Development Bank of Ethiopia (DBE)
23.3K subscribers
2.1K photos
76 videos
4 files
578 links
The development bank of Ethiopia (DBE) is one of the financial institutions engaged in providing short, medium and long term development credits.
Download Telegram
👍25❤6👏4
ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ ብድር ወስደው በሁሉም የሀገራችን አካባቢዎች ሃብት መፍጠር የቻሉ ኢንቨስተሮች ይገኛሉ፡፡ በመሆኑም በጥያቄያችሁ መሰረት የስኬታማ ሰዎችን የስራና የህይወት ልምድ አጋርተናል፡፡ መልካም ንባብ፡፡

ከአንድ ብርቱ….

በወረታ ከተማ በአነስተኛ የቢዝነስ መስክ ላይ በመሰማራት በህይወታቸው ያጋጠማቸውን ጉድለት ለመሙላት እረፍት የለሽ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ወጣቶች ናቸው፡፡ የተለመደ ስራቸውን በመከወን ላይ ሳሉ በ2010 ዓ.ም የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የጎንደር ዲስትሪክት ወረታ ቅርንጫፍ በከተማዋ ለሚገኙ ነዋሪዎች አንድ ዜና ይዞ ብቅ አለ፡፡

በተለያየ የስራ መስክ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ነገር ግን በፋይናንስ እጥረት ስራቸውን ማሳደግ ያልቻሉ ተሰባስበው ለስራ መነሻ የሚሆናቸውን ገንዘብ በማፈላለግ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሊዝ ፋይናንስ የብድር አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚጋብዝ መልካም ዜናን ሰሙ፡፡

ይህን የሰሙት አምስቱ ወጣቶች በጋራ ሆነው እንደ አንድ ለመስራትና ከተሰማሩበት የስራ መስክ ከፍ ወዳለው የቢዝነስ አማራጭ ለመሰማራት በማቀድ ወደ ልማት ባንክ አመሩ፡፡ ደርበውና መንግስቱ የድንጋይና ጠጠር ማምረት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በዚህ መንገድ ተመሰረተ፡፡ ከእኛ የሚገባውን ሁሉ አሟልተን በመሄዳችን የኢትዮጵያ ልማት ባንክን አገልግሎት መጠቀም ችለናል ይላል የማህበሩ ሰብሳቢ አቶ ደርበው ሙላት፡፡

ደርበውና መንግስቱ የድንጋይና ጠጠር ማምረት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር አባላት አምስት ሆነው የየራሳቸውን ስራ በመተው በጋራ ሆነው የትልቅ ድርጅት ባለቤት የመሆን ፍላጎታቸውን ልማት ባንክ አሟልቶላቸው ዛሬ በወረታ ከተማ የትልቅ ጠጠር ማምረቻ ባለቤት መሆን ችለዋል፡፡

ባንኩ በሊዝ ፋይናንስ የብድር አገልግሎት የጠጠር ማምራቻ ማሽኑን አቅርቦላቸዋል፡፡ እነዚህ ባለራዕዮች የተሻለ ስራ መስራት እንችላለን በሚል የስራ መነሳሳት የገቡበት ስራ ዛሬ የግል ሕይወታቸውን ከመቀየር አልፎ ድርጅታቸውን ማሳደግ እንደቻሉ የማህበሩ ሰብሳቢ ተናግሯል፡፡ ጤናማ የሆነ የብድር አመላለስ ውስጥ እንደሆነ የተናገረው ሰብሳቢው የብድር አመላለሳችን ወቅታዊ ችግር ቢገጥም እንኳን የባንኩን ብድር ከመመለስ ወደኋላ አንልም ሲል አክሏል፡፡

