Development Bank of Ethiopia (DBE)
23.3K subscribers
2.1K photos
76 videos
4 files
578 links
The development bank of Ethiopia (DBE) is one of the financial institutions engaged in providing short, medium and long term development credits.
Download Telegram
👍16❤6👏3
ስራን ማክበር ያስከብራል

በድሬዳዋ ከተማ ገነደ ቆሬ አካባቢ ነው ተወልዶ ያደገው የዛሬው ባለታሪካችን ቴዎድሮስ ተስፋዬ፡፡ ቴዎድሮስ ገና በልጅነቱ ነገውን እንዴት ማስተካከል እንደሚገባው እያሰላሰለ ለዛም የሚሆን ጥረት እያደረገ በልጅነቱ የሚገጥመውን ፈተና በትእግስት እያለፈ ዛሬን የደረሰ ወጣት ነው፡፡ በትምህርቱ ደከም ይል እንደነበረና ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም የሚያዘልቅ አቅም ላይ አለመሆኑን የተረዳው ወጣቱ በትምህርት ማምጣት የማይችለውን የስኬት መንገድ በጥረቱ ማሳካት እንደሚገባው በማመን የስኬት መንገዶቹን ማሰስ ጀመረ፡፡

<<ተመርህ ሰው ካልሆንክ ቦርሳ ተሸካሚ ነው የምትሆነው>>፣ <<በደሃ አገር አይተኛም>>፣ <<18 ዓመት ሲሞላህ ከቤት አስወጣሃለሁ>> የሚለው የቤተሰብ ንግግር ተደማምሮ ቴዎድሮስ ወደፊት ምን መስራት አለብኝ የሚለው ሳያሰላስል ያደረበት ጊዜ የለም፡፡ ቴዎድሮስ ለመጀመሪያ ጊዜ ጋራዥ ውስጥ ለአንድ አመት በሳምንት ሁለት ብር እየተከፈለው ተቀጥሮ ይሰራ ጀመር፡፡ ቴዎድሮስ የብሩ ብዛት ሳይሆን ስራ መጀመሩ አንድ እርምጃ መሆኑን ስለተረዳ አንድ አመት በሁለት ብር ክፍያ ታግሶ ሰራ፡፡ በዚህም አልቆመም ቴዎድሮስ ተማሪ እያለ ቆሎ በመሸጥ የራሱን ወጪ ለመሸፈን ሙከራ አድርጓል፡፡ ይሁንና ስራን አውቆ እና አምኖ መስራት በመሆኑ ስኬታማ የሚያደርገው የቆሎ ስራውን ሊገፋበት ባለመቻሉ ወደ አናጺነት ሙያ እንደተሸጋገረም ይናገራል፡፡ <<ወንድሜ ተመርቆ ዶክተር ሲባል የእኔ ቦታስ ምንድን ነው>> እያልኩ አሰላስል ስለነበረ የእንጨት ስራን ያለ እረፍት ነበር የምሰራው ይላል ቴዎድሮስ፡፡

የእንጨት ሙያን ቴክኒክና ሙያ ተቋም ውስጥ ገብቶ በመማር ያዳበረው ሲሆን በ1999 ዓ.ም የድሬዳዋ ቴክኒክና ሙያን ወክሎ ወደ አዲስ አበባ በማቅናት በእንጨት ስራ ባደረገው ውድድር የወርቅ ሜዳሊያ ማምጣት ችሏል፡፡ ቴዎድሮስ ምንም እንኳን ከቴክኒክና ሙያ በእንጨት ስራ በቂ ክህሎት ይዞ የወጣ ቢሆንም ተመልሶ ስራ ለመያዝ ፈተና እንደገጠመው ይናገራል፡፡ ቴዎድሮስ ሰውነቱ ቀጠን ያለ ስለነበረ የእንጨት ስራን ድካም ይቋቋማል ብለው ስለማያማኑ ለመቀጠር የሄደባቸው ቦታዎች በሙሉ እሱን ለማሰራት ፈቃደኛ አለመሆናቸው በመግለጽ ይመልሱት ነበር፡፡ ይህ ቁጭትን እየፈጠረበት ሄደ፡፡

