Development Bank of Ethiopia (DBE)
23.3K subscribers
2.11K photos
76 videos
4 files
580 links
The development bank of Ethiopia (DBE) is one of the financial institutions engaged in providing short, medium and long term development credits.
Download Telegram
👍48❤11👏3
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራበት መሰረታዊ ምክነያት ኢንተርፕራይዞች በረዥም ጊዜ በአገር እድገት ውስጥ የሚፈጥሩትን በጎ ተጽእኖ ከግምት ውስጥ በማስገባት ነው፡፡ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ሰፊ የስራ እድል የሚፈጥሩ ከመሆናቸው ባሻገር ለትላልቅ ኢንዲስትሪዎች ግብዓት የሚያቀርቡ እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ማዕከል የሚሆኑ ናቸው፡፡

የአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የአገርን ኢኮኖሚ አስተማማኝ በሆነ መሰረት ላይ በመገንባት በኩል ያላቸው ሚና የላቀ መሆኑን የአለም ተሞክሮ ያስገነዝበናል፡፡ ተወዳዳሪ እና የውስጥ አቅምን አሟጦ መጠቀም የሚችል መሰረተ ሰፊ ኢኮኖሚ ለመገንባት የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ድርሻ የላቀ ነው፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ በማለፈ የዳበረ ኢኮኖሚ መገንባት ጃፓን እና ቻይናን ጨምሮ አሜሪካ እና ጀርመን ተጠቃሽ ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ለአገራችን ከሚሰጡት የላቀ ፋይዳ በመነሳት ያሉባቸውን ተግዳሮቶች ለመቅረፍ የሚያስችል ስራ እየሰራ ይገኛል፡፡ ኢንተርፕራይዞቼ ሊያጋጥሟቸው የሚችሉ የቴክኖሎጂ ችግሮችን በመቅረፍ እና የማሽነሪ አቅርቦት ከነድጋፉ በማዘጋጀት፣ የክህሎት ክፈተታቸውን መሙላት የሚያስችል ስልጠና በመስጠት እና በተለይ በአምራች ኢንዱስትሪ ላይ ተሳትፏቸውን እንዲያሳድጉ በማገዝ በኩል ባንኩ ተጨባጭ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
👍77❤15
ዒድ ሙባረክ!

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1444ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል አደረሳችሁ እያለ መልካም ምኞቱን ይገልጻል።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
❤52👍32
የአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የአገር ልማት መሠረቶች!
በ ዜማ ያሬድ
በሌሎች ሀገራት አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የአገርን ኢኮኖሚ አስተማማኝ በሆነ መሠረት ላይ በመገንባት በኩል ያላቸው ሚና የላቀ መሆኑን የሀገራት ተሞክሮ ያስገነዝበናል፡፡ ተወዳዳሪ እና የውስጥ አቅምን አሟጦ መጠቀም የሚችል መሠረተ ሰፊ ኢኮኖሚ ለመገንባት የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ድርሻ የላቀ ነው፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ ኢንተርፕራይዞች ለልማት ተጠቅሞ በማለፍ ረገድ ዛሬ ላይ የዳበረ ኢኮኖሚ መገንባት የቻሉት ጃፓን፣ ቻይና፣ አሜሪካ እና ጀርመን ተጠቃሽ ናቸው፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ለአገራችን