Development Bank of Ethiopia (DBE)
23.3K subscribers
2.09K photos
76 videos
4 files
576 links
The development bank of Ethiopia (DBE) is one of the financial institutions engaged in providing short, medium and long term development credits.
Download Telegram
መንግስት ዋስትና ማቅረብ ለማይችሉና የፋይናንስ እጥረት ላለባቸው አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች (Missing Middle) እንዲሁም በስራ ፈጠራና ሀገራዊ ዕድገት ከፍተኛ ፋይዳ ያላቸው ኢንተርፕራይዞች ያሉባቸውን የፋይናንስ አቅርቦት ችግር ለመፍታት በፋይናንስ ስርዓቱ ላይ ባካሄደው መዋቅራዊ ለውጥ የካፒታል ዕቃ ኪራይ ንግድ ስራ አዋጅ ቁጥር 103/1990 እንዲሁም በተሻሻለው የማስፈጸሚያ አዋጅ ቁር 807/2005 መሰረት በግብርና፣ በግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ፣ በመፈብረኪያ፣ በአስጎብኝነት፣ በግንባታ ዕቃዎች፣ በማዕድን እንዲሁም በጤና ዘርፎች ለተሰማሩ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የፋይናንስ አቅርቦት ችግርን ለመፍታት የካፒታል ዕቃዎችን በኪራይ መልክ ለኢንተርፕራይዞቹ እንዲቀርቡ መፍቀዱ ይታወሳል፡፡
በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የተጣለበትን አገራዊ ኃላፊነት በመወጣት በአገራችን በተለይ አምራች ኢንዱስትሪዎች እንዲስፋፉ እና የካፒታል ክምችት እንዲያድግ እንዲሁም የስራ እድል እንዲሰፋ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
👍7721
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በሀገሪቱ የሚስተዋለውን የሲሚንቶ አቅርቦት ችግር በከፊል ለመቅረፍ የሚያስችለውን የግዙፍ ሲሚንቶ ፋብሪካዎችን ብድር ማጽደቁን አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ባለፉት ሶስት ዓመታት ሁለት ግዙፍ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች እና አንድ የቢቭሬጅ ፋብሪካ ብድር ያቀረበ ሲሆን፣ ግዙፍ ፋብሪካዎችን ለማቋቋም የሚቀርቡ ጥያቄዎች ቁጥር ባንኩ ከገነባው የፋይናንስ አቅም አንጻር በቂ አለመሆናቸውን የባንኩ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው አስታውቀዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ እንዳሉት የአምራች ኢንዱስትሪውን ዘርፍ ጥቅል የሀገር ውስጥ ምርት ድርሻ ለማሳደግና የአስር ዓመት መሪ የኢንዱስትሪ የልማት ግብን ለማሳካት ባንኩ በትኩረት እንደሚሰራም ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የካፒታል መጠኑን ከሶስት ዓመት በፊት ከነበረበት 2.6 ቢሊዮን ብር ወደ 38 ቢሊዮን ብር ማሳደጉንና በዚህም ባንኩ በዘንድሮ በጀት ዓመት 46.4 ቢሊዮን ብር ብድር ማጽደቅ መቻሉን ነው በጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት ያስታወቁት፡፡

ዶ/ር ዮሐንስ በተመሳሳይ በክልሎች ያለውን የፍትሃዊነትና፣ የተደራሽነት ጥያቄዎች ለመመለስ እንዲቻል ባንኩ በሁሉም ክልሎች የአቅም ግንባታ ስራዎች እና የግንዛቤ ማሳደግ ስራዎችን እየሰራ ከመሆኑም በላይ አገልግሎቱን በቅርበት ለመስጠት እንዲቻልም በሁሉም የአገሪቱ አካባቢዎች የዲስትሪክቶችን እና የቅርንጫፎችን ቁጥር የማሳደግ ስራ በሪፎርሙ እንደተከናወነ በመግለጫቸው አመላክተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በሀገራችን የልማት ስራዎች ውስጥ የመሪነት ሚናውን እየተወጣ መጓዝ የቻለ አንጋፋ ባንክ መሆኑ የተጠቀሰ ሲሆን፣ ባንኩ የሀገሪቱን የልማት ፕሮጀክቶችና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎችን በፋይናንስ በመደገፍ፣ በተለይ ለግብርና፣ ለአግሮ ፕሮሰሲንግ እና በአጠቃላይ ለአምራች ኢንዱስትሪው የፋይናንስ አቅርቦት ማድረግ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ተጠቅሷል፡፡

