Development Bank of Ethiopia (DBE)
23.3K subscribers
2.1K photos
76 videos
4 files
578 links
The development bank of Ethiopia (DBE) is one of the financial institutions engaged in providing short, medium and long term development credits.
Download Telegram
👍13❤7
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለመቄዶኒያ የበጎ አድራጎት ማኅበር የ15 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ማኔጅመንት አባላት በትናትናው እለት ለመቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማኅበር አስራ አምስት ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ፤ ለ7500 አረጋውያንም የምሳ ፕሮግራም አካሂዷል፡፡

በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው ዛሬ እንደ አንድ የመቄዶኒያ ቤተሰብ ማኅበሩ የደረሰበትን ደረጃ ለማየት እና ድጋፍ ለማድረግ እንደተገኙ አንሥተዋል፡፡ ዶ/ር ዮሐንስ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ መቄዶኒያ እያደረገ ያለውን በጎ ተግባር ወደፊትም ማገዙን እንደሚቀጥል በመግለጽ ይህን የበጎ አድራጎት ማህበር በማቋቋም ዜጎች ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ እድል መክፈቱ የሚመሰገን መሆኑን ተናግረዋል፡፡ መቄዶኒያ ጧሪና ደጋፊ የሌላቸውን ወገኖቻችንን ሰብስቦ እንደ ቤተሰብ ፍቅር እና እንክብካቤ በመስጠቱ ሊመሰገን እንደሚገባም አያይዘው ገልጸዋል፡፡

የመቄዶኒያ የበጎ አድራጎት ማህበር መስራች ክቡር ዶ/ር ቢኒያም በለጠን በመወከል መልዕክት ያስተላለፉት አቶ ማሞ ታደሠ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ቋሚ የመቄዶኒያ ቤተሰብ መሆኑን ጠቅሰው ባንኩ ባደረገው የ15 ሚሊዮን ብር ድጋፍ በእጅጉ መደሰታቸውን ገለጸዋል፡፡ ይህም ድጋፍ ላለፉት ዓመታት ሳይቋርጥ የቀጠለ መሆኑን አስታውሰው ምስጋና አቅርበዋል፡፡

መቄዶኒያ የበጎ አድራጎት ማህበር ምንም ጧሪና ደጋፊ የሌላቸውን በተለይም ደግሞ እራሳቸውን ችለው መጸዳዳት፣ መመገብ እና መንቀሳቀስ የማይችሉ የአልጋ ቁራኛ የሆኑና የሰው ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው አረጋውያንና የአእምሮ ሕሙማንን ከወደቁበት ጎዳና ላይ በማንሳት ከ 7500 በላይ የሚሆኑ ተረጂዎችን ሰብስቦ በወር 30 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች በሚገኙ 25 ከተሞች መጠለያ በማዘጋጀት እየረዳ ይገኛል፡፡

መቄዶኒያ የበጎ አድራጎት ማህበር መጠለያ የሚሹ ወገኖችን በበቂ ሁኔታ ማገዝ የሚችልበትን ሁኔታ ለመፍጠር ከ2.3 ቢሊዮን ብር በላይ የሚፈጅ ባለ 15 ወለል ዘመናዊ ሆስፒታል እና ምቹ የአረጋውያን መኖሪያ ሕንጻ በመገንባት ላይ ነው፡፡ የግንባታው 70 በመቶ መጠናቀቁን ከማህበሩ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል፡፡ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለሦስተኛ ዙር 15 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ያደረገ ሲሆን፣ ከአሁን ቀደምም ለማኅበሩ የተሸከርካሪ ድጋፍ በማድረግ ለወገን ደራሽነቱን እያረጋገጠ ይገኛል፡፡
👍60❤22
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በአገራችን ያለው የጤና አገልግሎት ሽፋን እንዲስፋፋ ሴክተሩን በፋይናንስ መደገፍ የሚያስችል ስርዓት የዘረጋው የፖሊሲ ማሻሻያ አድርጎ ወደ ተግባር ከገባበት እ.አ.አ. ነሐሴ 2022 ጀምሮ ነው፡፡


የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የጤናው ሴክተር በፕሮጀክት ፋይናንሲንግ አገልግሎት ሥርዓት የሚያካትታቸው አገልግሎቶች፣


• በገበያ አዋጪ የሆኑ እጅግ ዘመናዊ (tertiary) ሆስፒታሎችን ፋይናንስ ያደርጋል፤
o የሜዲካል ቱሪዝምን የማስፋፋት አቅም የሚኖራቸው፣
o ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ አገልግሎቶችን የሚያቀርቡ፣
o አገልግሎት በሚሰጥባቸው የሕክምና ዘርፎች እጅግ ብቁ የሆኑ ጤና ባለሙያዎችን የያዙ፣
o ልዩ ሕክምና (highly specialized medical care) አገልግሎት መስጠት ላይ ትኩረት ያደረጉ፣


በፕሮጀክት ፋይናንስ አገልግሎት ሥርዓት ተጠቃሚ ለመሆን የሚያበቁ መስፈርቶች፣


• የሚገነቡት ሆስፒታሎች በሚመለከተው የመንግሥት አካልና በባንኩ የሚጠበቅባቸውን ዝቅተኛ መመዘኛዎች ያሟሉ ሆነው መቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
• ሆስፒታሎች በቂ ሀብት (አቅም) ሊኖራቸው ይገባል፣
o ሦስት የሙሉ ሰዓት ሐኪሞች፣ እንዲሁም አንድ አጠቃላይ ሆስፒታል ሥራ ፈቃድ ይዞ የሚገኝ ማለት ነው፡፡
o ሪፈራል ለመቀበል የሚያበቃ በቂ ሀብት (አቅም) ያላቸው

በሊዝ ፋይናንስ አገልግሎት የጤናው ሴክተር በሊዝ ፋይናንስ አገልግሎት ሥርዓት

• ልዩ ልዩ የሕክምና መስጫ መሣሪያዎች፤
o የሕክምና ላብራቶሪ መሣሪያዎች (laboratory equipment)፣
o የምርመራ መሣሪያዎች (diagnostic equipment)፣
o የሕክምና ንጽህና መጠበቂያ መሣሪያዎች (medical sanitation equipment) እና ሌሎች የሕክምና መሣሪያዎች ናቸው፡፡
👍69❤15🤝5
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የ4ኛ ዙር አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ስልጠናን ሁሉንም የስልጠና ቀናት ሳያቆራርጡ ያጠናቀቁ ሰልጣኞች የቢዝነስ የአዋጭነት ምክረ ሀሳባቸውን እንዲያስገቡ ጥሪ አቀረበ፡፡

ባንኩ ከወራት በፊት በ4ኛ ዙር የኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ስልጠና 112 ሺህ ለሚሆኑ ስራ ፈጣሪዎች ስልጠና መስጠቱ ይታወሳል፡፡

ከሰልጣኞች መካከል አምስቱንም ቀናት ስልጠናውን የተከታተሉና ሰልጠነው ያጠናቀቁ ለምስክር ወረቀት ዝግጁ የሆኑ ሰልጣኖች ብቻ ወደ ባንኩ ዲስትሪክቶችና ቅርንጫፎች በመቅረብ ሪፖርት እንዲያደርጉና የቢዝነስ አዋጭነት ሀሳባቸውን እንዲያስገቡ ነው ባንኩ ያሳሰበው፡፡

ሙሉ በሙሉ ስልጠናውን ተከታትለው ለአጠናቀቁ ሰልጣኞች የምስክር ወረቀት የማዘጋጀቱ ስራ እየተሰራ ሲሆን፣ የሰልጣኞችን የስራ ጊዜ በአግባቡ ለመጠቀም ሲባል ቀሪ የሌለባቸው ሰልጣኞች የቅድመ ዝግጅት ስራቸውን እንዲጀምሩ ነው ባንኩ ሁኔታዎችን ያመቻችው፡፡

