Development Bank of Ethiopia (DBE)
23.3K subscribers
2.1K photos
76 videos
4 files
578 links
The development bank of Ethiopia (DBE) is one of the financial institutions engaged in providing short, medium and long term development credits.
Download Telegram
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በራሱ ወጭና ከጀርመን ልማት ባንክ ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ የገዛቸውን 27 ትራክተሮች ለደንበኞቹ አስረከበ፡፡

ባንኩ ለሊዝ ፋይናንስ ደንበኞቹ ካስረከባቸው ትራክተሮች ውስጥ 20ዎቹ ከጀርመን ልማት ባንክ ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ የተገዙ ሲሆን ቀሪዎቹን 7 ትራክተሮች ደግሞ በባንኩ ሙሉ ወጭ የተገኙ ናቸው፡፡

ትራክተሮቹን ለደንበኞቹ ያስረከቡት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ፋይናንሲንግ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አስፋው አበራ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የግብርና ሜካናይዜሽንን በሀገሪቱ ለማስፋፋት እና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

ማሽነሪዎቹን የተረከቡ ደንበኞች በበኩላቸው የግብርናውን ዘርፍ በማዘመን ምርትና ምርታማነትን ከማስፋፋቱ በተጨማሪ ለወጣቶች በሚፈጥሩት የስራ ዕድል እንደሀገር የሚኖራቸውን አስተዋጾ እንደሚያሳድግላቸው ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ግብርናውን ማዘመን የሚያስችሉ የእርሻ ማሽነሪዎችን በተከታታይ ዙሮች ለደንበኞቹ ሲያስተላልፍ የቆየ መሆኑን ያስታወሱት ም/ል ፕሬዝዳንቱ ባንኩ በቀጣይም ይህንኑ ተግባሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡
👍6020🤝2
Senior Officer Positions
👍2419
Officer Positions
👍4642👏7🤝3
How to Apply 👆🏾
👍6929🤝4
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Turn off your VPN to get access to the job application site.
👍7524🤝3👏2
መልሱን በፌስ ቡክ ገጻችን የውስጥ የመልእክት መቀበያ ሳጥን ይላኩልን፡፡
ቀድሞ በተሟላ መንገድ የመለሰ የባንኩን የህትመት ውጤቶች ከሞባይል ካርድ ጋር ይሸለማል፡፡
https://www.facebook.com/dbethiopia
👍7224👏3🤝1
ማስታወቂያ

የስራ ቅጥር ማመልከቻ ቀን ለተጨማሪ ሶስት ቀናት ተራዘመ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሰኔ 27 ቀን 2015 ዓ.ም 1 ሺህ 70 በሚሆኑ ክፍት የስራ መደቦች ላይ የተቀመጠውን መስፈርት የምታሟሉ አመልካቶችን አወዳድሮ ለመቅጠር ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወሳል፡፡ በተለይ ለቡድን ስራ አስኪያጅ፣ ለሲኒየር ኦፊሰር እና ለኦፊሰር የስራ መደቦች የማመልከቻ የጊዜ ገደብ የሚጠናቀቀው ዛሬ ሐምሌ 7 ቀን 2015 ዓ.ም መሆኑን አስታውቆ ነበር፡፡

ይሁን እንጂ አንዳንድ አመልካቶች በማመልከት ሂደት ወቅት በተሳካ መልኩ ማመልከቻዎቻችሁን ለማስተላለፍ እንዳልቻላችሁ በፌስ ቡክ ገጻችን፣ በአስተያየት መስጫ ሳጥንና በውስጥ መስመር ስልኮቻችን በመጀመሪያዎቹ ሁለት የማመልከቻ ቀናት ከፍተኛ መጨናነቅ እንደገጠማችሁ የገለፃችሁ በመሆኑና ባንኩም የሰጣችሁትን ጥቆማዎች ግምት ውስጥ በማስገባት የማመልከቻ ጊዜውን ለሚቀጥሉት ሶስት ቀናት ማለትም እስከ መጪው ሰኞ ሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ማራዘሙን እየገለፀ በተጠቀሱት ቀናት ውስጥ ማመልከት የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት ያሳውቃል፡፡