ከሚሰጡት የላቀ ፋይዳ በመነሣት ያሉባቸውን ተግዳሮቶች ለመቅረፍ የሚያስችል ሥራ እየሠራ ይገኛል፡፡ ባንኩ ኢንተርፕራይዞቼ ሊያጋጥሟቸው የሚችሉ የቴክኖሎጂ ችግሮችን በመቅረፍ እና የማሽነሪ አቅርቦት ከነድጋፉ በማዘጋጀት፣ የክህሎት ክፍተታቸውን መሙላት የሚያስችል ስልጠና በመስጠት እና በተለይ በአምራች ኢንዱስትሪ ላይ ተሳትፏቸውን እንዲያሳድጉ በማገዝ በኩል ተጨባጭ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራበት መሰረታዊ ምክንያት ኢንተርፕራይዞች በረዥም ጊዜ በአገር ልማት ውስጥ የሚፈጥሩትን በጎ ተጽእኖ ከግምት ውስጥ በማስገባት ነው፡፡ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ሰፊ የስራ እድል የሚፈጥሩ ከመሆናቸው ባሻገር ለትላልቅ ኢንዲስትሪዎች ግብዓት የሚያቀርቡ እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ማዕከል ሆነው የሚያገለግሉ ናቸው፡፡
ኢንተርፕራይዞች የገበያ ክፍተት ከመሙላት አንጻር ያላቸው ሚናም ቁልፍ ነው፡፡ በኢኮኖሚ ውስጥ የገበያ ክፍተት የምርት አቅርቦት ከሸማቹ ፍላጎት ጋር ባለመመጣጠኑ እና ገበያ ላይ ያለው ምርት ከሸማቹ ፍላጎት ያነሰ በመሆኑ በአቅርቦት እና በፍላጎት አለመጣጣም የሚፈጠር የገበያ መዛባትን የሚያመላክት ነው፡፡ ታዲያ በገበያ ውስጥ ያለውን የምርት አቅርቦት በማሳደግ የገበያ ክፈተትን መሙላት ጤናማ የሆነ የግብይት ስርዓት ለመገንባት እና በአቅርቦት እና በፍላጎት አለመጣጣም የሚከሰት የገበያ መናርን ለማርገብ ወሳኝ ነው፡፡ ከዚህ አኳያ ኢንዱስትሪዎችን ማስፋት፣ የውጭ ምንዛሬ የሚጠይቁ ምርቶችን በአገር ውስጥ በመተካት አንድም የመግዛት አቅምን ማሳደግ እና በሌላ በኩል ደግሞ በገበያው የምርት መትረፍረፍ እንዲፈጠር ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
እንደሚታወቀው በአገራችን ከ80 በመቶ በላይ የሚሆነው የአገራችን ሕዝብ የኑሮ መሰረት ግብርና እና ከግብርና ጋር የተያያዘ ሥራ ነው፡፡ ግብርና እና ከግብርና ጋር የተያያዘ ሥራ የአገራችንም የኢኮኖሚ መሰረት ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብት ስሩ ግብርና መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ግብርና ከኢንዱስትሪ ጋር ተናቦ እና አንዱ ሌላውን እየመገበ እንዲሄድ በማድረግ የኢንዲስትሪ መሰረቱን አስተማማኝ ማድረግ ይቻላል፡፡ ለአምራች ኢንዱስትሪዎች ትኩረት ተሰጥቶ መሠራት የሚገባው አንድም በአገራችን ዘላቂ እና አስተማማኝ ኢንዱስትሪ ለመገንባት፤ በሌላ መልኩም ሰፊ የሰው ጉልበት የሚይዝና የአገራችንን የግብርና ምርት ግብአቶችን በመጠቀም እሴት ጨምሮ የዓለም ገበያን ጭምር ለመቆጣጠር ሰፊ ዕድል የሚሰጥ በመሆኑ ነው፡፡
የብዙ አገራት ተሞክሮ የሚያሳየውም ግብርና ከኢንዱስትሪ ጋር ተመጋግቦ የሚሄድ ነው፤ አንዱ ለሌላው ዘርፍ ማደግ እንደ እርሾ የሚያገልግል ነው፡፡ በአገራችን ነባራዊ ሁኔታም የምንገነባው ኢንዱስትሪ የግብርና ምርቶቻችንን እንደ ግብዓት መጠቀሙ በዓለም ገበያ ላይ ተወዳዳሪነት ከመጨመሩ ባሻገር ለአገር ውስጥ ገበያ ጉድለትን በመሙላት የተረጋጋ ኢኮኖሚ እንዲፈጠር የሚያስችል ነው፡፡
ከዚህ አንጻር በየአካባቢው የሚፈጠሩ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች እንደ አገር ማምጣት ለምንፈልገው የኢንዱስትሪ ሽግግር መሰረት ናቸው፡፡ በተለይ በአገራችን ያለውን ሰፊ የሰው ሀብት በመያዝ፣ አነስተኛ ካፒታል እና ቴክኖሎጂን በመጠቀም ረገድ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች ተመራጭ ናቸው፡፡
