CompuTech©️
164 subscribers
359 photos
169 videos
28 files
208 links
Tech Update info
Computer and phones Security's
Computer Software Tips
Mobile Application Tips
Tutorial Point


Update " Yourself & Grow Knowledge also the Persons around you "
Download Telegram
CompuTech©️
Smart Police Station in Addis Ababa 🇪🇹 👮‍♂️ "ሰው አልባ" የፖሊስ ጣቢያ በአዲስ አበባ 🇪🇹 ​"በአፍሪካ የመጀመሪያው ነው የተባለለት ስማርት የፖሊስ ጣቢያ በቦሌ አገልግሎት ሊጀምር ነው" #Ethiopia  | ​በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ታሪክ አዲስ ምዕራፍ ተከፍቷል። በቦሌ ክፍለ ከተማ (ቦሌ ድልድይ አካባቢ) ፖሊስን በአካል ማግኘት ሳይጠበቅብዎት፤ በቴክኖሎጂ ብቻ ጉዳይዎን የሚያስፈጽሙበት…
"በአዲስ አበባ ቦሌ ሩዋንዳ አካባቢ የተገነባው 'ስማርት ፖሊስ ጣቢያ' (Smart Police Station) እንዴት ነው አገልግሎት የሚሰጠው?

በቅርቡ የሙከራውን ጊዜ አጠናቆ ሥራ የሚጀምረው ይህ ዘመናዊ የፖሊስ ጣቢያ፣ ልክ እንደ ኤቲኤም (ATM) ማሽን ሁሉ ከፖሊስ አባላት ጋር በአካል መገናኘት ሳያስፈልግ የፖሊስ አገልግሎቶችን በራስ-አገልግሎት (Self-service) ለማግኘት ያስችላል።

በማሽኑ ከሚሰጡ አገልግሎቶች መካከልም፦
የወንጀል ጥቆማና አቤቱታ ማቅረብ፦ ማንኛውንም የወንጀል ድርጊት ወይም ጥቆማ በማሽኑ አማካኝነት ለፖሊስ ማድረስ ይቻላል።

የምስክር ወረቀቶች፦ ከወንጀል ነፃ መሆኑን የሚገልጹ የምስክር ወረቀቶችን ለማግኘት።
ክፍያዎችን መፈጸም፦ ልዩ ልዩ የቅጣት ክፍያዎችን ለመፈጸም።

የጠፉ ንብረቶች ሪፖርት፦ ስልክና ጌጣጌጥን ጨምሮ ማንኛውንም የጠፋ ንብረት ለማመልከት ወይም ሪፖርት ለማድረግ፤ እንዲሁም ሪፖርት የተደረገው ንብረት ስለመገኘቱ በዚሁ ማሽን መከታተል ይቻላል።

የቪዲዮ ጥሪ፦ ተጨማሪ መረጃ ካስፈለገ በቪዲዮ ጥሪ በቀጥታ ከፖሊስ አባላት ጋር መገናኘት ያስችላል።

ከዚህም በተጨማሪ ክፍያ የተፈጸመባቸውን ደረሰኞችና የተፈቀዱ ሰነዶችን ለማተም የሚያገለግል ሲሆን፣ ሌሎች አገልግሎቶችንም በውስጡ አካትቷል።

በአፍሪካ የመጀመሪያው የሆነው ይህ ቴክኖሎጂ፣ በአሁኑ ወቅት በቦሌ ሩዋንዳ አካባቢ ተተክሎ አገልግሎት ለመጀመር ጥቂት ቀናት ብቻ ቀርተውታል።"

#techinfo #smartcity #digitalethiopa #ቴክኖሎጂኢትዮጵያ #አዲስመረጃ #smartpolice #sps #ስማርትፓሊስበአዲስአበባ

CompuTech©
***
👍2
የፌስቡክ ውልደት ከሃርቫርድ ዶርም ክፍል እስከ ሜታቨርስ ትልቅ ካምፓኒ
**

ልክ የዛሬ 22 ዓመት፣ ዓለማችንን የዲጂታል ሂደት የቀየረው "TheFacebook" በማርክ ዙከርበርግ እና ጓደኞቹ አማካኝነት በሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ነው የመወለዱ ታሪክ የሚጀምረው።

