የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የዘጠኝ ወራት የስራ አፈጻጸም ስኬት የተመዘገበበት እንደነበር የመንግስት የልማት ድርጅቶች አስተዳደር አስታወቀ፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ባስመዘገባቸው ስኬቶች ለአምራች ዘርፋ የተሰጠ ብድር ከፍተኛ መሆኑ፣ ትርፍ ከታክስ በፊት ብር 2.35 ቢሊዮን መድረሱ፣ ለሊዝ ፋይናንስ የተሰጠ ብድር ከፍተኛ መሆኑና ከታማሚ ብድር ወደ ጤነኛ ከገቡ ፕሮጀክቶች 177 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡን የመንግስት የልማት ድርጅቶች በሪፖርቱ አመላክቷል፡፡
ሰሞኑን በኢሊሌ ኢንተርናሽናል ሆቴል በተደረገው ውይይት የመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታ አስተዳደር የኢትዮጵያ ልማት ባንክን አፈጻጸም የገመገመ ሲሆን፣ በአፈጻጸሙ የታዩ ጥንካሬዎች እና በቀጣይ መሻሻል በሚገባቸው ጉዳዮች በትኩረት መስራት እንደሚገባ አሳስቧል፡፡
የባንኩ አፈፃፀም በተለይ በሃብት አሰባሰብ እና በተመላሽ ብድር በተከታታይ ዓመታት ውጤታማ መሆኑ እንዲሁም በሁሉም ክልሎች ያለው ተደራሽነት እያሳደገ መምጣቱ በጥንካሬ የሚታይ መሆኑ ተጠቅሷል።
የባንኩ የፕሮጀክት እና የሊዝ ብድር ገቢ እያደገ መምጣቱ፣ የፋይናንስ ጤናማነትን ማሻሻሉ፣ የሃብት እና የእዳዎች መመጣጠን መሻሻል ማሳየቱ እና የታማሚ ብድር ምጣኔ እየቀነሰ መምጣቱ አስተዳደሩ በሪፖርቱ አመላክቷል፡፡
የመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር በሪፖርት እንዳመላከተው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የስራ አመራር ቦርድ ስትራቴጂያዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ክትትል እና ድጋፍ ማድረጉ በጥንካሬ እንደሚገለጽ ያመላከተ ሲሆን፣ ባንኩ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት በርካታ ድጋፎችን ማድረጉም የሚያስመሰግንና በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል የሚገባው መሆኑን ጠቅሷል፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሪፎርም ስራዎች ትግበራ ላይ መዋላቸው፣ የብድርና የሊዝ ፋይናንስ መመሪያ አጽድቆ ተግባራዊ ማድረጉም ባንኩ የተሻለ አፈጻጸም እንዲያስመዘግብ ያስቻለው መሆኑም ተጠቁሟል፡፡
በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለሊዝ ፋይናንስ የሰጠው የብድር አቅርቦት የተሻለ አፈጻጸም ያሳየበት መሆኑን የጠቀሰው አስተዳደሩ 6.5 ቢሊዮን ብር ለሊዝ ፋይናንስ ለብድር እንዳቀረበና ከዚህም ውስጥ 52 በመቶ ለማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ የቀረበ መሆኑም ተመላክቷል፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከሶስት ዓመታት በፊት በሁሉም መለኪያዎች ዝቅተኛ አፈፃፀም ያስመዘግብ ስለነበር ትርፍ ማስመዝገብ ይቸገር እንደነበር፣ የሰጠውን ብድርም በአግባቡ ለመሰብሰብ ይቸገር