ቴዎድሮስ በዚህ ሁኔታ ውስጥ እያለ የህይወቱ አዲስ ምዕራፍ ለመጀመር የሚያስችል በጎ ዜና ሰማ፡፡ ጉብዝናውን የሚያውቅና ድካሙን የተረዳው ቴክኒክና ሙያ ያስተምረው የነበረ መምህር ሞዴፊክ እንጨት መሰንጠቂያ እንደሚገዛለት ነገረው፡፡ ቴዎድሮስ የእንጨት ስራን በራሱ አቅም አንድ ብሎ ጀመረው፡፡

ማሽኑ ከተተከለ በኋላ ስራ ትዛዝ የሚሰጠው አለማግኘቱ ደግሞ ሌላ ፈተና ሆነበት፡፡ ይሁንና እጁን አጣጥፎ መቀመጥን አልመረጠም፡፡ ለተማሪዎች የሚሆን የመመረቂያ ፎለደር የሰራውን ናሙና ይዞ በየኮሌጁ ስራ ማሰስ ጀመረ፡፡ አሁንም አምኖ ስራ የሚሰጠው አካል ማግኘት አልቻለም፡፡ አንድ ተቋም ግን ዘግይቶም ቢሆን እሺታውን ሲገልጽለት ለስራ ፈላጊው ቴዎድሮስ ትልቅ ሃሴትን የፈጠረ ነበር፡፡ ተቋሙም ያዘዘውን ስራ በውጤታማነት በማከናወን ለመጀመሪያ ጊዜ የስምንት ሺህ ብር ትርፍ አገኘ፡፡ ያገኘውን ትርፍ ተጨማሪ ማሽን ገዛበት፡፡ አሁን ለቴዎድሮስ ነገሮች መስመራቸውን እየያዙለት መሄድ ጀምረዋል፡፡ ይህን የተመለከቱ ቤተሰቦቹም ከጎረቤት ጀምሮ <<ኑ ልጃችን ጋር አሰሩ>> በሚል ገበያ ያፈላልጉለት ጀመር፡፡ ስራ በስራ ላይ እየተጨመረ ቴዎድሮስ ህልሙን ማሳካት በሚችልበትን ቁመና ላይ ሆነ፡፡

በዚህ ሁኔታ ውስጥ እያለ ነው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚሰጠውን አገልግሎት በአንድ ስብሰባ የሰማው፡፡ ሳያመነታ ወደ ልማት ባንክ በማቅናት በሊዝ ፋይናንስ የብድር አገልግሎት ስራውን ወደተሻለ ጥራትና ምርታማነት የሚያሸጋግር ማሽን አስገባ፡፡ ሰባት ዲጅታል ማሽን በልማት ባንክ አማካኝነት ገዝቷል፡፡ ጌጣጌጦችን በኮምፒውተር ታዞ የሚሰራ ማሽን፣ አበባና ጠርዝ የሚለጥፍ ማሞቂያ ማሽን፣ እንጨት መሰንጠቂያ እና ጠርዝ መላጊያ ማሽን ባለቤት ሆኗል፡፡

የልማት ባንክ ደጋፍ እንዳልተለየው የሚናገረው ቴዎድሮስ ብድሩን በአግባቡ በመመለስ ላይ እንደሚገኝ ይናገራል፡፡ <<ማሽን በመግዛታችን የምርት ደረጃችን ተቀይሯል>> የሚለው ቴዎድሮስ ድርጅታቸው በስፋትም በጥራትም ማምረት የሚያስችለው ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተናግሯል፡፡ <<ሕይወት ሁልጊዜ ፈተና ነች፡፡ በሚሰራ ሰው ህይወት ውስጥ ሁሌም ችግር አለ፡፡ ዋናው ችግሮቻችንን ለመፍታት ያለን ቆራጥነት እና ትዕግስት ነው የሚወስነው>> ሲልም ይመክራል፡፡