ዛሬ ግማሽ የዓለም ሕዝብ ወይም ከ3.27 ቢሊዮን በላይ ሰዎች የሚገናኙበት ግዙፍ ዲጂታል መንደር ሆኗል።

ይህ አስደናቂ ጉዞ በ2003 "Facemash" በሚል የፎቶ ንጽጽር ሙከራ ተጀምሮ፣ ዛሬ ዋትስአፕንና ኢንስታግራምን ወደሚያጠቃልለው "ሜታ" (Meta) አድጓል።

ፌስቡክ በ2005 "The" የሚለውን ቃል ለማስወገድ 200 ሺህ ዶላር ሲከፍል፣ በ2009 ደግሞ የዲጂታል ዘመን ስሜት መግለጫ የሆነውን "ላይክ" (Like) ቁልፍ አስተዋውቋል።

ከማኅበራዊ ትስስር አልፎ በ2021 ራሱን ወደ "ሜታቨርስ" በማሸጋገር የወደፊቱን የቴክኖሎጂ ዓለም እየመራ ይገኛል።

ናፍቆት በቤተሰቦች መካከል ለማቅለልም ሆነ የተጠፋፉ ጓደኛማቾች ማገናኘት ፣ እስከ ዓለም አቀፍ የንግድ መድረክነት የዘለቀው ፌስቡክ፣ ዛሬ የሁላችንም የዕለት ተዕለት ሕይወት አካል ሆኗል።

ውዶቼ 🥰 ፌስቡክን መጠቀም የጀመራችሁት በስንት ዓመተ ምህረት  ነበር?
መጀመሪያ የለጠፉችሁት ነገር ወይም የመጀመሪያውን የፌስቡክ ጓደኛዎን ያስታውሳሉ?
እስቲ ይሄንን መረጃ በማጋራት ይተባበሩን 👍 @compu_te


by jeminyem

#Facebook22 #Meta #MarkZuckerberg #DigitalRevolution #TechHistory #FacebookAnniversary
#Facebook
#ኢትዮጵያ #ቴክ

CompuTech©
  *
🔥3
SIM Cardቹን ከ አጭበርባሪዎች
(SIM Hack / SIM Swap)
ለመጠበቅ የሚረዱ ነገሮች

አይበለው እና ስልካቹ ቢሰረቅ 😳 የሰረቀው አካል SIM Swap ወይም ሲሙን አውጥቶ ሌላ ቀፎ ላይ አስገብተው የተለያዩ ነገሮች ማድረግ ይችላሉ።
ለምሳሌ OTP ኮድ በ SMS ፣ የተለያዩ የሶሻል ሚድያ አካውንት ለመክፈት ይሞክራሉ ማለት ነው ።
ሲማችሁን እስክታዘጉት የፈለጉትን ነገር ሊያደርጉ ይችላሉ።
ለመከላከል ይህንን ዘዴ አድርጉ።
መጀመሪያ ማድረግ ያለባቹ ነገር
📶 SIM PIN ማብራት
ሲማቹ ፒን ኮድ ማስገባት ከዛ ሲሙን ሌላ ቀፎ ላይ ሲገባ ፒን ይጠይቃል።
👉 ይህ በጣም አስፈላጊ ነው
ለማስተካከል ቀጥለው ያሉትን ነገሮች ተግብሩ:- ለ አንድሮይድ

⓵ Settings (ቅንብሮች) ግባ
⓶ Security / Privacy (ደህንነት)
⓷ SIM card Security
⓸ Lock SIM card ማብራት
⓹ SIM PIN አስገባ (4–8 ቁጥር)

📌 SIM ከስልክ ቢወጣም PIN ግድ ያስፈልገዋል ።
አንዱ መከላከያ ይህ ነው ።

🧷 ሌሎች የደህንነት ነጥቦች በሚቀጥለው የምናይ ይሆናል👍

#Ethiopia #Privacy #ደህንነት #cybersecurity #simsecurity #PIN #SMS #Two_Step_Verification


CompuTech©
***
👍2
SIM PIN CODE IN TECHNO

📱 በTecno(HiOS) & Infinx(XOS ) ስልኮች ለማስተካከል

SIM PIN code ለማብራት

1️⃣ Settings
2️⃣ Security
3️⃣ SIM card lock
4️⃣ Lock SIM card አብራ
5️⃣ SIM PIN አስገባ ዲፎልት ፒን 0000 → የማይገመት ፒን ቀይራቹ ማስገባት