እንደነበር ያስታወሰው የመንግስት የልማት ድርጅቶች አስተዳደር አሁን ላይ ባንኩ የብድር ተሰብሳቢ አፈጻጸሙ ከእቅዱ አንጻር የተሻለ እና አበረታች መሆኑን ጠቅሷል፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የሰጠው ስልጠና፣ የሊዝ ፋይናንስ ተበዳሪዎች ቁጥር ከፍተኛ መሆን፣ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎትን ጨምሮ የፈጠራ ሃሳብን ለማበረታታት እየሰራ ያለው ስራ በጥንካሬ የሚገለጽና ተጠናክሮ መቀጠል የሚገባው መሆኑን አስተዳደሩ ጠቁሟል፡፡
በሌላ በኩል ባንኩ ለግብርና ዘርፍ የፈቀደው ብድር አነስተኛ መሆን፣ የብድር ስርጭት አፈጻጸም ዝቅተኛ መሆን፣ የብድር ማጽደቅ ሂደቱ በሚፈለገው ፍጥነት ያለመሄድ፣ የግብርና ብድር ተሰብሳቢ እና የፕሮጀክት አፈጻጸም ክፍተት ያለው መሆኑን የመንግስት የልማት ድርጅቶች በሪፖርቱ ያመላከተ ሲሆን፣ የተነሱ ጉድለቶች ላይ በትኩረት መሰራት እንደሚገባው አመላክቷል፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው ባንኩ ባደረገው ሪፎርም ከዚህ ቀደም የነበሩ የብድር ማጽደቅ ሂደቶች ላይ ይታይ የነበሩ የግልጽነት ችግሮችን የቀረፈ እና ሂደቱም ለብልሹ አሰራር የማይመች ሆኖ የተስተካከለ መሆኑን ነው ያስታወቁት፡፡
በተጨማሪም ግብርና የመንግስት የትኩረት አቅጣጫ መሆኑን በማስታወስ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የግብርና ሜካናይዜሽንን ለማስፋፋት የትራክተር እና የኮምባይነር ሃርቨስተር ማሽኖች እያቀረበ መሆኑን የገለጹት ዶ/ር ዮሐንስ በቀጣይም በግብርና ዘርፍ ለሚመጡ ደንበኞች አስፈላጊውን አገልግሎት ለመስጠት ባንኩ ዝግጁ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የተሰጠውን ኃላፊነት በብቃት ለመወጣት እያደረገ ያለው ጅምር ውጤት እያመጣ በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ በግምገማው ተመላክቷል፡፡

👍49❤23
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ለአገራችን ከሚሰጡት የላቀ ፋይዳ በመነሳት ያሉባቸውን ተግዳሮቶች ለመቅረፍ የሚያስችል ስራ እየሰራ ይገኛል፡፡ ኢንተርፕራይዞቼ ሊያጋጥሟቸው የሚችሉ የቴክኖሎጂ ችግሮችን በመቅረፍ እና የማሽነሪ አቅርቦት ከነድጋፉ በማዘጋጀት፣ የክህሎት ክፍተታቸውን መሙላት የሚያስችል ስልጠና በመስጠት እና በተለይ በአምራች ኢንዱስትሪ ላይ ተሳትፏቸውን እንዲያሳድጉ በማገዝ በኩል ተጨባጭ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡
በአራተኛ ዙር የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ስልጠና ላይ ስራ ፈላጊው ወደስራ ሊገባ የሚችልበትን ቀላል እና አዋጭ መላ በማቅረብ የብዙዎቻችሁን ቀልብ የያዘው አባ መላ በስልጠና ወቅት ያቀረባቸውን የስራ አማራጮች በድጋሚ እንድናጋራችሁ በማህበራዊ ሚዲያ ገጻቻችን ላይ ጠይቃችኋል፡፡ በመሆኑም በአባ መላ የቀረቡ የስራ መላዎችን ቀላልና ተነባቢ በሆነ መልኩ እንዲህ አጋርተናል፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!

