Development Bank of Ethiopia (DBE)
23.3K subscribers
2.1K photos
76 videos
4 files
580 links
The development bank of Ethiopia (DBE) is one of the financial institutions engaged in providing short, medium and long term development credits.
Download Telegram
የተቀናጀ አሰራር በመዘርጋት የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ተግዳሮቶችን ለመፍታት እንደሚሰራ ተገለጸ፡፡
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በሚሊኒየም አዳራሽ ባዘጋጀው "ኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ 2015" ተከትሎ "የፋይናንስ ተደራሽነት ለአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ" በሚል ርዕስ የፓናል ውይይት የተካሄደ ሲሆን፣ በውይይቱ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ፣ ብሔራዊ ባንክ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተሳታፊ የነበሩ ሲሆን፣ የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ መልካም አጋጣሚዎች እና ተግዳሮቶች ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡
በፓናል ውይይቱ ተሳታፊ የነበሩት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ መልካም አጋጣሚዎችን እና ተግዳሮቶችን ያነሱ ሲሆን፣ እንደ አገር ያለን ሃብት ውስን መሆንና ባለሃብቱ በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ላይ ያለው ተሳትፎ አናሳ መሆን ዘርፉ የገበያ ፍትሃዊነት ችግር እንዲገጥመው ማድረጉን አንስተዋል፡፡ በአጭር ጊዜ ትርፍ ወደሚያስገኝ ዘርፍ የማተኮር ዝንባሌ መኖሩን ያነሱት ዶ/ር ዮሐንስ የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ በአጠቃላይ የጂዲፒ አስተዋጽዖ አናሳ እንዲሆን ምክንያት መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
በተመሳሳይ የኢንዱስትሪ ዘርፍን ለማሸጋገር የፋይናንስ ዘርፉ፣ የባለሃበቱ እና የባለድርሻ አካላት ድርሻ የላቀ መሆኑን በማብራሪያቸው አንስተዋል፡፡ የአገልግሎት ዘርፍ ገበያ አብዛኛውን አገር ውስጥ በመሆኑ የገበያ እክል የሚገጥመው ሆኖ አይታይም ያሉት ዶ/ር ዮሐንስ በተቃራኒው የኢንዱስትሪ ዘርፍ ገበያ አለም አቀፍ በመሆኑ ውድድሩም አለምአቀፍ እንዲሆን ያስገድዳል ብለዋል፡፡ በመሆኑም ጥራት፣ ዋጋ እና ፍጥነት በዓለም ገበያ ተወዳዳሪ ለመሆን ወሳኝ ቅድመ ሁኔታዎች በመሆናቸው የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ እነዚህን ቅድመ ሁኔታዎች ያሟላ እና ለተወዳዳሪነት ብቁ ሊሆን እንደሚገባ አመላክተዋል፡፡
የባለድርሻ አካላት በበኩላቸው ምቹ የሆነ የፖሊሲ ማዕቀፍ በማዘጋጀት፣ የመሬት አቅርቦትን በማስፋት እና ለኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታን በመፍጠር ለኢንዱስትሪ ማበብ የበኩላቸውን ሚና መወጣት እንደሚገባቸው ያነሱት ዶ/ር ዮሐንስ በፋይናንስ ዘርፉ፣ በባለሃብቱ እና በባለድርሻ አካላት የተቀናጀ አሰራር የኢንዱስትሪ ዘርፉን ማሳደግ እንደሚቻል ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ማሞ ምህረቱ በበኩላቸው የተረጋጋ የማክሮ ኢኮኖሚ አውድ በመፍጠር የአምራች ዘርፉን ችግር መፍታት እንደሚቻል ገልጸዋል፡፡ የተረጋጋ የዋጋ ሁኔታ መኖር፣ የተረጋጋ የውጭ ምንዛሬ ስርዓት እንዲኖር ማድረግ፣ የፋይናንስ ዘርፍ ጤንነትን በማረጋገጥ የብድር አቅርቦትን ማስፋት ለኢንዱስትሪ ማደግ ወሳኝ እንደሆኑ አብራርተዋል፡፡ የውጭ ምንዛሬ በኢንቨስትመንት ዘርፍ የሚታየውን የጥሬ እቃ አቅርቦት ችግር የሚፈታ በመሆኑ የብሔራዊ ባንክ ዋና ትኩረት የውጭ ምንዛሬ አቅርቦትን ማስፋት መሆኑንም አያይዘው ጠቅሰዋል፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የአምራች ዘርፍን ለማሳደግ በመዋቅር ደረጃ ባደረገው የሪፎርም ስራ ዘርፉን ለድጋፍ በሚመች መልኩ በክላስተር የማድራጀት ስራ የተሰራ መሆኑን በመግለጽ ተደራሽነትን የማስፋት እና የአገልግሎት ጥራትን ለማስጠበቅ በርካታ ስራዎችን መሰራታቸውን አብራርተዋል፡፡