መልካም እድል

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
👍22753🤝22👏18
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጋር በመተባበር አፍላገ ልማት የተሰኘ ሳምንታዊ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ማዘጋጀት ከጀመረ ዓመት አስቆጥሯል፡፡ በዚህ በባንኩ በሊዝ ፋይናንስ እና ፕሮጀክት ፋይናንስ የብር አቅርቦት ስርዓት ተጠቃሚ የሆኑ ተበዳሪዎችን የስኬት ታሪክ በማቅረብ ልምድ እንዲቀሰምበት አድርጓል፡፡ የሳምንታዊ ፕሮግራማችን አካል በሆነው አዝናኝ እና አስተማሪ የሆነ ድርማ፣ የአገር ውስጥ እና የውጭ የልማት ባንኮችን የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎችን ስናደርስ ቆይተናል፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ እንደ አገር እያደረገ ያለውን አስተዋጽዖ በቀጣይ ክፍሎች አሰናድቶ በማቅረብ ተጨማሪ አቅም ለመፍጠር ይሰራል፡፡

አፍላገ ልማት ፕሮግራምን መከታተል ለምትሹ ሁሉ እሁድ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በኢቲቪ ዜና ቻናል ዘወትር እሁድ ከምሽቱ 2፡50- 3፡30 በድጋሚ ማክሰኞ ከ10፡00 እስከ 10፡40 እንዲሁም በኢትዮጵያ ሬዲዮ ዘወትር ሰኞ ረፋድ ከ3፡20 – 4፡00 ላይ በመከታተል ስለ ባንካችን የበለጠ ማወቅ እና የበለጠ መጠቀም የምትችሉበት መረጃ እንድትወስዱ ተጋብዛችኋል፡፡
👍3314👏4🤝2
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በአገራችን መሰረታዊ የኢኮኖሚ ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉ ፕሮጀክቶችን በሊዝ እና በፕሮጀክት ፋይናንስ የፋይናንስ አቅርቦትን በማሳደግ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን ሲፈጽም ቆይቷል፡፡

ባንኩ የተረከበውን አገራዊ ኃላፊነት በተሻለ ለመወጣት የሚያስችለውን አሰራር በመዘርጋት፤ ራሱን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደራጀ እና ትርፋማ ወደመሆን እየተሸጋገር ያለ ባንክ ነው፡፡

ከ115 ዓመታት በፊት በግብርና ዘርፍ በበሬ ብድር አቅርቦት የተጀመረው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ እንቅስቃሴ ዛሬ ላይ ትራክተሮችን፣ የትራክተር ተቀጽላዎችን፣ ኮምባይን ሃርቨስተሮችን፣ የግብርና መለዋወጫዎችንና፣ ግብዓቶችን በማቅረብ ለግብርናው መዘመን የራሱን አስተዋጽዖ እያበረከተ ይገኛል፡፡

ከዚህ ባሻገር የኢንዱስትሪ ልማት ለአገር ኢኮኖሚ መሻሻል ካለው የላቀ ፋይዳ አንጻር ለአምራች ዘርፍ ልማት ትኩረት በመስጠት ተበዳሪዎች ትኩረት አድርገው እንዲሰሩ በማበረታት የፋይናንስ ውስንነት ያለባቸውን ተቋማት አቅም በማጎልበት የራሱን አሻራ እያሳረፈ ይገኛል፡፡

በቀጣይ በተለይ ለማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ትኩረት በመሰጠት የሚያቀርበውን ፋይናንስ በማሳደግ እና የቴክኒክ ድጋፍ መስጠቱን አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡
👍484👏2
ማክሰኞ ሐምሌ 4 ቀን 2015 ዓ.ም በፌስ ቡክ ገጻችን ባንካችንን የተመለከተ ጥያቄ ማቅረባችን ይታወሳል፡፡ በዚህም በእለቱ የተሟላ መልስ ቀድሞ በመስጠት ያዘጋጀነውን ማበረታቻ ሽልማት አሸናፊ የሆነው በፌስቡክ ገጹ በተገለጸው ስም መሰረት ይድነቃቸው ንጉሴ ነው፡፡
ተሳታፊያችን ላደረጉት መልካም ተሳትፎ እያመሰገንን ስጦታውን ካዛንችስ ከሚገኘው የባንካችን ዋና መስሪያ ቤት ሚዲያና ኮምዩኒኬሽን ቢሮ እንዲወስዱ እንጠይቃለን፡፡
ሳምንት የሚያሸልሙ ጥያቄዎቻችንን ይዘን እንመጣለን ይጠብቁን!
👍149👏2219🤝5