Development Bank of Ethiopia (DBE)
23.3K subscribers
2.1K photos
76 videos
4 files
578 links
The development bank of Ethiopia (DBE) is one of the financial institutions engaged in providing short, medium and long term development credits.
Download Telegram
Senior Officer Positions
👍24❤19
Officer Positions
👍46❤42👏7🤝3
How to Apply 👆🏾
👍69❤29🤝4
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Turn off your VPN to get access to the job application site.
👍75❤24🤝3👏2
መልሱን በፌስ ቡክ ገጻችን የውስጥ የመልእክት መቀበያ ሳጥን ይላኩልን፡፡
ቀድሞ በተሟላ መንገድ የመለሰ የባንኩን የህትመት ውጤቶች ከሞባይል ካርድ ጋር ይሸለማል፡፡
https://www.facebook.com/dbethiopia
👍72❤24👏3🤝1
ማስታወቂያ

የስራ ቅጥር ማመልከቻ ቀን ለተጨማሪ ሶስት ቀናት ተራዘመ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሰኔ 27 ቀን 2015 ዓ.ም 1 ሺህ 70 በሚሆኑ ክፍት የስራ መደቦች ላይ የተቀመጠውን መስፈርት የምታሟሉ አመልካቶችን አወዳድሮ ለመቅጠር ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወሳል፡፡ በተለይ ለቡድን ስራ አስኪያጅ፣ ለሲኒየር ኦፊሰር እና ለኦፊሰር የስራ መደቦች የማመልከቻ የጊዜ ገደብ የሚጠናቀቀው ዛሬ ሐምሌ 7 ቀን 2015 ዓ.ም መሆኑን አስታውቆ ነበር፡፡

ይሁን እንጂ አንዳንድ አመልካቶች በማመልከት ሂደት ወቅት በተሳካ መልኩ ማመልከቻዎቻችሁን ለማስተላለፍ እንዳልቻላችሁ በፌስ ቡክ ገጻችን፣ በአስተያየት መስጫ ሳጥንና በውስጥ መስመር ስልኮቻችን በመጀመሪያዎቹ ሁለት የማመልከቻ ቀናት ከፍተኛ መጨናነቅ እንደገጠማችሁ የገለፃችሁ በመሆኑና ባንኩም የሰጣችሁትን ጥቆማዎች ግምት ውስጥ በማስገባት የማመልከቻ ጊዜውን ለሚቀጥሉት ሶስት ቀናት ማለትም እስከ መጪው ሰኞ ሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ማራዘሙን እየገለፀ በተጠቀሱት ቀናት ውስጥ ማመልከት የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት ያሳውቃል፡፡

መልካም እድል

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
👍227❤53🤝22👏18
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጋር በመተባበር አፍላገ ልማት የተሰኘ ሳምንታዊ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ማዘጋጀት ከጀመረ ዓመት አስቆጥሯል፡፡ በዚህ በባንኩ በሊዝ ፋይናንስ እና ፕሮጀክት ፋይናንስ የብር አቅርቦት ስርዓት ተጠቃሚ የሆኑ ተበዳሪዎችን የስኬት ታሪክ በማቅረብ ልምድ እንዲቀሰምበት አድርጓል፡፡ የሳምንታዊ ፕሮግራማችን አካል በሆነው አዝናኝ እና አስተማሪ የሆነ ድርማ፣ የአገር ውስጥ እና የውጭ የልማት ባንኮችን የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎችን ስናደርስ ቆይተናል፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ እንደ አገር እያደረገ ያለውን አስተዋጽዖ በቀጣይ ክፍሎች አሰናድቶ በማቅረብ ተጨማሪ አቅም ለመፍጠር ይሰራል፡፡