በአገራችን ካለው ከፍተኛ የስራ አጥ ቁጥር አንጻር በቂ የስራ እድል በመፍጠር በኩል አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች የላቀ ፋይዳ አላቸው፡፡ በበለጸጉ አገራት ለትላልቅ ኢንዱስትሪዎች ግብዓት በማቅረብ እና ሰፊ የስራ እድል መሰረት በመሆን በኩል አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች የጎላ ድርሻ አላቸው፡፡
የአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የፋይናንስ አቅማቸውን በማሳደግ፣ ስልታዊ በሆነ መንገድ የገበያ ክፍተቱን ሊሞላ በሚችል ዘርፍ ላይ እንዲሰማሩ በማሠልጠንና የክህሎት እና የፋይናንስ ችግራቸውን መቅረፍ ቢቻል ከአገራችን አልፎ በጎሮቤት ሀገራት ያለውን ገበያ ሰብረው መግባት የሚችሉበትን እድል ጭምር ማስፋት ይቻላል፡፡
የውጭ ምንዛሪ የሚጠይቁ ምርቶችን በአገር ውስጥ መተካት የሚቻለውም የአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች በአገራችን ኢኮኖሚ ውስጥ ያላቸውን ድርሻ በማስፋት ነው፡፡ ከተለያዩ አገራት በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ እየተገዙ የሚገቡት የኢንዱስትሪ ምርቶች በአገር ውስጥ በመተካት የገበያ ጉድለቱን መሙላት የሚቻለው የአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎችን ተሳትፎ ማሳደግ ሲቻል ነው፡፡ በመሆኑም የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የሚያደርገውን ስልጠና አጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን፣ ኢንተርፕራይዞቹ በአምራች ኢንዱስትሪ ላይ ያላቸውን የተሳትፎ ድርሻ በማሳደግ የአገር ኢኮኖሚን ማሳደግ የሚያስችል አቅም እንዲፈጥሩ ማገዝ ይጠበቃል፡፡
👍81❤17👏7🤝5
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በ115 ዓመታት የአገልግሎት ዘመኑ አገራዊ ፋይዳቸው ላቅ ያለ ፕሮጀክቶችን የፋይናንስ ድጋፍ በማድረግ በሁለት እግራቸው እንዲቆሙ አስተዋጽዖ አድርጓል፡፡ በግብርና፣ አምራች ኢንዱስትሪ፣ በአግሮ ፐሮሰሲንግ እና በሌሎች የኢንቨስትመንት መስኮች መሰማራት ለሚፈልጉ ሁሉ የቢዝነስ አዋጭነት ፕሮፖዛላቸውን በመገምገም እና ስልጠና በመስጠት ለበርካታ ኢንዱስትሪዎች ለውጥ ምክነያት እየሆነ ነው፡፡
በአገራችን ላሉ ግዙፍ የቡናና የአትክልት እርሻ ልማቶች፣ ቆዳና ሌጦ ፋብሪካዎች፣ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካዎች ከስኬቶቻቸው ፊት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አበርክቶት የጎላ ነው፡፡ በባንኩ የሚሰጣቸውን የብድር እና የክህሎት ድጋፍ አገልግሎት በአግባቡ የተጠቀሙ ታሪካቸው ተቀይሮ የአገር ተስፋ መሆን ጀምረዋል፡፡
ከዚህ ባሻገር የኢትዮጵያ ልማት ባንክ እስካሁን በሶስት ዙር ካሰለጠናቸው 33 ሺህ የሚሆኑ የአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች አዋጪ የሆነ የስራ ሃሳባቸውን በማቅረብ፤ ባንካችን ያስቀመጠውን የብድር መስፈርት አሟልተው የቀረቡ ኢንተርፕራይዞች 20 ቢሊዮን ብር የሚሆነ ብድር በሊዝ ፋይናንስ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆን ችለዋል፡፡ እንደሚታወቀው ባንካችን በአራተኛ ዙር 112 ሺህ የሚሆኑ ተሳታፊዎችን ሲያሰለጥን አንድም ዙሪያቸውን በመመልክት በአቅራቢያቸው የሚገኙ አማራጮችን እንዲመለከቱ ማድረግ የተቻለበት ሲሆን፣ ባንካችን የሚሰጠውን የብድር አገልግሎት ከመጠቀም ባሻገር በቢዝነስ ላይ ያለቸውን የግል ምልከታ እየቀየረና በአነስተኛ ካፒታል አዋጭ የሆነ የስራ ሃሳብ በአጭር ጊዜ ውጤታማ ማድረግ እንደሚችል ማስገንዘብ የተቻለበት ነው፡፡