የሀገሪቱን ፈጣን ልማት ተከትሎ በመንግስትና በግሉ ዘርፍ የሚካሄዱ የልማት ፕሮጀክቶች በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ በመምጣቱ የኢትዮጵያ ልማት ባንክም ይህንኑ የሚመጥን ምላሽ በመስጠት ላይ እንደሚገኝ የገለጹት የባንኩ ፕሬዚዳንት በተለይ እ.ኤ.አ በ2030 ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የልማት ባንክ ለመሆን ያስቀመጠውን ርዕይ ለማሳካት እንዲያስችለው የተለያዩ የአሰራር ለውጦችንና ማሻሻያዎችን በማድረግ ለውጥ በማምጣት ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

የባንኩ የብድር ስርጭትና አሰባሰብን በተመለከተ በበጀት አመቱ ለልዩ ልዩ ኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች (በአምራች ኢንዱስትሪው፣ በግብርና፣ በማዕድንና ኃይል እንዲሁም በፋይናንስ አገልግሎቶች ለተሰማሩ ፕሮጀክቶች አዋጭነታቸውን በማረጋገጥ 46.4 ቢሊዮን ብር ብድር ለማቅረብ ያፀደቀ ሲሆን፣ ከ19.3 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር ማሰራጨቱ ተብራርቷል፡፡ በተጨማሪም በበጀት አመቱ 13.5 ቢሊዮን ብር ከብድር በውሉ መሠረት ለመሰብሰብ መቻሉንም ተጠቅሷል፡፡

ዶ/ር ዮሐንስ እንዳሉት በበጀት አመቱ መጨረሻ የባንኩን ጠቅላላ ሀብት 160.8 ቢሊዮን ብር ማድረስ የተቻለ ሲሆን፣ ዓመታዊ ትርፉም ከታክስ በፊት 6.4 ቢሊዮን ብር ሆኗል፡፡ ይህ የባንኩ ትርፍ በታሪኩ ከፍተኛው ሆኖ የተመዘገበ መሆኑን የጠቀሱት ፕሬዚዳንቱ የባንኩ አጠቃላይ ካፒታል ወደ 38 ቢሊዮን ብር ማድረስ መቻሉንም ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ተቋማዊ ለውጡን ለማረጋገጥ ከሚያስችሉት የማሻሻያ ስራዎች አንዱ የሆነው የዲቢኢ ቦንድ ሽያጭ በተያዘው በጀት ዓመት 14.59 ቢሊዮን ብር ማሰባሰብ መቻሉንና ይህም በአጠቃላይ ባንኩ ከዲቢኢ ቦንድ ሽያጭ 25 ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰብ መቻሉ ተጠቁሟል።

