CompuTech©️
164 subscribers
360 photos
169 videos
28 files
208 links
Tech Update info
Computer and phones Security's
Computer Software Tips
Mobile Application Tips
Tutorial Point


Update " Yourself & Grow Knowledge also the Persons around you "
Download Telegram
CompuTech©️
Photo
የቅርብ ጊዜ አጫጭር የቴክኖሎጂ ዜናዎች
🚀 የቴክ ዜና | አዲስ
📱 Samsung አዲሱን Galaxy S26 ስማርትፎን በAI የተሻሻለ ካሜራ እና ፍጥነት ሊያሳይ  ነው ተባለ።
⚠️ Microsoft Windows በአዲስ update በአንዳንድ ኮምፒውተሮች ችግኝ ፈጥሯል።
🤖AI በአሁን ሰዐት ቪዲዮ እና ሙዚቃ በቀላሉ በራሱ መፍጠር እየቻለ ነው።
💡 Nano-LED ቴክኖሎጂ አዲስ የዘመነ የስክሪን ጥራት  ሊጀምር ነው።
🎮 Nintendo Switch 2 ዋጋ ሊጨምር ይችላል ተብሏል።
📈 NVIDIA የGPU ዋጋ መጨመር ገበያው ላይ ተጠናክሮ ቀጥሎዋል።

#ኢትዮጵያ #ቴክ #ሳይንስና_ቴክኖሎጂ


CompuTech©
👍1🔥1
💡 የቴክ ምክሮች

🧷 📱 ስልክህን ፈጣን አድርግ – የማትጠቀማቸውን መተግበሪያዎችን ሰርዝ፣ background apps ዝጋ።
🧷 🔋 ባትሪ እንዲቆይ – Location, Bluetooth, Hotspot እየተጠቀምክበት ካልሆነ አጥፋ
🧷 🔐 ደህንነት – 2-Step Verification በTelegram ፣ Gmail ፣ በሌላ ጠቃሚ መተግበሪያ ላይ አብራ።
🧷 ☁️ ፋይል እንዳይጠፋብህ ክላውድ ላይ አስቀምጥ – Photos፣ Files፣ ዶክመንት ።፣ በGoogle Drive ወይም Telegram Saved Messages አስቀምጥ።
🧷 🚀 ኢንተርኔት Browser ላይ cache በየሳምንቱ አጽዳ።

#ቴክ #ሳይንስና_ቴክኖሎጂ #ኢትዮጵያ #Privacy #techinfo

CompuTech©
👍2
🗼በኢራን አብዮታዊው ዘብ ጃም የተደረገው ስታር ሊንክ ኢራናውያንን እየደለለ ነው

MFM| የዓለማችን ቁጥር አንድ ሀብታም ኢላን መስክ ንብረት የሆነው የሳተላይት ኢንተርኔት አቅራቢው ስታርሊንክ፤ ኢራን ውስጥ ከክፍያ ነጻ የሆነ የኢንተርኔት አገልግሎት አቀረበ።

ቢቢሲ የኢራን መንግሥት በአገሪቱ ውስጥ ያለውን የኢንተርኔት አቅርቦት በማቋረጡ ምክንያት በሳተላይት የሚሠራው ለስታርሊንክ ወርሃዊ ክፍያ እየፈጸሙ ይጠቀሙ የነበሩ ኢራናውያን አገልግሎቱን በነጻ እንዲያገኙ ፈቅዷል የሚል ዘገባ ይዞ ወጥቷል።

ከኢራን የሳይበር ተቋማት ጋር እልህ ውስጥ የገባው ኤሎን መስክ ለኢራናውያን ኢንተርኔት በነጻ አቅርቤያለሁ ቢልም የኢራንን የሳይበር ሴኩሪቲ ማለፍ የማይታሰብ ሆኖበታል።

አለም በሳይበር ሴኩሪቲ አቅሙ የሚመጻደቅበት ስታር ሊንክ ኔት ወርክ በተራቀቁት የኢራን ቴክኖሎጂዎች 80 በመቶ ጃም መደረጉን መዘገባችን ይታወሳል።

★ ★ ★
CompuTech©


🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟
👍2
#የቱርክ መከላከያ ኢንዱስትሪ በቴክኖሎጂው ዘርፍ ያለውን የበላይነት የሚያሳይ አዲስ ፈጠራ ይፋ አድርጓል።