👍53❤13👏5🤝4
የግብርና ሜካናይዜሽን የምርታማነት መሰረት
በ ዜማ ያሬድ
ለውጥ በባህሪው ሂደት ነው፡፡ የራሱን ጊዜና ስልት ይፈልጋል፡፡ ዛሬ ላይ የአለማችንን ኢኮኖሚ የሚዘውሩት አገራት መሰረታቸው ግብርና ሲሆን፣ በሂደት ስልታቸውን እየቀሩ ግብርናቸውን ከዘመኑ ጋር እያዘመኑ ወደፊት መስፈንጠር የቻሉ ናቸው፡፡
የግብርና ሜካናይዜሽን ላይ የተፃፉ ጽሁፎች እንደሚያመላክቱት የግብርና ሜካናይዜሽን በአገራት የለውጥ ሂደት ውስጥ የጎላ ድርሻ ያለው መሆኑን ነው፡፡ የግብርና ሜካናይዜሽን ቀላል የሆነ፣ ነገር ግን ምርታማነትን ሊያመጡ የሚችሉ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ግብርናን የማዘመን ሂደት ነው፡፡
ግብርና ለአብዛኛው የዓለማችን ክፍል የኑሮ መሰረት ሲሆን፣ እንደ አገር ደግሞ ለአጠቃላይ እድገት ከፍተኛውን አስተወጽዖ የሚያበረክት ነው፡፡ በዓለማችን እያደገ የመጣውን የህዝብ ቁጥር መመገብ የሚችል የግብርና ስርዓት አስፈላጊ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ የግብርና ሜካናይዜሽን ያለውን የምግብ ፍላጎት ማሟላት የሚችል ምርት ለማምረት የሚያግዝ ስልት ነው፡፡
በአገራችንም ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ የመጣውን የህዝብ ቁጥር የምግብ ፍላጎት ማሟላት የሚቻለው የግብርና ሜካናይዜሽንን በማስፋፋት እና ለዘርፉ ልዩ ትኩረት በመስጠት ነው፡፡ የግብርና ሜካናይዜሽን የአርሶ አደሩን ህይወት የሚቀይር፣ የግብርና ምርታማነትን የሚያሳድግ እና በአጠቃላይ ግብርና በአገር ኢኮኖሚ ላይ ያለው አሳተዋጽዖ እንዲያድግ የሚያደርግ ነው፡፡
በኢትዮጵያ የግብርና ሜካናይዜሽን እድገት ዝቅተኛ ሲሆን፣ ከአንድ በመቶ በታች የሚሆነው የግብርና መሬት ብቻ በትራክተር እንደሚታረስ ይነገራል፡፡ ይሁን እንጂ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የግብርና ማሽነሪዎችን በመጠቀም ግብርናን የማዘመን ሂደት እየተፋጠን ይገኛል፡፡ በአገራችን በገበሬው ጉልበት ብቻ ይሸፈን የነበረው የእርሻ ማሳ አሁን ላይ ወደአገራችን በስፋት እየገቡ ባሉ የአጭዶ መውቂያ እና ማረሻ ማሽኖች እየተተካ የግብርና ምርታማነትም እየጨመረ ይገኛል፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክም በግብርና ዘርፍ ላይ ለተሰማሩ የሊዝ ፋይናንስ ደንበኞቹ የአጭዶ መውቂያ እና ማረሻ ማሽኖችን በማቅረብ የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ይገኛል፡፡ ግብርናን ማዘመን የገበሬውን ጉልበት በመቆጠብ በሌሎች ተያያዥ የስራ መስኮች ላይ በመሰማራት ገቢውን እና የኑሮ ሁኔታውን እንዲያሻሽል ሰፊ እድል የሚፈጥር ነው፡፡
በአገራችን የግብርና ልማት ብክነትን የሚቀንሱ እና ምርታማነትን የሚጨምሩ ዘመኑ ያፈራቸውን የግብርና ቴክኖሎጂዎችን ተጠቅሞ የግብርና ስራን አድካሚ ባለሆነ መንገድ የመስራት ልምምድ ገና መሆኑ ይታመናል፡፡ ይሁንና ከ80 በመቶ በላይ አርሶ አደር ባለበት አገር ከራስ ፍጆታ አልፎ ለገበያ መትረፍ የሚችል ምርት ለማምረት ግብርናን ማዘመን ያለው ፋይዳ የላቀ መሆኑ የማይታበይ ሃቅ ነው፡፡
በኢትዮጵያ ግብርና ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት 33 በመቶ የሚሸፍን ሲሆን፣ የአገራችን የውጭ ምንዛሬ ገቢ ከ70 በመቶ በላይ ምንጩ ግብርና እንደሆነ ይጠቀሳል፡፡ በተመሳሳይ ከ60 በመቶ በላይ የሚሆኑ የሀገራችን ዜጎች መተዳደሪያቸው ግብርና እና ከግብርና ጋር ተያያዥ የሆኑ ዘርፎች ናቸው፡፡
