Development Bank of Ethiopia (DBE)
23.3K subscribers
2.11K photos
76 videos
4 files
581 links
The development bank of Ethiopia (DBE) is one of the financial institutions engaged in providing short, medium and long term development credits.
Download Telegram
ማሳሰቢያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በአክሲዮን ለማደራጀት ፈቃድ የሰጠው አካል የለም!
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ አንቀሰቃሾች ስልጠና በመስጠት ወደ ስራ በማስገባት ላይ ላይ መሆኑን ተከትሎ በአንዳንድ አካላት ተቋሙን የማይወክሉ የተሳሳቱ መረጃዎች እየወጡ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶችም ሆነ የአክሲዮን ማደራጀት ስራውን ባንካችን በራሱ አሰራር መሰረት የሚፈጽም እንጂ ሌላ ተቋም እንዲሰራለት ውክልና አልሰጠም።
በመሆኑም የአክስዮን አደረጃጀትን ጨምሮ ሌሎች ባንኩ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ከባንካችን ይፋዊ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን እና ዌብሳይታችን ላይ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን ለማስገንዘብ እንወዳለን፡፡
በመሆኑም ከዚህ በታች የተያያዘውን መረጃ እና ተያያዥ ጉዳዮችን የተመለከቱ ዜናዎች ከባንካችን ፈቃድ አግኝተው እየሰሩ አለመሆናቸውን እንድትረዱ እናሳስባለን።
ከሰሞኑ አንዳንድ አካላት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ እየሰጠ ያለውን ስልጠና እንደ መልካም አጋጣሚያቸው ተጠቅመው በአክሲዮን የመደራጀት መልካም እድል እንደተፈጠረላቸው በማስመሰል መኪናን ጨምሮ በወር እስከ 60,000 ብር የሚደርስ ገቢ የሚያስገኝ ስራ እንዳላቸው፣የትርፋማ አክስዮን ድርሻ ባለቤት፣የኤሌክትሪክ መኪና እንደሚያገኙ፣የልማት ባንክ ብድር እንደሚያመቻቹ በመግለፅ ቴሌግራምን ጨምሮ በተለያዩ የማህበራዊ የትስስር ገፆች ላይ በማስተዋወቅ ላይ ይገኛሉ።
በመሆኑም የባንካችንን ስም በመጠቀም እናደራጃለን፣ ብድር እናሰጣለን በሚል የትኛውም አካል የሚያሰራጨው መረጃ ህገወጥ የወንጀል ድርጊት መሆኑን እንድታውቁና ሳትጭበረበሩ እናሳስባለን።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በአክሲዮን ተደራጅቶ ለመምጣት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎችንና ሌሎች አስፈላጊ ሂደቶችን በይፋዊ የማህበራዊ የትስስር ገፆቻችን የምናሳውቅ ይሆናል፡፡
ተመሳሳይ ጥቆማዎችን ለባንካችን በማድረስ ሃሰተኞችን እንድታጋልጡ እየጠየቅን መሰል የማጭበርበር ድርጊቶችን በሚከተሉት ቁጥሮች እንድታሳውቁን በዚህ አጋጣሚ እንገልፃለን፡፡

ስልክ ቁጥሮቻችን
09 04 37 44 44
09 04 36 44 36
09 04 35 77 35
👍113👏109
ሐሳብ፣ ቁርጠኝነት፣ ተግባር የስኬት መሰረት መሆናቸውን ያሳየ ወጣት፡፡
https://www.youtube.com/watch?v=MLWSq1fa10o
አቶ አለባቸው ምህረቴ
የአለባቸው እና ማስተዋል ህብረት ሽርክና ማህበር ባለቤት እና ዋና ስራ አስኪያጅ
👍8224🤝11
ከወለድ ነፃ የሊዝ ፋይናንስ ምን ማለት ነው?

