CompuTech©️
164 subscribers
360 photos
169 videos
28 files
208 links
Tech Update info
Computer and phones Security's
Computer Software Tips
Mobile Application Tips
Tutorial Point


Update " Yourself & Grow Knowledge also the Persons around you "
Download Telegram
👍2
🏙 Smart City's

እንግዲ በዛሬው ፖስታችን ስለ ስማርት ከተማ (Smart City) ነው።
🌆 ስማርት ከተማ (Smart City) ማለት ምንድነው?
ስማርት ከተማ ማለት የቴክኖሎጂ መሰረተ-ልማት ፣ መረጀን Data center በመጠቀም፣ የከተማውን አገልግሎቶችን  እንዲሻሻሉ፣ የነዋሪዎችን ሕይወት የተሻለ እንዲሆን፣ እና ከተማውን በመቆጣጠር በተሻለ መልኩ ማህበረሰቡን  በ ቴክኖሎጂ በመታገዝ አገልግሎቶችን የሚሰጡ  ከተሞች ናቸው ።
ለስማርት ከተሞች ዋና እስፈላጊ IoT ነው ።
IoT ማለት Internet of Things –  ነገሮችን ሁሉ ከ ኢንተርኔት ጋር ማገናኘት ሲሆን  ለስማርት ከተማ ግንኙነት IoT በጣም አስፈላጊ ነው።

🔹 የስማርት ሲቲ አገልግሎትቶች:-

1️⃣ ስማርት ትራንስፖርት – ትራፊክን በራሱ የሚቆጣጠር መብራት፣ ኤሌክትሪክ ባሶች እና የመኪኖች መቆጣጠሪያዎች፣   መቆለፊያ መተግበሪያዎች ፣ የIoT ሴንሰሮችን በመጠቀም።
2️⃣ ስማርት ኃይል – የስማርት የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት እና የSolar Energy ፣  የስማርት መለኪያዎች እና መቆጣጠሪያዎች ።
3️⃣ ስማርት መንግሥታዊ አገልግሎት – ኢ-አገልግሎቶች እንደ ኢ-ታክስ፣ ኢ-ፍቃድ፣ ኢ-ክፍያ ወዘተ።
4️⃣ ስማርት የውሃ ማጣሪያ - የስማርት የውሃ አቅርቦት
በቤት ውስጥ ቆሻሻ ካለው ራሱ የሚያሳውቅ፣ በ IoT ሴንሰር በመታገዝ የውሃ ፍሳሽ የሚጠብቅ የሚያሳውቅ።
5️⃣ ስማርት የህክምና አገልግሎት – ቴሌሜዲሲን የስማርት የጤና አገልግሎት በቴክኖሎጂ የታገዘ ህክምና መስጠት  በጤና አገልግሎት ዘርፍ እገዛ ማድረግ።
6️⃣ ስማርት ደህንነት – በAI የሚተገበሩ CCTV ካሜራዎች፣ አደጋዎችን የሚያሳውቅ እና የድንገተኛ ጥሪ ስርዓት።
7️⃣ ስማርት ትምህርት – ዲጂታል ክፍሎች፣ የመማር መተግበሪያዎች ወዘተ።

🌍 በአለም ላይ የታወቁ የስማርት ከተሞች:

🏙️ 1. ሲንጋፖር (Singapore) – ትራፊክን በቀጥታ የሚቆጣጠር ስርዓት እና ንጹህ አካባቢ በአብዛኛው በቴክኖሎጂ የታገዘች ከተማ ነች ።
🏙️ 2. ዱባይ ፣ዩናይትድ አረብ ኤመረት ፡– በተለይ የመንግሥት አገልግሎቶች ሁሉ በሴንሰር እና  በመተግበሪያ ቁጥጥር  የሚደረግበት ከተማ።
🏙️ 3. ባርሴሎና ፣ ስፔን – የመንገድ መብራቶችን በሰው መንቀሳቀስ የሚቀነስ ሴንሰር እና ሌሎች የስማርት ቴክኖሎጂ አገልግሎቶች ።
🏙️ 4. ቶክዮ፣ ጃፓን – የድንገተኛ አደጋ አስተዳደር እና ከፍተኛ ቴክኖሎጂ ትራንስፖርት የተተገበረበት ከተማ።
🏙️ 5. ኒውዮርክ ፣ አሜሪካ – የስማርት መንግሥት ፕሮጀክቶችን በቴክኖሎጂ መሰረት የሚከታተል።

