ማክሰኞ ሐምሌ 4 ቀን 2015 ዓ.ም በፌስ ቡክ ገጻችን ባንካችንን የተመለከተ ጥያቄ ማቅረባችን ይታወሳል፡፡ በዚህም በእለቱ የተሟላ መልስ ቀድሞ በመስጠት ያዘጋጀነውን ማበረታቻ ሽልማት አሸናፊ የሆነው በፌስቡክ ገጹ በተገለጸው ስም መሰረት ይድነቃቸው ንጉሴ ነው፡፡
ተሳታፊያችን ላደረጉት መልካም ተሳትፎ እያመሰገንን ስጦታውን ካዛንችስ ከሚገኘው የባንካችን ዋና መስሪያ ቤት ሚዲያና ኮምዩኒኬሽን ቢሮ እንዲወስዱ እንጠይቃለን፡፡
ሳምንት የሚያሸልሙ ጥያቄዎቻችንን ይዘን እንመጣለን ይጠብቁን!

👍149👏22❤19🤝5
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ለአገራችን ከሚሰጡት የላቀ ፋይዳ በመነሳት ያሉባቸውን ተግዳሮቶች ለመቅረፍ የሚያስችል ስራ እየሰራ ይገኛል፡፡
ኢንተርፕራይዞቹ ሊያጋጥሟቸው የሚችሉ የቴክኖሎጂ ችግሮችን በመቅረፍ እና የማሽነሪ አቅርቦት ከነድጋፉ በማዘጋጀት፣ የክህሎት ክፍተታቸውን መሙላት የሚያስችል ስልጠና በመስጠት እና በተለይ በአምራች ኢንዱስትሪ ላይ ተሳትፏቸውን እንዲያሳድጉ በማገዝ በኩል ተጨባጭ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!

👍35❤16
እንደሚታወቀው ከ80 በመቶ በላይ የሚሆነው የአገራችን ህዝብ የኑሮ መሰረት ግብርና እና ከግብርና ጋር የተያያዘ ሥራ ነው፡፡ ግብርና ከኢንዱስትሪ ጋር ተናቦ እና አንዱ ሌላውን እየመገበ እንዲሄድ በማድረግ የኢንዲስትሪ መሰረቱን አስተማማኝ ማድረግ ይቻላል፡፡ ለማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች ትኩረት ተሰጥቶ መሰራት የሚገባው መሰረታዊ ምክነያትም አንድም በአገራችን ዘላቂ እና አስተማማኝ ኢንዱስትሪ ለመገንባት የሚያስችል በሌላ መልኩም ሰፊ የሰው ጉልበት የሚይዝና የአገራችንን የግብርና ምርት ግብአቶችን በመጠቀም እሴት ጨምሮ የአለም ገበያን ጭምር ለመቆጣጠር ሰፊ እድል የሚሰጥ በመሆኑ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
👍61❤22🤝3
የኢትዮጵያ ልማት በሊዝ ፋይናንስ እና በፕሮጀክት ፋይናንስ የብድር ሞዳሊቲ የብድር አገልግሎት እንደሚሰጥ ይታወቃል፡፡ ሆኖም አንዳንድ ግለሰቦች ባንኩ በተለየ ሁኔታ ለስልጠና ተሳታፊዎች ብድር ያመቻቸ በማስመሰል እያጭበረበሩ መሆኑን ባንኩ ደርሶበታል፡፡ በመሆኑም ባንኩ ከተለመደው የብድር አሰጣጥ ስርዓት ውጭ ምንም አይነት የተለየ የብድር አገልግሎት የማይሰጥ መሆኑን አውቃችሁ ለዚህም ከባንኩ ውጭ ለየትኛውም ግለሰብ ሆነ ድርጅት ኃላፊነት ያልሰጠና መረጃው ስህተት መሆኑን ተገንዝባችሁ ራሳችሁን ከአጭበርባሪዎች እንድትጠብቁ ያሳስባል፡፡
በዚህ አጋጣሚ ትክክለኛ መረጃዎችን ከባንኩ ድረ ገጽ እና ከትክክለኛ የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾቻችን ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
Website
https://www.dbe.com.et/
Facebook
https://www.facebook.com/dbethiopia
Telegram
https://t.me/DBE_1901Ethiopia
Twitter
https://twitter.com/DBE_Ethiopia
Youtube
https://www.youtube.com/@developmentbankofethiopia
Instagram
https://www.instagram.com/dbe_ethiopia/