ባንኩ ከጥቂት ዓመታት በፊት ከፍተኛ የገንዘብ ኪሳራ ውስጥ ገብቶ እንደነበር ያስታወሱት ፕሬዚዳንቱ አጠቃላይ የተበላሸ ብድር ምጣኔው ከ43 በመቶ በላይ ደርሶ የነበረ ቢሆንም ይህንን ለማስተካከል ባንኩ የአምስት ዓመት እ.ኤ.አ (2018/19-2023/24) ስትራቴጂክ እቅድ በመቅረጽ የአሰራር ስርዓቱን በማሻሻል፣ ጥንቃቄ የተሞላበት የብድር ስርዓትን በመዘርጋት የባንኩ የአገልግሎት መስጫ የስራ ክፍሎችን በመጨመርና ተደራሽነትን በማስፋት ውጤታማ ስራ ማከናወን መቻሉን ነው ለጋዜጠኞች ይፋ ያደረጉት፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የኮርፖሬት ግብርና ፋይናንሲንግ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ዋቄ በበኩላቸው ከጋዜጠኞች ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ በሰጡበት ወቅት እንዳሉት ባንኩ በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚያቀርበውን ብድር ፍትሃዊ ለማድረግ በአደረጃጀትና በአሰራር ለመመለስ ጥረት እያደረገ መሆኑን ጠቅሰው እንደማሳያም ከወለድ ነጻ የፋይናንስ አገልግሎት መስጠት መጀመሩንና መዋቅሩንም በየክልሉ እያሰፋ መሆኑን አንስተዋል፡፡
ባንኩ አድሎአዊ አሰራርን ለመቆጣጠር የሚያስችል ሰፊ አሰራር ያለው መሆኑን የገለጹት አቶ ጌታቸው የብድር አሰጣጡ ቁጥጥርና ክትትል ባረጋገጠ ሁኔታ የሚፈጸም መሆኑንና ይህም በአግባቡ ስለመፈጸሙ የሚከታተል እና የሚቆጣጠር የሥራ አመራር ቦርድ፣ ብሄራዊ ባንክ እና ሌሎች ተቆጣጣሪ ተቋማት እንዳሉ አስገንዝበዋል፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ኮርፖሬት አገልግሎት ተጠባባቂ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው በላይ በበኩላቸው ባንኩ ያካሄደው ሪፎርም የዲስትሪክቶችን ቁጥር ከ12 ወደ 24፤ የቅርንጫፎችን ቁጥር ከ78 ወደ 100 ማሳደጉ በሁሉም የአገሪቱ አካባቢዎች ተደራሽ እንዲሆን እንዳስቻለው አብራርተዋል፡፡
👍6313🤝1
👍4011👏6🤝1
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በቱሪዝም ዘርፍ ለተሰማሩ የሊዝ ፋይናንስ ደንበኞቹ በ4.1 ሚሊዮን ዶላር የገዛቸውን ተሸከርካሪዎች አስረከበ፡፡

ባንኩ ለቱሪዝም ዘርፍ ስራው በእጅጉ አስፈላጊ የሆኑ 87 ተሸከርካሪዎችን ነው ለዘርፉ የሊዝ ፋይናንስ ደንበኞች ያስረከበው፡፡

በርክክብ ስነስርዓቱ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ዶክተር ዮሐንስ አያሌው እንዳሉት የቱሪዝሙ ዘርፍ ካለው እምቅ አቅም አንጻር ሃገሪቱ ተገቢውን ጥቅም እንድታገኝ ለዘርፉ ድጋፍ ማድረግ በእጅጉ ተገቢ ነው፡፡

ባንኩም ዘርፉ ለሃገር ልማት ያለውን አስተዋጽዖ በመረዳት በሊዝ ፋይናንስ ለደንበኞቹ ያስረከባቸው ተሸከርካሪዎች ዘርፉ ለኢኮኖሚው የሚያበረክተውን አስተዋጽዖ ከማሳደጉም በላይ ለበርካቶች የስራ እድልን የሚፈጥር ነው ብለዋል ፕሬዝዳንቱ፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በቀጣይም ለቱሪዝም እና ለሌሎች የተመረጡ የልማት ዘርፎች የሚያደርገውን ድጋፍ በማጠናከር ሃገራዊ ሃብት እንዲፈጠር በትኩረት የሚሰራ ይሆናል ብለዋል፡፡

