CompuTech©️
164 subscribers
360 photos
169 videos
28 files
208 links
Tech Update info
Computer and phones Security's
Computer Software Tips
Mobile Application Tips
Tutorial Point


Update " Yourself & Grow Knowledge also the Persons around you "
Download Telegram
🔥2
Terabox

☁️ Terabox ምንድን ነው?
Terabox የክላውድ ስቶራጅ /Cloud Storage መተግበሪያ - ሲሆን፣ፋይሎችን ፎቶ፣ ቪዲዮ፣ PDF፣ APK፣ ዶክመንት እናም ሌሎች የመረጃ አይነቶችን በኢንተርኔት መረጃ ማስቀመጥ እና ለመጠበቅ ያግዛል።
ዋና ዋና አገልግሎትም
1TB -1024GB ነፃ ስቶራጅ
Android - iOS / Web ለ PC ላይ መጠቀም ያስችለናል
ፋይልን ለShare ወይም ለማጋራት Link መፍጠር ያስችላል በቀላሉ ማግኘት ያስችለናል
Backup Auto /በእራሱ upload
Online Video Preview
Download Resume እየወረደ ያለ ፋይል ተቋርጦ ከነበረ መቀጠል ይችላል
📲 Terabox እንዴት መጠቀም ይቻላል?
1️⃣ Play Store /App Store ያውርዱ
ወይም ለፒሲ ከኦፊሻል ዌብሳይት ማውረድ አልያም በዌብ አድራሻው አማካኝነት ልናገኘው እንችላለን።
2️⃣ በGoogle አካውንት ወይም በ Email አድራሻቹ ተመዝገቡ
3️⃣ ከዛ 1TB ነፃ ስቶራጅ ያገኛሉ
4️⃣ Upload → Share Link → በፈለጉት ቦታ  ላይ ማጋራት ይችላሉ
በኢንተርኔት አማካኝነት መረጃዎን ተደራሽ መሆን ትችላላቹ
📤 Terabox ለ ተለያዩ ፕላትፎርሞች ምን ይጠቅማል?
🔹 ትልቅ ፋይሎች እንደ Movies፣ Apps፣ Coursesች ለማጋራት
🔹 ፕላትፎርሞች ላይ የፋይል መጠን ገደብን መሻገር ሊኖር ስለሚችል ቴራ በጣም ጠቃሚ ነው
🔹 አንድ የማጋራት Link → ለብዙ ተጠቃሚዎች ተደራሽ በመሆኑ 
🔐 ደህንነት ለጥንቃቄ
🔹 Account Login በPassword ይጠበቃል
🔹 Private / Public Share መምረጥ ይቻላል
🔹የ ማጋሪያ Link ብቻ ያላቸው ሰዎች ጋር ተደራሽ ይሆናል
⚠️ በጣም አስፈላጊ የግል መረጃ መጫን አይመከርም በተለይ የባንክ መረጃ ፣ የይለፍ ቃሎችን አትጫኑ
⚠️  ደካማ ጎኑ
ነፃ Version ላይ Ads አሉ
Download Speed ዝቅተኛ ሊሆን ይችላል
ሙሉ Speed ለPremium ብቻ
💰 በPremium አገልግሎት ምን ተካቷል ?
✔️ ከፍተኛ Download Speed
✔️ Ads የለም
✔️ Large File Fast Download
📌 Terabox ለማን ይመከራል?
✔️ ብዙ ፋይሎችን ለሚጠቀሙ ተጠቃሚዎች
✔️ የስልካችሁን Storage ነፃ ለማድረግ ጠቃሚ
✔️ መረጃን Backup ለመያዝ ለሚፈልጉም እጅግ ጠቃሚ
✔️ ነፃ 1TB ለሚፈልጉ
📝 በአጠቃላይ
Terabox ቀላል፣ ነፃ እና ትልቅ ስቶራጅ የሚሰጥ ክላውድ አገልግሎት ነው።
ለBackup እና File Sharing በጣም ጠቃሚ ነው።