👍32❤10🤝2
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር እና ተጠሪ ተቋማቱ ጋር በጋራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሄዱ፡፡
በተከላ መርሃ ግብሩ የባንኩና የአስተዳደሩ የተጠሪ ተቋማቱ ሰራተኞችና የማኔጅመንት አባላት ተሳትፈዋል፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዝደንት ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው በዚሁ ወቅት እንደገለጹት ባንኩ ለግብርናው ዘርፍ ለሰጠው ልዩ ትኩረት የደን ልማት ወሳኝ በመሆኑ በየዓመቱ በሚዘጋጁ የተከላ ቦታዎች የችግኝ ተከላ እንደሚካሂድ ተገልጿል፡፡
በዚህም በጉለሌ እጸዋት ማዕከል በራሱ የወሰደውን መሬት በደንና ለእይታ ማራኪ በሆኑ እጸዋት በመሸፈን ውጤታማ ስራ መስራቱ ተገልጿል፡፡
ይህም ችግኝ መትከል ብቻ ሳይሆን መንከባከብ እንደሚገባ ማሳያ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን በተለያዩ አካባዎች የሚካሄዱ ተከላዎች በጥበቃና በእንክብካቤ ቢታገዙ በአጭር ጊዜ የሀገሪቱን የደን ሀብት ማሳደግ እንደሚቻል በዚሁ ወቅት ተገልጿል፡፡

👍62❤24👏4
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ማኔጅመንት እና ሰራተኞች የኢትዮጵያ የቅርስ ባለደራ ማህበር በሚያስተዳድረው የእንጦጦ የተፈጥሮ ፓርክ ውስጥ ችግኝ ተከሉ፡፡
👍23👏6❤5🤝1

የባንኩ ማኔጅመንት እና ሰራተኞች ከኢትዮጵያ ቅርስ ባላደራ ማኅበር ጋር በመተባበር በዛሬው እለት በርካታ የተፈጥሮ ችግኞችን በእንጦጦ የተፈጥሮ ፓርክ ውስጥ ተክለዋል፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የኮርፖሬት ግብርና ፋይናንሲንግ ም/ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ዋቄ እንዳሉት ተፈጥሮ የሰው ልጆችን ከእጽዋት ጋር ያቆራኘችው የአንዳችን መኖር በሌላችን ላይ የተመሰረት በመሆኑ ነው ብለዋል፡፡
ምክትል ፕሬዚዳንቱ አያይዘውም የእንጦጦ እጽዋት የአዲስ አበባ ሳንባዎች መሆናቸውን ጥናቶች ሳይቀር የሚያመላክቱ መሆኑን በመግለጽ ያልተበረዘ ንጹህ አየር መተንፈስ የምንችለው ተፈጥሮን መንከባከብ ስንችል ነውና ሁሌም ከራሳችን ነጥለን ማሰብ እንደማይገባ አስገንዝበዋል፡፡
የኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማኅበር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ መቆያ ማሞ በበኩላቸው ማኅበሩ እየጠፉ ያሉ አገር በቀል ችግኞች በስፋት እንዲተከሉ እየሰራ መሆኑን የገለጹ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ልማት ባንክም በዚህ ሂደት ውስጥ እየተወጣ ያለው አገራዊ ኃላፊነት የሚያስመሰግንና ተጠናክሮ መቀጠል የሚገባው መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በችግኝ ተከላው ተሳታፊ የነበሩ ሰራተኞች በበኩላቸው ችግኞችን መትከል እና መንከባከብ ላይ የሚያደርጉትን ተሳትፎ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የኢትዮጵያ ቅርስ ባላደራ ማህበር አባል ሲሆን ማህበሩ ተፈጥሮን ለመጠበቅ እና ለመንከባከብ በሚያደርገው አገራዊ እንቅስቃሴ ውስጥ በአጋርነት እንደሚቀጥል አረጋግጧል፡፡
በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ማኔጅመንት እና ሰራተኞች ከመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ጋር በጋራ በመሆን ሐምሌ 20 ቀን 2015 ዓ.ም በሞጆ ሐዋሳ የፍጥነት መንገድ መውጫ በር ላይ በርካታ ችግኞች መትከላቸው የሚታወስ ነው፡፡

