Development Bank of Ethiopia (DBE)
23.3K subscribers
2.1K photos
76 videos
4 files
580 links
The development bank of Ethiopia (DBE) is one of the financial institutions engaged in providing short, medium and long term development credits.
Download Telegram
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዲጂታል ዜና መጽሔት

ቁጥር 1

ሚያዚያ 2015 ዓ.ም
👍404👏4🤝3
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የ4ዙር የመጀመሪያ ምዕራፍ ሰልጣኞች በቦረና በድርቅ ለተጐዱ ወገኖች ያሰባሰቡትን ገንዘብ አስረከቡ።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በሰጠው የአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ስልጠና የ4 ዙር የመጀመሪያ ምዕራፍ ላይ ተሳታፊ የነበሩ ሰልጣኞች ናቸዉ ድጋፉን አሰባስበው ያስረከቡት።
ባንኩ የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሰጠ ላለዉ ሀገራዊ ስልጠና እና ጉልህ አበርክቶ ከባንኩ ጎን በመቆም እኛ ሰልጣኞች የበኩላችንን ድጋፍ በቦረና በድርቅ ለተጐዱ ወገኖቻችን በማድረሳችን ደስተኞች ነን ሲሉ የየማዕከላቱ አስተባባሪዎች ተናግረዋል።
አዳማ፣ ቢሾፍቱ፣ ሚሊኒየም፣ ሲኒማ ኢትዮጵያ፣ ጉለሌና ጽዮን ሆቴል በጋራ፣ ግልገል በለስ፣ ቂርቆስ፣ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አዳራሽ፣ ኮልፌ የስልጠና ማዕከላትን እና በሌሎች ማዕከላት ከነበሩ ሰልጣኞች የተሰበሰበዉ ከ445 ሺ ብር በላይ ገንዘብ ለኦሮሚያ ክልል ቡሳ ጉኖፋ ገቢ ተደርጓል።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከዚህ ቀደም ለወገን ደራሽነቱን በማስመስከር በቦረና በድርቅ ለተጐዱ ወገኖቻችን የ20 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን ያስታወሱት ኃላፊው አቶ ሀብታሙ ሲሳይ በአሁኑ ሰዓት በኦሮሚያ ክልል በ10 ዞኖች በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የእለት ደራሽ እርዳታ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
እንደ ኃላፊዉ ገለፃ የባንኩ ሰልጣኞች እና ባንኩ ላደረጉት ድጋፍ ምስጋና በማቅረብ በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ዞኖች እየተደረገ ያለዉን ርብርብ መላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ የበኩሉን ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።
👍6845👏5🤝4
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለኢንዱስትሪ ዘርፍ ዘላቂ እድገትና ተወዳዳሪነት እንዲሁም ለአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ መነቃቃት "ኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ 2015" ያለውን ፋይዳ በመረዳት ኤክስፖውን ስፖንሰር በማድረግ አጋርነቱን አሳይቷል፡፡

ሶስተኛ ቀኑን የያዘውና በሚሊኒየም አዳራሽ የተከፈተው "ኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ 2015" "የፋይናንስ ተደራሽነት ለአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ" በሚል ርዕስ አምራቾች፣ የብሔራዊ ባንክ ገዥ፣ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት እና የንግድ ባንክ ምክትል ፕሬዝዳንት በፓናሊስትነት የተሳተፉበት የፓናል ውይይት የተካሄደ ሲሆን የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ በፋይናንስ አቅርቦት በኩል የሚገጥማቸው ችግሮች እና በቀጣይ መፈታት የሚገባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡

ለዘላቂ እድገት ኢትዮጵያ ታምርት!