በፓናል ውይይቱ የፋይናንስ አቅርቦት ችግር፣ የውጭ ምንዛሬ እጥረት፣ የብድር ጊዜ መራዘም እና የቢሮክራሲ ችግሮች ለባለሃባቱ ማነቆ መሆናቸውን ተሳታፊዎች አንስተዋል፡፡ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ከባለሃባቱ የተነሱ ጥያቄዎችን በተቀናጀ መልኩ በመፍታት የአምራች ዘርፍን ለማሳደግ የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በመግለጽ የፓናል ውይይቱ የሚነሱ ጥያቄዎችን በተደራጀ መልኩ ለመመለስ እድል የሚሰጥ መሆኑን አንስተዋል፡፡
👍33❤7👏4
የካፒታል ዕቃ ኪራይ አገልግሎት ፋይዳዎች

- ለዜጎች የሥራ እድል ይፈጥራል፤
- ምርት እና ምርታማነትን ይጨምራል፤
- ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን የሚተካ ምርቶችን ለማምረት ያግዛል፣ በዚህም የውጭ ምንዛሬ እንዲቆጠብ ይረዳል፤
- የቴክኖሎጂ ሽግግርን ለመፍጠር እድል ያመቻቻል፤
- ጥራት ያለው ምርት በማምረት በዓለም ገበያ ተወዳዳሪነት ይጨምራል፡፡ ለመሆን የሚያስችል የውጭ ምንዛሪ ለማስገኘት ያስችላል፤
- ለግብርና ዘርፉ ግብርናውን ከማዘመን፣ የምርት ብክነትን ከመቀነስና ምርትና ምርታማነትን ከመጨመር አንጻር ጉልህ ሚና ይጫወታል፤

በአጠቃላይ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ለሀገራችን የኢኮኖሚ እድገትና መዋቅራዊ ሽግግር ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንዲያበረክቱ ያስችላቸዋል፡፡
❤33👍28🤝5👏4
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በዘጠኝ ወራት የስራ አፈጻጸሙ ዘርፈ ብዙ ስኬቶች ማስመዝገቡን የመንግስት የልማት ድርጅቶች አስተዳደር ባካሄደው ግምገማ ማረጋገጡን አስታውቋል፡፡
ዝርዝር መረጃውን እንመለስበታለን፡፡
👍55❤8👏8
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የዘጠኝ ወራት የስራ አፈጻጸም ስኬት የተመዘገበበት እንደነበር የመንግስት የልማት ድርጅቶች አስተዳደር አስታወቀ፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ባስመዘገባቸው ስኬቶች ለአምራች ዘርፋ የተሰጠ ብድር ከፍተኛ መሆኑ፣ ትርፍ ከታክስ በፊት ብር 2.35 ቢሊዮን መድረሱ፣ ለሊዝ ፋይናንስ የተሰጠ ብድር ከፍተኛ መሆኑና ከታማሚ ብድር ወደ ጤነኛ ከገቡ ፕሮጀክቶች 177 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡን የመንግስት የልማት ድርጅቶች በሪፖርቱ አመላክቷል፡፡
ሰሞኑን በኢሊሌ ኢንተርናሽናል ሆቴል በተደረገው ውይይት የመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታ አስተዳደር የኢትዮጵያ ልማት ባንክን አፈጻጸም የገመገመ ሲሆን፣ በአፈጻጸሙ የታዩ ጥንካሬዎች እና በቀጣይ መሻሻል በሚገባቸው ጉዳዮች በትኩረት መስራት እንደሚገባ አሳስቧል፡፡
የባንኩ አፈፃፀም በተለይ በሃብት አሰባሰብ እና በተመላሽ ብድር በተከታታይ ዓመታት ውጤታማ መሆኑ እንዲሁም በሁሉም ክልሎች ያለው ተደራሽነት እያሳደገ መምጣቱ በጥንካሬ የሚታይ መሆኑ ተጠቅሷል።
የባንኩ የፕሮጀክት እና የሊዝ ብድር ገቢ እያደገ መምጣቱ፣ የፋይናንስ ጤናማነትን ማሻሻሉ፣ የሃብት እና የእዳዎች መመጣጠን መሻሻል ማሳየቱ እና የታማሚ ብድር ምጣኔ እየቀነሰ መምጣቱ አስተዳደሩ በሪፖርቱ አመላክቷል፡፡
የመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር በሪፖርት እንዳመላከተው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የስራ አመራር ቦርድ ስትራቴጂያዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ክትትል እና ድጋፍ ማድረጉ በጥንካሬ እንደሚገለጽ ያመላከተ ሲሆን፣ ባንኩ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት በርካታ ድጋፎችን ማድረጉም የሚያስመሰግንና በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል የሚገባው መሆኑን ጠቅሷል፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሪፎርም ስራዎች ትግበራ ላይ መዋላቸው፣ የብድርና የሊዝ ፋይናንስ መመሪያ አጽድቆ ተግባራዊ ማድረጉም ባንኩ የተሻለ አፈጻጸም እንዲያስመዘግብ ያስቻለው መሆኑም ተጠቁሟል፡፡
በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለሊዝ ፋይናንስ የሰጠው የብድር አቅርቦት የተሻለ አፈጻጸም ያሳየበት መሆኑን የጠቀሰው አስተዳደሩ 6.5 ቢሊዮን ብር ለሊዝ ፋይናንስ ለብድር እንዳቀረበና ከዚህም ውስጥ 52 በመቶ ለማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ የቀረበ መሆኑም ተመላክቷል፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከሶስት ዓመታት በፊት በሁሉም መለኪያዎች ዝቅተኛ አፈፃፀም ያስመዘግብ ስለነበር ትርፍ ማስመዝገብ ይቸገር እንደነበር፣ የሰጠውን ብድርም በአግባቡ ለመሰብሰብ ይቸገር እንደነበር ያስታወሰው የመንግስት የልማት ድርጅቶች አስተዳደር አሁን ላይ ባንኩ የብድር ተሰብሳቢ አፈጻጸሙ ከእቅዱ አንጻር የተሻለ እና አበረታች መሆኑን ጠቅሷል፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የሰጠው ስልጠና፣ የሊዝ ፋይናንስ ተበዳሪዎች ቁጥር ከፍተኛ መሆን፣ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎትን ጨምሮ የፈጠራ ሃሳብን ለማበረታታት እየሰራ ያለው ስራ በጥንካሬ የሚገለጽና ተጠናክሮ መቀጠል የሚገባው መሆኑን አስተዳደሩ ጠቁሟል፡፡
በሌላ በኩል ባንኩ ለግብርና ዘርፍ የፈቀደው ብድር አነስተኛ መሆን፣ የብድር ስርጭት አፈጻጸም ዝቅተኛ መሆን፣ የብድር ማጽደቅ ሂደቱ በሚፈለገው ፍጥነት ያለመሄድ፣ የግብርና ብድር ተሰብሳቢ እና የፕሮጀክት አፈጻጸም ክፍተት ያለው መሆኑን የመንግስት የልማት ድርጅቶች በሪፖርቱ ያመላከተ ሲሆን፣ የተነሱ ጉድለቶች ላይ በትኩረት መሰራት እንደሚገባው አመላክቷል፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው ባንኩ ባደረገው ሪፎርም ከዚህ ቀደም የነበሩ የብድር ማጽደቅ ሂደቶች ላይ ይታይ የነበሩ የግልጽነት ችግሮችን የቀረፈ እና ሂደቱም ለብልሹ አሰራር የማይመች ሆኖ የተስተካከለ መሆኑን ነው ያስታወቁት፡፡
በተጨማሪም ግብርና የመንግስት የትኩረት አቅጣጫ መሆኑን በማስታወስ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የግብርና ሜካናይዜሽንን ለማስፋፋት የትራክተር እና የኮምባይነር ሃርቨስተር ማሽኖች እያቀረበ መሆኑን የገለጹት ዶ/ር ዮሐንስ በቀጣይም በግብርና ዘርፍ ለሚመጡ ደንበኞች አስፈላጊውን አገልግሎት ለመስጠት ባንኩ ዝግጁ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የተሰጠውን ኃላፊነት በብቃት ለመወጣት እያደረገ ያለው ጅምር ውጤት እያመጣ በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ በግምገማው ተመላክቷል፡፡
👍49❤23
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከሚሰጣቸው መደበኛ አገልግሎቶች ባሻገር ማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ የሚገኝ የህዝብ ባንክ ነው፡፡

ባንካችን ባለፉት ዘጠኝ ወራት ብቻ የብር 193 ሚሊዮን ድጋፍ ለተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ማድረግ ችሏል፡፡
👍54❤10🤝2
❤19👍14
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ለአገራችን ከሚሰጡት የላቀ ፋይዳ በመነሳት ያሉባቸውን ተግዳሮቶች ለመቅረፍ የሚያስችል ስራ እየሰራ ይገኛል፡፡ ኢንተርፕራይዞቼ ሊያጋጥሟቸው የሚችሉ የቴክኖሎጂ ችግሮችን በመቅረፍ እና የማሽነሪ አቅርቦት ከነድጋፉ በማዘጋጀት፣ የክህሎት ክፍተታቸውን መሙላት የሚያስችል ስልጠና በመስጠት እና በተለይ በአምራች ኢንዱስትሪ ላይ ተሳትፏቸውን እንዲያሳድጉ በማገዝ በኩል ተጨባጭ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡

በአራተኛ ዙር የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ስልጠና ላይ ስራ ፈላጊው ወደስራ ሊገባ የሚችልበትን ቀላል እና አዋጭ መላ በማቅረብ የብዙዎቻችሁን ቀልብ የያዘው አባ መላ በስልጠና ወቅት ያቀረባቸውን የስራ አማራጮች በድጋሚ እንድናጋራችሁ በማህበራዊ ሚዲያ ገጻቻችን ላይ ጠይቃችኋል፡፡ በመሆኑም በአባ መላ የቀረቡ የስራ መላዎችን ቀላልና ተነባቢ በሆነ መልኩ እንዲህ አጋርተናል፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
👍53❤13👏5🤝4