👍66❤15👏4
መንግስት ዋስትና ማቅረብ ለማይችሉና የፋይናንስ እጥረት ላለባቸው አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች (Missing Middle) እንዲሁም በስራ ፈጠራና ሀገራዊ ዕድገት ከፍተኛ ፋይዳ ያላቸው ኢንተርፕራይዞች ያሉባቸውን የፋይናንስ አቅርቦት ችግር ለመፍታት በፋይናንስ ስርዓቱ ላይ ባካሄደው መዋቅራዊ ለውጥ የካፒታል ዕቃ ኪራይ ንግድ ስራ አዋጅ ቁጥር 103/1990 እንዲሁም በተሻሻለው የማስፈጸሚያ አዋጅ ቁር 807/2005 መሰረት በግብርና፣ በግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ፣ በመፈብረኪያ፣ በአስጎብኝነት፣ በግንባታ ዕቃዎች፣ በማዕድን እንዲሁም በጤና ዘርፎች ለተሰማሩ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የፋይናንስ አቅርቦት ችግርን ለመፍታት የካፒታል ዕቃዎችን በኪራይ መልክ ለኢንተርፕራይዞቹ እንዲቀርቡ መፍቀዱ ይታወሳል፡፡
በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የተጣለበትን አገራዊ ኃላፊነት በመወጣት በአገራችን በተለይ አምራች ኢንዱስትሪዎች እንዲስፋፉ እና የካፒታል ክምችት እንዲያድግ እንዲሁም የስራ እድል እንዲሰፋ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

