Development Bank of Ethiopia (DBE)
23.3K subscribers
2.1K photos
76 videos
4 files
578 links
The development bank of Ethiopia (DBE) is one of the financial institutions engaged in providing short, medium and long term development credits.
Download Telegram
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ለአገራችን ከሚሰጡት የላቀ ፋይዳ በመነሳት ያሉባቸውን ተግዳሮቶች ለመቅረፍ የሚያስችል ስራ እየሰራ ይገኛል፡፡ ኢንተርፕራይዞቼ ሊያጋጥሟቸው የሚችሉ የቴክኖሎጂ ችግሮችን በመቅረፍ እና የማሽነሪ አቅርቦት ከነድጋፉ በማዘጋጀት፣ የክህሎት ክፍተታቸውን መሙላት የሚያስችል ስልጠና በመስጠት እና በተለይ በአምራች ኢንዱስትሪ ላይ ተሳትፏቸውን እንዲያሳድጉ በማገዝ በኩል ተጨባጭ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡

በአራተኛ ዙር የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ስልጠና ላይ ስራ ፈላጊው ወደስራ ሊገባ የሚችልበትን ቀላል እና አዋጭ መላ በማቅረብ የብዙዎቻችሁን ቀልብ የያዘው አባ መላ በስልጠና ወቅት ያቀረባቸውን የስራ አማራጮች በተከታታይ ማስነበባችን ይታወቃል አማራጭ ሶስትን እንዲህ ያቀርብን ሲሆን በቀጣይ ክፍል ሌላ አዋጭ የስራ መስኮችን ይዘን የምንቀርብ ይሆናል፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
👍55❤11👏1
❤25👍16
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች በአራት ዙር ስልጠና ሰጥቷል፡፡ የአራተኛ ዙር ስልጠናን ጨምሮ እስካሁን 120 ሺህ የሚጠጉ ሰልጣኞች ስልጠና ወስደዋል፡፡ በአራተኛ ዙር ስልጠናውን ወስደው ያጠናቀቁ ሰልጣኞችን ሰርተፊኬት ለመስጠት የሚያስችል ቅድም ዝግጅት የተጠናቀቀ ሲሆን በቀጣይ በጀት ዓመት ቀሪዎችን ለማሰልጠን ሃብት የማሰባሰብ ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡

ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚሰጠውን የሊዝ ፋይናንሲንግ የብድር አገልግሎት ተጠቃሚ ለመሆን ወደባንካችን የሚመጣ ደንበኛ ማመልከቻ፣ ሊሠሩት ያሰቡትን ሥራ እና የመስሪያ ቦታውን አድራሻ የሚጠቅስ ማመልከቻ፣ ባንኩ ለአዲስ ደንበኞች ያዘጋጀውን ሥልጠና መውሰዱን የሚያሳይ የምስክር ወረቀት ኮፒ፣ የንግድ ሥራ ፍቃድ (ለማስፋፊያ)፣ የመስሪያ /የማምረቻ/፣ ዋጋ ማሳወቂያ ደረሰኝ /Pro-forma invoice/፣ የቅድመ ሥራ ታሪክን በሚመለከት (Track Record)፣ የግብር ግዴታ፣ የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ ጥናት እና ደብዳቤ፣ አስተዳደርን በሚመለከት፣ ዝርዝር የንግድ ሥራ ዕቅድ ወይም የአዋጭነት ጥናት (በተያያዘው ቅጽ መሠረት) አሟልቶ መምጣት ይኖርበታል፡፡ ደንበኞች ወደ ባንካችን ከመምጣታችሁ በፊት ልታሟሏቸው የሚገቡ መረጃዎችን የሚያሳይ ዝርዝር አያይዘንላችኋል፡፡

