CompuTech©️
164 subscribers
359 photos
169 videos
28 files
208 links
Tech Update info
Computer and phones Security's
Computer Software Tips
Mobile Application Tips
Tutorial Point


Update " Yourself & Grow Knowledge also the Persons around you "
Download Telegram
⚠️ ማሳሰቢያ
👍2
CompuTech©️
⚠️ ማሳሰቢያ
የሳይበር ደህንነት ከINSA የተሰጠ መረጃ

በዋትሳፕ፣ በቴሌግራም እና በሌሎች የመልዕክት መላላኪያ ፕላትፎርሞች የሚፈጸሙ የሳይበር ጥቃቶችን አስመልክቶ የቀረበ የጥንቃቄ መልዕክት

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ)፤ በሀገራችን የዲጂታል ትስስር መስፋፋትን ተከትሎ በዋትሳፕ (WhatsApp)፣ በቴሌግራም (Telegram) እና በሌሎች የመልዕክት መላላኪያ ፕላትፎርሞች አማካኝነት በዜጎች ላይ የሚሰነዘሩ የሳይበር ጥቃቶችና የማጭበርበር ድርጊቶች በአሳሳቢ ሁኔታ እየጨመሩ መምጣታቸዉን በተለያዩ መንገዶች ማረጋገጥ ችሏል።

በአሁኑ ወቅት በሀገራችን የሚካሄዱ የተለያዩ ሲምፖዚየሞችን፣ ዓለም አቀፍ መድረኮችን እና የኦንላይን ስብሰባዎችን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም፣ የሳይበር ወንጀለኞች የእነዚህን ኩነቶች ስም ለሀሰተኛ ድርጊቶቻቸው መጠቀሚያ እያደረጉት ይገኛሉ።

እነዚህ አካላት የማህበረሰቡን የግል መረጃ ለመስረቅ፣ የባንክ ሂሳቦችን ለመመዝበር እና የዲጂታል ደህንነትን ለማናጋት በተቀናጀ መልኩ እየሰሩ መሆኑን አስተዳደሩ በክትትልና በምርመራ አረጋግጧል።

እነዚህ የሳይበር ጥቃቶች የሚፈጸሙት ማህበረሰቡ ትኩረት የሚሰጣቸውን "ተፈላጊ" እና "ወቅታዊ" የሆኑ ጉዳዮችን መነሻ በማድረግ በተዘረጋ ስልታዊ የማታለያ ዘዴ ነው።

አጭበርባሪዎቹ "ለሲምፖዚየሙ ተሳታፊዎች የተዘጋጀ ነጻ የኢንተርኔት ፓኬጅ"፣ "ልዩ የስራ ቅጥር" ወይም "ይህ የስብሰባ መሳተፊያ ሊንክ ነው፤ ከፍተው ይግቡ" የሚሉ አሳሳችና ማራኪ መልዕክቶችን በማሰራጨት ተጠቃሚዎች በመልዕክቱ ውስጥ የተካተተውን ሊንክ (Link) እንዲጫኑ ያደርጋሉ።

ይህ ድርጊት ተጠቃሚው ሳያውቀው ወደ አጥፊ ተልዕኮ ወዳላቸዉ ድረ-ገጾች እንዲያመራና ለጥቃት ተጋላጭ እንዲሆን የሚያደርግ የመጀመሪያው የወንጀለኞች እርምጃ እንደሆነ አስተዳደሩ ይገልጻል።

ጥቃት አድራሾቹ የአንዳንድ ግለሰቦች የግንዛቤ እጥረትና ትኩረት ማጣት የተነሳ የሚላኩላቸውን ሊንኮችና መልዕክቶች በጥንቃቄ የመመርመር ዕድላቸው አነስተኛ መሆኑን ተከትሎ ወንጀለኞቹ ይህን ሁኔታ እንደ ምቹ አጋጣሚ እየተጠቀሙበት ይገኛሉ።