በአገራችን እየተስፋፋ የመጣ የግብርና ሜካናይዜሽን በተለይ የስንዴ ምርታማነትን እየጨመረ መሆኑን በመንግስት በኩል ሲገለጽ ይደመጣል፡፡ በመሆኑም ከአገር ውስጥ ፍጆታ አልፎ ለዓለም ገበያ መቅረብ የሚችል የሰብል ምርታማነትን ለማምጣት የግብርና ሜካናይዜሽንን ማስፋፋት ያስፈልጋል፡፡
ለግብርና ዘርፍ በቂ ሃብት በመመደብ ግብርናን የማዘመን ስራ ተጠናክሮ መቀጠል ይገባዋል፡፡ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከዚህ አኳያ እየሰራቸው ያሉ ተግባራት የሚበረታቱና ሌሎች ባለድርሻ አካላትም ግብርናን ፋይናንስ በማድረግ በኩል የበኩላቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ የሚያነቃ ተግባር ነው የሚል እይታ አለኝ፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በአዲሱ ሪፎርምና የቢዝነስ ሞዴል ራሱን እንደገና ካደራጀና ወደስራ ከገባ በኋላ የተለያዩ የፋይናስ ምንጮችን በማሰባበስ ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቁ የእርሻ ማሽኖችን እያቀረበ መሆኑን በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች ሲገለጽ ሰምተናል፡፡ 303 ዋና ዋና የግብርና ማሽነሪዎች ለደንበኞች አቅርቧል፡፡ አሁንም በግዥ ሂደት ላይ ካሉት በተጨማሪ ከደንበኞች እየቀረበ ያለውን ፍላጎት መመለስ የሚያስችል ፋይናንስ ለማሰባሰብ ባንኩ እየሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው በአንድ ወቅት ባደረጉት ቃለምልልስ ሲናገሩ ተደምጧል፡፡
የኢትዮጵያ መንግስትም የግብርና ሜካናይዜሽንን የማስፋፋት ስራ በትኩረት እየሰራ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ግብርናን እንደግብዓት የሚጠቀሙ የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ዘርፎችን የማስፋፋት ስራም በስፋት እየተሰራ መሆኑ በተለያየ አጋጣሚ ሲጠቀስ ይሰማል፡፡
ከ120 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ያላት ኢትዮጵያ ከአጠቃላይ ሕዝቧ 76 ሚሊዮን የሚሆነው እድሜው ከ29 ዓመት በታች እንደሆነ ይነገራል፡፡ ይህ ቁጥር ትልቅ የአገር አቅም እንደሚሆንም ይታመናል፡፡ በመሆኑም ለአንድ አገር እድገት ለውጥ መሰረት የሆነው አምራች የሰው ሃይል ለግብርና ምቹ የሆነ መሬት በአገራችን በበቂ ሁኔታ ያለ መሆኑ እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም መንግስት፣ ባለድርሻ አካላት እና ሌሎች የፋይናንስ ተቋማት በቅንጅት ሆነው የግብርና ዘርፍን ለውጥ ለማፋጠን መስራት እንደሚገባቸው የሚያመላክት ነው፡፡
በአጠቃላይ ያለንን የሰው ሃይልና የመሬት ሃብት እንደ መልካም እድል ተጠቅሞ አገራችንን ከጥገኝነት የሚያላቅቅ፤ የህዝባችንን የምግብ ዋስትናውን ማረጋገጥ የሚችልበት ሁኔት ለመፍጠር መትጋት ያስፈልጋል፡፡ ጉልበት፣ መሬት፣ ፋይናንስና ቴክኖሎጂ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ መሰረቶች በመሆናቸው ትኩረታችን እነዚህ መሰረታዊ ጉዳዮችን አቀናጅቶ ተግባር ላይ በማዋል ለውጥ ማምጣት ሊሆን ይገባል፡፡

👍60🤝5❤4👏1