ሰልጣኞች ወደ አምራች ኢንዱትሪ ዘርፍ ለመግባት ያላቸውን የስራ ተነሳሽነት ባንኩ መደገፍና ማበረታታት ስላለበት የስልጠና የምስክር ወረቀቱ እስኪሰራጭ ድረስ በልዩ ሁኔታ ማስታናገድ እንደሚገባ ስለታመነበት ነው፡፡

በዚህም መሰረት ሙሉ በሙሉ ሁሉንም የስልጠና ቀናት ሳያቆራርጡ የሰለጠኑ ሰልጣኞች እድሉን በመጠቀም ወደ ተመዘገቡባቸው የባንኩ ዲስትሪክቶችና ቅርንጫፎች በመቅረብ በተመቻቸው እድል እንዲጠቀሙ ባንኩ ጥሪ አቅርቧል፡፡
👍235❤49👏29🤝4
ፍላጎትዎን ይመርምሩ!
ለመነሻ የሚሆንዎን የሥራ ሐሳብ ይወጥኑ!
‹‹ከልብ ካለቀሱ እንባ አይገድም›› ነውና ብሂሉ እንደ አቅምዎ ለሥራ የሚሆን ካፒታል በተናጠል ወይም በጋራ ያዘጋጁ!
ቀሪውን ባንካችን በአጋርነት ክፍተትዎን ሊሞላ ዝግጁ ነው፡፡

መልካም የሥራ ሳምንት ይሁንልዎ!

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
❤78👍42🤝10
👍17👏14❤13
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በኢቢሲ ቤተሰብ የእግር ኳስ ውድድር ሶስተኛ በመውጣት የነሐስ ሜዳሊያ ተበረከተለት፡፡
ስምንት ቡድኖችን አካቶ ሲካሄድ በነበረው ውድድር የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በመጨረሻው ጨዋታ የገቢዎች ሚኒስቴርን በማሸነፍ ነበር የሶስተኛ ደረጃን ያገኘው፡፡
ኢቢሲ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባደረጉት ጨዋታ ኢቢሲ 1 ለ 0 በማሸነፍ ሻምፒዮን ሆኗል፡፡
የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት፡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝደንት ኢሳያስ ጂራና ሌሎች የክብር እንግዶች በተገኙበት የሜዳሊያና ሽልማት ስነስርአቱ ተካሂዷል፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የእግር ኳስ ቡድን አባላትም በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው የሽልማት ስነስርአት ላይ ተገኝተው ሜዳሊያቸውን ተረክበዋል፡፡
አዲሱን የኢቢሲ ዋና መስሪያ ቤት ምርቃትን ምክንያት በማድረግና በሰራተኞች መካከል መቀራረብን ብሎም ወንድማማችነትን ማጎልበት አላማ ያደረገው የእግር ኳስ ውድድር በደማቅ ሁኔታ ተጠናቋል፡፡
👍44❤24👏3
ሕልሙን እየኖረ ያለው ወጣት
ገና በለጋ እድሜው ወደ እንግሊዝ አገር ለትምህርት እንደተሰደደ ይናገራል፡፡ ከአገር ሲወጣ ትምህርቱን እየተከታተለ ለመነሻ የሚሆነውን ገንዘብ አጠራቅሞ መመለስ እንደሚገባው አምኖ ነው፡፡ ታዲያ ለቃሉ ታማኝ የሆነው የዛሬው ባለታሪካችን ዘካርያስ ዳኜ ብዙዎች ለመሰደድ የሚመኙበትን አገር ጥሎ ወደ እናት አገሩ ተመለሰ፡፡