«ትራኮን ላይት 134» (Tracon Lite 134) የተሰኘውና ለድሮን መከላከያ ተብሎ የተሰራው ይህ ዘመናዊ መሳሪያ እጅግ ከፍተኛ የሆነ የተኩስ ፍጥነትና ኃይል እንዳለው ተገልጿል። ይህ መተኮሻ በደቂቃ ውስጥ እስከ 3,000 ጥይቶችን የማዝነብ አቅም ያለው ሲሆን ይህም በሰማይ ላይ የሚንቀሳቀሱ ትናንሽና ፈጣን ድሮኖችን በቀላሉ ለመምታት ያስችለዋል።

መሳሪያው ሰው ሳይጠጋው በሩቅ መቆጣጠሪያ (Remote Control) የሚታዘዝ በመሆኑ ወታደሮች ለአደጋ ሳይጋለጡ ጥቃቶችን እንዲመክቱ ይረዳል። በቅርብ ጊዜ በጦርነቶች ላይ ትልቅ ስጋት እየሆኑ የመጡትን "ሰው አልባ አውሮፕላኖች" ለመመከት በልዩ ሁኔታ የተገጠመ የራዳር እና የዒላማ መቆጣጠሪያ ዘዴ አለው።

ቱርክ ይህንን መሳሪያ ይፋ ማድረጓ፣ በዓለም አቀፍ የጦር መሣሪያ ገበያ ላይ ያላትን ተወዳዳሪነት ከፍ የሚያደርገው ሲሆን፣ በተለይም የድሮን ቴክኖሎጂ ስጋት በጨመረበት በዚህ ወቅት ለብዙ አገራት ተመራጭ መከላከያ እንደሚሆን ተገምቷል።


CompuTech©
🔥2
CompuTech©️
Video
😂😂 ስለወደድኩት አጋራዋቹ።
👍1
CompuTech©️
Photo
  የተለመዱ  የኮምፒዩተር ችግሮችን ለማስተካከል የሚረዱ ምክሮች 💻🛠️

💻 የኮምፒዩተር  ማስተካከያ መፍትሔዎች
1️⃣ ኮምፒዩተርህ እየተንቀራፈፈ ከሆነ
ኮምፒዩተሩን እንደገና አስነሳ(restart)
የማትጠቀማቸውን ፕሮግራሞችን ዝጋ(End)
👉Ctrl + Shift + Esc → Processes - right click End task
Startup ፕሮግራሞችን አጥፋ
👉 Ctrl + Shift + Esc → Startup
2️⃣ ኢንተርኔት አይሰራም? 🌐
Router እንደገና አስነሳ
Network adapter አጥፋና እንደገና አብራ
Network Troubleshooter ተጠቀም
3️⃣ ኮምፒዩተርህ እየዘገመብህ  ነው? ❄️
የRAM አጠቃቀም መርምር
ትልቅ ቦታ የያዙ መተግበሪያዎችን ዝጋ
በአንቲ ቫይረስ ስካን አድርግ
4️⃣ Hard disk (Storage) ሞልቷል? 💾
Temporary files ሰርዝ
👉 Win + R → temp → delete
ያልተጠቀሙ ፕሮግራሞችን አስወግድ
5️⃣ ኮምፒዩተር አይነሳም?
የኤሌክትሪክ ገመድ መርምር
ሌላ ሶኬት ላይ ሞክር
USB መሳሪያዎችን አስወግድ
6️⃣ Keyboard / Mouse አይሰራም? ⌨️🖱️
የተሰኩትን ነቅለህ  እንደገና ሰካቸው
ሌላ USB ፖርት ሞክር
Driverህን አዘምን
7️⃣ Blue Screen Death  ሰማያዊ (🟦) ስክሪን ላይ በተደጋጋሚ ይፈጠራል?
ኮምፒዩተሩን እንደገና አስነሳው
Driver አዘምን
አዲስ የተጫነ ሶፍትዌር ካለ አስወግድ
8️⃣ ኮምፒዩተር በጣም ይሞቃል? 🔥
የፋን አካባቢ  አጽዳው
Laptopህን ፋኑ ባለበት በኩል ክፍተት ሳታደርግ አታስቀምጥ
ከቻልክ Cooling pad ገዝተህ ተጠቀም
  ማጠቃለያ  ምክር
Windows እና Drivers ማዘመን = ከፍተኛ ችግሮችን አስቀድመህ ለመከላከል ሞክር