👍61❤49👏9
በ ዓለም አቀፍ ደረጃ ለ 134 ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ48ኛ ጊዜ ለሚከበረው ዓለም አቀፍ የሰራተኞች ቀን እንኳን አደረሳችሁ።

የዘንድሮው የሰራተኞች ቀን (ሜይ ዴይ) በዓል "ለሰራተኞች መሰረታዊ ጥያቄዎች አፋጣኝ መፍትሔ" በሚል መሪ ቃል ይከበራል። Instagram
https://www.instagram.com/dbe_ethiopia/
Twitter
https://twitter.com/DBE_Ethiopia
You tube
https://www.youtube.com/@developmentbankofethiopia
Facebook
https://www.facebook.com/dbethiopia
👍39❤6🤝4
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ባዘጋጀው የኢቢሲ ቤተሰብ የወዳጅነት የእግር ኳስ ውድድር የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወደግማሽ ፍጻሜ አለፈ፡፡
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን አዲሱን የሚዲያ ኮምፕሌክስ ግንባታ መጠናቀቅ ተከትሎ ለግንባታው መጠናቀቅ በአጋርነት አብረው የሰሩ 8 ያህል ተቆማትን ያሳተፈ የወዳጅነት ውድድር እየተካሄደ ይገኛል፡፡
በውድድሩ እየተሳተፉና አጋርነታቸውን ሲያሳዩ ከቆዩት ከተቋማቱ መካከል የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አንዱ መሆኑን የጠቀሱት የኢቢሲ ስፖርት ክፍል ዳይሬክተር አቶ ግርማ በቀለ ተቋማቱን እውቅና ለመስጠት ውድድሩ መዘጋጀቱን አስታውቀዋል፡፡
የኢቢሲ አዲሱ የሚዲያ ኮምፕሌ አሁን ለደረሰበት ደረጃ እንዲደርስ የኢትዮጵያ ልማት ባንክም የራሱን አስተዋጾ በማድረጉ ያመሰገኑት አቶ ግርማ የእግር ኳስ የወዳጅነት ውድድሩ በቀጣይ በተቋማቱ መካከል ያለውን የስራ ግንኙነት እና ወዳጅነት/ አጋርነት ይበልጥ እንደሚያጠነክረው ገልጸዋል፡፡
በውድድሩ ተሳታፊ የነበሩት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የኮርፖሬት ባንኪንግ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው በላይ ባንካችን ኢትዮ ቴሌኮምን አሸንፎ ወደግማሽ ፍጻሜ መግባቱን ጠቅሰው ውድድሩ በሰራተኛው መካከል ያለውን ቅርርብ ይበልጥ እንደሚያጠናክረው አመላክተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሰራተኞች ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ዮሴፍ ተስፋዬ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከዚህ ቀደም ዋንጫ ማንሳቱን አውስተው በዚህ ውድድር በማሸነፍ ባንካችንን እናስጠራለን ብለዋል፡፡
የፍጻሜ ውድድሩ የኢቢሲ የሚዲያ ኮምፕሌክስ የምርቃት ስነስርአት በሚከናወንበት ማግስት እንደሚደረግም ተገልጿል፡፡
👍38❤16
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዲጂታል ዜና መጽሔት

ቁጥር 1

ሚያዚያ 2015 ዓ.ም
👍40❤4👏4🤝3
