CompuTech©️
164 subscribers
359 photos
169 videos
28 files
208 links
Tech Update info
Computer and phones Security's
Computer Software Tips
Mobile Application Tips
Tutorial Point


Update " Yourself & Grow Knowledge also the Persons around you "
Download Telegram
📱 የXender መተግበሪያ እውነታ
Xender የፋይል መላኪያ መተግበሪያ ሲሆን ፎቶ፣ ቪዲዮ፣ ሙዚቃ እና ሌሎች ፋይሎችን ያለ ኢንተርኔት በፍጥነት WiFi 📶 direct በመጠቀም መላክ ያስችላል።
ዋና አላማው የ Bluetooth ፍጥነት በማሻሻል በፍጥነት ፋይሎችን ለመላለክ እንዲያስችል ነው።
👉 ይህ መተግበሪያ በቻይና የቴክኖሎጂ ኩባንያ Amobi ተፈጥሯል።
👨‍💻 የኩባንያው ዋና መስራች Peter Jiang እና በባልደረቦቹ ተሰርቷል ።
በ2012 ጀምሮ ዛሬ በአፍሪካ እና በእስያ በጣም ታዋቂ ሆኗል።
ኢንተርኔት አያስፈልግም
ፈጣን ነው
ነፃ ነው
📢 በተለይ የኢንተርኔት ዳታ አገልግሎት ውድ በሆነባቸው አገሮች ውስጥ ብዙ ሰዎች ይጠቀሙበታል።


#xender #apptips #ኢትዮጵያ #ቴክመረጃ #ቴክኖሎጂመረጃ #አፕልኬሽንመረጃ #መተግበሪያ


CompuTech©
👍2
CompuTech©️
PLAYFy_TV_1.5.apk
ይሄን የኳስ አፕ 7 አይነት ችግሮች ታይተውበታል ሪፖርትም ተደርጎበታል። ደህንነቱ እስኪረጋገጥ ለ ጊዜው PLAYFy TV 1.5 ተዉት/ አጥፉት እና ሌላ በጣም አሪፍ አፕ እለቅላችኋለው።👍
SportzX_2.1vC.apk
13.6 MB
ይሄን አፕ ከዚህ በፊት ታውቁታላቹ ብዬ አስባለሁ ። ይሄ የኳስ  አፕ 99% ደህንነቱ የተረጋገጠ ነው።
RongyTV_2.1.apk
12.4 MB
100% safe የሆነ የኳስ አፕ ነው።
የመጨረሻው አፕዴት ነው።
መስራት በምትችሉት የስራ መደቦች
freelance ፕላትፎርም ላይ ለመስራት ሞክሩ ከላይ ያያችሁት፣ዝም ብሎ [ with international tax % ]earn ያደረኩት አደለም ወደዚህ መስመር ለመግባት ቢያንስ ከ አራት አመት በላይ ፈጅቶብኛል ከብዙ ትግል በኋላ ስራዎችን በአግባቡ እና በቅልጥፍና እየሰራሁ እገኛለው። 🙏
በተለይ Upwork ሞክሩት ። እንዴት እንደምትመዘገቡ ደረጃ በደረጃ አሳያችኋለው።
👍2
ከላይ ባያችሁት ሁለት ምስሎች ዳታ ከደህንነት አንፃር ልዩነታቸው ምን ይመስላችኋል ? በኮሜንት ይግለፁ👍

በተለይ አፕ ከ ፕለይ ስቶር ስናወርድ
detail ላይ -
🔓 🚫 "Security Practices"
ላይ ይገኛል።

What do you think is the difference between the two images below in terms of data security? Leave a comment 👇

#computech #cybersecurity #AppTips #trading #EthiopiaTech #ቴክኖሎጂመረጃ #ICT

CompuTech©
👍2
📱 Samsung Galaxy S26 – ተለቀቀ
🔥 አዲሱ Galaxy S26 በከፍተኛ ፍጥነት፣ አሪፍ ምስል ማሳያ እና ዘመናዊ የAI ባህሪያት የተላበሰ ስልክ ነው።

📌 ዋና ባህሪያትም

• 6.3" Dynamic AMOLED 120Hz display የምስል ጥራት
• Snapdragon 8 Elite / Exynos

"ምርቱ ከአገር ወደ አገር ይለያያል "
• 12GB RAM + 256/512GB ውስጣዊ ሚሞሪ
• 50MP ዋና ካሜራ + 12MP Ultra-wide + 10MP  Telephoto የካሜራ ጥራት
• 4300mAh ባትሪ አቅም – 25W  ፈጣን ቻርጅ
• Android 16 + One UI 8 የሶፍትዌር ቨርዥን
• IP68 የውሃ እርጥበት እና የአቧሯ መከላከያ
ፈጣን Performance (አፈጻጸም)
ጥሩ የካሜራ ጥራት
ቀላል እና ስማርት  display

💬 በአጠቃላይ: Galaxy S26 ለጌም፣ ለፎቶ እንዲሁም  ለዕለታዊ አጠቃቀም አሪፍ ነው።
ከS25 ጋር እንብዛም ልዩነት የላቸውም ነገር ግን በ Performance S26 የተሻለ ሆኖ አግኝተነዋል ።