#techinfo #ሳይንስና_ቴክኖሎጂ #TechTips # Windows

CompuTech©
👍1🔥1
የፌስቡክ፣ ኢንስታግራም እና ዋትስአፕ እናት ኩባንያ የሆነው ሜታ (Meta)፣ በሶስቱ ታዋቂ የማህበራዊ ትስስር መተግበሪያዎቹ ላይ የክፍያ ወይም "ፕሪሚየም" የአገልግሎት አማራጮችን ለመሞከር ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ።

ሜታ ጥር 26 ቀን 2026 ለቴክክራንች እንዳረጋገጠው፣ ይህ አዲስ የክፍያ አማራጭ ምርታማነትን፣ የፈጠራ ችሎታን እና አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) አቅምን የሚያጎለብቱ ልዩ አገልግሎቶችን ለተጠቃሚዎች ይከፍታል። ይሁን እንጂ ኩባንያው መደበኛዎቹ እና ዋናዎቹ የአፕሊኬሽኖቹ አገልግሎቶች ለሁሉም ተጠቃሚዎች በነጻ ክፍት ሆነው እንደሚቀጥሉ አረጋግጧል።

ለእያንዳንዱ መተግበሪያ የተለየ የክፍያ ፓኬጅ እንደሚዘጋጅ የተገለጸ ሲሆን፣ ለኢንስታግራም ይለቀቃሉ ተብለው ከሚጠበቁት የ"ፕሪሚየም" ጥቅማ ጥቅሞች መካከል፡-

- ያልተገደበ የተመልካች ዝርዝር፣
- ተመልሰው "ፎሎው" ያላደረጉ ተከታዮችን የመለየት አቅም፣ እና
- የሌሎችን "ስቶሪ" ባለቤቱ ሳያውቅ በድብቅ መመልከት የሚሉት ይገኙበታል።

ሜታ በቅርቡ በ2 ቢሊዮን ዶላር እንደገዛው የሚነገርለትን "ማነስ ኤአይ" እና "ቫይብስ" የተሰኘውን የኤአይ ቪዲዮ መሥሪያ ቴክኖሎጂ በዚሁ የክፍያ አገልግሎት ውስጥ ለማካተት ማቀዱም ተገልጿል።

በተያያዘ ዜና፣ ኤል ፓይስ እንደዘገበው፣ ሜታ በዋትስአፕ ስታተስ እና ቻናሎች ላይ የሚታዩ ማስታወቂያዎችን ለማስቀረት የሚያስችል የክፍያ አማራጭ ላይ እየሰራ መሆኑን ጠቁሟል።
ይህ ሙከራ በሚቀጥሉት ወራት ተግባራዊ መሆን እንደሚጀምር ኩባንያው ገልጿል።
ቴክኖሎጂ መረጃ

አሜሪካ ሚሳኤል ሳተኩስ የኢራንን ራዳር ጥቅም አልባ ማድረግ ትችላለች

የአሜሪካ ጦር ያለምንም ሚሳይል ጥቃት የኢራንን የአየር መከላከያ ራዳሮች እና ሴንሰሮች ሰብሮ በመግባት የማሰናከል እና የመጥለፍ (Hack የማድረግ) ከፍተኛ የቴክኖሎጂ ብቃት እንዳለው ወታደራዊ ተንታኞች ገለጹ።

​እንደ ዘገባዎች ከሆነ፣ አሜሪካ 'Suter' የተባለ ሚስጥራዊ የቴክኖሎጂ ፕሮግራምን በመጠቀም የጠላትን የተቀናጀ የአየር መከላከያ መረብ ሰብራ በመግባት፣ የራዳር ሲግናሎችን የመቆጣጠር አልፎ ተርፎም አሜሪካዊያን የጦር አውሮፕላኖች በራዳር እንዳይታዩ የማድረግ አቅም አላት።