#terabox #tech #TechTips #ቴክ #TechEthiopia #phonetips

CompuTech©
👍2
👍2
FRP by pass
🔥2
👍2
CompuTech©️
Photo
Starlink Internet

ያው ስታርሊንክ ሲባል ሰምታችኋል ብዬ አስባለሁ እስቲ ምን እንደሆነ ለማየት እንሞክር:-
🌍 Starlink የኢንተርኔት አገልግሎት ሲሆን – ፈጣን ኢንተርኔት እና በማንኛውም ቦታ! 🚀 ልናገኘው እንችላለን።
Starlink የSpaceX ሲሆን ይሄም ተቋም የElon Musk እንደሆነ ይታወቃል።
ይህ አገልግሎት የሳተላይት ኢንተርኔት አገልግሎት ሲሆን፣ በከተማም ሆነ በገጠር አካባቢዎች ፈጣን የኢንተርኔት አገልግሎት ያቀርባል።
Starlink ለምን ይመረጣል?
ፋይበር ወይም የሞባይል ኔትወርክ አያስፈልግም
ራቅ ያለ ወይም በገጠር አካባቢ ይሰራል
ፍጥነት፡ 50–200+ Mbps
በተለይ ለስትሪሚንግ   በጣም ተስማሚ
ቀላል አሰራር
ዲሽ + ራውተር
📡 እንዴት ይሰራል? Starlink ለመሬት ያለው ርቀት ቅርብ ሲሆን በታችኛው ኦርቢት ያሉ በሺዎች የሚቆጠሩ የሳተላይት መረቦችን በመጠቀም ኢንተርኔትን ቀጥታ ወደ መሬት  ያደርሳል።
💡 ለገጠራማ አካባቢዎች በተለይ አስፈላጊ ነው
• የይዘት ፈጣሪዎች
• ኢንተርኔት የፋይበር ወይም የ Cellular ዳታ ኔትዎርክ ተደራሽ የማይሆንበት ቦታ አሪፍ አማራጭ  ነው::
⚠️ ማሳሰቢያ
አገልግሎቱ በአገር ፈቃድ አሰጣጥ ይወሰናል። የመሳሪያ እና ወርሃዊ ክፍያ አለው።
ኢትዮጵያ ላይ ፍቃድ የለውም።
📢 በሁሉም ቦታዎች ላይ Starlink ይሰራል !

🔔 ለቴክኖሎጂ እና ለወቅታዊ መረጃዎች  ቻናላችንን ይከታተሉ!

#TechEthiopia #TechTips #ቴክ #starlink #spacex

CompuTech©
👍2
🏷 App Permissions (ፍቃዶች)

የአንድ አፕሊኬሽን ስትጭኑ የሚጠይቃቹህን ፍቃድ ወይም Permission አስተውላቹህ ታውቃላችሁ?

"Least Privilege" / የፍቃድ ደረጃ የመስጠት መርህ። ይህ ማለት አንድ ሶፍትዌር ስራውን ለመስራት የግድ የሚያስፈልገውን ፍቃድ ብቻ ማግኘት አለበት ማለት ነው።አንድ አፕሊኬሽን ከስራው ጋር የማይገናኙ ፍቃዶችን ሲጠይቅ የዳታ ስርቆት Data Mining፣ ስለላ /Spying፣ ማጭበርበር /Fraud/ ስጋቶች ሊኖሩ ይችላሉ፡
 
ለምሳሌ፡ አንድ የ"Calculator" /ካልኩሌተር አፕ የ"Contact" የስልክ ቁጥር ወይም የ"Location" የቦታ ፍቃድ ቢጠይቅ፥ ካልኩሌተር ቁጥር ለመደመር የሰውን ስልክ ቁጥር ማየት አያስፈልገውም ስለዚህ እንደዚህ አይነት አፖችን በፍጹም አትጫኑ። ከጠቀሜታቸው ጋር የማይገናኝ ከሆነ ተውት።
app permission ሲጠይቅ ሁኔታውን ማየት አለባችሁ።