አፍላገ ልማት ፕሮግራምን መከታተል ለምትሹ ሁሉ እሁድ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በኢቲቪ ዜና ቻናል ዘወትር እሁድ ከምሽቱ 2፡50- 3፡30 በድጋሚ ማክሰኞ ከ10፡00 እስከ 10፡40 እንዲሁም በኢትዮጵያ ሬዲዮ ዘወትር ሰኞ ረፋድ ከ3፡20 – 4፡00 ላይ በመከታተል ስለ ባንካችን የበለጠ ማወቅ እና የበለጠ መጠቀም የምትችሉበት መረጃ እንድትወስዱ ተጋብዛችኋል፡፡
👍33❤14👏4🤝2
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በአገራችን መሰረታዊ የኢኮኖሚ ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉ ፕሮጀክቶችን በሊዝ እና በፕሮጀክት ፋይናንስ የፋይናንስ አቅርቦትን በማሳደግ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን ሲፈጽም ቆይቷል፡፡

ባንኩ የተረከበውን አገራዊ ኃላፊነት በተሻለ ለመወጣት የሚያስችለውን አሰራር በመዘርጋት፤ ራሱን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደራጀ እና ትርፋማ ወደመሆን እየተሸጋገር ያለ ባንክ ነው፡፡

ከ115 ዓመታት በፊት በግብርና ዘርፍ በበሬ ብድር አቅርቦት የተጀመረው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ እንቅስቃሴ ዛሬ ላይ ትራክተሮችን፣ የትራክተር ተቀጽላዎችን፣ ኮምባይን ሃርቨስተሮችን፣ የግብርና መለዋወጫዎችንና፣ ግብዓቶችን በማቅረብ ለግብርናው መዘመን የራሱን አስተዋጽዖ እያበረከተ ይገኛል፡፡

ከዚህ ባሻገር የኢንዱስትሪ ልማት ለአገር ኢኮኖሚ መሻሻል ካለው የላቀ ፋይዳ አንጻር ለአምራች ዘርፍ ልማት ትኩረት በመስጠት ተበዳሪዎች ትኩረት አድርገው እንዲሰሩ በማበረታት የፋይናንስ ውስንነት ያለባቸውን ተቋማት አቅም በማጎልበት የራሱን አሻራ እያሳረፈ ይገኛል፡፡

በቀጣይ በተለይ ለማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ትኩረት በመሰጠት የሚያቀርበውን ፋይናንስ በማሳደግ እና የቴክኒክ ድጋፍ መስጠቱን አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡
👍48❤4👏2
ማክሰኞ ሐምሌ 4 ቀን 2015 ዓ.ም በፌስ ቡክ ገጻችን ባንካችንን የተመለከተ ጥያቄ ማቅረባችን ይታወሳል፡፡ በዚህም በእለቱ የተሟላ መልስ ቀድሞ በመስጠት ያዘጋጀነውን ማበረታቻ ሽልማት አሸናፊ የሆነው በፌስቡክ ገጹ በተገለጸው ስም መሰረት ይድነቃቸው ንጉሴ ነው፡፡
ተሳታፊያችን ላደረጉት መልካም ተሳትፎ እያመሰገንን ስጦታውን ካዛንችስ ከሚገኘው የባንካችን ዋና መስሪያ ቤት ሚዲያና ኮምዩኒኬሽን ቢሮ እንዲወስዱ እንጠይቃለን፡፡
ሳምንት የሚያሸልሙ ጥያቄዎቻችንን ይዘን እንመጣለን ይጠብቁን!
👍149👏22❤19🤝5
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ለአገራችን ከሚሰጡት የላቀ ፋይዳ በመነሳት ያሉባቸውን ተግዳሮቶች ለመቅረፍ የሚያስችል ስራ እየሰራ ይገኛል፡፡