ይህ አይነቱ ጥቃት ከግለሰቦች መረጃ ስርቆት ባለፈ፣ በእጃቸው የሚገኙ ሚስጥራዊ መረጃዎች በጠላፊዎች እጅ እንዲወድቁ በማድረግ በሀገር ደህንነትና ሉዓላዊነት ላይ ከፍተኛ አደጋ የሚጋርጥ መሆኑን አስተዳደሩ በጥብቅ ያሳስባል።

በዚህም ተጠቃሚዎች የተላከላቸውን ሊንክ ሲጫኑ ወይም የተጠየቁትን መረጃ ሲሞሉ፣ የዋትሳፕ ወይም የቴሌግራም አካውንታቸው ወዲያውኑ በጠላፊዎች ቁጥጥር ስር እንዲዉል ያደርጋል።

ወንጀለኞቹ አንዴ የአንድን ሰው አካውንት ከተቆጣጠሩ በኋላ፣ የተጠለፈውን አካውንት በመጠቀም በተጎጂው ስም ለቅርብ ወዳጅ ዘመዶቹና ለስራ ባልደረቦቹ "ድንገተኛ ችግር አጋጥሞኛል" የሚሉ የሀሰት የገንዘብ ድጋፍ ጥያቄዎችን ይልካሉ።

ይህም ድርጊት በማህበረሰቡ መካከል ያለውን መተማመን ከመሸርሸሩ ባለፈ፣ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ በማጭበርበር እንዲመዘበር በማድረግ መጠነ-ሰፊ የኢኮኖሚና የስነ-ልቦና ጉዳት እያደረሰ ይገኛል።

ከላይ የተጠቀሱና መሰል የሳይበር ደህንነት ስጋቶችን ለመቀነስ፣ የመንግስትና የግል ተቋማት እንዲሁም ማህበረሰቡ ከመቼውም ጊዜ በላይ ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ ኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ያሳስባል።

ከማይታወቁ ወይም ካልተረጋገጡ አድራሻዎች በዋትሳፕ፣ በቴሌግራም እና በሌሎች መድረኮች የሚላኩ ሊንኮችን ካለመክፈት ባለፈ፣ አጠራጣሪ መልዕክቶች ሲደርሱ ወዲያውኑ "Report" እና "Block" በማድረግ የጥቃቱን ስርጭት መግታት ይገባል።

በተጨማሪም ማንኛውንም አይነት ሚስጥራዊ የይለፍ ቃል ወይም በስልክ የሚላክ የማረጋገጫ ኮድ (Verification Code) ለማንም አካል አለመስጠት ለዲጂታል ደህንነታችን ወሳኝ መሆኑን አስተዳደሩ በድጋሚ ያስገነዝባል።

አስተዳደሩ እያንዳንዱ ተጠቃሚ በተለይም ማህበረሰቡ በመተግበሪያዎቹ ላይ የሁለትዮሽ ማረጋገጫ (Two-Step Verification) በአስቸኳይ እንዲተገብር ይመክራል።
ይህ የቴክኖሎጂ የመረጃ ጠላፊዎች የግለሰቦችን አካውንት በቀላሉ እንዳይቆጣጠሩ የሚያደርግ እና ተጨማሪ የደህንነት ቁልፍ የሚፈጥር አስተማማኝ የመከላከያ ዘዴ ነው።

ዜጎች ይህንን ቀላል ግን ውጤታማ የሆነ የደህንነት ጥንቃቄ ተግባራዊ በማድረግ፣ ራሳቸውን በቴክኖሎጂ ከታገዙ የማጭበርበር ድርጊቶች ሊታደጉና የሳይበር ወንጀለኞችን ሴራ ሊያከሽፉ እንደሚገባ ኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ይመክራል።

በመጨረሻም፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እነዚህን የሳይበር ወንጀለኞች በህግ ተጠያቂ ለማድረግ ከሚመለከታቸው የጸጥታና የፍትህ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ ይገኛል።

ማህበረሰቡ ማንኛውም የሳይበር ጥቃት ሙከራ ሲያጋጥመው ወይም አጠራጣሪ እንቅስቃሴዎችን ሲመለከት በነጻ ስልክ መስመር 933 በመደወል ለኢመደአ ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ እናቀርባለን።