"ብዙዎች ወደ አገር መመለሴን እንደ እብደት ቆጥረውበኛል፡፡" ይላል ዘካርያስ፡፡ እንግሊዝን ያህል የግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤት እና የሰለጠነ አገር ትቶ ወደ ኢትዮጵያ መምጣት ከብዙዎች ሐሳብ የታቀረነ ነበርና ከዚህም ከዚያም ይደርስበት የነበረው ጫና ቀላል እንዳልነበረ የሚያስረዳው ዘካርያስ እኔ የሄደበትን ዓላማ ካሳካ ወደ አገሩ ተመልሶ ሥራውን መሥራት እንዳለበት በመወሰን ወደ አገሩ ተመለሰ፡፡

ዘካርያስ ወደ አገሩ ከተመለሰ በኋላ በ2002 ዓ.ም የመጀመሪያውን የኅትመት ቤት ሐዋሳ በመክፈት መንቀሳቀስ ጀመረ፡፡ ሆኖም የኅትመት ቤቱ አዲስ እንደመሆኑ መጠን ሥራ ማግኘት ቀላል እንዳልነበረ ይናገራል፡፡ ዘካርያስ የማተሚያ ቤቱን ብቃት ለማሳየት ለሌላ ማተሚያ ቤት የተሰጠ ትዕዛዝ ከፍሎ በመውሰድ ጭምር በትዕዛዙ መሰረት በጥራት ሰርቶ በማስረከብ ማተሚያ ቤቱ ተወዳዳሪ ማተሚያ ቤት እንደሆነ ለማሳመን የሄደበትን ርቀት የማይረሳው ትዝታ መሆኑን አጫውቶናል፡፡

ዳኜ የሐዋሳ ዲስትሪክት የሊዝ ፋይናንስ ተበዳሪ ነው፡፡ በማኑፋክቸሪንግ ሲስተምስ ኢንጂነሪንግ የመጀመሪያ ዲግሪ ይዟል፡፡ በ2002 ዓ.ም ወደ ንግዱ ዓለም እንደተቀላቀለ የሚናገረው ዘካርያስ በዙሪያው ካለው ችግር ተነሥቶ ለእሱ መፍትሄ ለመስጠት የሚያደርገው ትግል ዛሬ ለደረሰበት ደረጃ መሠረት እንደሆነው ይናገራል፡፡

ዘካርያስ ዛሬ ላይ እውን ያደረገው የሶፍት ማምረቻ ፋብሪካ መነሻ ከኅትመት ቤቱ የሚወጣው የወረቀት ቁርጥራጭ ነው፡፡ እለት እለት ከህትመት ቤቱ የሚወጣው የወረቀት ቁርጥራጭ ብዛት መላ እንደሚያስፈልገው ያውጠነጥን የነበረው ዘካርያስ ወረቀቶቹ ድጋሚ ለሥራ የሚውሉበት ሁኔታ ሲያጠና ፐልፕ ምርት ማምረት እንደሚቻል ደረሰበት፡፡ ሳያመነታ ሐሳቡን በወረቀተ አሰፈረው፡፡ ህልሙን እውን ማድረግ ይችል ዘንድ ያጋጠመውን የፋይናንስ ችግር እንዴት መቅረፍ እንደሚችል ሲያማክር ልማት ባንክ ሁነኛ መላ መሆኑን ሹክ አሉት፡፡

ሁለት ልብ ሆኖ ወደ ባንኩ እንዳቀና ዘካርያስ ይናገራል፡፡ "በብድር ሥርዓት ውስጥ አልፌ ስለማላውቅ ይሆናል አይሆንም የሚለው ብዙ እርግጠኛ አልነበርኩም" የሚለው ዘካርያስ ልማት ባንክ ከጠበቀው ባነሰ ጊዜ ለሥራ የሚያስፈልገውን ማሽን በስድስት ወራት ውስጥ በማስረከብ አስደመመው፡፡ ልማት ባንክ 280 ሺህ ዶላር የሚሆን ማሽን በማቅረብ ከወረቀት ቁርጥራጮች ፐልፕ እያመረተ የገበታ ሶፍት፣ የሆስፒታል፣ የመጸዳጃ ቤት፣ እና መሰል የሶፍት ወረቀቶች ለገበያ በማቅረብ ላይ ይገኛል፡፡