​ከዚህም በተጨማሪ EA-18G Growler የተባሉ የኤሌክትሮኒክ ውጊያ አውሮፕላኖች አዳዲስ የሲግናል ማወኪያ (Jamming) ዘዴዎችን በመጠቀም የኢራንን መከላከያ አይን እና ጆሮ ማሳወር እንደሚችሉ ተጠቁሟል።

ይህም የኢራን ጦር ጥቃት ሳይሰነዘርበት መከላከያው እንዲልቆም ወይም የተሳሳተ መረጃ እንዲያምን ያደርገዋል።

​ይህ የቴክኖሎጂ የበላይነት አሜሪካ በቀጥታ ጦርነት ውስጥ ሳትገባ የኢራንን ወታደራዊ መዋቅር እንድታዳክም ትልቅ እድል እንደሚሰጣት ይታመናል።

​መሰል ወቅታዊ መረጃዎች እንዲደርስዎ ቻናላችንን Follow ያድርጉ፤ ለሌሎችም እንዲደርስ Share ያድርጉልን!

#TechTips #ሳይንስና_ቴክኖሎጂ
#techinfo

CompuTech
👍2
🧷 ሳይበር ቴክ መረጃ

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ የሞባይል ስልካቸው ካሜራዎች ስቲከር /በማጣበቂያ ተሸፍነው ሲጠቀሙ የሚያሳዩ ምስሎች በስፋት ተሰራጭተዋል። ይህ ድርጊት በዋናነት የሚከተሉትን ምክንያቶች ይይዛል፡
                                                                                                                                                                                                     
 👉🏽የደህንነት ጥንቃቄ :- እንደ ጠቅላይ ሚኒስትር ከፍተኛ ሚስጥራዊ የሆኑ ሰነዶች እና መረጃዎች የሚያዙ በመሆኑ፣ ስልኩ ቢጠለፍ እንኳ በካሜራው በኩል ምስል ወይም ቪዲዮ እንዳይቀረጽ ለመከላከል የተወሰደ ጥንቃቄ ነው።

👉🏽የተለመደ አሰራር:- ይህ በስሱ የደህንነት ተቋማት ውስጥ ስልክ ሲገቡ ካሜራዎችን የመሸፈን ወይም የማስ ወገድ (Cam-block) የተለመደ አሰራር አካል ነው።

👉🏽የሰላዮች ስጋት:- በቅርብ ዓመታት የስልክ ቫይ ረሶችን በመጠቀም የሀገር መሪዎች ላይ የስለላ ጥርጣሬዎች መኖራቸው ተዘግቧል፣ ይህም እንደዚህ አይነት ጥንቃቄዎችን አስፈላጊ ያደርገዋል።
                                                                                                                                                             
   ስለዚህ፣ ኔታንያሁ ካሜራቸውን በቴፕ የሸፈኑት ለግል ደህንነት እና ከፍተኛ ሚስጥራዊ መረጃዎችን ለመጠበቅ ተብሎ ነው።


#techinfo #TechTips #TechEthiopia

CompuTech©
👍2
⚠️ ማሳሰቢያ
👍2
CompuTech©️
⚠️ ማሳሰቢያ
የሳይበር ደህንነት ከINSA የተሰጠ መረጃ

በዋትሳፕ፣ በቴሌግራም እና በሌሎች የመልዕክት መላላኪያ ፕላትፎርሞች የሚፈጸሙ የሳይበር ጥቃቶችን አስመልክቶ የቀረበ የጥንቃቄ መልዕክት

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ)፤ በሀገራችን የዲጂታል ትስስር መስፋፋትን ተከትሎ በዋትሳፕ (WhatsApp)፣ በቴሌግራም (Telegram) እና በሌሎች የመልዕክት መላላኪያ ፕላትፎርሞች አማካኝነት በዜጎች ላይ የሚሰነዘሩ የሳይበር ጥቃቶችና የማጭበርበር ድርጊቶች በአሳሳቢ ሁኔታ እየጨመሩ መምጣታቸዉን በተለያዩ መንገዶች ማረጋገጥ ችሏል።

በአሁኑ ወቅት በሀገራችን የሚካሄዱ የተለያዩ ሲምፖዚየሞችን፣ ዓለም አቀፍ መድረኮችን እና የኦንላይን ስብሰባዎችን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም፣ የሳይበር ወንጀለኞች የእነዚህን ኩነቶች ስም ለሀሰተኛ ድርጊቶቻቸው መጠቀሚያ እያደረጉት ይገኛሉ።