አንድ ሰው ብቻውን ማድረግ ወይም ማሳካት የማይችለውን ሰብሰብ ብሎ እንደኛ ማድረግ ይችላል፡፡ እኛ በግላችን ስራ የነበረን ሰዎች ብንሆንም እያንዳንዳችን በተናጥል ማድረግ የማንችለውን ሰብሰብ ብለን አቅም በመፍጠር ተጠቃሚ መሆን ችለናል ብሏል የማህበሩ ሰብሳቢ፡፡
የነበረባችውን የፋይናንስ ችግር በመፍታት ህብረታቸውን ወደ ውጤት ከቀየረው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጋር በሌላ ስኬት ለመምጣት ዝግጅታችንን አጠናቀናል ይላሉ፡፡

በቀጣይም እንደ እነ ደርበውና ጓደኞቹ ሁሉ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ስራ ጀምረው ስራቸውን ማሳደግ ለሚሹ፣ ወደ ቢዝነስ ለመግባት እቅድ ያላቸውን ሁሉ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አስተማማኝ አጋር በመሆን የድርሻውን ለመወጣት ዝግጁ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
👍72❤12
👍46❤6
❤23👍16🤝4
👍24❤6
የጠባቧ ቤት ሰፊ በረከት

ብዙዎች የግል ሥራቸውን ለመጀመር እንቅፋት የሆነባቸው የቦታ እጦት እንደሆነ ሲናገሩ ይደመጣል፡፡ የመንቀሳቀሻ ገንዘብ አይቸግረኝም፤ ሆኖም የመሥሪያ ቦታ የለኝም የሚሉ ግለሰቦችን በተለያየ አጋጣሚ እንሰማለን፡፡ ወደምስራቅ ያገኘናቸው የቢዝነስ ሰው ‹‹የለም ለሥራ መሠረቱ ፍላጎትና እና ቁርጠኝነት ነው እሱ ካለ መላ አለ›› ይላሉ፤ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ድሬዳዋ ዲስትሪክት ሐረር ቅርንጫፍ ደንበኛ አቶ ሳሊ መሐመድ፡፡

ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ በሊዝ ፋይናንስ የጥልፍ እና የስፌት ማሽኖችን ተረክበው እየሠሩ ነው፡፡ 35 ካሬ በሆነች ቦታቸው 24 ሰዓት በፈረቃ ይሠራሉ ለነገ ስኬት ዛሬ ላይ የሚጣለው መሰረት ወሳኝ ነውና፡፡ አቶ ሳሊ ባላቸው ቦታ ላይ ትልቁን የቢዝነስ ትልማቸውን እስኪያሳኩ ድረስ ሌት ተቀን እየሠሩ መሠረታቸውን አስተማማኝ በሆነ ልምድና እና ካፒታል ላይ እየገነቡ ይገኛል፡፡

በ1994 ዓ.ም ከቤተሰብ ጋር ወደ ጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ውስጥ የገቡት አቶ ሳሊ የቤተሰባቸውን ሥራ ጥለው በራሳቸው ሥራ የጀመሩት በ2000 ዓ.ም እንደነሆነ ይናገራሉ፡፡ የጨርቃ ጨርቅ ሥራን ከቤተሰብ የወረሱት ሙያ ሲሆን፣ በእውቀት እና በፍላጎት እየሠሩት እንደሚገኙም አጫውተውናል፡፡

ሐረር ከተማ የስፌት ማዕከል ናት፡፡ አቶ ሳሊም የጨርቃጨርቅ ሥራቸውን ለማስፋፋት ጥናት ጨርሰው ለኢንቨስትመንት የሚሆን ቦታ ተረክበው በግንባታ ሂደት ላይ ናቸው፡፡ ወደ ትልቁ የቢዝነስ ሥራቸው ከመግባታቸው በፊት ባላቸው ቦታ ላይ እዳቸውን እየከፈሉ፣ ሠራተኞቻቸውንም ቤታቸውንም እየመሩ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

አንድ ሰው ወደ ሥራ ከመሰማራቱ በፊት ለሥራው ያለውን ፍላጎት እና በሚሰማራበት መስክ ላይ ያለውን እውቀት ማጤን እንዳለበትም ይመክራሉ፡፡ የአቶ ሳሊ 35 ካሬ የሥራ ቦታ ላይ 12 የድርጅቱ ሠራተኞች በፈረቃ ለ24 ሰዓት ይሠሩበታል፡፡ ግለሰቡ ቱርክ በነበራቸው የጉብኝት ቆይታ በጠባብ ቤት ተሠርተው ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ ምርቶችን መመልከታቸው በትንሽ ቦታ ላይ ምርታማ መሆን እንደሚቻል ልምድ እንደቀሰሙበት አልሸሸጉም፡፡