ከወለድ ነፃ የሊዝ ፋይናንስ ማለት የሸሪዓ ህግን ተከትሎ የኪራይ አገልግሎት መስጠት ማለት ነው፡፡ ይህ ማለት ወለድ መክፈልም ሆነ መቀበልን የሚከለክል የሊዝ ፋይናንስ ስርዓት ነው፡፡

ከወለድ ነፃ የፋይናንስ አገልግሎት የሸሪዓ ህግ በማይጥስ ሁኔታ በባንኩ የኢጃራ ሊዝ ፋይናንስ መርህ መሠረት በባንኩና በደንበኛው መካከል በሚደረግ ስምምነት መሠረት የካፒታል ዕቃ ዋጋና የኪራይ ዋጋ ለክፍያ በተሰጠው ጊዜ ውስጥ እየከፈለ ዕቃዎቹን በኪራይ መልክ የሚጠቀምበት እና ባንኩም የኪራይ ውሉ ሲያበቃ እንደሌሎች ባንኩ ፋይናንስ እንዳቀረበላቸው ደንበኞች ባለቤትነቱን ለደንበኛው የሚያስተላልፍበት አሰራር ማለት ነው።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
👍9224👏1
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ግልጽ በሆነ አሰራር በመንግስት የልማት እቅዶች ቀዳሚ ስፍራን የሚይዙ አዋጭ የልማት ፕሮጀክቶች ከሀገር ውስጥና ከውጪ የብድር ገንዘብ በማሰባሰብ የተሰጠውን የፋይናንስና የቴክኒክ ድጋፍ የመስጠት ተልዕኮ መወጣት የሚያስችለውን የውስጥ ጥንካሬ በመገንባት ሀገራዊ ተልዕኮውን በመወጣት ላይ ይገኛል፡፡
ባንካችን ለአገራችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ፋይዳ ባላቸው ተመራጭ ፕሮጀክቶች ላይ ለሚሳተፉ የሃገር ውስጥ እና የውጭ ባለሃብቶች የፋይናንስ ብድር በመስጠት የልማት አጋርነቱን እያረጋገጠ ያለ ባንክ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
👍9517🤝4
የሥራ ፈጠራ ሐሳብን ፋይናንስ ማድረግ ማለት ምን ማለት ነው?
የሥራ ፈጠራ ሐሳብን ፋይናንስ ማድረግ ማለት ከሚመለከተው የመንግስት አካል የባለቤትነት ማረጋገጫ ያገኘ የፈጠራ ስራን ማስያዣ በማድረግ የፋይናንስ አቅርቦት የሚገኝበት ነው፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክም ይህንን የተረጋገጠ የፈጠራ ሃሳብ ባለቤትነትን በማስያዣነት በመጠቀም የኪሳራ ስጋቱንም ተጋርቶ የስራ ፈጠራ ሐሳቡ ወደ ፕሮጀክት እንዲቀየር በማድረግ ፕሮጀክቱን ለገበያ ያቀርባል፡፡ ወደገበያ የሚወጣው የስራ ሃሳብ ደግሞ ተወዳዳሪ እና በገበያ ውስጥ አሸናፊ እንዲሆን ልማት ባንክ አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ ያደርጋል፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
👏56👍4310🤝9
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለደንበኞች የሚሰጣቸው አገልግሎቶች ባንኩ ከተቋቋመበት ዓላማ አንፃር የተቀረፁና የአገራችንን ኢኮኖሚያዊ ሽግግር የሚያፋጥኑ ናቸው። ባንካችን በሊዝ ፋይናንስ አሰራር  የሚሰጠው የብድር አሰጣጥ የራሱ መንገድ ያለው መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል።

ደንበኞች አንድም የሚያቀርቡት ፕሮፖዛል አዋጭነቱን ደጋግሞ ማየት ይጠብቅባቸዋል። ባንካችን ሁሉንም የብድር ሂደቶች ካላቸው አገራዊ ፋይዳ አንፃር እየመዘነ እንደአመጣጣቸው የሚያስተናግድ መሆኑን መገንዘብ ይገባል።