🇪🇹 በኢትዮጵያ – አዲስ አበባ ከተማ  እንዴት የስማርት ከተማ ሊሆን ይችላል?
ያው ከተማችን ባለፉት ጊዜያቶች በተወሰነ ደረጃ  ስማርት ለማድረግ
እየጣረች ትገኛለች እናም ከዚህ ቀጥሎ ያሉትን የስማርት ሲቲ  አገልግሎቶች በከተማዋ እየተተገበረ ይገኛል።
የተሰሩ እና ወደፊት ልትሰራቸው የታቀዱ የቴክኖሎጂ ግልጋሎቶች አሉ።
እነሱም፡
-
• በመንገዶች እና በመኪኖች ላይ የትራፊክ ሴንሰሮች
• የውሃ እና የኤሌክትሪክ ኃይልን  የስማርት መለኪያ መቆጣጠሪያ
• የመንግሥት አገልግሎቶች online ማድረግ፣ (e-services)
• ኢ-ትራንስፖርት እና የኤሌክትሪክ ባሶች
• በAi የታገዘ የደህንነት ቁጥጥሮች
• በማዕከላዊ መንገዶች  ላይ የ ኤሌክትሪክ መኪኖች ቻርጀር እና የነፃ Wi-Fi አገልግሎት
• የስማርት የውሃ እንቅስቃሴ አገልግሎት
እና ሌሎች አገልግሎቶች

🚀 “አዲስ አበባ የ 2030 Smart City” ዕቅድ
• ኤሌክትሪክ ባሶች
• የኤሌክትሮኒክ መንግስታዊ አገልግሎት
• የአየር ጥራት ክትትል
• ንጹህ ከተማ ወዘተ..

📊 እነዚህ የስማርት ከተሞች  ተመሳሳይ አገልግሎቶች እና ዓላማዎች አላቸው፦

🧷 የህዝብን ሕይወት መሻሻል

🧷 ትራፊክ  እንቅስቃሴዎች መቀነስ

🧷 ንጹህ አካባቢ እና የኤነርጂ ተደራሽነት

🧷 የመንግሥት አገልግሎትን በቴክኖሎጂ ማቀናበር ወዘተ

💬 በአጠቃላይ ፦
“ስማርት ከተማን መፍጠር የመንግሥት ሥራ ብቻ አይደለም፣
የዜጎችም ተሳትፎ እና ተግባር አስፈላጊ ነው።”

#technology #smarycity #ቴክ
#ቴክኖሎጂ #TechEthiopia #TechTips

CompuTech©
👍2
👏2
CompuTech©️
Photo
🤖 AI — Artificial Intelligence-ሰው ሰራሽ አስተውሎት
የዛሬው አለም ላይ በቴክኖሎጂው በፍጥነት እየተሻሻለ ነው፣ ከቴክኖሎጂ ውስጥም አንዱ AI -አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እጅግ ትልቅ ሚና እያጫወተ ይገኛል።
AI ማለት መሣሪያዎች እንደ ሰው እንዲያስቡ፣ እንዲማሩ፣ እንዲገመቱ የሚያደርግ  ብልህ ቴክኖሎጂ ነው።
ይህ ቴክኖሎጂ በተለያዩ ስራዎች ላይ በማበር ግንዛቤ በመጨመር ስራን እንዲቀላጠፍ እና ውጤት እንዲሻሻል በጣም ተጠቃሚ እየሆነ ይገኛል።

👉 በመቀጠልም የAI ምንነት ፣ አስተዋጽኦዎች፣ ዋና ጥቅሞችን እና ተግባራዊ ምሳሌዎችን እንመለከታለን።
👍3
👍3
Artificial Intelligence (Ai) 🤖

AI ምንድን ነው? — አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ
AI (Artificial Intelligence) ወይም አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ማለት፣
(AI) የሰው ልጅ የማሰብ ችሎታ በሚያስፈልጋቸው ተግባራቶች ላይ በመግባት የተለያዩ ስራዎችን ማከናወን እንዲችሉ እና ስርዓቶችን በመፍጠር ላይ ያተኮረ የኮምፒውተር ሳይንስ መስክ ነው።