ቴዎድሮስ ማንም ሰው ስራ ለመስራት ሲነሳ ከቤተሰብ፣ ከጓደኛ እንዲሁም ከማህበረሰብ የሚደርስበትን ትችትና ተጽእኖ ወደኋላ በመተው በስኬት ማስተማር እንደሚቻል ማሳያ ምስክር ነው፡፡ አንድ ሰው የሚሰራውን ስራ አምኖና ለዛ የሚሆን እውቀት ጨብጦ የሚሰራ ከሆነ ፈተና ቢያጋጥመው እንኳን ማለፍ እንደሚቻል ከባለታሪኩ መረዳት ይቻላል፡፡ ስራን ማክበር ያስከብራል፡፡
👍82❤17👏4
👍32❤3
👍30❤9
❤26👍22👏1
❤23👍22👏1
❤29👍18👏1
👍13❤7
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለመቄዶኒያ የበጎ አድራጎት ማኅበር የ15 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ማኔጅመንት አባላት በትናትናው እለት ለመቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማኅበር አስራ አምስት ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ፤ ለ7500 አረጋውያንም የምሳ ፕሮግራም አካሂዷል፡፡

በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው ዛሬ እንደ አንድ የመቄዶኒያ ቤተሰብ ማኅበሩ የደረሰበትን ደረጃ ለማየት እና ድጋፍ ለማድረግ እንደተገኙ አንሥተዋል፡፡ ዶ/ር ዮሐንስ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ መቄዶኒያ እያደረገ ያለውን በጎ ተግባር ወደፊትም ማገዙን እንደሚቀጥል በመግለጽ ይህን የበጎ አድራጎት ማህበር በማቋቋም ዜጎች ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ እድል መክፈቱ የሚመሰገን መሆኑን ተናግረዋል፡፡ መቄዶኒያ ጧሪና ደጋፊ የሌላቸውን ወገኖቻችንን ሰብስቦ እንደ ቤተሰብ ፍቅር እና እንክብካቤ በመስጠቱ ሊመሰገን እንደሚገባም አያይዘው ገልጸዋል፡፡

የመቄዶኒያ የበጎ አድራጎት ማህበር መስራች ክቡር ዶ/ር ቢኒያም በለጠን በመወከል መልዕክት ያስተላለፉት አቶ ማሞ ታደሠ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ቋሚ የመቄዶኒያ ቤተሰብ መሆኑን ጠቅሰው ባንኩ ባደረገው የ15 ሚሊዮን ብር ድጋፍ በእጅጉ መደሰታቸውን ገለጸዋል፡፡ ይህም ድጋፍ ላለፉት ዓመታት ሳይቋርጥ የቀጠለ መሆኑን አስታውሰው ምስጋና አቅርበዋል፡፡

መቄዶኒያ የበጎ አድራጎት ማህበር ምንም ጧሪና ደጋፊ የሌላቸውን በተለይም ደግሞ እራሳቸውን ችለው መጸዳዳት፣ መመገብ እና መንቀሳቀስ የማይችሉ የአልጋ ቁራኛ የሆኑና የሰው ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው አረጋውያንና የአእምሮ ሕሙማንን ከወደቁበት ጎዳና ላይ በማንሳት ከ 7500 በላይ የሚሆኑ ተረጂዎችን ሰብስቦ በወር 30 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች በሚገኙ 25 ከተሞች መጠለያ በማዘጋጀት እየረዳ ይገኛል፡፡