👍77❤21
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በሀገሪቱ የሚስተዋለውን የሲሚንቶ አቅርቦት ችግር በከፊል ለመቅረፍ የሚያስችለውን የግዙፍ ሲሚንቶ ፋብሪካዎችን ብድር ማጽደቁን አስታወቀ፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ባለፉት ሶስት ዓመታት ሁለት ግዙፍ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች እና አንድ የቢቭሬጅ ፋብሪካ ብድር ያቀረበ ሲሆን፣ ግዙፍ ፋብሪካዎችን ለማቋቋም የሚቀርቡ ጥያቄዎች ቁጥር ባንኩ ከገነባው የፋይናንስ አቅም አንጻር በቂ አለመሆናቸውን የባንኩ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው አስታውቀዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ እንዳሉት የአምራች ኢንዱስትሪውን ዘርፍ ጥቅል የሀገር ውስጥ ምርት ድርሻ ለማሳደግና የአስር ዓመት መሪ የኢንዱስትሪ የልማት ግብን ለማሳካት ባንኩ በትኩረት እንደሚሰራም ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የካፒታል መጠኑን ከሶስት ዓመት በፊት ከነበረበት 2.6 ቢሊዮን ብር ወደ 38 ቢሊዮን ብር ማሳደጉንና በዚህም ባንኩ በዘንድሮ በጀት ዓመት 46.4 ቢሊዮን ብር ብድር ማጽደቅ መቻሉን ነው በጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት ያስታወቁት፡፡
ዶ/ር ዮሐንስ በተመሳሳይ በክልሎች ያለውን የፍትሃዊነትና፣ የተደራሽነት ጥያቄዎች ለመመለስ እንዲቻል ባንኩ በሁሉም ክልሎች የአቅም ግንባታ ስራዎች እና የግንዛቤ ማሳደግ ስራዎችን እየሰራ ከመሆኑም በላይ አገልግሎቱን በቅርበት ለመስጠት እንዲቻልም በሁሉም የአገሪቱ አካባቢዎች የዲስትሪክቶችን እና የቅርንጫፎችን ቁጥር የማሳደግ ስራ በሪፎርሙ እንደተከናወነ በመግለጫቸው አመላክተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በሀገራችን የልማት ስራዎች ውስጥ የመሪነት ሚናውን እየተወጣ መጓዝ የቻለ አንጋፋ ባንክ መሆኑ የተጠቀሰ ሲሆን፣ ባንኩ የሀገሪቱን የልማት ፕሮጀክቶችና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎችን በፋይናንስ በመደገፍ፣ በተለይ ለግብርና፣ ለአግሮ ፕሮሰሲንግ እና በአጠቃላይ ለአምራች ኢንዱስትሪው የፋይናንስ አቅርቦት ማድረግ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ተጠቅሷል፡፡
የሀገሪቱን ፈጣን ልማት ተከትሎ በመንግስትና በግሉ ዘርፍ የሚካሄዱ የልማት ፕሮጀክቶች በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ በመምጣቱ የኢትዮጵያ ልማት ባንክም ይህንኑ የሚመጥን ምላሽ በመስጠት ላይ እንደሚገኝ የገለጹት የባንኩ ፕሬዚዳንት በተለይ እ.ኤ.አ በ2030 ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የልማት ባንክ ለመሆን ያስቀመጠውን ርዕይ ለማሳካት እንዲያስችለው የተለያዩ የአሰራር ለውጦችንና ማሻሻያዎችን በማድረግ ለውጥ በማምጣት ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
የባንኩ የብድር ስርጭትና አሰባሰብን በተመለከተ በበጀት አመቱ ለልዩ ልዩ ኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች (በአምራች ኢንዱስትሪው፣ በግብርና፣ በማዕድንና ኃይል እንዲሁም በፋይናንስ አገልግሎቶች ለተሰማሩ ፕሮጀክቶች አዋጭነታቸውን በማረጋገጥ 46.4 ቢሊዮን ብር ብድር ለማቅረብ ያፀደቀ ሲሆን፣ ከ19.3 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር ማሰራጨቱ ተብራርቷል፡፡ በተጨማሪም በበጀት አመቱ 13.5 ቢሊዮን ብር ከብድር በውሉ መሠረት ለመሰብሰብ መቻሉንም ተጠቅሷል፡፡
ዶ/ር ዮሐንስ እንዳሉት በበጀት አመቱ መጨረሻ የባንኩን ጠቅላላ ሀብት 160.8 ቢሊዮን ብር ማድረስ የተቻለ ሲሆን፣ ዓመታዊ ትርፉም ከታክስ በፊት 6.4 ቢሊዮን ብር ሆኗል፡፡ ይህ የባንኩ ትርፍ በታሪኩ ከፍተኛው ሆኖ የተመዘገበ መሆኑን የጠቀሱት ፕሬዚዳንቱ የባንኩ አጠቃላይ ካፒታል ወደ 38 ቢሊዮን ብር ማድረስ መቻሉንም ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ተቋማዊ ለውጡን ለማረጋገጥ ከሚያስችሉት የማሻሻያ ስራዎች አንዱ የሆነው የዲቢኢ ቦንድ ሽያጭ በተያዘው በጀት ዓመት 14.59 ቢሊዮን ብር ማሰባሰብ መቻሉንና ይህም በአጠቃላይ ባንኩ ከዲቢኢ ቦንድ ሽያጭ 25 ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰብ መቻሉ ተጠቁሟል።
ባንኩ ከጥቂት ዓመታት በፊት ከፍተኛ የገንዘብ ኪሳራ ውስጥ ገብቶ እንደነበር ያስታወሱት ፕሬዚዳንቱ አጠቃላይ የተበላሸ ብድር ምጣኔው ከ43 በመቶ በላይ ደርሶ የነበረ ቢሆንም ይህንን ለማስተካከል ባንኩ የአምስት ዓመት እ.ኤ.አ (2018/19-2023/24) ስትራቴጂክ እቅድ በመቅረጽ የአሰራር ስርዓቱን በማሻሻል፣ ጥንቃቄ የተሞላበት የብድር ስርዓትን በመዘርጋት የባንኩ የአገልግሎት መስጫ የስራ ክፍሎችን በመጨመርና ተደራሽነትን በማስፋት ውጤታማ ስራ ማከናወን መቻሉን ነው ለጋዜጠኞች ይፋ ያደረጉት፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የኮርፖሬት ግብርና ፋይናንሲንግ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ዋቄ በበኩላቸው ከጋዜጠኞች ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ በሰጡበት ወቅት እንዳሉት ባንኩ በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚያቀርበውን ብድር ፍትሃዊ ለማድረግ በአደረጃጀትና በአሰራር ለመመለስ ጥረት እያደረገ መሆኑን ጠቅሰው እንደማሳያም ከወለድ ነጻ የፋይናንስ አገልግሎት መስጠት መጀመሩንና መዋቅሩንም በየክልሉ እያሰፋ መሆኑን አንስተዋል፡፡
ባንኩ አድሎአዊ አሰራርን ለመቆጣጠር የሚያስችል ሰፊ አሰራር ያለው መሆኑን የገለጹት አቶ ጌታቸው የብድር አሰጣጡ ቁጥጥርና ክትትል ባረጋገጠ ሁኔታ የሚፈጸም መሆኑንና ይህም በአግባቡ ስለመፈጸሙ የሚከታተል እና የሚቆጣጠር የሥራ አመራር ቦርድ፣ ብሄራዊ ባንክ እና ሌሎች ተቆጣጣሪ ተቋማት እንዳሉ አስገንዝበዋል፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ኮርፖሬት አገልግሎት ተጠባባቂ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው በላይ በበኩላቸው ባንኩ ያካሄደው ሪፎርም የዲስትሪክቶችን ቁጥር ከ12 ወደ 24፤ የቅርንጫፎችን ቁጥር ከ78 ወደ 100 ማሳደጉ በሁሉም የአገሪቱ አካባቢዎች ተደራሽ እንዲሆን እንዳስቻለው አብራርተዋል፡፡