#Samsung #GalaxyS26 #TechNews #አዲስስልክ #newsmartphone #techtips #smartphonetips #phonereviews #computech

CompuTech©
👍2
Electronic warfare ምንድ ነው?
የኤሌክትሮማግኔቲክ ጦርነት ወይም የኤሌክትሮኒክስ ጦርነት (EW) የኤሌክትሮማግኔቲክ ስፔክትረም ወይም ቀጥተኛ ኃይልን በመጠቀም ስፔክትረምን ለመቆጣጠር፣ ጠላትን ለማጥቃት ወይም የጠላትን ተግባራት ለማደናቀፍ የሚያካትት ጦርነት ነው። የኤሌክትሮማግኔቲክ ጦርነት ዓላማ የተቃዋሚውን ጥቅም መከልከል እና ወደ EM ስፔክትረም ወዳጃዊ መዳረሻን ማረጋገጥ ነው። የኤሌክትሮማግኔቲክ ጦርነት ከአየር፣ ከባህር፣ ከመሬት ወይም ከጠፈር በተሰሩ እና ባልተሰሩ ስርዓቶች ሊተገበር ይችላል ግንኙነትን፣ ራዳርን ወይም ሌሎች ወታደራዊ እና ሲቪል ንብረቶችን ኢላማ ማድረግ ይችላል።


CompuTech®
የኤሌክትሮማግኔቲክ አካባቢዎች
በተለይ ወታደራዊ ስራዎች የሚከናወኑት በኤሌክትሮማግኔቲክ ስፔክትረም እየጨመረ በሚሄድ ውስብስብ የመረጃ አካባቢ ውስጥ ነው።
የመረጃ አካባቢው የኤሌክትሮማግኔቲክ ስፔክትረም ክፍል ኤሌክትሮማግኔቲክ አካባቢ Electromagnetic Environment (EME) ተብሎ ይጠራል። ወታደራዊ ኃይሎች የኤሌክትሮማግኔቲክ አካባቢን ያለ ምንም እንቅፋት ተደራሽነት እና አጠቃቀም እንዲኖራቸው የታወቀ አስፈላጊነት ወታደራዊ ስራዎችን ለመደገፍ የኤሌክትሮኒክስ ጦርነት ተጋላጭ የመሆን እድሎችን ይከላከላል።

በመረጃ ኦፕሬሽን ግንባታ ውስጥ፣ Electronic warfare ( EW) የመረጃ ጦርነት አካል ነው።

CompuTech©
👍2
ቢሮ 121 ፡ ናሳን ለሶስት ወራት ሀክ ያደረገው የሰሜን ኮሪያ የሳይበር ተቋም ።
ሰሜን ኮሪያን በተመለከተ በምእራባውያን ሚዲያዎች ተወርተው ባብዛኛው ሰው የሚታመኑ  ብዙ ተረት መሳይ ወሬዎች  አሉ ። ከነዚህም መካከል። በሰሜን ኮሪያ ጅንስ መልበስ ክልክል ነው ።በሰሜን ኮሪያ ኮምፒውተር የሚጠቀሙ ሰወች ቁጥር ከአራትመቶ አይበልጥም ።ስማርት ስልክ እና መኪና የሚፈቀደው ለባለስልጣናት ብቻ ነው ።ሁሉም የሰሜን ኮሪያ ወንዶች ፀጉራቸውን በፈለጉት አይነት መቆረጥ አይችሉም ።እንዲሁም በየአመቱ ታስቦ በሚውለው የቀድሞው መሪ የሙት አመት እለት በመላ ሀገሪቱ መሳቅ ክልክል ብቻ ሳይሆን ለእስር የሚያበቃ ወንጀል ነው የሚሉና ሌሎች በርካታ የሀሰት  ወሬዎች በሰፊው ከመወራታቸው የተነሳ ፡ ብዙ ሰው እውነት ናቸው ብሎ ያምናል ።በነዚህ በምእራባውያን ሚዲያዎች ለአመታት ሲወሩ ከቆዩ ፕሮፖጋንዳዎች የተነሳም ስለ  ሰሜን ኮሪያ ሲወራ ባብዛኛው ሰው አእምሮ የተከሰተው በአምባገነን መሪ የምትተዳደር ፡ ከኑክሌርና ወታደራዊ ሀይል በቀር በሌሎች ጉዳዮች ከአለም ስልጣኔ የተገለለች እና የተጨቆኑ ህዝቦች መኖሪያ የሆነች ምስኪን ሀገር እንደሆነች ነው ። ሰሜን ኮሪያን ሆን ተብሎ ለማሳነስ ከሚወሩት መካከል ከሁሉ የሚያስቀው ኮምፒውተርና ኢንተርኔት የሚጠቀሙ በመቶ የሚቆጠሩ ሰወች እንደሆኑ  የሚወራው ነገር ነው ። እውነታው ምንድነው ካልን ሰሜን ኮሪያ  የራሷ የሆነ የኢንተርኔት ሲስተም ያላት ፡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የስልክና የዋይፋይ ተጠቃሚዎች የሚገኙባት ፡ በኮምፒውተር እውቀታቸው የመጠቀ እውቀት ያላቸው በሺህ የሚቆጠሩ ወጣቶች ያሉባት ሀገር ናት ።