በተጨማሪም ባንካችን የሚሰጠውን ስልጠና በቅርብ ጊዜ እንዲያካሄድ በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾቻችን እየጠየቃችሁ ያላችሁ ተመዝጋቢዎች ባንኩ በያዝነው በጀት ዓመት 50 ሺህ ለሚሆኑ ተመዝጋቢዎች ስልጠና ለመስጠት ያሰበ ቢሆንም የተመዝጋቢው ቁጥር ከእጥፍ በላይ የጨመረ በመሆኑ ከተመዘገቡት 435 ሺህ ሰልጣኞች መካከል በመጀመሪያ ምዕራፍ ከፍተኛ በጀት በመመደብ 112 ሺህ ለሚሆኑ ሰልጣኞች ስልጠናውን ሰጥቷል፡፡ ለቀሪ ተመዝጋቢዎች ስልጠናውን ለመስጠት ዝግጅት እያደረገ ሲሆን ሁሉም ተመዝጋቢዎች ሰልጥነው ለአገር አቅም የሚሆኑበትን መንገድ ለመፍጠር ልማት ባንክ እንደሚሰራ ያረጋግጣል፡፡
👍70❤14
❤45👍34
ትችት ያበረታት የታታሪነት ተምሳሌት

ተስፋ የሚያስቆርጡ ብዙ ፈተናዎችን አሳልፋለች፡፡ ወደ ሥራ ለመግባት ባሰበችበት ወቅት ሁሉ ‹‹አትችዪም! ይቅርብሽ!›› የሚል ተስፋ የሚያስቆርጥ ቃል ሲወረውርላት እሷ ግን ራሷን እያበረታች ወደፊት መትመም የቻለች የትጉህነት ተምሳሌት ናት፡፡

ወጣት ልያ በለጠ ትባላለች፡፡ የማዕድ ምግብ ማምረቻ እና ማቀነባበሪያ መሥራች እና ሥራ አስኪያጅ ናት፡፡ የቤት ወጪሽን መሸፈን እንድትችዪ ይሁንሽ ተብላ እንድትሠራበት የተሰጣትን ትንሽ ኬክ ቤት በትጋቷ ወደ ፋብሪካ በመቀየር ችላ ያሳየች ታታሪ ሴት ናት፡፡

ሊያ በሥራ ሕይወቴ የገጠመኝ ከባዱ ፈተና ‹‹አትችዪም!›› በሚል የሚሰነዘርልኝ አስተያየት ነው ትላለች፡፡ ጉዳይ ለማስፈጸም በሄደችባቸው ቦታዎች ሁሉ ወጣት ሴት መሆኗ ሥራ ከመሥራት የሚያግዳት ያህል ‹‹ትችያለሽ ወይ!›› የሚለው ጥያቄ የሚያበሳጫት ቢሆንም ከመጉበጥ ይልቅ በርትታ እንድትቆም የበለጠ ጉልበት እንደጨመረላት ነግራናለች፡፡ እንስቷ ባላስታውሳቸው የምትላቸው ከባድ ፈተናዎች ገጥመዋት በብልሃት አልፋቸዋለች፡፡ ዛሬ ላይ ለደረሰችበት ስኬት መሠረቱም ትጋት እና ተስፋ አለመቁረጥ መሆኑን አልሸሸገችም፡፡ ‹‹ተስፋ ሳልቆርጥ ሁሉንም በመታገስ መጨረሻውን ለማየት ስለምጥር ለዛሬ ስኬት በቅቻለሁ›› ብላለች፡፡

የልማት ባንክ ለአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የሚሰጠውን ስልጠና የወሰደችው ሊያ 2010 ላይ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሐዋሳ ቅርንጫፍ የሊዝ ፋይናንስ ደንበኛ በመሆን የብድር አገልግሎት ተጠቃሚ ሆናለች፡፡

ልማት ባንክ ለሥራ የሚሆናትን ሙሉ ማሽን ገዝቶ በሊዝ ፋይናንስ የብድር አገልግሎት አቅርቦላታል፡፡ ድርጅቷ 52 ሠራተኞችን ቀጥሮ ያሠራል፡፡ በቀጣይ በሦስት ፈረቃ ሥራ ሲጀምሩ 180 ሠራተኞችን መቅጠር እንደሚቻል ትናገራለች፡፡ የሊያ ብስኩት ፋብሪካ እስከ 70 ሚሊዮን ብር በሚገመት ካፒታል እውን የሆነ ነው፡፡ ሊያ አሁን የምትሠራው ከባለቤቷ ጋር ነው፡፡