መቄዶኒያ የበጎ አድራጎት ማህበር መጠለያ የሚሹ ወገኖችን በበቂ ሁኔታ ማገዝ የሚችልበትን ሁኔታ ለመፍጠር ከ2.3 ቢሊዮን ብር በላይ የሚፈጅ ባለ 15 ወለል ዘመናዊ ሆስፒታል እና ምቹ የአረጋውያን መኖሪያ ሕንጻ በመገንባት ላይ ነው፡፡ የግንባታው 70 በመቶ መጠናቀቁን ከማህበሩ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል፡፡ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለሦስተኛ ዙር 15 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ያደረገ ሲሆን፣ ከአሁን ቀደምም ለማኅበሩ የተሸከርካሪ ድጋፍ በማድረግ ለወገን ደራሽነቱን እያረጋገጠ ይገኛል፡፡
👍60❤22
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በአገራችን ያለው የጤና አገልግሎት ሽፋን እንዲስፋፋ ሴክተሩን በፋይናንስ መደገፍ የሚያስችል ስርዓት የዘረጋው የፖሊሲ ማሻሻያ አድርጎ ወደ ተግባር ከገባበት እ.አ.አ. ነሐሴ 2022 ጀምሮ ነው፡፡


የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የጤናው ሴክተር በፕሮጀክት ፋይናንሲንግ አገልግሎት ሥርዓት የሚያካትታቸው አገልግሎቶች፣


• በገበያ አዋጪ የሆኑ እጅግ ዘመናዊ (tertiary) ሆስፒታሎችን ፋይናንስ ያደርጋል፤
o የሜዲካል ቱሪዝምን የማስፋፋት አቅም የሚኖራቸው፣
o ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ አገልግሎቶችን የሚያቀርቡ፣
o አገልግሎት በሚሰጥባቸው የሕክምና ዘርፎች እጅግ ብቁ የሆኑ ጤና ባለሙያዎችን የያዙ፣
o ልዩ ሕክምና (highly specialized medical care) አገልግሎት መስጠት ላይ ትኩረት ያደረጉ፣


በፕሮጀክት ፋይናንስ አገልግሎት ሥርዓት ተጠቃሚ ለመሆን የሚያበቁ መስፈርቶች፣


• የሚገነቡት ሆስፒታሎች በሚመለከተው የመንግሥት አካልና በባንኩ የሚጠበቅባቸውን ዝቅተኛ መመዘኛዎች ያሟሉ ሆነው መቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
• ሆስፒታሎች በቂ ሀብት (አቅም) ሊኖራቸው ይገባል፣
o ሦስት የሙሉ ሰዓት ሐኪሞች፣ እንዲሁም አንድ አጠቃላይ ሆስፒታል ሥራ ፈቃድ ይዞ የሚገኝ ማለት ነው፡፡
o ሪፈራል ለመቀበል የሚያበቃ በቂ ሀብት (አቅም) ያላቸው

በሊዝ ፋይናንስ አገልግሎት የጤናው ሴክተር በሊዝ ፋይናንስ አገልግሎት ሥርዓት

• ልዩ ልዩ የሕክምና መስጫ መሣሪያዎች፤
o የሕክምና ላብራቶሪ መሣሪያዎች (laboratory equipment)፣
o የምርመራ መሣሪያዎች (diagnostic equipment)፣
o የሕክምና ንጽህና መጠበቂያ መሣሪያዎች (medical sanitation equipment) እና ሌሎች የሕክምና መሣሪያዎች ናቸው፡፡
👍69❤15🤝5
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የ4ኛ ዙር አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ስልጠናን ሁሉንም የስልጠና ቀናት ሳያቆራርጡ ያጠናቀቁ ሰልጣኞች የቢዝነስ የአዋጭነት ምክረ ሀሳባቸውን እንዲያስገቡ ጥሪ አቀረበ፡፡

ባንኩ ከወራት በፊት በ4ኛ ዙር የኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ስልጠና 112 ሺህ ለሚሆኑ ስራ ፈጣሪዎች ስልጠና መስጠቱ ይታወሳል፡፡