የሳይበር ደህንነትን ማስጠበቅ የአንድ ተቋም ብቻ ሳይሆን የሁላችንም የጋራ ሀላፊነት በመሆኑ፣ የቴክኖሎጂ አጠቃቀማችንን በንቃትና በጥንቃቄ በመምራት የሀገራችንን ሰላምና ደህንነት በጋራ እንጠብቅ።
ይለናል።



#cybersecurity #ደህንነት #intelligence #insa #techinfo #Privacy


CompuTech©

🧷🧷🧷
🔥2
በቲክቶክ አዲስ የአሠራር ለውጥ ምክንያት የተጠቃሚዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ማሽቆልቆሉ ተነገረ

ታዋቂው የማህበራዊ ትስስር ገጽ ቲክቶክ (TikTok) በቅርቡ ተግባራዊ ያደረገው የአሠራር ደንብ (Algorithm) ለውጥ፣ በመድረኩ ላይ በሚንቀሳቀሱ የይዘት አዘጋጆች እና ተመልካቾች ዘንድ ከፍተኛ መነጋጋሪያ ሆኗል።

ይህ አዲስ አሠራር በተለይ በኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ ተከታዮች ያላቸውን ታዋቂ ግለሰቦች የቪዲዮ እይታ በከፍተኛ ሁኔታ እንዲቀንስ ማድረጉ የታወቀ ሲሆን፣ መተግበሪያውን ከስልካቸው ላይ የሚያጠፉ (Uninstall) ሰዎች ቁጥርም እስከ 150 በመቶ ማደጉ ተመልክቷል።

ለዚህ የተመልካች ቁጥር መቀነስና የተጠቃሚዎች መስተጋብር መውረድ በዋናነት የተጠቀሰው መድረኩ ረዘም ያሉ ቪዲዮዎችን እና ፍጹም አዲስ (Original) የሆኑ ይዘቶችን ብቻ ቅድሚያ እየሰጠ መሆኑ ነው።

ይህም በቀድሞው መንገድ ይንቀሳቀሱ የነበሩ አካውንቶች የእይታ ቁጥራቸው እንዲያሽቆለቁል ምክንያት ሆኗል።

በተጨማሪም ቲክቶክ የውሸት (Fake) እና ሥራ ያቆሙ አካውንቶችን በብዛት የማጥፋት እርምጃ መውሰዱ በአጠቃላይ የእይታ ቁጥሮች ላይ ተጽዕኖ ማሳረፉ ተገልጿል።

ከመድረኩ የሚገኘው ገቢ መቀነስና የይዘት ውድድሩ መክበድ በርካታ ታዋቂ የይዘት አዘጋጆች መድረኩን እንዲለቁ እያደረጋቸው ሲሆን፣ ይህ ለውጥ በቀጣይ በቲክቶክ ተጠቃሚዎች ብዛት እና በይዘት ጥራት ላይ የሚያመጣው ተፅዕኖ በቅርበት የሚጠበቅ ይሆናል።

#techinfo #TechTips #TechEthiopia #ቴክ


CompuTech©
👍2
የመረጃ መንታፊዎች የዋትሳፕ አካዉንትዎን ለመጥለፍ ምን አይነት ስልቶችን ይጠቀማሉ?

በሀገራችን በአሁኑ ወቅት የሚፈጸሙ የዋትሳፕ ጥቃቶች ከረቀቀ የቴክኖሎጂ ስርቆት ይልቅ፣ የሰዎችን ስነ-ልቦናዊ ክፍተት እና ማህበራዊ ትስስርን መነሻ ያደረጉ ናቸው።

ጠላፊዎች የእኛን ጠንካራ ማህበራዊ መስተጋብር፣ ለሃይማኖታዊ ተቋማት ያለንን ጥልቅ አክብሮት እና ለጋራ ጉዳዮች (ግሩፖች) የምንሰጠውን ከፍተኛ እምነት እንደ ጥቃት መሳሪያ በመጠቀም አካውንታችንን ይዘርፋሉ።