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
👍486👏5🤝4
የተቀናጀ አሰራር በመዘርጋት የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ተግዳሮቶችን ለመፍታት እንደሚሰራ ተገለጸ፡፡
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በሚሊኒየም አዳራሽ ባዘጋጀው "ኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ 2015" ተከትሎ "የፋይናንስ ተደራሽነት ለአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ" በሚል ርዕስ የፓናል ውይይት የተካሄደ ሲሆን፣ በውይይቱ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ፣ ብሔራዊ ባንክ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተሳታፊ የነበሩ ሲሆን፣ የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ መልካም አጋጣሚዎች እና ተግዳሮቶች ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡
በፓናል ውይይቱ ተሳታፊ የነበሩት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ መልካም አጋጣሚዎችን እና ተግዳሮቶችን ያነሱ ሲሆን፣ እንደ አገር ያለን ሃብት ውስን መሆንና ባለሃብቱ በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ላይ ያለው ተሳትፎ አናሳ መሆን ዘርፉ የገበያ ፍትሃዊነት ችግር እንዲገጥመው ማድረጉን አንስተዋል፡፡ በአጭር ጊዜ ትርፍ ወደሚያስገኝ ዘርፍ የማተኮር ዝንባሌ መኖሩን ያነሱት ዶ/ር ዮሐንስ የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ በአጠቃላይ የጂዲፒ አስተዋጽዖ አናሳ እንዲሆን ምክንያት መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
በተመሳሳይ የኢንዱስትሪ ዘርፍን ለማሸጋገር የፋይናንስ ዘርፉ፣ የባለሃበቱ እና የባለድርሻ አካላት ድርሻ የላቀ መሆኑን በማብራሪያቸው አንስተዋል፡፡ የአገልግሎት ዘርፍ ገበያ አብዛኛውን አገር ውስጥ በመሆኑ የገበያ እክል የሚገጥመው ሆኖ አይታይም ያሉት ዶ/ር ዮሐንስ በተቃራኒው የኢንዱስትሪ ዘርፍ ገበያ አለም አቀፍ በመሆኑ ውድድሩም አለምአቀፍ እንዲሆን ያስገድዳል ብለዋል፡፡ በመሆኑም ጥራት፣ ዋጋ እና ፍጥነት በዓለም ገበያ ተወዳዳሪ ለመሆን ወሳኝ ቅድመ ሁኔታዎች በመሆናቸው የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ እነዚህን ቅድመ ሁኔታዎች ያሟላ እና ለተወዳዳሪነት ብቁ ሊሆን እንደሚገባ አመላክተዋል፡፡
የባለድርሻ አካላት በበኩላቸው ምቹ የሆነ የፖሊሲ ማዕቀፍ በማዘጋጀት፣ የመሬት አቅርቦትን በማስፋት እና ለኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታን በመፍጠር ለኢንዱስትሪ ማበብ የበኩላቸውን ሚና መወጣት እንደሚገባቸው ያነሱት ዶ/ር ዮሐንስ በፋይናንስ ዘርፉ፣ በባለሃብቱ እና በባለድርሻ አካላት የተቀናጀ አሰራር የኢንዱስትሪ ዘርፉን ማሳደግ እንደሚቻል ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ማሞ ምህረቱ በበኩላቸው የተረጋጋ የማክሮ ኢኮኖሚ አውድ በመፍጠር የአምራች ዘርፉን ችግር መፍታት እንደሚቻል ገልጸዋል፡፡ የተረጋጋ የዋጋ ሁኔታ መኖር፣ የተረጋጋ የውጭ ምንዛሬ ስርዓት እንዲኖር ማድረግ፣ የፋይናንስ ዘርፍ ጤንነትን በማረጋገጥ የብድር አቅርቦትን ማስፋት ለኢንዱስትሪ ማደግ ወሳኝ እንደሆኑ አብራርተዋል፡፡ የውጭ ምንዛሬ በኢንቨስትመንት ዘርፍ የሚታየውን የጥሬ እቃ አቅርቦት ችግር የሚፈታ በመሆኑ የብሔራዊ ባንክ ዋና ትኩረት የውጭ ምንዛሬ አቅርቦትን ማስፋት መሆኑንም አያይዘው ጠቅሰዋል፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የአምራች ዘርፍን ለማሳደግ በመዋቅር ደረጃ ባደረገው የሪፎርም ስራ ዘርፉን ለድጋፍ በሚመች መልኩ በክላስተር የማድራጀት ስራ የተሰራ መሆኑን በመግለጽ ተደራሽነትን የማስፋት እና የአገልግሎት ጥራትን ለማስጠበቅ በርካታ ስራዎችን መሰራታቸውን አብራርተዋል፡፡
በፓናል ውይይቱ የፋይናንስ አቅርቦት ችግር፣ የውጭ ምንዛሬ እጥረት፣ የብድር ጊዜ መራዘም እና የቢሮክራሲ ችግሮች ለባለሃባቱ ማነቆ መሆናቸውን ተሳታፊዎች አንስተዋል፡፡ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ከባለሃባቱ የተነሱ ጥያቄዎችን በተቀናጀ መልኩ በመፍታት የአምራች ዘርፍን ለማሳደግ የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በመግለጽ የፓናል ውይይቱ የሚነሱ ጥያቄዎችን በተደራጀ መልኩ ለመመለስ እድል የሚሰጥ መሆኑን አንስተዋል፡፡
👍337👏4
የካፒታል ዕቃ ኪራይ አገልግሎት ፋይዳዎች

- ለዜጎች የሥራ እድል ይፈጥራል፤
- ምርት እና ምርታማነትን ይጨምራል፤
- ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን የሚተካ ምርቶችን ለማምረት ያግዛል፣ በዚህም የውጭ ምንዛሬ እንዲቆጠብ ይረዳል፤
- የቴክኖሎጂ ሽግግርን ለመፍጠር እድል ያመቻቻል፤
- ጥራት ያለው ምርት በማምረት በዓለም ገበያ ተወዳዳሪነት ይጨምራል፡፡ ለመሆን የሚያስችል የውጭ ምንዛሪ ለማስገኘት ያስችላል፤
- ለግብርና ዘርፉ ግብርናውን ከማዘመን፣ የምርት ብክነትን ከመቀነስና ምርትና ምርታማነትን ከመጨመር አንጻር ጉልህ ሚና ይጫወታል፤

በአጠቃላይ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ለሀገራችን የኢኮኖሚ እድገትና መዋቅራዊ ሽግግር ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንዲያበረክቱ ያስችላቸዋል፡፡
33👍28🤝5👏4
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በዘጠኝ ወራት የስራ አፈጻጸሙ ዘርፈ ብዙ ስኬቶች ማስመዝገቡን የመንግስት የልማት ድርጅቶች አስተዳደር ባካሄደው ግምገማ ማረጋገጡን አስታውቋል፡፡
ዝርዝር መረጃውን እንመለስበታለን፡፡
👍558👏8