ከሰልጣኞች መካከል አምስቱንም ቀናት ስልጠናውን የተከታተሉና ሰልጠነው ያጠናቀቁ ለምስክር ወረቀት ዝግጁ የሆኑ ሰልጣኖች ብቻ ወደ ባንኩ ዲስትሪክቶችና ቅርንጫፎች በመቅረብ ሪፖርት እንዲያደርጉና የቢዝነስ አዋጭነት ሀሳባቸውን እንዲያስገቡ ነው ባንኩ ያሳሰበው፡፡

ሙሉ በሙሉ ስልጠናውን ተከታትለው ለአጠናቀቁ ሰልጣኞች የምስክር ወረቀት የማዘጋጀቱ ስራ እየተሰራ ሲሆን፣ የሰልጣኞችን የስራ ጊዜ በአግባቡ ለመጠቀም ሲባል ቀሪ የሌለባቸው ሰልጣኞች የቅድመ ዝግጅት ስራቸውን እንዲጀምሩ ነው ባንኩ ሁኔታዎችን ያመቻችው፡፡

ሰልጣኞች ወደ አምራች ኢንዱትሪ ዘርፍ ለመግባት ያላቸውን የስራ ተነሳሽነት ባንኩ መደገፍና ማበረታታት ስላለበት የስልጠና የምስክር ወረቀቱ እስኪሰራጭ ድረስ በልዩ ሁኔታ ማስታናገድ እንደሚገባ ስለታመነበት ነው፡፡

በዚህም መሰረት ሙሉ በሙሉ ሁሉንም የስልጠና ቀናት ሳያቆራርጡ የሰለጠኑ ሰልጣኞች እድሉን በመጠቀም ወደ ተመዘገቡባቸው የባንኩ ዲስትሪክቶችና ቅርንጫፎች በመቅረብ በተመቻቸው እድል እንዲጠቀሙ ባንኩ ጥሪ አቅርቧል፡፡
👍235❤49👏29🤝4
ፍላጎትዎን ይመርምሩ!
ለመነሻ የሚሆንዎን የሥራ ሐሳብ ይወጥኑ!
‹‹ከልብ ካለቀሱ እንባ አይገድም›› ነውና ብሂሉ እንደ አቅምዎ ለሥራ የሚሆን ካፒታል በተናጠል ወይም በጋራ ያዘጋጁ!
ቀሪውን ባንካችን በአጋርነት ክፍተትዎን ሊሞላ ዝግጁ ነው፡፡

መልካም የሥራ ሳምንት ይሁንልዎ!

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
❤78👍42🤝10
👍17👏14❤13
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በኢቢሲ ቤተሰብ የእግር ኳስ ውድድር ሶስተኛ በመውጣት የነሐስ ሜዳሊያ ተበረከተለት፡፡
ስምንት ቡድኖችን አካቶ ሲካሄድ በነበረው ውድድር የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በመጨረሻው ጨዋታ የገቢዎች ሚኒስቴርን በማሸነፍ ነበር የሶስተኛ ደረጃን ያገኘው፡፡
ኢቢሲ እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባደረጉት ጨዋታ ኢቢሲ 1 ለ 0 በማሸነፍ ሻምፒዮን ሆኗል፡፡
የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት፡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝደንት ኢሳያስ ጂራና ሌሎች የክብር እንግዶች በተገኙበት የሜዳሊያና ሽልማት ስነስርአቱ ተካሂዷል፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የእግር ኳስ ቡድን አባላትም በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው የሽልማት ስነስርአት ላይ ተገኝተው ሜዳሊያቸውን ተረክበዋል፡፡
አዲሱን የኢቢሲ ዋና መስሪያ ቤት ምርቃትን ምክንያት በማድረግና በሰራተኞች መካከል መቀራረብን ብሎም ወንድማማችነትን ማጎልበት አላማ ያደረገው የእግር ኳስ ውድድር በደማቅ ሁኔታ ተጠናቋል፡፡
👍44❤24👏3