ለእነዚህ ተሸከርካሪዎቹ የወጣው ወጪም ከግዥው ውጭ ያሉ ተጨማሪ ወጪዎችን የማያካትት መሆኑን ባንኩ አስታውቋል፡፡

ተሸከርካሪዎቹ በቱሪዝም ዘርፍ ለተሰማሩ 36 የሊዝ ፋይናንስ ደንበኞች ነው የተላለፉት፡፡

ለደንበኖች ከተላለፉት በተጨማሪ የቀሪ 28 ተሸከርካሪዎች ግዥም በሂደት ላይ መሆኑን ባንኩ አስታውቋዋል፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ትኩረት ሰጥቶ ከሚደግፋቸው ዘርፎች መካከል ቱሪዝም አንደኛው ሲሆን ዘርፉ ለሃገር ኢኮኖሚ የሚያበረክተው አስተዋጽዎ ከፍያለ እንዲሆን በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡
👍6418👏1
2015 በጀት ዓመት ክንውን በቁጥራዊ መረጃ ሲታይ፤

- 160.8 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ሀብቱን ማድረስ መቻሉ፣
- 46.4 ቢሊዮን ብር ብድር ለማቅረብ ያፀደቀው፣
- 19.3 ቢሊዮን ብር ለተሰራጨ ብድር፣
- 13.5 ቢሊዮን ብር ከብድር ያሰባሰበው (ተመላሽ) ያደረገው፣
- 75.7 ቢሊዮን ብር ባንኩ እስካሁን ያበደረው የገንዘብ መጠን፣
- 13.74 ቢሊዮን ብር የባንኩ ዓመታዊ ገቢ፣
- 62.4 በመቶ የሚሆነውን ለአምራች ኢንዱስትሪ፣ 16.6 በመቶ ለግብርና፣ 17.4 በመቶውን ለፋይናንስ አገልሎት፣ 2 በመቶውን ለማዕድንና ለኃይል ልማት አበድሯል፣
- 6.4 ቢሊዮን ብር ከታክስ በፊት ትርፍ ማግኘቱ፣
- 1.93 በመቶ የባንኩ የሊዝ ፋይናንስ የተበላሸ ብድር ምጣኔ የደረሰበት ደረጃ፣
- 7.2 በመቶ አጠቃላይ የተበላሸ የብድር ምጣኔ አሁን ላይ የደረሰበት ደረጃ ( በጋፕ አፕሮች)
- 14.59 ቢሊዮን ብር ከዲቢኢ ቦንድ ሽያጭ ማሰባሰብ የተቻለበት በጀት ዓመት ሆኗል፡፡
👍6213🤝8👏6
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከብድር አቅርቦት ፍትሃዊነት ጋር ተያይዞ ቀደም ሲል የነበሩ መዋቅራዊ ችግሮችን በመለየት መፍታቱን የባንኩ የኮርፖሬት ግብርና ፋይናንሲንግ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ዋቄ ተናገሩ፡፡

በዋናነት ሁለት መዋቅራዊ ችግሮች ነበሩ ያሉት አቶ ጌታቸው በሃይማኖታቸው ምክንያት ከባንኩ ጋር መስራት የማይችሉ ዜጎች መኖራቸው አንደኛው ነው፡፡

የባንኩ ዲስትሪክቶች እና ቅርንጫፎች ቁጥር እንዲሁም ስርጭት ውስንነት የነበረው መሆኑ ሁለተኛው ችግር ሲሆን ይህም መዋቅራዊ መፍትሄ እንዲያገኝ ተደርጓል ብለዋል ምክትል ፕሬዚዳንቱ፡፡

ባንኩ እነዚህን ችግሮች ለመፍታት ሰፋፊ ስራዎችን ያከናወነ ሲሆን ከሃይማኖት ጋር በተገናኘ ከባንኩ ብድር መውሰድ የማይችሉ ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎትን ለመስጠት የሚያስችለውን ስራዎች አጠናቋል፡፡