ኢንቨስትመንት የራሱ የሆነ ጊዜ የሚፈልግ በመሆኑ በተገኘው ቦታ ሥራን እየሠሩ ወደ ትልቅ የኢንቨስትመንት ሥራ መሸጋገር እንደሚቻል አቶ ሳሊ ምስክር ናቸው፡፡ 24 ሰዓት እረፍት በሌላት ጠባቧ ክፍል በርካታ ጥልፍ፣ የሎጎ ሥራ፣ የፖለሲ አርማዎች ተሠርቷል፡፡ የ12 ሰው ደሞዝ የሚከፈል ገቢን ከመሸፈን ባሻገር፣ እዳ እየከፈለች የአቶ ሳሊን ቤተሰብ እያስተዳደረች ትገኛለች፡፡ ለዛም ነው አቶ ሳሊ ‹‹ይህቺ ቤት ታምረኛ ናት›› የሚሉት፡፡ ለብዙ ሰዎች የሥራ እድል የሚፈጥር ፕሮጀክት ለመጀመር በሂደት ላይ ያሉት አቶ ሳሊ ህልማቸውን እንደሚያሳኩ ጅምር እንቅስቃሴያቸው ምስክር ነው፡፡

በአቶ ሳሊ ድርጅት የሚመረቱ ትራስ ጨርቆች ከ40 በመቶ በላይ ወደ ውጭ ነው የሚላኩት፡፡ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለአቶ ሳሊ የስፌትና የጥልፍ ማሽኖች በሊዝ ፋይናንስ የብድር አገልግሎት አቅርቦላቸዋል፡፡ የባንኩ ባለሙያዎች በቅርብ እየተከታተሉ የሚደግፉ፤ የሚያነቁ መሆኑን የሚናገሩት አቶ ሳሊ የባንክ የብድር ሂደትን በመሰልቸት የሚያፈገፍጉ ወደባንኩ ጠጋ ብለው የሊዝ ፋይናንስ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይመክራሉ፡፡

ትልልቅ ቢዝነሶች ገበያውን በመቋቋም ሳይናጉ ቀጣይ መሆን የሚችሉት መሠረታቸው ጠንካራ ሲሆን ነው፡፡ ሥራን በእውቀት እና በፍላጎት መምራት ውጤታማ ያደርጋል፡፡ አንድ ሥራ ለመሥራት ቦታ ወሳኝ ሚና የሚጫወት ሆኖ ሳለ ባለ ውስን ካፒታል እና ቦታ ውጤታማ ሥራ መሥራት እንደሚቻል አቶ ሳሊን ጨምሮ የብዙ ግለሰቦች ታሪክ ያስተምረናል፡፡ ሁሉንም ነገር በአንዴ ማሟላት የማይቻልበት ምክንያቶች ቢኖሩ ፍላጎት እና ቁርጠኝነት ተደምረው የምንፈልገውን ውጤት ማምጣት ይቻላል፡፡
👍54❤8👏3🤝1
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ለአገራችን ከሚሰጡት የላቀ ፋይዳ በመነሳት ያሉባቸውን ተግዳሮቶች ለመቅረፍ የሚያስችል ስራ እየሰራ ይገኛል፡፡ ኢንተርፕራይዞቼ ሊያጋጥሟቸው የሚችሉ የቴክኖሎጂ ችግሮችን በመቅረፍ እና የማሽነሪ አቅርቦት ከነድጋፉ በማዘጋጀት፣ የክህሎት ክፍተታቸውን መሙላት የሚያስችል ስልጠና በመስጠት እና በተለይ በአምራች ኢንዱስትሪ ላይ ተሳትፏቸውን እንዲያሳድጉ በማገዝ በኩል ተጨባጭ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡

በአራተኛ ዙር የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ስልጠና ላይ ስራ ፈላጊው ወደስራ ሊገባ የሚችልበትን ቀላል እና አዋጭ መላ በማቅረብ የብዙዎቻችሁን ቀልብ የያዘው አባ መላ በስልጠና ወቅት ያቀረባቸውን የስራ አማራጮች በተከታታይ ማስነበባችን ይታወቃል አማራጭ ሶስትን እንዲህ ያቀርብን ሲሆን በቀጣይ ክፍል ሌላ አዋጭ የስራ መስኮችን ይዘን የምንቀርብ ይሆናል፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
👍55❤11👏1
❤25👍16
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች በአራት ዙር ስልጠና ሰጥቷል፡፡ የአራተኛ ዙር ስልጠናን ጨምሮ እስካሁን 120 ሺህ የሚጠጉ ሰልጣኞች ስልጠና ወስደዋል፡፡ በአራተኛ ዙር ስልጠናውን ወስደው ያጠናቀቁ ሰልጣኞችን ሰርተፊኬት ለመስጠት የሚያስችል ቅድም ዝግጅት የተጠናቀቀ ሲሆን በቀጣይ በጀት ዓመት ቀሪዎችን ለማሰልጠን ሃብት የማሰባሰብ ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡

ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚሰጠውን የሊዝ ፋይናንሲንግ የብድር አገልግሎት ተጠቃሚ ለመሆን ወደባንካችን የሚመጣ ደንበኛ ማመልከቻ፣ ሊሠሩት ያሰቡትን ሥራ እና የመስሪያ ቦታውን አድራሻ የሚጠቅስ ማመልከቻ፣ ባንኩ ለአዲስ ደንበኞች ያዘጋጀውን ሥልጠና መውሰዱን የሚያሳይ የምስክር ወረቀት ኮፒ፣ የንግድ ሥራ ፍቃድ (ለማስፋፊያ)፣ የመስሪያ /የማምረቻ/፣ ዋጋ ማሳወቂያ ደረሰኝ /Pro-forma invoice/፣ የቅድመ ሥራ ታሪክን በሚመለከት (Track Record)፣ የግብር ግዴታ፣ የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ ጥናት እና ደብዳቤ፣ አስተዳደርን በሚመለከት፣ ዝርዝር የንግድ ሥራ ዕቅድ ወይም የአዋጭነት ጥናት (በተያያዘው ቅጽ መሠረት) አሟልቶ መምጣት ይኖርበታል፡፡ ደንበኞች ወደ ባንካችን ከመምጣታችሁ በፊት ልታሟሏቸው የሚገቡ መረጃዎችን የሚያሳይ ዝርዝር አያይዘንላችኋል፡፡

በተጨማሪም ባንካችን የሚሰጠውን ስልጠና በቅርብ ጊዜ እንዲያካሄድ በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾቻችን እየጠየቃችሁ ያላችሁ ተመዝጋቢዎች ባንኩ በያዝነው በጀት ዓመት 50 ሺህ ለሚሆኑ ተመዝጋቢዎች ስልጠና ለመስጠት ያሰበ ቢሆንም የተመዝጋቢው ቁጥር ከእጥፍ በላይ የጨመረ በመሆኑ ከተመዘገቡት 435 ሺህ ሰልጣኞች መካከል በመጀመሪያ ምዕራፍ ከፍተኛ በጀት በመመደብ 112 ሺህ ለሚሆኑ ሰልጣኞች ስልጠናውን ሰጥቷል፡፡ ለቀሪ ተመዝጋቢዎች ስልጠናውን ለመስጠት ዝግጅት እያደረገ ሲሆን ሁሉም ተመዝጋቢዎች ሰልጥነው ለአገር አቅም የሚሆኑበትን መንገድ ለመፍጠር ልማት ባንክ እንደሚሰራ ያረጋግጣል፡፡
👍70❤14
❤45👍34