ከባንካችን አገልግሎት የሚጠይቅ አካል ግዴታውን ማሟላቱን እና ጥያቄው ባንኩ ብድር ከሚሰጥባቸው ዘርፎችና ንዑስ ዘርፎች መካከል መሆናቸውን ማረጋገጥ እንደሚገባ እየገለፅ የሊዝ ፋይናንስ አገልግሎት ተጠቃሚ ለመሆን የሚያስፈልጉ ዝርዝር መስፈርቶች አያይዘንላችኋል።



የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
👍8228🤝3👏1
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ያካሄደውን ሪፎርም ተከትሎ ተደራሽነቱን ለማስፋት በወሰደው እርምጃ በሶማሌ ክልል ዲስትሪክት በመክፈቱ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ደንበኛ ወደ ባንኩ እንዲመጣ እያደረገ መሆኑን የባንኩ ጂግጂጋ ዲስትሪክት አስታወቀ፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የጂግጂጋ ዲስትሪክት ስራ አስኪያጅ አቶ ወንድወሰን ተመስገን እንዳሉት ባንኩ ዲስትሪክቱን በክልሉ መክፈቱ ቀደም ሲል የነበረውን ከፍያለ የደንበኞች ቁጥር እና የሚቀርበውን የብድር ጥያቄ በእጅጉ አሳድጎታል፡፡
ቀደም ሲል በሁለት ቅርንጫፎች ብቻ በክልሉ ይሰጥ የነበረውን አገልግሎት የባንኩን ሪፎርም ተከትሎ በአሁኑ ወቅት ወደ አንድ ዲስትሪክት እና ወደ አራት ቅርንጫፎች ማሳደግ በመቻሉ ከፍተኛ የሆነ የብድር ጥያቄ እየቀረበ መሆኑን ነው ስራ አስኪያጁ አቶ ወንድወሰን የተናገሩት፡፡
ከሚቀርቡ ጥያቄዎች መካከል በአዋጭነታቸው የተለዩ 53 ኢንተርፕራይዞች መኖራቸውን የተናገሩት አቶ ወንድወሰን ከነዚህም ውስጥ 17 ወደ ስራ ገብተው ማምረት የጀመሩ ናቸው ብለዋል፡፡
ቀሪዎቹም በተከላ እና በግዥ ሂደት ላይ የሚገኙ መሆኑን የተናገሩት አቶ ወንድወሰን 15ቱ በመጽደቅ ሂደት ላይ የሚገኙ ናቸው ብለዋል፡፡
ለነዚህ ፕሮጄክቶች የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከ1.2 ቢሊዮን ብር ብር በላይ ፋይናንስ ማድረጉን ነው የባንኩ የጂግጂጋ ዲስትሪክት ስራ አስኪያጅ አቶ ወንድወሰን ተመስገን የተናገሩት፡፡
እነዚህ የሊዝ ፋይናንስ ፕሮጄክቶች በሶማሌ ክልል ያለውን ከፍተኛ የገበያ ፍላጎትን ታሳቢ ያደረጉ ፤ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን የሚያስቀሩ እና ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል የሚያስገኙ ሲሆን የአካባቢውን ኢኮኖሚ ከንግድና አርብቶ አደርነት ወደ አምራችና ግብርና እንዲሰማሩ የሚያደርጉ መሆናቸውንም ነው የገለጹት፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሪፎርም ከማካሄዱ በፊት ባንኩ በሶማሌ ክልል ብዙም የማይታወቅ እንደነበር ያስታወሱት ስራ አስኪያጁ አሁን ላይ ዲስትሪክት እና አራት ቅርንጫፎችን ከፍቶ እየተንቀሳቀሰ በመሆኑ ማህበረሰቡ ደስታውን እየገለጸ እና ከባንኩ ጋር አብሮ ለመስራት ጥያቅዎችን እያቀረበ ይገኛል ብለዋል፡፡
በኢትዮጵያ ልማት ባንክ የጂግጂጋ ዲስትሪክት በስሩ የጂግጂጋ ፤ ቀብሪደሃር፡ ደጋሃቡር እና ጎዴ ቅርንጫፎችን ከፍቶ እየሰራ ይገኛል፡፡
👍47👏21🤝1