ኢንተርፕራይዞቹ ሊያጋጥሟቸው የሚችሉ የቴክኖሎጂ ችግሮችን በመቅረፍ እና የማሽነሪ አቅርቦት ከነድጋፉ በማዘጋጀት፣ የክህሎት ክፍተታቸውን መሙላት የሚያስችል ስልጠና በመስጠት እና በተለይ በአምራች ኢንዱስትሪ ላይ ተሳትፏቸውን እንዲያሳድጉ በማገዝ በኩል ተጨባጭ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
👍35❤16
እንደሚታወቀው ከ80 በመቶ በላይ የሚሆነው የአገራችን ህዝብ የኑሮ መሰረት ግብርና እና ከግብርና ጋር የተያያዘ ሥራ ነው፡፡ ግብርና ከኢንዱስትሪ ጋር ተናቦ እና አንዱ ሌላውን እየመገበ እንዲሄድ በማድረግ የኢንዲስትሪ መሰረቱን አስተማማኝ ማድረግ ይቻላል፡፡ ለማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች ትኩረት ተሰጥቶ መሰራት የሚገባው መሰረታዊ ምክነያትም አንድም በአገራችን ዘላቂ እና አስተማማኝ ኢንዱስትሪ ለመገንባት የሚያስችል በሌላ መልኩም ሰፊ የሰው ጉልበት የሚይዝና የአገራችንን የግብርና ምርት ግብአቶችን በመጠቀም እሴት ጨምሮ የአለም ገበያን ጭምር ለመቆጣጠር ሰፊ እድል የሚሰጥ በመሆኑ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
👍61❤22🤝3
የኢትዮጵያ ልማት በሊዝ ፋይናንስ እና በፕሮጀክት ፋይናንስ የብድር ሞዳሊቲ የብድር አገልግሎት እንደሚሰጥ ይታወቃል፡፡ ሆኖም አንዳንድ ግለሰቦች ባንኩ በተለየ ሁኔታ ለስልጠና ተሳታፊዎች ብድር ያመቻቸ በማስመሰል እያጭበረበሩ መሆኑን ባንኩ ደርሶበታል፡፡ በመሆኑም ባንኩ ከተለመደው የብድር አሰጣጥ ስርዓት ውጭ ምንም አይነት የተለየ የብድር አገልግሎት የማይሰጥ መሆኑን አውቃችሁ ለዚህም ከባንኩ ውጭ ለየትኛውም ግለሰብ ሆነ ድርጅት ኃላፊነት ያልሰጠና መረጃው ስህተት መሆኑን ተገንዝባችሁ ራሳችሁን ከአጭበርባሪዎች እንድትጠብቁ ያሳስባል፡፡
በዚህ አጋጣሚ ትክክለኛ መረጃዎችን ከባንኩ ድረ ገጽ እና ከትክክለኛ የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾቻችን ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
Website
https://www.dbe.com.et/
Facebook
https://www.facebook.com/dbethiopia
Telegram
https://t.me/DBE_1901Ethiopia
Twitter
https://twitter.com/DBE_Ethiopia
Youtube
https://www.youtube.com/@developmentbankofethiopia
Instagram
https://www.instagram.com/dbe_ethiopia/
👍32❤10🤝2
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር እና ተጠሪ ተቋማቱ ጋር በጋራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሄዱ፡፡

በተከላ መርሃ ግብሩ የባንኩና የአስተዳደሩ የተጠሪ ተቋማቱ ሰራተኞችና የማኔጅመንት አባላት ተሳትፈዋል፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዝደንት ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው በዚሁ ወቅት እንደገለጹት ባንኩ ለግብርናው ዘርፍ ለሰጠው ልዩ ትኩረት የደን ልማት ወሳኝ በመሆኑ በየዓመቱ በሚዘጋጁ የተከላ ቦታዎች የችግኝ ተከላ እንደሚካሂድ ተገልጿል፡፡

በዚህም በጉለሌ እጸዋት ማዕከል በራሱ የወሰደውን መሬት በደንና ለእይታ ማራኪ በሆኑ እጸዋት በመሸፈን ውጤታማ ስራ መስራቱ ተገልጿል፡፡

ይህም ችግኝ መትከል ብቻ ሳይሆን መንከባከብ እንደሚገባ ማሳያ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን በተለያዩ አካባዎች የሚካሄዱ ተከላዎች በጥበቃና በእንክብካቤ ቢታገዙ በአጭር ጊዜ የሀገሪቱን የደን ሀብት ማሳደግ እንደሚቻል በዚሁ ወቅት ተገልጿል፡፡
👍62❤24👏4