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የ4ዙር የመጀመሪያ ምዕራፍ ሰልጣኞች በቦረና በድርቅ ለተጐዱ ወገኖች ያሰባሰቡትን ገንዘብ አስረከቡ።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በሰጠው የአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ስልጠና የ4 ዙር የመጀመሪያ ምዕራፍ ላይ ተሳታፊ የነበሩ ሰልጣኞች ናቸዉ ድጋፉን አሰባስበው ያስረከቡት።
ባንኩ የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሰጠ ላለዉ ሀገራዊ ስልጠና እና ጉልህ አበርክቶ ከባንኩ ጎን በመቆም እኛ ሰልጣኞች የበኩላችንን ድጋፍ በቦረና በድርቅ ለተጐዱ ወገኖቻችን በማድረሳችን ደስተኞች ነን ሲሉ የየማዕከላቱ አስተባባሪዎች ተናግረዋል።
አዳማ፣ ቢሾፍቱ፣ ሚሊኒየም፣ ሲኒማ ኢትዮጵያ፣ ጉለሌና ጽዮን ሆቴል በጋራ፣ ግልገል በለስ፣ ቂርቆስ፣ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አዳራሽ፣ ኮልፌ የስልጠና ማዕከላትን እና በሌሎች ማዕከላት ከነበሩ ሰልጣኞች የተሰበሰበዉ ከ445 ሺ ብር በላይ ገንዘብ ለኦሮሚያ ክልል ቡሳ ጉኖፋ ገቢ ተደርጓል።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከዚህ ቀደም ለወገን ደራሽነቱን በማስመስከር በቦረና በድርቅ ለተጐዱ ወገኖቻችን የ20 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን ያስታወሱት ኃላፊው አቶ ሀብታሙ ሲሳይ በአሁኑ ሰዓት በኦሮሚያ ክልል በ10 ዞኖች በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የእለት ደራሽ እርዳታ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
እንደ ኃላፊዉ ገለፃ የባንኩ ሰልጣኞች እና ባንኩ ላደረጉት ድጋፍ ምስጋና በማቅረብ በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ዞኖች እየተደረገ ያለዉን ርብርብ መላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ የበኩሉን ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።
👍68❤45👏5🤝4
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለኢንዱስትሪ ዘርፍ ዘላቂ እድገትና ተወዳዳሪነት እንዲሁም ለአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ መነቃቃት "ኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ 2015" ያለውን ፋይዳ በመረዳት ኤክስፖውን ስፖንሰር በማድረግ አጋርነቱን አሳይቷል፡፡

ሶስተኛ ቀኑን የያዘውና በሚሊኒየም አዳራሽ የተከፈተው "ኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ 2015" "የፋይናንስ ተደራሽነት ለአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ" በሚል ርዕስ አምራቾች፣ የብሔራዊ ባንክ ገዥ፣ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት እና የንግድ ባንክ ምክትል ፕሬዝዳንት በፓናሊስትነት የተሳተፉበት የፓናል ውይይት የተካሄደ ሲሆን የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ በፋይናንስ አቅርቦት በኩል የሚገጥማቸው ችግሮች እና በቀጣይ መፈታት የሚገባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡

ለዘላቂ እድገት ኢትዮጵያ ታምርት!

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
👍48❤6👏5🤝4