🛑የጥለፋው ሂደት ደረጃ በደረጃ

👉1.ስልክ ቁጥርን ማደን: ጠላፊው መጀመሪያ የእርስዎን ስልክ ቁጥር ከተለያዩ የዋትሳፕ ግሩፖች የተቋም፣ የእቁብ፣ የሃይማኖት፣ የሰፈር ወይም የገበያ ግሩፖች ላይ ያገኛል።

👉2.በእርስዎ ቁጥር አካዉንት የመክፈት እንቅስቃሴ: ጠላፊው በራሱ ስልክ ላይ የዋትሳፕ አፕሊኬሽኑን ከፍቶ የእርስዎን ስልክ ቁጥር ያስገባል። በዚህ ጊዜ ዋትሳፕ ትክክለኛው ባለቤት መሆንዎን ለማረጋገጥ ወደ እርስዎ ስልክ በኤስኤምኤስ (SMS) ባለ 6 አሃዝ ኮድ ይልካል።

👉3. የማታለያ መልእክት: ይህ የጥቃቱ አደገኛ ክፍል ነው። ኮዱ ወደ ስልክዎ እንደደረሰ፣ ጠላፊው በሚከተሉት መንገዶች በማታለል ኮዱን እንዲነግሩት ያደርጋል፦

#የግሩፕ_አድሚን_በመምሰል፦ "ከግሩፑ እንዳትወጣ አሁን የደረሰህን የደህንነት ኮድ ላክልኝ" በማለት ያስፈራራል።

#የቅርብ_ሰው_በመምሰል፦ ቀድሞ የተጠለፈ የጓደኛዎን አካውንት በመጠቀም "በስህተት ወደ አንተ ስልክ ኮድ ልኬያለሁ፣ እባክህ መልስልኝ" ይላል።

#የሽልማት_ድርጅት_በመምሰል፦ "የቴሌ ወይም የባንክ ሽልማት ደርሶዎታል፣ ለማረጋገጥ ኮዱን ይንገሩን" በማለት የሰዉን የማግኘት ጉጉትን እንደ ማታለያ ይጠቀማል።

👉4.አካውንቱን መረከብ: እርስዎ ኮዱን እንደነገሩት ጠላፊው የራሱ ስልክ ላይ ያስገባዋል። በዚህ ቅጽበት የእርስዎ ዋትሳፕ ከስልክዎ ላይ ይዘጋና ወደ ጠላፊው ስልክ ይዛወራል።

👉5.አካውንቱን መቆለፍ: ጠላፊው እንደገባ መጀመሪያ የሚያደርገው Two-Step Verification (ባለ ሁለት ደረጃ ማረጋገጫ) ማብራት ነው። ይህን ካደረገ እርስዎ አካውንትዎን መልሰው ለማግኘት ቢሞክሩ እንኳ ጠላፊው የቆለፈበትን ምስጢራዊ ቁጥር (PIN) ስለማያውቁት በቀላሉ መልሰው ማግኘት አይችሉም።

🚨ማሳሰቢያ!
ዋትሳፕ በኤስኤምኤስ የሚልክላችሁን ማንኛውንም ኮድ ለየትኛውም አካል (ለቤተሰብም ቢሆን) በፍጹም አትስጡ! ዋትሳፕ በማንኛውም ሁኔታ ኮድ እንዲሰጡት በውስጥ መስመር አይጠይቅዎትም።

•CompuTech©
👍2
💻 ሁሉም ሰው ማወቅ ያለባት 5 ወሳኝ የኮምፒዩተር ሾርትከቶች ለ Windows ተጠቃሚዎች

1️⃣ Ctrl + Shift + Esc → Task Manager በፍጥነት ይከፍታል
2️⃣ Win + D → Desktop ያሳያል / ወደነበረበት ይመለሳል
3️⃣ Alt + Tab → ክፍት አፕሊኬሽኖች መካከል ይቀያይራል
4️⃣ Ctrl + C / Ctrl + V → Copy & Paste
5️⃣ Win + L → ኮምፒዩተርዎን በፍጥነት ይቆልፋል🔒 የተጠቃሚ ዩዘር log interface ይወስደናል