#tech
#privacy
#DataProtection
#cybersecurity
#techinfo

CompuTech©
👍2
🏷 ይወቁት
Lawrence Edward Page
ላውረንስ ኤድዋርድ ፔጅ
እ.ኤ.አ. መጋቢት 26፣ 1973 ተወለደ ከሰርጌይ ብሪን ጋር Google (ጉግልን) በጋራ መሠረቱ አሜሪካዊ ነጋዴ እና የኮምፒውተር ሳይንቲስት ነው።
ፔጅ ቢሊየነር ነው። እና በዓለም ላይ ካሉት እጅግ ባለጸጎች መካከል አንዱ ነው።
እንደ ፎርብስ ዘገባ፣ እ.ኤ.አ. እስከ ጥር 2026 ድረስ የፔጅ የተጣራ ሀብት 269 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ደርሷል፣ ይህም በዓለም ላይ ሁለተኛው ባለጸጋ ሰው ያደርገዋል።

CompuTech©
🔥2
የቴክኖሎጂ እና የጂኦፖለቲካ ትስስር፣የስታርሊንክ "የማይደፈር" ምሽግ መፍረስ እና የሶስቱ ሀገራት የቴክኖሎጂ ጦርነት

ለዓመታት በቴክኖሎጂው ዓለም አንድ የጋራ እምነት (Consensus) ነበር፤ ይኸውም "LEO satellites are unjammable" የሚል ነው። የስታርሊንክ ሳተላይቶች በፍጥነት ስለሚንቀሳቀሱ እና ፍሪኩዌንሲያቸውን ስለሚቀያይሩ፣ ማፈን አይቻልም ተብሎ ይታመን ነበር። ዋል ስትሪትም ቢሆን ይህንን Business Model "Immune to jamming" አድርጎ ነበር የወሰደው። ነገር ግን በቴህራን ሰማይ ላይ የተከሰተው ነገር ይህንን እምነት ሙሉ በሙሉ ገልብጦታል። አንድ ለ20 ዓመታት የኢራንን ኢንተርኔት ሲከታተል የኖረ ባለሙያ "I have never seen such a thing in my life" እስኪል ድረስ፣ ስታርሊንክ አስደንጋጭ የሆነ 80% Packet loss አስተናግዷል። የዚህ ኦፕሬሽን ምስጢር የአንድ ሀገር አቅም ሳይሆን፣ የሶስት ኃያላን ሀገራት የተቀናጀ ሴራ ውጤት ነው። ነገሩ በአጭሩ ሲቀመጥ፡ Russia supplied the hardware, China published the playbook, and Iran just proved it works.
በዩክሬን ጦርነት ወቅት፣ ሩሲያ ስታርሊንክን ለማፈን ስትሞክር ኢሎን ማስክ በ Software patch ብቻ ነበር ያከሸፈው።

አሁን ኢራን ውስጥ እየሆነ ያለው ግን Software issue አይደለም። This is purely HARDWARE. ሩሲያ እስከ 5,000 ኪሎ ሜትር የሚሸፍኑ እንደ Murmansk-BN እና Krasukha-4 ያሉ ግዙፍ የኤሌክትሮኒክስ ጃመሮችን በ IL-76 transports አጓጉዛ ለኢራን አስረክባለች። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ቻይና ከሁለት ወራት በፊት ስታርሊንክን በታይዋን ላይ እንዴት ማጨለም (Black out) እንደሚቻል አንድ ጥናት አውጥታ ነበር። ጥናቱ 935 Ground-based jammers በመጠቀም Ku-band frequencies እንዴት እንደሚዘጉ የሚያሳይ ነው። ቴህራን ለዚህ ቲዎሪ Field test ሆናለች። ውጤቱም፣ 40,000 የሚጠጉ ተርሚናሎች Near-total degradation ደርሶባቸዋል።