በቀጣይ ዱቄት ፋብሪካና ፓስታ የማምረት እቅድ እንዳላት ትገልጻለች፡፡ ሴት ልጅ የሚገጥማትን ፈተና ሁሉ ተቋቁማ ጠንክራ በመቆም መሥራትና ቤቷን ማገዝ እንደሚገባት ትመክራለች፡፡ የሊያ ሕይወት በውጣ ውረዶች ተስፋ ከመቁረጥና የሚያሰናክል እንቅፋት ቢገጥምም ከማፈግፈግ ይልቅ በትጋት ወደፊት በመገስገስ ሕልምን ማሳካት እንደሚቻል ማሳያ ናት፡፡
👍39👏8❤7
👍38👏9❤5
👍11❤2
የካራማራው ጀግና ዓሊ በርኬ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
****************

የቀድሞው የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባል የነበሩት የካራማራው ጀግና ዓሊ በርኬ ባደረባቸው ሕመም በ72 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ኦቢኤን ዘግቧል።

ጀግናው ዓሊ በርኬ በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ1969 ዓ.ም የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ ወረራ የፈፀመውን የሶማሊያው ዚያድ ባሬ ጦር ለመመከት ለሕዝቡ የተላለፈውን የእናት ሀገር ጥሪ ተቀብለው በሚሊሻ ወታደርነት ተመልምለው ከሰለጠኑ በኋላ ወደ ምሥራቅ የጦር ግንባር ዘምተዋል።

በጊዜው ወዶ ዘማች የነበሩት ዓሊ በርኬ በምሥራቅ ግንባር በተለይም በጅግጅጋ እና በጭናክሰን እንዲሁም በኦጋዴን ውስጥ ከወራሪው ጦር ጋር በተደረገው ፍልሚያ ተሰልፈው በቆራጥነት የተዋጉ እና ደማቸውን አፍስሰው የሀገር ድንበር ካስከበሩ እና ታሪክ ከማይረሳቸው ጀግኖቻችን አንዱ ነበሩ።

ኢትዮጵያን ለመውረር ለዓመታት ሲዘጋጅ የኖረው የዚያድ ባሬ መንግሥት በጦርነቱ ያስሰለፈው ታንክ እና መድፍ ቁጥር ከወገን ጦር ጋር ሲነጻጸር አንድ ለአምስት የሆነ ልዩነት እና ብልጫ በነበረበት ሁኔታ ውስጥ ነበር ዓሊ በርኬ ወደ ጦርሜዳ የገቡት።

በተለይ በጥር ወር 1970 ዓ.ም ዳካታ እና ካራማራ ላይ የጠላት የበላይነት አይሎ በነበረበት ወቅት የወሰዱት ቆራጥ እርምጃ ለወገን ጦር ወደ ድል መገስገስ ዋና ምክንያት መሆኑ ይነገራል።

በዚህም የወገን ጦር በተጠናከረ የመልሶ ማጥቃት እርምጃ ኢትዮጵያ በዚያድ ባሬ የጠላት ጦር ላይ ታሪካዊ እና የማይረሳ ድልን ልትቀዳጅ የቻለችው።

ቆራጡ ጀግና ዓሊ በርኬ የያዙዋቸውን 5 ተቀጣጣይ ቦምቦች ተጠቅመው አምስት የጠላት ታንኮችን አመድ በማድረግ የጠላት ጦር እንዲበተን እና ወደ ኋላ እንዲያፈገፍግ ያስቻለ ደማቅ ታሪክ ጽፈዋል።

ዓሊ በርኬ ለዚያ ወደር የለሽ የጀግንነት ተግባራቸው በ1971 ዓ.ም የሀገሪቷን ከፍተኛ የጦር ሜዳ ጀብዱ ኒሻን በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ማግኘት ችለዋል።
👍50❤15👏2
❤45👍8
👍16❤6👏3