ዛሬ የዘካርያስ ፋብሪካ ከኅትመት ቤት በሚወጣ የወቀረት ተረፈ ምርት አንድም ወረቀቱ ሲወገድ የሚፈጠረውን የአየር ብክለት በማስወገድ በሌላ መልኩ ደግሞ አላስፈላጊ ተብሎ የሚወገዱ ወረቀቶችን መልሶ ጥቅም ላይ በማዋል 70 በመቶ በአገር ውስጥ ግብዓት፣ 30 በመቶ ከውጭ በሚገባ ጥሬ እቃ ግብዓት ጥራቱን የጠበቀ የሶፍት ምርት እያመረተ ይገኛል፡፡ "ሪሳይክሊንግ አገር ይጠቅማል፡፡ በእርግጥ የሶፍት ፋብሪካዎች አሉ፤ ነገር ግን የሚሰሩት ፐልፕ ከውጭ እያስገቡ ነው፡፡ ይህ ለተጨማሪ የውጭ ምንዛሬ ይዳርጋል፡፡ የእኛ ፋብሪካ እሱን ያስቀረ ነው፡፡" የሚለው ዘካሪያስ 74 የሚሆኑ ሠራተኞቹን ቀጥሮ ያሠራል፡፡ ከሌሎች ቦታዎች ወረቀት እየሰበሰቡ የሚመጡ በርካታ የተደራጁ ወጣቶች የሥራ እድል ተፈጥሮላቸዋል፡፡ የካፒታል መጠኑም 50 ሚሊዮን ብር በላይ ሆኗል፡፡

ዘካሪያስ ህልሙ ትልቅ ነው፡፡ ዘካሪያ ህልሙ በአገሩ ሠርቶ ተለውጦ መኖር ነበር፡፡ አቋሙ ለስራ ያለው ጽናት ደግሞ ህልሙን እንዲኖር እረድቶታል፡፡ በቀጣይ ለፕልፕ ምርት የሚሆን የደን ልማት ላይ ለመሰማራት እቅድ ይዟል፡፡ ጥቅጥቅ የደን ማሳ ይፈልጋል፡፡ በዚህም ወረቀት ማምረት፤ ከውጭ የሚገባውን በአገር ውስጥ በማምረት ለሌላ አገራት የሚተርፍ ነገር ይዞ ብቅ ለማለት አቅዷል፡፡ ለዚህ ደግሞ ልማት ባንክ ትክክለኛ አጋር ነው ይላል፡፡ "የኢትዮጵ ልማት ባንክ ለእኔ እናት ነው፡፡ በችግራችን ጊዜ እንክብካቤ አድርገውልናል፡፡ ክትትል ያደርጋሉ፡፡ አዳዲስ ፕሮጀክት እንድንጀምር ያበረታታሉ፡፡ ብዙ ጊዜዬን በአገሬ እንዳሳልፍ እና በስራ እንድወጠር ያደረገኝ ከልማት ባንክ መበደሬ ነው፡፡ ከዚህ በኋላም ከልማት ባንክ ጋር በአጋርነት ወደፊት ነው" ይላል ዘካርያስ፡፡ በእርግጥም የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሠረቶ አገርና ሕዘቡን ማሻገር ለሚፈልግ ሁሉ የሚተማመኑበት የልማት አጋር ነው፡፡
👍63👏29❤16
👍102❤49👏18
የስራ ማስታወቂያ
መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች ከታች ባለው ሊንክ በመግባት ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
መልካም እድል
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ

https://jobs.dbe.com.et
👍150❤91👏56🤝32
Team Manager Position
👍45❤13