AI ኮምፒዩተሮች እንደ ሰው እንዲያስቡ፣ እንዲማሩ እና ውሳኔ እንዲያወጡ የሚያደርገው ቴክኖሎጂ ነው።
አንዳንድ ጊዜ ለእያንዳንዱ እርምጃ በግልጽ ፕሮግራም ሳይደረግላቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እራሳቸውን እንዲያሻሽሉ ይደረጋሉ። በዛሬው ዓለም በስራ፣ በትምህርት እና በቢዝነስ ላይ ወሳኝ አዲስ ኃይል ሆኖዋል ።🚀
የAI  የስራ ችሎታዎች የተወሰኑት፦
• ቋንቋን መረዳት
• ንድፎችን መለየት 
• ውሳኔዎችን ወይም ትንበያዎችን ማድረግ
• ማስተካከያ ውጤት መስጠት
• ከዳታ መረጃ በመውሰድ መማር
   ለምሳሌ:- Machine Learning
በቀላሉ ፣ AI = እንደ ሰው የሚያስተስተውል ብልህ መሣሪያ ነው።

🤖 AI የሚሰራቸው ዋና ስራዎች
AI ዛሬ በብዙ መስኮች ውስጥ የሰውን ስራ በማጎልበት ስራዎች ላይ በመቀላጠፍ እየተሳተፈ ይገኛል።
እነሆ ዋና ተግባሮቹ ለመተንተን ሞክረናል፦
✔️ 1. መረጃ መተንተን
AI ብዙ መረጃ በጥቂት ሰዓት ይተንትናል፣
ትክክለኛ ውጤት ያወጣል።
✔️ 2. ስሜት እና ቋንቋ መረዳት
በቋንቋ ትርጉም፣ ድምጽ በመለየት፣
ተጠቃሚው ምን እንደሚል መረዳት ይችላል።
✔️ 3. ማስተላለፊያ ውሳኔ መውሰድ
AI ምሳሌዎች እየተመለከቱ እና እየተማሩ
የተሻለ ውሳኔ ይወስዳሉ።
✔️ 4. ተስማሚ የስራ ሚና
• ኢሜይል መጻፍ
• የጽሁፍ ማዘጋጀት
• ፎቶ ማቀናበር
• የተለያዩ የዝግጅቶችን ሂደቶችን በማቀላጠፍ ፣በፍጥነት ይፈጽማል።
✔️ 5. የአስተዳደር ስራዎች ማቀላጠፍ
AI ሰነዶችን ማዘጋጀት፣ በየስራ ቀኑ ስራዎችን
በማቀናበር፣ የማዕከላዊ መረጃ ቁጥጥር
ያቀላጥፋል።
🧠 እንግዲህ ለምን AI ጠቃሚ ነው እንደሆነ የተረዳን ይመስለኛል።
ትክክለኛ ፣ ፈጣን ፣ የተሻለ ውጤት ለማግኘት፣
ሰውንም ከከባድ ስራ ያግዛል ማለት ነው።

🤖 የAI ተግባሮች — ጠቃሚ ምሳሌዎች
AI በስራዎች ላይ እንዴት እንደሚረዱ  በግልጽ ምሳሌዎች ለመመልከት እንሞክር፦
✔️ 1. ፈጠራዊ ይዘት(Content Creation)
AI ፈጣን ጽሁፍ፣ caption፣ blog፣ የንግድ መልዕክት ይፃፋል ያዘጋጃል።
🌟 ከዚህ በፊህ 10 ደቂቃ የሚፈጅብን ከሆነ Ai በ5 ሰከንድ ያዘጋጅልናል!
✔️ 2. የቋንቋ ትርጉም
ከአማርኛ ወደ እንግሊዝኛ፣ ከእንግሊዝኛ ወደ ሌሎች ቋንቋዎች
በፍጥነት ይተርጎማል።
✔️ 3. ፎቶ እና ዲዛይን ፈጠራ
የመግለጫ ፎቶ፣ ቫክቶር ዲዛይን፣ ሎጎ፣ poster ማቀናበር
በAI አስቸጋሪ አይሆንም።
✔️ 4. ትምህርት ማስተማር
AI ትምህርት ላይ ወሳኝ ነው። ትምህርታዊ የሆኑ ነገሮችን ማስረዳት፣ ቀለል ባለ መልኩ ትምህርቶችን ይሰጣል፣ እናም
የትምህርት ምድቦችን መግለጽ ይችላል።
✔️ 5. የንግድ ስራ ማቀላጠፍ
• የደንበኛ መልስ ማቀናበር
• የንግድ ዕቅዶችን ማዘጋጀት
• የሽያጭ ትንበያዎችን ማውጣት
AI በንግድ ክፍል በተሻለ ውጤት ይረዳል።
✔️ 6. የጤና መረጃ ትንተና
በAI ህመሞችን መለየት፣ የመድሀኒት መለኪያ፣
የህክምና ትንተና ለመስጠት በብዙ አገሮች ተጠቃሚ እየሆነ መጥቶዋል ።
✔️ 7. የኢንተርኔት ፍለጋ ና ማስረዳት
AI የትኛውም መረጃ በፈጣን ሁኔታ ፈልጎ ያስረዳናል፣
የምርምር ማጠቃለያ ማቅረብ ይችላል።
🌟 በአጠቃላይ
AI በመጠቀም ስራዎን በፍጥነት፣ በትክክል እና በቀላሉ ለማከናወን ያስችላል።

AI = ለምርታማ ስራ + የተሻለ ውጤት ነው!