ተጨማሪ 👇

Ctrl + Z → የሠሩትን ይመልሳል (Undo)
Ctrl + Y → እንደገና ይመልሳል (Redo)


#windows #keyboardshortcuts #TechTips

CompuTech©
****
👍1
🧑‍💻አጭር Tutorial #1 ክፍል አንድ (ለጀማሪዎች)

💻 ኮምፒዩተር ለማብራት እና ማጥፋት ትክክለኛ መንገድ
1️⃣ ኮምፒዩተር ለማብራት
Power button መጫን
Windows እስኪከፍት መጠበቅ
2️⃣ ኮምፒዩተር ለማጥፋት
Start Menu → Power → Shut down
Power button ብቻ በመጫን አታጥፉ በተደጋጋሚ እንደዚህ የምታደርጉ ከሆነ os ኮራፕት ሊያደርግ ይችላል በተለይ ደግሞ እየሰራቹ ሴቭ ካላደረጋችሁት መልሳቹ አታገኙትም። ስለዚህ እዚህ ላይ መጠንቀቅ ያስፈልጋል።

#Tutorial #computertutorial #Windows

CompuTech©
***
👍2
🧑‍💻 ኮምፒውተር Tutorial #2 ክፍል ሁለት

📁 Folder ለመፍጠር እና File ለማስቀመጥ

1️⃣ Desktop ላይ Right Click
(CTRL+SHIRT + ENTER)
2️⃣ New → Folder
3️⃣ Folder ስም አስገቡ
4️⃣ File መሳብ (Drag) አልያም copy & paste Folder ላይ

