Development Bank of Ethiopia (DBE)
23.3K subscribers
2.1K photos
76 videos
4 files
578 links
The development bank of Ethiopia (DBE) is one of the financial institutions engaged in providing short, medium and long term development credits.
Download Telegram
👍38👏9❤5
👍11❤2
የካራማራው ጀግና ዓሊ በርኬ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
****************

የቀድሞው የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባል የነበሩት የካራማራው ጀግና ዓሊ በርኬ ባደረባቸው ሕመም በ72 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ኦቢኤን ዘግቧል።

ጀግናው ዓሊ በርኬ በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ1969 ዓ.ም የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ ወረራ የፈፀመውን የሶማሊያው ዚያድ ባሬ ጦር ለመመከት ለሕዝቡ የተላለፈውን የእናት ሀገር ጥሪ ተቀብለው በሚሊሻ ወታደርነት ተመልምለው ከሰለጠኑ በኋላ ወደ ምሥራቅ የጦር ግንባር ዘምተዋል።

በጊዜው ወዶ ዘማች የነበሩት ዓሊ በርኬ በምሥራቅ ግንባር በተለይም በጅግጅጋ እና በጭናክሰን እንዲሁም በኦጋዴን ውስጥ ከወራሪው ጦር ጋር በተደረገው ፍልሚያ ተሰልፈው በቆራጥነት የተዋጉ እና ደማቸውን አፍስሰው የሀገር ድንበር ካስከበሩ እና ታሪክ ከማይረሳቸው ጀግኖቻችን አንዱ ነበሩ።

ኢትዮጵያን ለመውረር ለዓመታት ሲዘጋጅ የኖረው የዚያድ ባሬ መንግሥት በጦርነቱ ያስሰለፈው ታንክ እና መድፍ ቁጥር ከወገን ጦር ጋር ሲነጻጸር አንድ ለአምስት የሆነ ልዩነት እና ብልጫ በነበረበት ሁኔታ ውስጥ ነበር ዓሊ በርኬ ወደ ጦርሜዳ የገቡት።

በተለይ በጥር ወር 1970 ዓ.ም ዳካታ እና ካራማራ ላይ የጠላት የበላይነት አይሎ በነበረበት ወቅት የወሰዱት ቆራጥ እርምጃ ለወገን ጦር ወደ ድል መገስገስ ዋና ምክንያት መሆኑ ይነገራል።

በዚህም የወገን ጦር በተጠናከረ የመልሶ ማጥቃት እርምጃ ኢትዮጵያ በዚያድ ባሬ የጠላት ጦር ላይ ታሪካዊ እና የማይረሳ ድልን ልትቀዳጅ የቻለችው።

ቆራጡ ጀግና ዓሊ በርኬ የያዙዋቸውን 5 ተቀጣጣይ ቦምቦች ተጠቅመው አምስት የጠላት ታንኮችን አመድ በማድረግ የጠላት ጦር እንዲበተን እና ወደ ኋላ እንዲያፈገፍግ ያስቻለ ደማቅ ታሪክ ጽፈዋል።

ዓሊ በርኬ ለዚያ ወደር የለሽ የጀግንነት ተግባራቸው በ1971 ዓ.ም የሀገሪቷን ከፍተኛ የጦር ሜዳ ጀብዱ ኒሻን በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ማግኘት ችለዋል።
👍50❤15👏2
❤45👍8
👍16❤6👏3
ስራን ማክበር ያስከብራል

በድሬዳዋ ከተማ ገነደ ቆሬ አካባቢ ነው ተወልዶ ያደገው የዛሬው ባለታሪካችን ቴዎድሮስ ተስፋዬ፡፡ ቴዎድሮስ ገና በልጅነቱ ነገውን እንዴት ማስተካከል እንደሚገባው እያሰላሰለ ለዛም የሚሆን ጥረት እያደረገ በልጅነቱ የሚገጥመውን ፈተና በትእግስት እያለፈ ዛሬን የደረሰ ወጣት ነው፡፡ በትምህርቱ ደከም ይል እንደነበረና ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም የሚያዘልቅ አቅም ላይ አለመሆኑን የተረዳው ወጣቱ በትምህርት ማምጣት የማይችለውን የስኬት መንገድ በጥረቱ ማሳካት እንደሚገባው በማመን የስኬት መንገዶቹን ማሰስ ጀመረ፡፡