ከዲስትሪክትና ቅርንጫፎች ቁጥር እና ስርጭት ጋር ተያይዞ ለነበረው ችግርም በተሰጠው መዋቅራዊ መፍትሄ 12 የነበረው ዲስትሪክት ወደ 24፣ ቅርንጫፎቹንም ከ72 ወደ 100 በማሳደግ ለህብረተሰቡ ይበልጥ ተደራሽ ለመሆን ተሰርቷል፡፡

እነዚህ ሁለት መዋቅራዊ ስራዎች ወደ ባንኩ መምጣት ያልቻሉ እንዲሁም ስለባንኩ አገልግሎቶች ያላወቁ ዜጎችን በመሳብ ከብድር አቅርቦት ፍትሃዊነት ጋር ተያይዞ አገልግሎቱን ፍትሃዊ ለማድረግ ያስቻሉ ተግባራት መከናወናቸውን ነው አቶ ጌታቸው ዋቄ የተናገሩት፡፡

ባንኩ በእንዲህ መልኩ የተገበረውን ሪፎርም ተከትሎ ቀደም ሲል ለነበሩ ችግሮች መዋቅራዊ መፍትሄዎችን መስጠቱ እንደተጠበቀ ሆኖ ለባንኩ ስራ መሳካት ሌሎች ባለድርሻ አካላትም የድርሻቸውን ሊወጡ ይገባልም ብለዋል፡፡
👍6416👏4🤝4
ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከኢትዮጲያ ልማት ባንክ እና ከተባበሩት መንግስታት ልማት ፕሮግራም ጋር በመተባበር ኢኖቬቲቭ የንግድ ሀሳብ እና ምርት ያላቸውን ጀማሪ እና ነባር ኢንተርፕራይዞችን የብድር ዋስትና የፋይናንስ አቅርቦት ለማመቻቸት ጥሪ ያቀርባል፡፡

መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች ከታች በተቀመጠው መስፈንጠሪያ በመጠቀም እስከ ነሀሴ 24/2015 ዓ.ም ማመልከት እንደምትችሉ እያሳወቅን

http://registration.mint.gov.et/

ለበለጠ መረጃ በ +251993530103 /+2519118252 99 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ

Ministry of Innovation and Technology in partnership with Development Bank of Ethiopia and UNDP call innovative startups and SMEs to apply for access the credit risk guarantee fund provision.

Applicants fulfill the eligibility criteria should apply with the link below until 30th August 2023

For further enquiry: call +251993530103

http://registration.mint.gov.et/
👍5613👏4🤝3
👏4722👍8
👍4110👏2
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በ2016 በጀት ዓመት 51 ቢሊዮን ብር ብድር ለመስጠት መዘጋጀቱን አስታወቀ።

የባንኩ ፕሬዚዳንት ዶክተር ዮሐንስ አያሌው እንደገለጹት፤ ባለፉት ዓመታት በባንኩ ላይ ይነሱ የነበሩ የፍትሃዊነት ጥያቄዎች እየተቀረፉ በመምጣታቸው ከተለያየ የሀገሪቱ ክፍሎች በርካታ ባለሀብቶች ለባንኩ የብድር ጥያቄ እያቀረቡ ነው።

ይህንን ጥያቄ ለመመለስም በ2016 በጀት ዓመት 51 ቢሊዮን ብር ብድር ለመስጠት ዝግጅት ተደርጓል። ባንኩ የፖሊሲ ባንክ እንደመሆኑ ግብርናና አምራች ኢንዱስትሪ ዘርፎች ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሠራ የጠቆሙት ፕሬዚዳንቱ፤ ባለፈው በጀት ዓመት የሁለት ግዙፍ የሲሚንቶ ፋብሪካዎችን የብድር ጥያቄ አጽድቋል።