👍63❤13🤝1
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በቱሪዝም ዘርፍ ለተሰማሩ የሊዝ ፋይናንስ ደንበኞቹ በ4.1 ሚሊዮን ዶላር የገዛቸውን ተሸከርካሪዎች አስረከበ፡፡
ባንኩ ለቱሪዝም ዘርፍ ስራው በእጅጉ አስፈላጊ የሆኑ 87 ተሸከርካሪዎችን ነው ለዘርፉ የሊዝ ፋይናንስ ደንበኞች ያስረከበው፡፡
በርክክብ ስነስርዓቱ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ዶክተር ዮሐንስ አያሌው እንዳሉት የቱሪዝሙ ዘርፍ ካለው እምቅ አቅም አንጻር ሃገሪቱ ተገቢውን ጥቅም እንድታገኝ ለዘርፉ ድጋፍ ማድረግ በእጅጉ ተገቢ ነው፡፡
ባንኩም ዘርፉ ለሃገር ልማት ያለውን አስተዋጽዖ በመረዳት በሊዝ ፋይናንስ ለደንበኞቹ ያስረከባቸው ተሸከርካሪዎች ዘርፉ ለኢኮኖሚው የሚያበረክተውን አስተዋጽዖ ከማሳደጉም በላይ ለበርካቶች የስራ እድልን የሚፈጥር ነው ብለዋል ፕሬዝዳንቱ፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በቀጣይም ለቱሪዝም እና ለሌሎች የተመረጡ የልማት ዘርፎች የሚያደርገውን ድጋፍ በማጠናከር ሃገራዊ ሃብት እንዲፈጠር በትኩረት የሚሰራ ይሆናል ብለዋል፡፡
ለእነዚህ ተሸከርካሪዎቹ የወጣው ወጪም ከግዥው ውጭ ያሉ ተጨማሪ ወጪዎችን የማያካትት መሆኑን ባንኩ አስታውቋል፡፡
ተሸከርካሪዎቹ በቱሪዝም ዘርፍ ለተሰማሩ 36 የሊዝ ፋይናንስ ደንበኞች ነው የተላለፉት፡፡
ለደንበኖች ከተላለፉት በተጨማሪ የቀሪ 28 ተሸከርካሪዎች ግዥም በሂደት ላይ መሆኑን ባንኩ አስታውቋዋል፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ትኩረት ሰጥቶ ከሚደግፋቸው ዘርፎች መካከል ቱሪዝም አንደኛው ሲሆን ዘርፉ ለሃገር ኢኮኖሚ የሚያበረክተው አስተዋጽዎ ከፍያለ እንዲሆን በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡

👍64❤18👏1