🌐 በተጨማሪም
👉 Screen lockቹን ማጠናከር
👉 Fingerprint / Face unlock
በፊት መክፈት ብዙ ግዜ አይመከርም
👉 App permissions /ፍቃዶችን ዘወትር ቼክ አድርጉ

⚠️ ማሳሰቢያ
SIM PIN 3 ጊዜ ከተሳሳታቹ → SIM PUK ይጠይቃል ጥንቃቄ አድርጉ።

በተጨማሪም OTP ኮድ ለማንም አታጋሩ

#ቴክ #PIN #privacy #ደህንነት #ቴክኖሎጂ #ቴክኖሎጂመረጃ #HiOS #tecno #infinx #XOS


CompuTech©
****
👍2
SIM Card ታወር Cellular 🗼🚏 Tower ምን ግኑኙነት አላቸው?

SIM ካርድ ከታወር ጋር ያለው ግንኝነት የስልክ አገልግሎት መሠረት ነው። ታወሮች (Cell Towers) እንደ መስመር መካከለኛ ይሰራሉ፣ SIM ካርድ ያለው ስልክ ከእነዚህ ታወሮች ጋር በሬዲዮ ምልክት ይገናኛል። ይህ ግንኝነት የድምፅ ጥራት፣ የኢንተርኔት ፍጥነት እና የአገልግሎት ስፋትን ይወስናል።

1. SIM ካርድ ምን ያደርጋል?
- መለያ እና ማረጋገጫ: SIM ካርድ የተጠቃሚውን መለያ (IMSI) ይይዛል፣ ይህም በታወር ላይ ያለው መስመር እንዲያውቅ ያደርገዋል።
- አገልግሎት መፍትሄ: የድምፅ ጥራት፣ የSMS እና የዳታ አገልግሎት በSIM ካርድ እና ታወር ግንኝነት ላይ ይመሠረታል።
- አዲስ ቴክኖሎጂ: LTE/4G/5G SIM ካርዶች በታወሮች ላይ ያለው አዲስ መስመር (eNodeB/5G gNodeB) ጋር በቀጥታ ይገናኛሉ።

2. ታወር ምን ያደርጋል?
- መስመር መካከለኛ: ታወር የስልክ ምልክትን ከስልክ ወደ ኔትወርክ እና ከኔትወርክ ወደ ስልክ ይላካል።
- አገልግሎት ስፋት: በታወሮች ብዛት እና ቦታ ላይ የሚመሠረት ነው። በከተሞች ውስጥ ብዙ ታወሮች ስለሚኖሩ አገልግሎት ጥራት ከፍ ነው።
- አዲስ ኃይል መፍትሄ: ኢትዮ ቴሌኮም በፀሐይ ኃይል የሚሰሩ ታወሮችን እየገባ ነው፣ ይህም አረንጓዴ አየርን ይደግፋል።

3. SIM – Tower ግንኝነት የሚሰራበት ደረጃ

1. ስልክ እንዲጠራ: ስልክ የሬዲዮ ምልክት ይልካል።

2. ታወር ምልክትን ይቀበላል: ታወር እንደ መካከለኛ ይሰራ።

3. ኔትወርክ ማረጋገጫ: SIM ካርድ መለያ በኔትወርክ ይረጋገጣል።

4. አገልግሎት ይሰጣል: ድምፅ፣ SMS፣ ዳታ እና ኢንተርኔት ይሰጣል።

4. በአማራጭ ቃል
- SIM ካርድ የተጠቃሚውን መለያ ይይዛል።
- ታወር የምልክት መካከለኛ ነው።
- ኔትወርክ አገልግሎትን ይሰጣል።