የግብርና ሚኒስቴር የግብርና ምርታማነትን በማሳደግ የህብረተሰቡን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል ብሎም የግብርናውን ዘርፍ ለሀገራዊ ኢኮኖሚው ዕድገት የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ ከፍ ለማድረግ ከክልሎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡
የግብርና ግብዓት አቅርቦትና ምርት ግብይት ኤክስፖ 2015 በሚል ርዕስ ኤግዚቢሽንና ባዛር እንዲሁም ንዑስ ዘርፉን የሚያመለክቱ ጥናታዊ ጽሑፎች የሚቀርቡበት ሲምፖዚየም በአዲስ አበባ ከሰሞኑ ተከፍቷል፡፡
ኤክስፖው ከመጋቢት 26 እስከ ሚያዝያ 5 የሚቆይ ሲሆን የሰብልና የእንስሳት ምርት ማሳደጊያ ግብዓቶችንና የተመረጡ የግብርና ምርቶች ለዕይታ ቀርበውበታል፡፡
ምርቶችን ለገበያ ለማስተዋወቅ እና ደንበኞችንና አምራቾችን ለማገናኜት መልካም አጋጣሚን እንደፈጠረም ተሳታፊዎች ገልጸዋል፡፡
አንዱ-በኤክስፖው ላይ ከሀገሪቱ ሁሉም አካባቢዎች የተለዩ ዋና ዋና ግብዓት አምራቾች፣ በአቅራቢነት የተሰማሩ ድርጅቶች፣ የሕብረት ስራ ማህበራት፣ የግብርና ምርት አምራቾች እና ፣ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡
የግብርናው ዘርፍ እንዲያድግ በትኩረት የሚደግፈው የኢትዮጵያ ልማት ባንክም የግብርና ሚኒስቴር ያዘጋጀውን ኤክስፖ ስፖንሰር በማድረግ አጋርነቱን አሳይቷል፡፡
👍6414👏2
በአክሲዮን ማኅበር የመሥራት ምቹ ሁኔታ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ እያንዳንዱ ሠልጣኝ በሥልጠናው ከሚያገኘው የቢዝነሥ ሥራውን ለመሥራት ክህሎት ከማግኘት በተጨማሪ ለሥራ ማስኬጃ (መዋጮ) የሚጠየቁትን 20 በመቶ ካፒታል ለሌላቸውና ወደ ቢዝነስ መግባት ለሚፈልጉ አዲስ አማራጭ አዘጋጅቷል፡፡ በመሆኑም ባለፉት ሦስት ዙሮች ሥልጠና ወስደው ብቁ ሆነው የምስክር ወረቀት የተቀበሉ በአክሲዮን ማኅበር ወደ ቢዝነስ እንዲገቡ በባንካችን ተፈቅዷል፡፡ ባንኩ በአክሲዮን አደራጅቶ ፋይናንስ በማድረግ ለበርካቶች የሥራ ዕድል በመፍጠር ልማትን ለማፋጠን እንቅስቃሴ ጀምሯል፡፡ ለዚህም እያንዳንዱ ሼር 1000 ብር ዋጋ ያለው ሆኖ ዝቅተኛው የሚሸጥ የሼር መጠን አምስት ወይም 5000 ብር ይሆናል፡፡ በአክሲዮን ለመሥራት ሠልጣኞች ራሳቸውንና ሌሎች አብረዋቸው ሊሠሩ የተዘጋጁ የአክሲዮን አባላቶቻቸውን በማስመዝገብ የዚህ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ምቹ ሁኔታ ተዘርግቷል፡፡
በሚፈጠረው የአክሲዮን ማኅበር ውስጥ ዋነኛ (አስተባባሪ) የሚሆኑት ሥልጠና ወስደው ምስክር ወረቀት ያገኙ አባላቱ ቁጥር አንድ ወይም ከዚያ በላይ መሆን የሚገባቸው ሲሆን፣ የሚያስመዘግቧቸው ሌሎች አባላት ግን ሥልጠናውን ያልወሰዱ ከሆነ በቀጣይ በሚኖሩ የሥልጠና ዙሮች መሠልጠን ይገባቸዋል፡፡ በአክሲዮን ማኅበር ለመሥራት የሚመዘገቡ የአክሲዮን ባለቤቶች አብረው ለመሥራት ተስማምተው የቆዩ፣ ሕጋዊ ለመሆን በሂደት ላይ ያሉና በጋራ የሚጠሩበት ስም ካላቸው ማስመዝገብ ይችላሉ፡፡ በአዲስ መልክ የሚቋቋም ከሆነ ግን በሚመዘገቡበት ቀን የባንኩ ቅርንጫፍ ለጊዜው በሚሰጣቸው መለያ ስም ወይም ቁጥር ይመዘገባሉ፡፡ ተመዝጋቢዎች ኢንቨስት ማድረግ የሚፈልጉበትን ቦታና የኢኮኖሚ ዘርፍ እንዲሁም ንዑስ ዘርፍ መምረጥ ይጠበቅባቸዋል፡፡ በግላቸው ለመሥራት አቅሙ ያላቸውና የተዘጋጁ ሠልጣኞች በዚህ መንገድ ለመሥራት መዘጋጀታቸውን ማስመዝገብ ይኖርባቸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