እነዚህ አካላት የማህበረሰቡን የግል መረጃ ለመስረቅ፣ የባንክ ሂሳቦችን ለመመዝበር እና የዲጂታል ደህንነትን ለማናጋት በተቀናጀ መልኩ እየሰሩ መሆኑን አስተዳደሩ በክትትልና በምርመራ አረጋግጧል።

እነዚህ የሳይበር ጥቃቶች የሚፈጸሙት ማህበረሰቡ ትኩረት የሚሰጣቸውን "ተፈላጊ" እና "ወቅታዊ" የሆኑ ጉዳዮችን መነሻ በማድረግ በተዘረጋ ስልታዊ የማታለያ ዘዴ ነው።

አጭበርባሪዎቹ "ለሲምፖዚየሙ ተሳታፊዎች የተዘጋጀ ነጻ የኢንተርኔት ፓኬጅ"፣ "ልዩ የስራ ቅጥር" ወይም "ይህ የስብሰባ መሳተፊያ ሊንክ ነው፤ ከፍተው ይግቡ" የሚሉ አሳሳችና ማራኪ መልዕክቶችን በማሰራጨት ተጠቃሚዎች በመልዕክቱ ውስጥ የተካተተውን ሊንክ (Link) እንዲጫኑ ያደርጋሉ።

ይህ ድርጊት ተጠቃሚው ሳያውቀው ወደ አጥፊ ተልዕኮ ወዳላቸዉ ድረ-ገጾች እንዲያመራና ለጥቃት ተጋላጭ እንዲሆን የሚያደርግ የመጀመሪያው የወንጀለኞች እርምጃ እንደሆነ አስተዳደሩ ይገልጻል።

ጥቃት አድራሾቹ የአንዳንድ ግለሰቦች የግንዛቤ እጥረትና ትኩረት ማጣት የተነሳ የሚላኩላቸውን ሊንኮችና መልዕክቶች በጥንቃቄ የመመርመር ዕድላቸው አነስተኛ መሆኑን ተከትሎ ወንጀለኞቹ ይህን ሁኔታ እንደ ምቹ አጋጣሚ እየተጠቀሙበት ይገኛሉ።

ይህ አይነቱ ጥቃት ከግለሰቦች መረጃ ስርቆት ባለፈ፣ በእጃቸው የሚገኙ ሚስጥራዊ መረጃዎች በጠላፊዎች እጅ እንዲወድቁ በማድረግ በሀገር ደህንነትና ሉዓላዊነት ላይ ከፍተኛ አደጋ የሚጋርጥ መሆኑን አስተዳደሩ በጥብቅ ያሳስባል።

በዚህም ተጠቃሚዎች የተላከላቸውን ሊንክ ሲጫኑ ወይም የተጠየቁትን መረጃ ሲሞሉ፣ የዋትሳፕ ወይም የቴሌግራም አካውንታቸው ወዲያውኑ በጠላፊዎች ቁጥጥር ስር እንዲዉል ያደርጋል።

ወንጀለኞቹ አንዴ የአንድን ሰው አካውንት ከተቆጣጠሩ በኋላ፣ የተጠለፈውን አካውንት በመጠቀም በተጎጂው ስም ለቅርብ ወዳጅ ዘመዶቹና ለስራ ባልደረቦቹ "ድንገተኛ ችግር አጋጥሞኛል" የሚሉ የሀሰት የገንዘብ ድጋፍ ጥያቄዎችን ይልካሉ።

ይህም ድርጊት በማህበረሰቡ መካከል ያለውን መተማመን ከመሸርሸሩ ባለፈ፣ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ በማጭበርበር እንዲመዘበር በማድረግ መጠነ-ሰፊ የኢኮኖሚና የስነ-ልቦና ጉዳት እያደረሰ ይገኛል።

ከላይ የተጠቀሱና መሰል የሳይበር ደህንነት ስጋቶችን ለመቀነስ፣ የመንግስትና የግል ተቋማት እንዲሁም ማህበረሰቡ ከመቼውም ጊዜ በላይ ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ ኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ያሳስባል።