📌 ፋይሎችን በትክክል ማደራጀት ኮምፒዩተርን ላይ ፋይሎችን ለመጠቀም ቀላል ያደርግልናል።

#TechTips # Windows #tech #tutorial_point


CompuTech©
~~~~
👍2
Tech fact (የቴክ እውነታ)

ይህን 😲 ያውቁ ኖርዋል?
📌 Google በየቀኑ ከቢልዮን በላይ ፍለጋዎችን ያስተናግዳል
📌 First computer /የመጀመሪያው ኮምፒውተር አንድ ክፍል ቤት ያክል ነበር
📌 Internet መጀመሪያ ለወታደሮች ነበር የተፈጠረው

🤯 ቴክ አስገራሚ ነው! ውዶቼ🥰
ለሌሎች መረጃዎች ሼር & ቻናላችንን ተቀላቀሉን

CompuTech©
****
👍2
PLAYFy_TV_1.5.apk
15.8 MB
PLAYFy TV 1.5
የመጨረሻው አፕዴት 100% safe
🔥1
የሞባይል ኢንተርኔት እንዴት ይሰራል?

የሞባይል ኢንተርኔት እንዴት እንደሚሰራ በቀላሉ በምስል ለማሳየት ሞክረናል

የሞባይል ዳታ ሲበራ ምን እንደሚፈጠር አስበው ያውቃሉ? ከላይ በእጅ የተሳለ ስዕላዊ ዲያግራም ከሲም ካርድዎ እስከ ቅርብ የሞባይል ማማ፣ እስከ ኢንተርኔት ሰርቨሮች እና ወደ ስልክዎ ደረጃ በደረጃ ገልፆታል

🌐 ስልኩ የሬዲዮ ዌቭ ሲግናሎችን ይልካል

🌐 ከዛ ታወሩ (ማማ) ከበይነመረቡ ጋር ያገናኛል

🌐 መረጃ በሰከንዶች ውስጥ ወደ ኋላ ተመልሶ ምላሽ ወደ ዲቫይስ ይሰጣል ማለት ነው

🌐 በ4ጂ/5ጂ የሬዲዮ ሞገዶች በላቀ ሁኔታ ይሰራል

የሞባይል ኔትወርኮች ከበስተጀርባ እንዴት እንደሚሰሩ በቀላሉ ለማሳየት ሞክረናል እናተም እንደተረዳችሁት ተስፋ እናደርጋለን።

#network #mobile #5g #tech


CompuTech©
****
👍2
🧑‍💻ኮምፒውተር Tutorial #3 ክፍል ሶስት

🌐 ኢንተርኔት ለመጠቀም
ኢንተርኔት ማፋለጊያ ወይም Browser ሊኖር ግድ ነው።

1️⃣ Google Chrome / Edge መክፈት (Double click /right click - open
2️⃣ Address bar ላይ የፈለግነውን የዌብ አድራሻ መፃፍ ለምሳሌ: "www.google.com"
3️⃣Google Search 🔎 box ላይ የምትፈልጉትን መፃፍ
4️⃣ ከዛ Enter - ያመጣልንን አድራሻ ማስፈንጠሪያ መክፈት ወይም right click - open in new tab 🖱️ click ማድረግ ይሄም አዲስ Tab ላይ ይከፍትልናል

💡 Chrome ለጀማሪ ቀላል ነው
አልያም Microsoft edge ይሄ ብራውዘር windows OS default የሚጫን ነው። እና በedge መጠቀም እንችላለን።

#tutorial #TechTips #TechTips
#Windows

CompuTech©
**
👍3
👍1🔥1
CompuTech©️
Photo
📁 File Extension ምንድነው?
File Extension ማለት 👉ፋይሉ ምን ዓይነት እንደሆነ ለኮምፒዩተር የሚነግር አጭር ስም ነው።
📌 ብዙ ጊዜ ከፋይሉ ስም በኋላ . (dot) ተከትሎ ይመጣል።
🧠 ለምሳሌ
photo.jpg → ለፎቶ ፋይል
song.mp3 → ድምፅ (ሙዚቃ)
video.mp4 → ለቪዲዮ
document.pdf → ለዶክመንት
👉 .jpg .mp3 .mp4 .pdf የተባሉት File Extensions ናቸው ማለት ነው።
🤔 File Extension ለምን አስፈላጊ ነው?
✔️ ኮምፒዩተር ፋይሎችን  በየ ሶፎትዌሮች  ባህሪ በመለየት እንዲከፍት ያስችለዋል
✔️ ፋይሉ ምን እንደሆነ እንድናውቅ
✔️ ትክክለኛ App እንድንጠቀም
ለምሳሌ፦
.mp3 → Music Player - Window media player ሶፍትዌር ፣ VLC  ..ወዘተ
.jpg → Photo Viewer
.pdf → PDF Reader

⚠️ ማሳሰቢያ