ይህ ጉዳይ የኢራንን ተቃውሞ ከማፈን ያለፈ ሰፊ ትርጉም አለው። ይህ The authoritarian electronic warfare axis ጽንሰ-ሀሳቡን (Concept) በተግባር ያረጋገጠበት ክስተት ነው። ገበያው "አይኖርም" ብሎ የገመተውን አደጋ (Risk) አሁን በ280 ቢሊዮን ዶላር የሳተላይት ገበያ ላይ Repricing እያደረገው ነው። በዚህም ምክንያት Defense stocks are about to enter a new cycle. አገዛዙ Starlink dish ይዞ የተገኘን ሰው "Enemy of God" እያለ በሚቀጣበት በዚህ ሰዓት፣ ቤጂንግ ውስጥ የተቀመጠ አንድ አካል፣ ኢራን ውስጥ የሰራውን ስልት ለነገዋ ታይዋን በደንብ እየመዘገበ (Taking detailed notes) እንደሆነ መገመት አያዳግትም።
2
የአልፋቤትን (Google) አስደናቂ ትንሳኤ እና የ 4 ትሪሊዮን ዶላር ታሪክ፡ የሲሊኮን ቫሊ አዲሱ ንጉስ

በቴክኖሎጂው ዓለም ሰኞ ዕለት የተመዘገበው ታሪክ ቀላል አልነበረም። የጉግል እናት ኩባንያ የሆነው አልፋቤት (Alphabet)፣ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የገበያ ዋጋው (Market Valuation) 4 ትሪሊዮን ዶላር ($4 Trillion) የሚለውን አስማታዊ ቁጥር በመንካት፣ የፋይናንስ ዓለምን ጉድ አሰኝቷል። ይህ ክስተት ዝም ብሎ የተፈጠረ የቁጥሮች ጨዋታ ሳይሆን፣ ኩባንያው ከጥቂት ጊዜያት በፊት ገብቶበት ከነበረው የጥርጣሬ ደመና እንዴት እንደወጣ የሚያሳይ ህያው ምስክር ነው።

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ፣ "ጉግል በ Artificial Intelligence ውድድር ወደኋላ ቀረ?" ወይም "የ OpenAI እና ማይክሮሶፍት ጥምረት ጉግልን ከገበያ ሊያወጣው ነው?" የሚሉ ስጋቶች እና ጥርጣሬዎች (Doubts about its strategy) በኢንቨስተሮች ዘንድ ሰፍኖ ነበር። ብዙዎች የጉግልን Search Engine የበላይነት የሚያከትምለት ጊዜ የመጣ መስሏቸው ነበር። ነገር ግን፣ አልፋቤት ይህንን ስጋት ወደ እድል ቀየረው። ኩባንያው ስልቱን በፍጥነት በማስተካከል እና ትኩረቱን ሙሉ በሙሉ ወደ AI በማዞር (Sharpened artificial intelligence focus)፣ የጠፋውን መተማመን መልሶ መገንባት ቻለ።

ይህ አዲስ ስትራቴጂ ውጤቱ በግልጽ ታይቷል። የ Gemini ሞዴሎች መጠናከር እና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እንደ አፕል ካሉ ግዙፎች ጋር የተደረጉ ስትራቴጂካዊ እንቅስቃሴዎች፣ አልፋቤትን እንደገና ወደ ቴክኖሎጂው ሩጫ ግንባር ቀደምነት (Thrust it back to the forefront) መልሰውታል። አሁን ላይ ውድድሩ ቀላል አይደለም፤ High-stakes race ነው። ነገር ግን ጉግል በ Cloud፣ በ Search እና በ Generative AI ላይ እያሳየ ያለው ብቃት፣ ባለሀብቶች በኩባንያው ላይ ያላቸውን እምነት እንዲያድሱ እና የኩባንያውን ዋጋ ወደ ታሪካዊ ጣራ እንዲሰቅሉት ምክንያት ሆኗል። ይህ የ 4 ትሪሊዮን ዶላር ድል፣ ጉግል አሁንም የቴክኖሎጂው ዓለም "Heavyweight Champion" መሆኑን ያረጋገጠበት ቅጽበት ነው።
👍1
የዓለማችን የቴክኖሎጂ "ሞተር" TSMC ሪከርድ የሰበረ ትርፍ አስመዘገበ!

