Development Bank of Ethiopia (DBE)
23.3K subscribers
2.1K photos
76 videos
4 files
578 links
The development bank of Ethiopia (DBE) is one of the financial institutions engaged in providing short, medium and long term development credits.
Download Telegram
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በራሱ ወጭና ከጀርመን ልማት ባንክ ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ የገዛቸውን 27 ትራክተሮች ለደንበኞቹ አስረከበ፡፡

ባንኩ ለሊዝ ፋይናንስ ደንበኞቹ ካስረከባቸው ትራክተሮች ውስጥ 20ዎቹ ከጀርመን ልማት ባንክ ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ የተገዙ ሲሆን ቀሪዎቹን 7 ትራክተሮች ደግሞ በባንኩ ሙሉ ወጭ የተገኙ ናቸው፡፡

ትራክተሮቹን ለደንበኞቹ ያስረከቡት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ፋይናንሲንግ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አስፋው አበራ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የግብርና ሜካናይዜሽንን በሀገሪቱ ለማስፋፋት እና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

ማሽነሪዎቹን የተረከቡ ደንበኞች በበኩላቸው የግብርናውን ዘርፍ በማዘመን ምርትና ምርታማነትን ከማስፋፋቱ በተጨማሪ ለወጣቶች በሚፈጥሩት የስራ ዕድል እንደሀገር የሚኖራቸውን አስተዋጾ እንደሚያሳድግላቸው ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ግብርናውን ማዘመን የሚያስችሉ የእርሻ ማሽነሪዎችን በተከታታይ ዙሮች ለደንበኞቹ ሲያስተላልፍ የቆየ መሆኑን ያስታወሱት ም/ል ፕሬዝዳንቱ ባንኩ በቀጣይም ይህንኑ ተግባሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡
👍6020🤝2
Senior Officer Positions
👍2419
Officer Positions
👍4642👏7🤝3
How to Apply 👆🏾
👍6929🤝4
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Turn off your VPN to get access to the job application site.
👍7524🤝3👏2
መልሱን በፌስ ቡክ ገጻችን የውስጥ የመልእክት መቀበያ ሳጥን ይላኩልን፡፡
ቀድሞ በተሟላ መንገድ የመለሰ የባንኩን የህትመት ውጤቶች ከሞባይል ካርድ ጋር ይሸለማል፡፡
https://www.facebook.com/dbethiopia
👍7224👏3🤝1
ማስታወቂያ

የስራ ቅጥር ማመልከቻ ቀን ለተጨማሪ ሶስት ቀናት ተራዘመ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሰኔ 27 ቀን 2015 ዓ.ም 1 ሺህ 70 በሚሆኑ ክፍት የስራ መደቦች ላይ የተቀመጠውን መስፈርት የምታሟሉ አመልካቶችን አወዳድሮ ለመቅጠር ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወሳል፡፡ በተለይ ለቡድን ስራ አስኪያጅ፣ ለሲኒየር ኦፊሰር እና ለኦፊሰር የስራ መደቦች የማመልከቻ የጊዜ ገደብ የሚጠናቀቀው ዛሬ ሐምሌ 7 ቀን 2015 ዓ.ም መሆኑን አስታውቆ ነበር፡፡

ይሁን እንጂ አንዳንድ አመልካቶች በማመልከት ሂደት ወቅት በተሳካ መልኩ ማመልከቻዎቻችሁን ለማስተላለፍ እንዳልቻላችሁ በፌስ ቡክ ገጻችን፣ በአስተያየት መስጫ ሳጥንና በውስጥ መስመር ስልኮቻችን በመጀመሪያዎቹ ሁለት የማመልከቻ ቀናት ከፍተኛ መጨናነቅ እንደገጠማችሁ የገለፃችሁ በመሆኑና ባንኩም የሰጣችሁትን ጥቆማዎች ግምት ውስጥ በማስገባት የማመልከቻ ጊዜውን ለሚቀጥሉት ሶስት ቀናት ማለትም እስከ መጪው ሰኞ ሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ማራዘሙን እየገለፀ በተጠቀሱት ቀናት ውስጥ ማመልከት የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት ያሳውቃል፡፡

መልካም እድል

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
👍22753🤝22👏18