File Extensionን  በrename ብቻ  የፋይሉን ባህሪ መቀየር አንችልም በአፃፃፍ ማለት ነው።
ለምሳሌ: .mp3 → .mp4
ነገር ግን በሶፍትዌር የተለያዩ  ፎርማቶችን ልንቀይራቸው እንችላለን።

💡 በአጭሩ
File Extension = የፋይል መታወቂያ ሲሆን
የኮምፒዩተር “ይህ ፋይል ምንድን ነው?” ብሎ እንዲያውቅ ይረዳዋል 👍

🌐 ሌላ የፋይል ፎርማቶች በሚቀጥለው ፖስታችን የምንዘረዝር ይሆናል።

#techinfo #TechTips #TechEthiopia #Windows #microsoft

CompuTech©
  ****
👍2
CompuTech©️
🏙 Smart City's እንግዲ በዛሬው ፖስታችን ስለ ስማርት ከተማ (Smart City) ነው። 🌆 ስማርት ከተማ (Smart City) ማለት ምንድነው? ስማርት ከተማ ማለት የቴክኖሎጂ መሰረተ-ልማት ፣ መረጀን Data center በመጠቀም፣ የከተማውን አገልግሎቶችን  እንዲሻሻሉ፣ የነዋሪዎችን ሕይወት የተሻለ እንዲሆን፣ እና ከተማውን በመቆጣጠር በተሻለ መልኩ ማህበረሰቡን  በ ቴክኖሎጂ በመታገዝ አገልግሎቶችን…
Smart Police Station in Addis Ababa 🇪🇹

👮‍♂️ "ሰው አልባ" የፖሊስ ጣቢያ በአዲስ አበባ 🇪🇹

​"በአፍሪካ የመጀመሪያው ነው የተባለለት ስማርት የፖሊስ ጣቢያ በቦሌ አገልግሎት ሊጀምር ነው"

#Ethiopia  | ​በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ታሪክ አዲስ ምዕራፍ ተከፍቷል። በቦሌ ክፍለ ከተማ (ቦሌ ድልድይ አካባቢ) ፖሊስን በአካል ማግኘት ሳይጠበቅብዎት፤ በቴክኖሎጂ ብቻ ጉዳይዎን የሚያስፈጽሙበት "ስማርት የፖሊስ ጣቢያ" (Smart Police Station) ለአገልግሎት ዝግጁ ሆኗል።

​የጣቢያው ልዩነቶች ምንድን ናቸው?
ሰው አልባ ነው: በአካል የሚገኝ ፖሊስ የለም፤ በቪዲዮ እና በድምጽ ከዋናው ማዕከል ኦፊሰሮች ጋር በመገናኘት ጉዳይዎን ያስፈጽማሉ።

ብዙ ቋንቋዎች: በአማርኛ፣ ኦሮምኛ፣ ትግርኛ፣ ሱማሊኛ፣ እንግሊዝኛ እና በሌሎችም ቋንቋዎች አገልግሎት ይሰጣል።

ሁለገብ: ከወንጀል ሪፖርት በተጨማሪ እስከ 46 የሚደርሱ የመንግስት አገልግሎቶችን ይሰጣል።

ከሙስና የጸዳ: የሰው ንክኪን ስለሚቀንስ ለሙስና እና ለእንግልት የሚዳርጉ አሰራሮችን ያስቀራል።

​ይህ በቦሌ የተጀመረው የሙከራ ፕሮጀክት በቀጣይ መርካቶ እና መገናኛን ጨምሮ በሌሎችም አካባቢዎች ይስፋፋል ተብሏል።


​ቴክኖሎጂን ለህዝብ ደህንነት!

#technology #techinfo #አዲስመረጃ #TechEthiopia #smartpolice #digitalethiopa
#ሳይንስና_ቴክኖሎጂ

CompuTech©
****
👍2
🔥2
CompuTech©️
Photo
📜 File extensions

ፋይል ፎርማቶች - File Formats ዝርዝር

📁 1) የሰነድ (Document) ፋይሎች
• .doc / .docx → Microsoft Word ሰነድ
• .pdf → PDF ለሰነድ
• .txt → ቀላል ጽሑፍ
• .ppt / .pptx → PowerPoint
• .xls / .xlsx → Excel

🖼 2) የምስል (Image) ፋይሎች
• .jpg / .jpeg → ፎቶ (በብዛት የሚጠቀም)
• .png → Background ያለው ፎቶ
• .gif → እንቅስቃሴ ፎቶ (Animated)
• .bmp → የድሮ ፎቶ
• .webp → ዘመናዊ ፎቶ (ትንሽ መጠን)

🎵 3) የድምፅ (Audio) ፋይሎች
• .mp3 → ሙዚቃ (በጣም የተለመደ)
• .wav → ጥራት ከፍተኛ
• .aac → ዘመናዊ ድምፅ
• .ogg → Open-source audio