በተጨማሪም የቡናን ምርታማነት በሦስት እጥፍ ማሳደግ ለሚችል ሥራ ብድር ማጽደቁንም ገልጸዋል። በቀጣይ ጊዜያትም የውጭ ምንዛሪ ለሚያስገኙ ምርቶች እና ተኪ ምርቶች ላይ ትኩረት አድርጎ ፋይናንስ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል።

አሁን ላይ ዜጎችን አሰልጥኖ ወደ ኢንቨስትመንት እንዲገቡ ለማድረግ በሚያቀርቡት የአዋጭነት ጥናት መሠረት የብድር አገልግሎት እያቀረበ መሆኑን የጠቀሱት ዶክተር ዮሐንስ፤ በ2015 በጀት ዓመት 50 ሺህ ዜጎችን ለማሰልጠን አቅዶ የተፈጠረው ፍላጎት ከፍተኛ በመሆኑ ለ110 ሺህ ዜጎች ሥልጠና ሰጥቷል።

በ2016 በጀት ዓመትም ሥልጠናው ተጠናክሮ ይቀጥላል፤ ያለውን ፍላጎት መሠረት በማድረግም ከፍ ያለ በጀት ተይዟል ብለዋል። ለእነዚህ ዜጎች ፋይናንስ ለማቅረብም ባንኩ ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በቅርበት እየሠራ መሆኑንም አስታውቀዋል።

ከዚህ ቀደም በዋስትና ምክንያት የብድር አቅርቦት ችግር እንዳያጋጥማቸው ፕሮጀክቶችን በማስያዣነት ተጠቅሞ ብድር ሲሰጥ መቆየቱን ያስታወሱት ዶክተር ዮሐንስ፤ ይህም ባለሀብቶች በዋስትና ችግር ከኢንቨስትመንት እንዳይወጡ ማድረግ አስችሏል ሲሉ አስረድተዋል።

በቀጣይነትም ሀሳብ ላላቸው ዜጎች ፋይናንስ ለማቅረብ መዘጋጀቱን ገልጸዋል። በተጨማሪም በ2016 የተያዘው በጀት ከወለድ ነጻ የፋይናንስ አቅርቦትን የሚያካትት መሆኑ ተጠቁሟል፡፡ ባንኩ ብድር ሰጥቶ የማያስመልስ ከሆነ የሕዝብ ገንዘብ ብክነት ምክንያት ይሆናል ያሉት ዶክተር ዮሐንስ፤ ለዚህም ለብድር ማስመለስ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑን ጠቁመዋል፤ በተጠናቀቀው በጀት ዓመትም 13 ነጥብ አምሥት ቢሊዮን ብር ማስመለስ ችሏል ብለዋል።

ከብድር አቅርቦት ፍትሃዊነት ጋር ተያይዘው የሚቀርቡ ቅሬታዎችን ለማስወገድ ትኩረት ሰጥቶ ሲሠራ መቆየቱን ጠቁመው፤ ከሁሉም ክልሎች የሚቀርቡ ጥያቄዎችን በሙሉ እያስተናገደ ነው ብለዋል።

በቀጣይነትም ፍትሐዊ የፋይናንስ አቅርቦት እንዲኖር ትኩረት ሰጥቶ ይሠራል ብለዋል። የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አጠቃላይ የብድር መጠኑ 75 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱም ተመላክቷል።

ባንኩ በ2015 በጀት ዓመት ስድስት ነጥብ አራት ቢሊዮን ብር ማትረፉን እና የባንኩ አጠቃላይ ካፒታልም በ2011 በጀት ዓመት ከነበረበት ሁለት ነጥብ ስድስት ቢሊዮን ብር፤ በ2015 በጀት ዓመት ወደ 38 ቢሊዮን ብር ከፍ ማለቱን መግለጹ ይታወሳል።
👍5810👏4
👍7224👏10🤝1
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ትኩረት በተሰጣቸው የልማት ዘርፎች እድገትና ልማት እንዲመጣ የሚያደርገውን ድጋፍ እና ተሳትፎ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዝደንት ዶክተር ዮሐንስ አያሌው የባንኩን የ2015 በጀት አመት አፈጻጸም እና የ2016 እቅድን አስመልክቶ ከማኔጅመንት አባላትና በተለያዩ ደረጃዎች ከሚገኙ የስራ መሪዎች ጋር ባደረጉት ውይይት ነው ይህን የገለጹት፡፡