ለዘመናዊው አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ቴክኖሎጂ ወሳኝ የሆኑ "ቺፖችን" በማምረት የዓለማችን ቁጥር አንድ የሆነው የታይዋኑ TSMC፣ በገበያ ግምቶች ላይ አናት ላይ መቀመጡን ቀጥሏል።

ኩባንያው ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት፣ በተጠናቀቀው የ4ኛ ሩብ ዓመት ብቻ ትርፉን በ35% በማሳደግ አዲስ የገቢ ሪከርድ ማስመዝገብ ችሏል። ይህ አፈጻጸም ተንታኞች ከሰጡት ግምት እጅግ የላቀ እና ግዙፍ ስኬት ነው።

TSMC በዚህ ብቻ አላበቃም፤ የዘንድሮው ዓመትም ጠንካራ የዕድገት ዓመት እንደሚሆን ትንበያውን አስቀምጧል። ከዚህም ባሻገር፣ ኩባንያው በአሜሪካ ምድር ተጨማሪ የማምረቻ ተቋማትን ለመገንባት እና የማምረት አቅሙን ለማስፋት እየሰራ መሆኑንም ጠቁሟል።

ምንጭ፡ Reuters
ትኩስ መረጃ


CompuTech©
ቻይና የመጀሪያውን የፖሊስ የኤሌክትሪክ ሄሊኮፕተር (eVTOL) ይፋ አደረገች
******

ቻይና ለፖሊስ አገልግሎት የሚውል የመጀመሪያው ሁለት ሰዎች የመጫን አቅም ያለው የኤሌክትሪክ ሄሊኮፕተር የተሳካ የሙከራ በረራ ማካሄድ መቻሏን አስታውቃለች።

በደቡባዊ ቻይና ጓንዡ ከተማ በተደረገው የሙከራ በረራ በቀጥታ መነሳት እና ማረፍ እንደሚችል የታየው ቴክኖሎጂው (eVTOL) ከሄሊኮፕተር፣ አውሮፕላን እና ድሮን በተወሰደ ንድፈ-ሃሳብ የተሻለ ተደርጎ በኢ-ሀንግ ኩባንያ የተመረተ ነው።

በቀጥታ መነሳት እና ወደ ግዳጁ በማቅናት በፈለገው ቦታ ማረፍ የሚችለው የኢቪቶል ቴክኖሎጂው 650 ኪሎ ግራም ጭነትን የመያዝ አቅም አለው። የኤሌክትሪክ ሄሊኮብተሩ በአንድ ግዜ ቻርጅ 30 ኪሎ ሜትር መጓዝ የሚችል ነውም ተብሏል።

ከአረንጓዴ ኢኮኖሚ ጋር የተጣጣመ ሲሆን በግዳጅ ወቅት ለሚዘውረው ሰው ቀለል ያለ የአጠቃቀም ሲስተም የተገጠመለት እና ባሉት የአማራጭ ሞተሮች አማካኝነት ደህንነቱ አስተማማኝ የሆነ ነው።

ችግሮች ሲፈጠሩ ፖሊስ ያለምንም የትራፊክ መጨናነቅ ወደ ቦታው በደቂቃዎች ውስጥ መድረስ የሚያስችል ቴክኖሎጂ ሲሆን በበረራ ወቅት የሚረብሽ ድምፅ እንዳያወጣ ተደርጎ የተሰራ ነው።

የሙከራ በረራውን ተከትሎ በአየር ላይ ለሚካሄድ የህግ ማስከበር ጅማሮ እንደሚሆን የተገለፀ ሲሆን በተለይም ለፖሊሶች አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጡ እና የፀጥታ ክትትላቸውን ለማጎልበት የሚያስችል እንደሚሆን ተስፋ ተጥሎበታል።

ምንጭ #EBC

CompuTech©