🎬 4) የቪዲዮ (Video) ፋይሎች
• .mp4 → ቪዲዮ (በጣም የተለመደ)
• .mkv → HD / 4K ቪዲዮ
• .avi → የድሮ ቪዲዮ
• .mov → Apple video
• .webm → Web video

💻 5) የፕሮግራም (Executable) ፋይሎች
• .exe → Windows program
• .msi → Windows installer
• .apk → Android app
• .app → macOS app

⚠️ ከማይታወቁ-ካልተፈተሹ .exe / .apk ፋይሎች ተጠንቀቁ!

🗜 6)  የተጨፈለቀ/ዚፕ -ፋይሎችን በአንድ ላይ   (Compressed) ፋይሎች
• .zip → Compressed folder
• .rar → Compressed file
• .7z → High compression

🌐 7) የዌብ / ኮዲንግ (Web / Code) ፋይሎች
• .html → Web page
• .css → Website design
• .js → JavaScript
• .php → Web backend
• .json → Data format

🧠 ለአዳዲስ መረጃእና ትምህርታዊ ጉዳዮች ሼር በማድረግ ቻናላችንን join እንዲያደርጉ ይተባበሩን።
👉@compu_te

#TechTips #Ethiopia #አዲስመረጃ #ቴክኖሎጂ #ቴክ #technews #ፋይል #ሶፍትዌሮች

CompuTech©
    ~~~~
👍1🔥1
CompuTech©️
Smart Police Station in Addis Ababa 🇪🇹 👮‍♂️ "ሰው አልባ" የፖሊስ ጣቢያ በአዲስ አበባ 🇪🇹 ​"በአፍሪካ የመጀመሪያው ነው የተባለለት ስማርት የፖሊስ ጣቢያ በቦሌ አገልግሎት ሊጀምር ነው" #Ethiopia  | ​በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ታሪክ አዲስ ምዕራፍ ተከፍቷል። በቦሌ ክፍለ ከተማ (ቦሌ ድልድይ አካባቢ) ፖሊስን በአካል ማግኘት ሳይጠበቅብዎት፤ በቴክኖሎጂ ብቻ ጉዳይዎን የሚያስፈጽሙበት…
"በአዲስ አበባ ቦሌ ሩዋንዳ አካባቢ የተገነባው 'ስማርት ፖሊስ ጣቢያ' (Smart Police Station) እንዴት ነው አገልግሎት የሚሰጠው?

በቅርቡ የሙከራውን ጊዜ አጠናቆ ሥራ የሚጀምረው ይህ ዘመናዊ የፖሊስ ጣቢያ፣ ልክ እንደ ኤቲኤም (ATM) ማሽን ሁሉ ከፖሊስ አባላት ጋር በአካል መገናኘት ሳያስፈልግ የፖሊስ አገልግሎቶችን በራስ-አገልግሎት (Self-service) ለማግኘት ያስችላል።

በማሽኑ ከሚሰጡ አገልግሎቶች መካከልም፦
የወንጀል ጥቆማና አቤቱታ ማቅረብ፦ ማንኛውንም የወንጀል ድርጊት ወይም ጥቆማ በማሽኑ አማካኝነት ለፖሊስ ማድረስ ይቻላል።

የምስክር ወረቀቶች፦ ከወንጀል ነፃ መሆኑን የሚገልጹ የምስክር ወረቀቶችን ለማግኘት።
ክፍያዎችን መፈጸም፦ ልዩ ልዩ የቅጣት ክፍያዎችን ለመፈጸም።

የጠፉ ንብረቶች ሪፖርት፦ ስልክና ጌጣጌጥን ጨምሮ ማንኛውንም የጠፋ ንብረት ለማመልከት ወይም ሪፖርት ለማድረግ፤ እንዲሁም ሪፖርት የተደረገው ንብረት ስለመገኘቱ በዚሁ ማሽን መከታተል ይቻላል።

የቪዲዮ ጥሪ፦ ተጨማሪ መረጃ ካስፈለገ በቪዲዮ ጥሪ በቀጥታ ከፖሊስ አባላት ጋር መገናኘት ያስችላል።

ከዚህም በተጨማሪ ክፍያ የተፈጸመባቸውን ደረሰኞችና የተፈቀዱ ሰነዶችን ለማተም የሚያገለግል ሲሆን፣ ሌሎች አገልግሎቶችንም በውስጡ አካትቷል።

በአፍሪካ የመጀመሪያው የሆነው ይህ ቴክኖሎጂ፣ በአሁኑ ወቅት በቦሌ ሩዋንዳ አካባቢ ተተክሎ አገልግሎት ለመጀመር ጥቂት ቀናት ብቻ ቀርተውታል።"

#techinfo #smartcity #digitalethiopa #ቴክኖሎጂኢትዮጵያ #አዲስመረጃ #smartpolice #sps #ስማርትፓሊስበአዲስአበባ

CompuTech©
***
👍2