#ቴክኖሎጂመረጃ #technews #ሶፍትዌሮች #TechEthiopia #ሳይንስና_ቴክኖሎጂ #TechEthiopia #Network



CompuTech©
**
👍2
🚦 የዱባይ የትራፊክ ስርዓት (Dubai Traffic System)
ዱባይ በዓለም ላይ ከፍተኛ የሆነ ዘመናዊ የትራፊክ ስርዓት አለ። ይህ ስርዓት በቴክኖሎጂ፣ AI (አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ)፣ ካሜራዎች እና ሴንሰሮችን በመጠቀም ይሰራል።
🛣️ ዋና ዋና ስራቸውም
የመንገድ አውታረ መንገዶች
ሰፊ እና በደንብ የተመረጡ
Sheikh Zayed Road, Al Khail Road የሚታወት የዱባይ መንገዶች ናቸው
ዘመናዊ የትራፊክ መብራቶች
በAI የሚቆጣጠሩ
የመኪና ብዛትን ይለያሉ
መንገድ መጨናነቅን ይቀንሳሉ
Salik (የኤሌክትሮኒክ ቶል ስርዓት)
ቶል ጌት የለም
መኪና ሲያልፍ ገንዘብ በራስ-ሰር ይቆረጣል።ቆመን መክፈል የለም
የፍጥነት እና ደንብ ቁጥጥር
ብዙ የፍጥነት ካሜራዎች
ፍጥነት፣ ሬድ ላይት መሻገር ይቆጣጠራሉ
ቅጣት በራስ-ሰር ይላካል፡ ካስፈለገም ቅጣቱ ቤታችን ድረስ ይመጣልናል 🙄ማለት ነው።
የህዝብ ትራንስፖርት
ዱባይ ሜትሮ ያለ ሹፌር
አውቶቡስ፣ ትራም፣ ታክሲ አለ።
⚙️ እንዴት አገልግሎት ይሰጣሉ?
1️⃣ መኪናዎች መንገድ ይገባሉ
2️⃣ ሴንሰሮች እና ካሜራዎች ይመረምራሉ
3️⃣ መብራቶች በራስ-ሰር ይቀየራሉ
4️⃣ ህግ መጣስ ይመዘገባል
5️⃣ ትራፊክ መቆጣጠሪያ ማዕከል ይከታተላል
🎯 ጥቅሞች ✔️ የትራፊክ መጨናነቅ ይቀንሳል
✔️ አደጋ ይቀንሳል
✔️ ጊዜና ነዳጅ ይቆጠባል
✔️ ፈጣን የአደጋ ምላሽ
📢 ቴክኖሎጂ + ህግ = የተስተካከለ ትራፊክ ስርዓት

#Dubai #TrafficSystem #Technology #SmartCity


CompuTech©
~
👍2
CompuTech©️
Photo
አልፋቤት የጎግልን Cloud Security ለማጠናከር Wizን በከፍተኛ ዋጋ ለመግዛት ተስማማ

​አልፋቤት (Alphabet)፣ የጎግልን የዳመና ደህንነት (Cloud Security) አቅም ለማጠናከር ያቀረበው የ32 ቢሊዮን ዶላር የግዢ ስምምነት እውን እየሆነ ነው። ይህ ስምምነት አልፋቤት እ.ኤ.አ. በ2012 ሞቶሮላ ሞቢሊቲን (Motorola Mobility) ለመግዛት አውጥቶት የነበረውን 12.5 ቢሊዮን ዶላር በማለፍ፣ በታሪኩ ከፍተኛው የግዢ ውል ሆኗል።

​እ.ኤ.አ. በ2024 በተደረገው የገንዘብ ማሰባሰብ ሂደት Wiz በ12 ቢሊዮን ዶላር ተገምቶ የነበረ ሲሆን፣ ጎግል በዓመቱ አጋማሽ ላይ የ23 ቢሊዮን ዶላር የግዢ ጥያቄ አቅርቦ ውድቅ ተደርጎበት ነበር። ነገር ግን ጎግል በ2025 መጀመሪያ ላይ የተሻሻለ እና ከፍ ያለ ዋጋ ይዞ የተመለሰ ሲሆን፣ በዚህ አዲስ ስምምነት ውስጥ የህግ እና የቁጥጥር እንቅፋቶች ቢገጥሙ የሚከፈል 3.2 ቢሊዮን ዶላር የውል ማፍረሻ ካሳ (breakup fee) አካቶ አቅርቧል። ይህም ኩባንያቸውን ለአክሲዮን ገበያ (IPO) ለማቅረብ አቅደው የነበሩትን የWiz አመራሮች ሐሳብ ለማስቀየር አስችሏል።