ባንኩ በሃገሪቱ ኢኮኖሚ ውስጥ ሰፊ አሻራን የማሳረፍ ሃላፊነት ያለበት መሆኑን ያብራሩት ዶክተር ዮሐንስ ሃገራዊ ሃብት እንዲፈጠር ብሎም የዜጎች ፍትሃዊ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ ከእስካሁኑ የበለጠ ስራ ከፊታችን ይጠብቀናል ብለዋል፡፡

ከዚህ አንጽር ባንኩ የተገበረውን ሪፎርም ተከትሎ እየተመዘገበ ያለውን ስኬት በላቀ ደረጃ ማስቀጠል በቀጣይ በከፍተኛ ትኩረት የሚከናወን ተግባር ይሆናል ነው ያሉት፡፡

ባንኩ 11.1 በመቶ የደረሰውን የተበላሸ ብድር ምጣኔ በ2016 በጀት አመት ወደ 5 በመቶ በማውረድ በአለም አቀፍ የልማት ባንኮች ደረጃ የመሰለፍ ግቡን ለማሳካት ማቀዱን በውይይቱ ተገልጿል፡፡

ከብድር አቅርቦት ጋር ተያይዞ ባንኩ በ2016 በጀት አመት 51 ቢሊዮን ብር ለማበደር ያቀደ ሲሆን ፣ይህም ከ2015 በጀት አመት አንጻር የ10 በመቶ እድገት ያለው ነው፡፡

ባንኩ በ2015 በጀት አመት ላስመዘገበው ስኬት የባንኩ የስራ አመራር ቦርድ፤ ማኔጅመንት እና መላው ሰራተኛ ከፍተኛ አስተዋጽዖ የነበራቸው መሆኑን የገለጹት የባንኩ ፕሬዝደንት ዶክተር ዮሐንስ አያሌው ለ2016 በጀት አመት እቅድ መሳካትም ሁሉም ባለድርሻ አካል ይህንኑ አስተዋጽዖ አጠናክሮ እንዲቀጥል መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
👍45👏2319
የመንግሰት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የ2022/2023 ዓ.ም የስራ አፈጻጸምን በዛሬው እለት የገመገመ ሲሆን በቀጣይ እቅዶች ላይም ውይይት በማድረግ መሻሻል የሚገባቸው ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡

በውይይቱ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ያለፈው በጀት ዓመት አፈጻጸምን በተመለከተ ሪፖርት ያቀረቡት የባንኩ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው ባንኩ በሪፎርሙ እተገብራቸዋለሁ ብሎ ካስቀመጣቸው ሰባት ምሰሶች አኳያ በበጀት ዓመቱ በሁሉም መለኪያ የተሻለ የሚባል አፈጸጸም ማስመዝገቡን ተናግረዋል፡፡

የመንግሰት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አቶ ሃብታሙ ኃ/ሚካኤል በበኩላቸው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በጥሩ መሰረት ላይ እየተገነባ የሚገኝ ባንክ መሆኑን በመግለጽ የባንኩ ቦርድ፣ ማኔጅመነት እና ሰራተኞች በተቀናጀ መልኩ በመስራት የመበተን አደጋ ውስጥ የነበረን ባንክ እንዲያንሰራራ በማድረግ ትርፋማ እንዲሆን በማድረጋቸው ሊመሰገኑ ይገባል ብለዋል፡፡

በመንግሰት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር የቀረቡ ዝርዝር ግምገማዎችን በዝርዝር የምንመለስበት ይሆናል፡፡
👍65👏1510