ከማይታወቁ ወይም ካልተረጋገጡ አድራሻዎች በዋትሳፕ፣ በቴሌግራም እና በሌሎች መድረኮች የሚላኩ ሊንኮችን ካለመክፈት ባለፈ፣ አጠራጣሪ መልዕክቶች ሲደርሱ ወዲያውኑ "Report" እና "Block" በማድረግ የጥቃቱን ስርጭት መግታት ይገባል።

በተጨማሪም ማንኛውንም አይነት ሚስጥራዊ የይለፍ ቃል ወይም በስልክ የሚላክ የማረጋገጫ ኮድ (Verification Code) ለማንም አካል አለመስጠት ለዲጂታል ደህንነታችን ወሳኝ መሆኑን አስተዳደሩ በድጋሚ ያስገነዝባል።

አስተዳደሩ እያንዳንዱ ተጠቃሚ በተለይም ማህበረሰቡ በመተግበሪያዎቹ ላይ የሁለትዮሽ ማረጋገጫ (Two-Step Verification) በአስቸኳይ እንዲተገብር ይመክራል።
ይህ የቴክኖሎጂ የመረጃ ጠላፊዎች የግለሰቦችን አካውንት በቀላሉ እንዳይቆጣጠሩ የሚያደርግ እና ተጨማሪ የደህንነት ቁልፍ የሚፈጥር አስተማማኝ የመከላከያ ዘዴ ነው።

ዜጎች ይህንን ቀላል ግን ውጤታማ የሆነ የደህንነት ጥንቃቄ ተግባራዊ በማድረግ፣ ራሳቸውን በቴክኖሎጂ ከታገዙ የማጭበርበር ድርጊቶች ሊታደጉና የሳይበር ወንጀለኞችን ሴራ ሊያከሽፉ እንደሚገባ ኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ይመክራል።

በመጨረሻም፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እነዚህን የሳይበር ወንጀለኞች በህግ ተጠያቂ ለማድረግ ከሚመለከታቸው የጸጥታና የፍትህ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ ይገኛል።

ማህበረሰቡ ማንኛውም የሳይበር ጥቃት ሙከራ ሲያጋጥመው ወይም አጠራጣሪ እንቅስቃሴዎችን ሲመለከት በነጻ ስልክ መስመር 933 በመደወል ለኢመደአ ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ እናቀርባለን።

የሳይበር ደህንነትን ማስጠበቅ የአንድ ተቋም ብቻ ሳይሆን የሁላችንም የጋራ ሀላፊነት በመሆኑ፣ የቴክኖሎጂ አጠቃቀማችንን በንቃትና በጥንቃቄ በመምራት የሀገራችንን ሰላምና ደህንነት በጋራ እንጠብቅ።
ይለናል።



#cybersecurity #ደህንነት #intelligence #insa #techinfo #Privacy


CompuTech©

🧷🧷🧷
🔥2
በቲክቶክ አዲስ የአሠራር ለውጥ ምክንያት የተጠቃሚዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ማሽቆልቆሉ ተነገረ

ታዋቂው የማህበራዊ ትስስር ገጽ ቲክቶክ (TikTok) በቅርቡ ተግባራዊ ያደረገው የአሠራር ደንብ (Algorithm) ለውጥ፣ በመድረኩ ላይ በሚንቀሳቀሱ የይዘት አዘጋጆች እና ተመልካቾች ዘንድ ከፍተኛ መነጋጋሪያ ሆኗል።

ይህ አዲስ አሠራር በተለይ በኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ ተከታዮች ያላቸውን ታዋቂ ግለሰቦች የቪዲዮ እይታ በከፍተኛ ሁኔታ እንዲቀንስ ማድረጉ የታወቀ ሲሆን፣ መተግበሪያውን ከስልካቸው ላይ የሚያጠፉ (Uninstall) ሰዎች ቁጥርም እስከ 150 በመቶ ማደጉ ተመልክቷል።

ለዚህ የተመልካች ቁጥር መቀነስና የተጠቃሚዎች መስተጋብር መውረድ በዋናነት የተጠቀሰው መድረኩ ረዘም ያሉ ቪዲዮዎችን እና ፍጹም አዲስ (Original) የሆኑ ይዘቶችን ብቻ ቅድሚያ እየሰጠ መሆኑ ነው።

