩ ድጋፎችን አድርጓል፡፡
በአዲሱ 2016 ዓመት አከባበርን ምክንያት በማድረግም ከልብስ ስፌት ማሽን እስከ ተሸከርካሪ ድጋፎችን አድርጓል፡፡
ለወጣት ምንታምር በለጠ ግምቱ ከ1 ሚሊዮን 6 መቶ ሺህ ብር በላይ የሆነ የልብስ ስፌት ማሽን፤ በእግር ሕመም ለሚሰቃየው ወጣት አማረ አምሳሉ ከቀረጥ ነጻ ተሸከርካሪ ማስገቢያ እና ለህክምና 800 ሺህ ብር፤ ለቀድሞው የሰርከስ ስፖርተኛ ለአቶ አረጋ ታደሰ ለሕክምና ወጭ የ500 ሺህ ብር ድጋፍ፤ ለቀድሞው የባንኩ ሰራተኛና የባንኩን ረቂቃ ታሪክ ለጻፉት ለአቶ አባት ባዬ 500 ሺህ ብር በተለያዩ አካባበዎች ለተፈናቀሉ ወገኖች 19 ሚሊዮን ብር በድምሩ 23,167,500 ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡
ባንኩ ለኢትዮጵያ የልብ ሕሙማን መርጃ ማዕከል 31,000,000 ብር፤ ለነቀምቴ ከተማ አቅመ ደካማ ሴቶች የቤት እድሳት ማሰሪያ 1,009,900 ብር፣ በተለያዩ ምክንያቶች ተፈናቅለው በወለጋ መጠለያ ጣቢያ ለሚገኙ ተፈናቃዮች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ድጋፍ ለማድረግ 7,000,000፣ በሌሎች አካባቢዎች ተፈናቅለው ለሚገኙ ወገኖች 12 ሚሊዮን ብር፣ ለእንሰት ምርምር ፕሮጀክት ለምርምር ቡድኑ አባላት 2,250,000 ብር በድምሩ 41,259,900 ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡
ድጋፉን ያስረከቡት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዝደንት ዶክተር ዮሐንስ አያሌው ባንኩ በማሕበራዊ ሃላፊነት ዘርፍ የሚያከናውናቸውን መልካም ተግባራት በአዲሱ ዓመትም አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡
አሁን ድጋፍ የተደረገላቸው አካላት ለናሙና ባንኩ ደገፈ እንጂ በየአካባቢው ያሉ ለችግር የተጋለጡ ወገኖቻችን ሁሉም በጋራ በመረባረብ መረዳዳት ቢቻል ለብዙዎች መድረስ እንደሚቻል ዶክተር ዮሐንስ ጠይቀዋል፡፡

👍58❤19🤝3
የሥልጠናው ዓላማ ምንድነው?
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ሥልጠና በመስጠት ወደ ቢዝነስ እንዲገቡ ድጋፍ የሚያደርግበት መሠረታዊ ዓላማ አለው፡፡
የዳበረ ኢኮኖሚ ባላቸው አገራት ውስጥ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የሥራ ዕድል ፈጠራን በማስፋት፣ ለግዙፍ ኩባንያዎች ግብዓት በማቅረብ እና የገበያ ክፍተትን በመሙላት ኢኮኖሚያዊ እድገትን የሚያፋጥኑ ናቸው፡፡ በበርካታ ያደጉ አገራት ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት እድገት ውስጥ የአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ድርሻ ላቅ ያለ እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
የዓለምን ኢኮኖሚ እየመሩ ከሚገኙ አገራት መካከል ቻይና ተጠቃሽ ናት፡፡ ሰፊ የሕዝብ ቁጥር እንዳላት በሚነገርላት ቻይና የአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች በአጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት እድገት ያላቸው ድርሻ ከ60 በመቶ በላይ ነው፡፡ ከ75 በመቶ በላይ ያለውን የሰው ኃይል የሚሸከሙትም የአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ናቸው፡፡ በጀርመን እና አሜሪካ ያለው ልምድም ከዚህ የተለየ አይደለም፡፡ በአገራችን የአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ሰፊ የሥራ ዕድል በመፍጠር በኵል የላቀ ድርሻ እንዳላቸው ይታወቃል፡፡
በኢትዮጵያም ኢንተርፕራይዞችን በፋይናንስ እና በሥልጠና በመደገፍ በማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ላይ እንዲሰማሩ በማድረግ በኵል መንግሥት የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ዕድገት ለማፋጠን፣ ብልጽግናንም ለማረጋገጥ ሀገር በቀል የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን በሊዝ ፋይናንሲንግ ሞዳሊቲ መደገፍን እንደ አንድ አማራጭ ወስዶ በከፍተኛ ትኩረት እየሠራ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ እንደ አንድ የፖሊሲ ባንክ ለአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና በመስጠት እና በሊዝ ፋይናንስ የብድር ሞዳሊት የፋይናንስ ድጋፍ በማድረግ ኢንተርፕራይዞች ለአገር ልማት የላቀ ሚና እንዲወጡ ለማስቻል እየሠራ ይገኛል፡፡
ባንኩ በሊዝ ፋይናንስ አገልግሎቱ አሁን ባለው የፋይናንስ ገበያ ውስጥ ዋስትና (collateral) አስይዞ ብድር ለመበደርና ሥራ ለመሥራት ዕድሉ የሌላቸውን ነገር ግን በሀገር በኢኮኖሚ ውስጥ የላቀ ትርጉም ማምጣት የሚችሉትን የኅብረተሰብ ክፍሎች (The missing middle) ለመደገፍ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ ይገኛል፡፡ ባንኩ ለአገር ልማት ከፍተኛ አስተዋጽዖ ባላቸው ዘርፎች ላይ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች እንዲሰማሩ ለማነቃቃት ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ መድቦ በተከታታይ እያሠለጠነ ነው፡፡
በመሆኑም የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በአገራችን ያለውን እምቅ አቅም አሟጦ በመጠቀም ለአገር ልማት እንዲውል ለማድረግ ዘርፈ ብዙ ተግባራቱን አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡

👍91❤16👏10
ህብረተሰቡ ለታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ቦንድ እንዲገዛና ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ ቀረበ።
መስከረም 10 ቀን 2016 ዓ.ም በሳይንስ ሙዚየም በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ይፋ እንደተደረገው ለ አንድ ወር የሚቆይ ንቅናቄ "ግድቤን ለማጠናቀቅ ቃሌን አድሳለሁ" በሚል መርህ የሚካሄድ ሲሆን፣ ግድቡን በስኬት ለማጠናቀቅ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ቀርቧል፡፡
የ4ኛ ዙር የውሃ ሙሌት በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን ተከትሎ ሀገር አቀፍ የሀብት ማሰባሰብ ንቅናቄ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት፣ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በጋራ ለመስራት ዝግጅት ማጠናቀቃቸውን ነው በጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት ያስታወቁት።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የካፒታል ገበያና የሀብት ማሰባሰብ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ዳዊት አማረ እንዳስታወቁት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለአንድ ወር ለሚካሄደው የቦንድ ሽያጭና ሀብት ማሰባሰብ ንቅናቄን ጨምሮ በ2016 በጀት ዓመት ከ3.3 ቢሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው ቦንዶች ታትመው ተሰራጭተዋል።
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ምትል ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ፍቅርተ ታምር በተያዘው 2016 ዓ.ም ከ1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ ሀብት ለመሰብሰብ እቅድ መያዙን ገልጸው ቦንድ በማዘጋጀት እና በማስተባበር በኩል የኢትዮጵያ ልማት ባንክ እና ንግድ ባንክ በዋናነት የሚሰሩት ይሆናልም ነው ያሉት።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ከተጀመረ ጀምሮ ላለፉት 12 ዓመታት ቦንድ በማተም፣ በማሰራጨትና በመሸጥ እየተሳተፈ ሲሆን፣ ግንባታው እየተጠናቀቀ በመሆኑ ህብረተሰቡ ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርቧል።

👍49❤14🤝3
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የመንግስት እና የግል የቢዝነስ ፕሮጀክቶችን በፋይናንስ በመደገፍ ከአንድ ክፍለ ዘመን በላይ ለአገር ልማት የጀርባ አጥንት ሆኖ እያገለገለ የሚገኝ የፖሊሲ ባንክ ነው።
ባንኩ በእነዚህ ዓመታት በበርካታ ውጣ ውረዶች ውስጥ እያለፈ ዛሬ ላይ ተግዳሮቶቹን ነቅሎ በመጣል በስኬት ወደፊት እየገሰገሰ ያለ ባንክ ነው፡፡
የኢትዮዽያ ልማት ባንክ የሪፎርም ትግበራዎች ውጤት እያመጡ ለመሆናቸው ባንኩ በ 2015 በጀት ዓመት ያስመዘገባቸው ስኬቶች ማሳያዎች ናቸው፡፡ ባንኩ በመላ ሀገሪቱ ፍትሐዊ የፋይናንስ አቅርቦትን እውን ለማድረግ አዳዲስ ዲስትሪክቶችንና ቅርንጫፎችን ከመክፈቱ ባሻገር የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ስልጠና በመስጠት ተደራሽነቱን እያሰፋ ይገኛል፡፡

👍51❤18👏10
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በቱሪዝምና ጤና መስኮች ብድር በማቅረብ አገልግሎቱን እያሰፋፋ ይገኛል፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ መንግሥት ትኩረት በሚሰጣቸው ዘርፈች ላይ ብድር በማቅረብና የቴክኒክ ድጋፍ በመስጠት የልማት አጋርነቱን በማረጋገጥ ዛሬ ላይ ደርሷል፡፡ ባንኩ በፕሮጀክትና ሊዝ ፋይናንሲንግ አገልግሎቱ እስካሁን ዘመናዊ የእርሻ ልማቶችን፣ የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ እና የማምረቻ ኢንዱስትሪዎችን ፋይናንስ በማድረግ ለሀገር ልማት አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ እያደረገ ይገኛል፡፡
ባንኩ ባለፉት አራት ዓመታት ባከናወነው ሪፎርም አገልግሎቱን ለማስፋት እየተንቀሳቀሰ ሲሆን ከግብርናና ኢንዱስትሪ ዘርፎች በተጨማሪ በአገልግሎት ዘርፍ ደግሞ የውጪ ምንዛሪ በሚያስገኙና ከፍተኛ ማኅበራዊ ፋይዳ ባላቸው የቱሪዝምና የጤና መስኮችም ብድር በማቅረብ አገልግሎቱን እያስፋፋ ይገኛል፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚለቃቸውን ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ዌብሳይት፡- www.dbe.com.et
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/dbethiopia
ቴሌግራም፦ https://t.me/DBE1900
ትዊተር፡- https://twitter.com/DBE_Ethiopia
ሊንክድኢን፡- https://www.linkedin.com/in/dbe1900/ በመወዳጀት፣ ለሌሎች በማጋራትና ገንቢ አስተያየትዎን በመስጠት ቤተሰብ ይሁኑ፡፡

👍44❤3👏3