<<ተመርህ ሰው ካልሆንክ ቦርሳ ተሸካሚ ነው የምትሆነው>>፣ <<በደሃ አገር አይተኛም>>፣ <<18 ዓመት ሲሞላህ ከቤት አስወጣሃለሁ>> የሚለው የቤተሰብ ንግግር ተደማምሮ ቴዎድሮስ ወደፊት ምን መስራት አለብኝ የሚለው ሳያሰላስል ያደረበት ጊዜ የለም፡፡ ቴዎድሮስ ለመጀመሪያ ጊዜ ጋራዥ ውስጥ ለአንድ አመት በሳምንት ሁለት ብር እየተከፈለው ተቀጥሮ ይሰራ ጀመር፡፡ ቴዎድሮስ የብሩ ብዛት ሳይሆን ስራ መጀመሩ አንድ እርምጃ መሆኑን ስለተረዳ አንድ አመት በሁለት ብር ክፍያ ታግሶ ሰራ፡፡ በዚህም አልቆመም ቴዎድሮስ ተማሪ እያለ ቆሎ በመሸጥ የራሱን ወጪ ለመሸፈን ሙከራ አድርጓል፡፡ ይሁንና ስራን አውቆ እና አምኖ መስራት በመሆኑ ስኬታማ የሚያደርገው የቆሎ ስራውን ሊገፋበት ባለመቻሉ ወደ አናጺነት ሙያ እንደተሸጋገረም ይናገራል፡፡ <<ወንድሜ ተመርቆ ዶክተር ሲባል የእኔ ቦታስ ምንድን ነው>> እያልኩ አሰላስል ስለነበረ የእንጨት ስራን ያለ እረፍት ነበር የምሰራው ይላል ቴዎድሮስ፡፡

የእንጨት ሙያን ቴክኒክና ሙያ ተቋም ውስጥ ገብቶ በመማር ያዳበረው ሲሆን በ1999 ዓ.ም የድሬዳዋ ቴክኒክና ሙያን ወክሎ ወደ አዲስ አበባ በማቅናት በእንጨት ስራ ባደረገው ውድድር የወርቅ ሜዳሊያ ማምጣት ችሏል፡፡ ቴዎድሮስ ምንም እንኳን ከቴክኒክና ሙያ በእንጨት ስራ በቂ ክህሎት ይዞ የወጣ ቢሆንም ተመልሶ ስራ ለመያዝ ፈተና እንደገጠመው ይናገራል፡፡ ቴዎድሮስ ሰውነቱ ቀጠን ያለ ስለነበረ የእንጨት ስራን ድካም ይቋቋማል ብለው ስለማያማኑ ለመቀጠር የሄደባቸው ቦታዎች በሙሉ እሱን ለማሰራት ፈቃደኛ አለመሆናቸው በመግለጽ ይመልሱት ነበር፡፡ ይህ ቁጭትን እየፈጠረበት ሄደ፡፡

ቴዎድሮስ በዚህ ሁኔታ ውስጥ እያለ የህይወቱ አዲስ ምዕራፍ ለመጀመር የሚያስችል በጎ ዜና ሰማ፡፡ ጉብዝናውን የሚያውቅና ድካሙን የተረዳው ቴክኒክና ሙያ ያስተምረው የነበረ መምህር ሞዴፊክ እንጨት መሰንጠቂያ እንደሚገዛለት ነገረው፡፡ ቴዎድሮስ የእንጨት ስራን በራሱ አቅም አንድ ብሎ ጀመረው፡፡