👍13917👏7
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከጀርመን ልማት ባንክ ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ በወረታ ኢንተርናሽናል ቢዝነስ የቀረቡ 17 የእርሻ ትራክተሮች ለሊዝ ፋይናንስ ደንበኞቹ አስረክቧል፡፡

ዘመናዊ ግብርና ማስፋፋት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ መሰረት ነው፡፡ በመሆኑም ግብርናን በማዘመን ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ኢትዮጵያውያን 20 በመቶ የስራ ማስኬጃ በመክፈል 80 በመቶውን በአምስት ዓመታት ተከፍሎ የሚያልቅ የሊዝ ፋይናንስ ብድር አሰጣጥ ስርዓትን በመዘርጋት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለግብርና ሜካናይዜሽን ስራ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
👍86👏5🤝31
👍4811👏3
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራበት መሰረታዊ ምክነያት ኢንተርፕራይዞች በረዥም ጊዜ በአገር እድገት ውስጥ የሚፈጥሩትን በጎ ተጽእኖ ከግምት ውስጥ በማስገባት ነው፡፡ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ሰፊ የስራ እድል የሚፈጥሩ ከመሆናቸው ባሻገር ለትላልቅ ኢንዲስትሪዎች ግብዓት የሚያቀርቡ እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ማዕከል የሚሆኑ ናቸው፡፡

የአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የአገርን ኢኮኖሚ አስተማማኝ በሆነ መሰረት ላይ በመገንባት በኩል ያላቸው ሚና የላቀ መሆኑን የአለም ተሞክሮ ያስገነዝበናል፡፡ ተወዳዳሪ እና የውስጥ አቅምን አሟጦ መጠቀም የሚችል መሰረተ ሰፊ ኢኮኖሚ ለመገንባት የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ድርሻ የላቀ ነው፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ በማለፈ የዳበረ ኢኮኖሚ መገንባት ጃፓን እና ቻይናን ጨምሮ አሜሪካ እና ጀርመን ተጠቃሽ ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ለአገራችን ከሚሰጡት የላቀ ፋይዳ በመነሳት ያሉባቸውን ተግዳሮቶች ለመቅረፍ የሚያስችል ስራ እየሰራ ይገኛል፡፡ ኢንተርፕራይዞቼ ሊያጋጥሟቸው የሚችሉ የቴክኖሎጂ ችግሮችን በመቅረፍ እና የማሽነሪ አቅርቦት ከነድጋፉ በማዘጋጀት፣ የክህሎት ክፈተታቸውን መሙላት የሚያስችል ስልጠና በመስጠት እና በተለይ በአምራች ኢንዱስትሪ ላይ ተሳትፏቸውን እንዲያሳድጉ በማገዝ በኩል ባንኩ ተጨባጭ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የልማት አጋርዎ!
👍7715