ይህም በቀድሞው መንገድ ይንቀሳቀሱ የነበሩ አካውንቶች የእይታ ቁጥራቸው እንዲያሽቆለቁል ምክንያት ሆኗል።

በተጨማሪም ቲክቶክ የውሸት (Fake) እና ሥራ ያቆሙ አካውንቶችን በብዛት የማጥፋት እርምጃ መውሰዱ በአጠቃላይ የእይታ ቁጥሮች ላይ ተጽዕኖ ማሳረፉ ተገልጿል።

ከመድረኩ የሚገኘው ገቢ መቀነስና የይዘት ውድድሩ መክበድ በርካታ ታዋቂ የይዘት አዘጋጆች መድረኩን እንዲለቁ እያደረጋቸው ሲሆን፣ ይህ ለውጥ በቀጣይ በቲክቶክ ተጠቃሚዎች ብዛት እና በይዘት ጥራት ላይ የሚያመጣው ተፅዕኖ በቅርበት የሚጠበቅ ይሆናል።

#techinfo #TechTips #TechEthiopia #ቴክ


CompuTech©
👍2
የመረጃ መንታፊዎች የዋትሳፕ አካዉንትዎን ለመጥለፍ ምን አይነት ስልቶችን ይጠቀማሉ?

በሀገራችን በአሁኑ ወቅት የሚፈጸሙ የዋትሳፕ ጥቃቶች ከረቀቀ የቴክኖሎጂ ስርቆት ይልቅ፣ የሰዎችን ስነ-ልቦናዊ ክፍተት እና ማህበራዊ ትስስርን መነሻ ያደረጉ ናቸው።

ጠላፊዎች የእኛን ጠንካራ ማህበራዊ መስተጋብር፣ ለሃይማኖታዊ ተቋማት ያለንን ጥልቅ አክብሮት እና ለጋራ ጉዳዮች (ግሩፖች) የምንሰጠውን ከፍተኛ እምነት እንደ ጥቃት መሳሪያ በመጠቀም አካውንታችንን ይዘርፋሉ።

🛑የጥለፋው ሂደት ደረጃ በደረጃ

👉1.ስልክ ቁጥርን ማደን: ጠላፊው መጀመሪያ የእርስዎን ስልክ ቁጥር ከተለያዩ የዋትሳፕ ግሩፖች የተቋም፣ የእቁብ፣ የሃይማኖት፣ የሰፈር ወይም የገበያ ግሩፖች ላይ ያገኛል።

👉2.በእርስዎ ቁጥር አካዉንት የመክፈት እንቅስቃሴ: ጠላፊው በራሱ ስልክ ላይ የዋትሳፕ አፕሊኬሽኑን ከፍቶ የእርስዎን ስልክ ቁጥር ያስገባል። በዚህ ጊዜ ዋትሳፕ ትክክለኛው ባለቤት መሆንዎን ለማረጋገጥ ወደ እርስዎ ስልክ በኤስኤምኤስ (SMS) ባለ 6 አሃዝ ኮድ ይልካል።

👉3. የማታለያ መልእክት: ይህ የጥቃቱ አደገኛ ክፍል ነው። ኮዱ ወደ ስልክዎ እንደደረሰ፣ ጠላፊው በሚከተሉት መንገዶች በማታለል ኮዱን እንዲነግሩት ያደርጋል፦

#የግሩፕ_አድሚን_በመምሰል፦ "ከግሩፑ እንዳትወጣ አሁን የደረሰህን የደህንነት ኮድ ላክልኝ" በማለት ያስፈራራል።

#የቅርብ_ሰው_በመምሰል፦ ቀድሞ የተጠለፈ የጓደኛዎን አካውንት በመጠቀም "በስህተት ወደ አንተ ስልክ ኮድ ልኬያለሁ፣ እባክህ መልስልኝ" ይላል።

#የሽልማት_ድርጅት_በመምሰል፦ "የቴሌ ወይም የባንክ ሽልማት ደርሶዎታል፣ ለማረጋገጥ ኮዱን ይንገሩን" በማለት የሰዉን የማግኘት ጉጉትን እንደ ማታለያ ይጠቀማል።

👉4.አካውንቱን መረከብ: እርስዎ ኮዱን እንደነገሩት ጠላፊው የራሱ ስልክ ላይ ያስገባዋል። በዚህ ቅጽበት የእርስዎ ዋትሳፕ ከስልክዎ ላይ ይዘጋና ወደ ጠላፊው ስልክ ይዛወራል።