​የWiz መድረክ በAmazon Web Services፣ Microsoft Azure እና Oracle Cloud ባሉ የተለያዩ የደመና አገልግሎቶች ላይ የደህንነት ክትትል እና ታይነትን (Security visibility) ያቀርባል። ጎግልም የWiz ምርቶች በሁሉም ዋና ዋና የደመና መድረኮች ላይ መስራታቸውን እንደሚቀጥሉ ቃል ገብቷል።

​እንደ 'ሲነርጂ ሪሰርች ግሩፕ' (Synergy Research Group) መረጃ፣ በዓለም አቀፍ የደመና መሠረተ ልማት ገበያ ውስጥ ጎግል ክላውድ ከ12–13 በመቶ የሚሆነውን ድርሻ ይይዛል። ይህም 30 በመቶ ድርሻ ካለው ከአማዞን (AWS) እና 20 በመቶ ድርሻ ካለው ከማይክሮሶፍት (Azure) በመቀጠል በሶስተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጠዋል።

** CompuTech© *


#Network #ሳይንስና_ቴክኖሎጂ #ደህንነት #privacy #Google #alphabetinc #googlealphabet #cybersecurity


CompuTech©
*****
🔥2👍1
CompuTech©️
Photo
መጨረሻውን ያሳምረው ያአሏህ


Jemal Ali
Regards !

CompuTech©
👍31
🥰2
CompuTech©️
Photo
💻 የኮምፒውተር Tutorial #4
ስልጠና – ክፍል 4

📝 Microsoft Word ለመጀመሪ ስልጠና Beginner Level

📌 Microsoft Word ምንድነው?
Microsoft Word ዶክመንት ለLetter/ደብዳቤ፣ CV፣ Report፣ Application፣ ዶክመንቶችን ለማዘጋጀት የሚጠቅመን ፕሮግራም ነው።

1. Ms Word አከፋፈት ፒሲያችን ላይ ከተጫነ ቀጥሎ ባሉት መንገዶች እንክፈት

1️⃣ Start Menu ንኩ
2️⃣ "Microsoft Word "ብላቹ ፃፉ-ፈልጉ
3️⃣ Click አድርግ- መክፈት -ባዱ ዶክ መክፈት
***
2. መጻፍ መጀመር

👉 Blank Document ምረጥ
👉 በKeyboard መጻፍ የፈለግነውን መፃፍ
ለምሳሌ:- “My Name is ___”
***

3. ፊደል ለመቀየር Font & Size ላይ

1️⃣ ጽሁፉን ምረጥ (CTRL + A) መንካት
2️⃣ Font ላይ የፈለግነውን መምረጥ ለምሳሌ:- Arial, Times New Roman
3️⃣ Size መቀያየር ለምሳሌ:-12፣14፣ 16…ወዘተ
***

4. Bold, Italic, Underline
B = Bold ፅሁፍ ደመቀ ለማድረግ
I = Italic ፅሁፍ ገደድ ለማድረግ
U = Underline ከፅሁፍ ስር መስመር ለማስገባት
*

5. ዶክመንት ስቶሬጅ ላይ ለማስቀመጥ Save

1️⃣ File → Save As
2️⃣ ቦታ ምረጥ ለምሳሌ Desktop ላይ
3️⃣ ዶክ ስም ማስገባት
4️⃣ Save

Shortcut: Ctrl + S

🎯 ልምምድ
👉 ስምህን ፃፍ
👉 አድራሻህን ፃፍ
👉 ስምህን Bold አድርግ
👉 ፋይሉን Document ላይ Save አድርግ

📢 ክፍል 5 በቅርቡ…
CV እንዴት እንደሚሰራ የምናይ ይሆናል👍

ቻናላችንን ሌሎች ጆይን እንዲያደርጉ ቼር ይደረግ @Compu_tr

#የኮምፒውተርስልጠና
#ComputerTraining #BeginnerComputer
#MicrosoftWord
#ComputerBasics
#ICT
#DigitalSkills
#MiraTech
#TechEducation
#EthiopiaTech #ቴክ #ሶፍትዌሮች #ኢትዮጵያ


CompuTech©
👍2