ማሽኑ ከተተከለ በኋላ ስራ ትዛዝ የሚሰጠው አለማግኘቱ ደግሞ ሌላ ፈተና ሆነበት፡፡ ይሁንና እጁን አጣጥፎ መቀመጥን አልመረጠም፡፡ ለተማሪዎች የሚሆን የመመረቂያ ፎለደር የሰራውን ናሙና ይዞ በየኮሌጁ ስራ ማሰስ ጀመረ፡፡ አሁንም አምኖ ስራ የሚሰጠው አካል ማግኘት አልቻለም፡፡ አንድ ተቋም ግን ዘግይቶም ቢሆን እሺታውን ሲገልጽለት ለስራ ፈላጊው ቴዎድሮስ ትልቅ ሃሴትን የፈጠረ ነበር፡፡ ተቋሙም ያዘዘውን ስራ በውጤታማነት በማከናወን ለመጀመሪያ ጊዜ የስምንት ሺህ ብር ትርፍ አገኘ፡፡ ያገኘውን ትርፍ ተጨማሪ ማሽን ገዛበት፡፡ አሁን ለቴዎድሮስ ነገሮች መስመራቸውን እየያዙለት መሄድ ጀምረዋል፡፡ ይህን የተመለከቱ ቤተሰቦቹም ከጎረቤት ጀምሮ <<ኑ ልጃችን ጋር አሰሩ>> በሚል ገበያ ያፈላልጉለት ጀመር፡፡ ስራ በስራ ላይ እየተጨመረ ቴዎድሮስ ህልሙን ማሳካት በሚችልበትን ቁመና ላይ ሆነ፡፡

በዚህ ሁኔታ ውስጥ እያለ ነው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚሰጠውን አገልግሎት በአንድ ስብሰባ የሰማው፡፡ ሳያመነታ ወደ ልማት ባንክ በማቅናት በሊዝ ፋይናንስ የብድር አገልግሎት ስራውን ወደተሻለ ጥራትና ምርታማነት የሚያሸጋግር ማሽን አስገባ፡፡ ሰባት ዲጅታል ማሽን በልማት ባንክ አማካኝነት ገዝቷል፡፡ ጌጣጌጦችን በኮምፒውተር ታዞ የሚሰራ ማሽን፣ አበባና ጠርዝ የሚለጥፍ ማሞቂያ ማሽን፣ እንጨት መሰንጠቂያ እና ጠርዝ መላጊያ ማሽን ባለቤት ሆኗል፡፡

የልማት ባንክ ደጋፍ እንዳልተለየው የሚናገረው ቴዎድሮስ ብድሩን በአግባቡ በመመለስ ላይ እንደሚገኝ ይናገራል፡፡ <<ማሽን በመግዛታችን የምርት ደረጃችን ተቀይሯል>> የሚለው ቴዎድሮስ ድርጅታቸው በስፋትም በጥራትም ማምረት የሚያስችለው ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተናግሯል፡፡ <<ሕይወት ሁልጊዜ ፈተና ነች፡፡ በሚሰራ ሰው ህይወት ውስጥ ሁሌም ችግር አለ፡፡ ዋናው ችግሮቻችንን ለመፍታት ያለን ቆራጥነት እና ትዕግስት ነው የሚወስነው>> ሲልም ይመክራል፡፡

ቴዎድሮስ ማንም ሰው ስራ ለመስራት ሲነሳ ከቤተሰብ፣ ከጓደኛ እንዲሁም ከማህበረሰብ የሚደርስበትን ትችትና ተጽእኖ ወደኋላ በመተው በስኬት ማስተማር እንደሚቻል ማሳያ ምስክር ነው፡፡ አንድ ሰው የሚሰራውን ስራ አምኖና ለዛ የሚሆን እውቀት ጨብጦ የሚሰራ ከሆነ ፈተና ቢያጋጥመው እንኳን ማለፍ እንደሚቻል ከባለታሪኩ መረዳት ይቻላል፡፡ ስራን ማክበር ያስከብራል፡፡
👍82❤17👏4
👍32❤3
👍30❤9
❤26👍22👏1
❤23👍22👏1
❤29👍18👏1
👍13❤7