👉5.አካውንቱን መቆለፍ: ጠላፊው እንደገባ መጀመሪያ የሚያደርገው Two-Step Verification (ባለ ሁለት ደረጃ ማረጋገጫ) ማብራት ነው። ይህን ካደረገ እርስዎ አካውንትዎን መልሰው ለማግኘት ቢሞክሩ እንኳ ጠላፊው የቆለፈበትን ምስጢራዊ ቁጥር (PIN) ስለማያውቁት በቀላሉ መልሰው ማግኘት አይችሉም።

🚨ማሳሰቢያ!
ዋትሳፕ በኤስኤምኤስ የሚልክላችሁን ማንኛውንም ኮድ ለየትኛውም አካል (ለቤተሰብም ቢሆን) በፍጹም አትስጡ! ዋትሳፕ በማንኛውም ሁኔታ ኮድ እንዲሰጡት በውስጥ መስመር አይጠይቅዎትም።

•CompuTech©
👍2
💻 ሁሉም ሰው ማወቅ ያለባት 5 ወሳኝ የኮምፒዩተር ሾርትከቶች ለ Windows ተጠቃሚዎች

1️⃣ Ctrl + Shift + Esc → Task Manager በፍጥነት ይከፍታል
2️⃣ Win + D → Desktop ያሳያል / ወደነበረበት ይመለሳል
3️⃣ Alt + Tab → ክፍት አፕሊኬሽኖች መካከል ይቀያይራል
4️⃣ Ctrl + C / Ctrl + V → Copy & Paste
5️⃣ Win + L → ኮምፒዩተርዎን በፍጥነት ይቆልፋል🔒 የተጠቃሚ ዩዘር log interface ይወስደናል

ተጨማሪ 👇

Ctrl + Z → የሠሩትን ይመልሳል (Undo)
Ctrl + Y → እንደገና ይመልሳል (Redo)


#windows #keyboardshortcuts #TechTips

CompuTech©
****
👍1
🧑‍💻አጭር Tutorial #1 ክፍል አንድ (ለጀማሪዎች)

💻 ኮምፒዩተር ለማብራት እና ማጥፋት ትክክለኛ መንገድ
1️⃣ ኮምፒዩተር ለማብራት
Power button መጫን
Windows እስኪከፍት መጠበቅ
2️⃣ ኮምፒዩተር ለማጥፋት
Start Menu → Power → Shut down
Power button ብቻ በመጫን አታጥፉ በተደጋጋሚ እንደዚህ የምታደርጉ ከሆነ os ኮራፕት ሊያደርግ ይችላል በተለይ ደግሞ እየሰራቹ ሴቭ ካላደረጋችሁት መልሳቹ አታገኙትም። ስለዚህ እዚህ ላይ መጠንቀቅ ያስፈልጋል።

#Tutorial #computertutorial #Windows

CompuTech©
***
👍2
🧑‍💻 ኮምፒውተር Tutorial #2 ክፍል ሁለት

📁 Folder ለመፍጠር እና File ለማስቀመጥ

1️⃣ Desktop ላይ Right Click
(CTRL+SHIRT + ENTER)
2️⃣ New → Folder
3️⃣ Folder ስም አስገቡ
4️⃣ File መሳብ (Drag) አልያም copy & paste Folder ላይ

📌 ፋይሎችን በትክክል ማደራጀት ኮምፒዩተርን ላይ ፋይሎችን ለመጠቀም ቀላል ያደርግልናል።

#TechTips # Windows #tech #tutorial_point


CompuTech©
~~~~
👍2
Tech fact (የቴክ እውነታ)

ይህን 😲 ያውቁ ኖርዋል?
📌 Google በየቀኑ ከቢልዮን በላይ ፍለጋዎችን ያስተናግዳል
📌 First computer /የመጀመሪያው ኮምፒውተር አንድ ክፍል ቤት ያክል ነበር
📌 Internet መጀመሪያ ለወታደሮች ነበር የተፈጠረው

🤯 ቴክ አስገራሚ ነው! ውዶቼ🥰
ለሌሎች መረጃዎች ሼር & ቻናላችንን ተቀላቀሉን

CompuTech©
****
👍2