በቀጣይ ተወዳጅ የሆኑ AI የሆኑ የመጠቀሚያ አፕልኬሽኖችን የምናይ ይሆናል።👍

#Ai #tech #ቴክኖሎጂ #technology #TechTips #techinfo

CompuTech©
👍3
🔥1
Top AI Apps

የAI መጠቀሚያ አፕሊኬሽኖች (Apps) እንደየጠቄሜታቸው ዘርዝረናችዋል።
🤖 AI በመጠቀም የተለያዩ አገልግሎትን የሚሰጡ አፕሊኬሽኖች - Top AI Apps
✔️ 1. ChatGPT
ለጽሁፍ፣ ለትርጉም፣ ለቢዝነስ እቅድ፣ ለተለያዩ ትምህርቶች ለመማር የተለያዩ ግብአቶች ለማግኘት በጣም ተጠቃሚ ነው።
✔️ 2. Google Gemini
ለመረጃ ፍለጋ፣ ለምርምር፣ ለጽሁፍ ፈጠራ፣ በተጨማሪም በGoogle አገልግሎቶች ጋር አብሮ አካቶቷል።
✔️ 3. Microsoft Copilot
Word፣  Excel፣ PowerPoint ስራዎችን ለመስራት AI  ያግዘናል፣ በፍጥነት ለመተንተንም ይረዳናል ።
✔️ 4. DeepSeek
DeepSeek እንደ ChatGPT ሲሆን ፈጣን  ነው። ለተለያዩ ትምህርታዊ ነገሮች ጠቃሚ ና ጥሩ የሆነ የቻት አይነት አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ነው።
ለመማር፣ ለመጻፍ፣ ለኮዲንግ skill፣ ለተለያዩ ኮዶችላይ የሚፈጠሩ ችግሮችን መፍትሄ ለማግኘት ና ለዕለት ተዕለት ስራዎችን በማቅለል ፈጣን እገዛን ለማግኘት ያስችለናል። በAI የተመረጠ ፍለጋ እና የጽሁፍ ፈጠራ በአንድ ቦታ ለማግኘት ጠቃሚ ነው።
✔️ 5. Claude AI
ከፍተኛ ጥራት ለጽሁፍ ማዘጋጀት፣ ለአንባቢ ተመራጭ የሆነ ፅሁፎችን ለማዘጋጀት  የሚረዳን የAI አፕ ነው።
✔️ 6. Canva AI
ፎቶ ለመቀነባበር፣ የተለያዩ ዲዛይን ለማዘጋጀት፣ ሎጎ ለመስራት በAI  ቀላል ሆኖዋል ።
✔️ 7. Grammarly - AI Writing Assistant
ፊደል ለማስተካከያ፣ ቃላቶችን ለማሻሻል፣ ለጽሁፍ አቀራረብ  ተጠቃሚ ነው።
✔️ 8. Lensa AI
የፎቶ ማቀናበር፣ የፊት ገፅታን ለመቀያየር፣ በAI ሰዎችን ና ገፅታቸውን በፎቶ ለመፍጠር ለሚፈልጉ በጣም ጠቃሚ ነው።
✔️ 9. Replika AI
ከሰዎች ጋር የምክክር መድረክ ላይ የምንሳተፍ ከሆነ ፣ ይህ ፕላትፎርም የተለያዩ አመለካከቶችን ለመለዋወጥ እንዴት  እንደምናደረግ የሚያሳየን AI ነው።
✔️ 10. CapCut AI Editor
የቪዲዮ እና የፎቶ ማቀናበር ስራ በጠጨማሪም ዘፈኖችን በመቀላቀል በተለያየ መልኩ ያዘጋጃል፡  ይህም በ  Ai ቀላል አድርጎታል። በተጨማሪም የAuto-caption፣ የማይፈለጉ ነገሮችን ለማስወገድ፣ Short Videoዎችን ለመስራት አስቸጋሪ የሆኑትን ነገሮች Ai በቀላሉ ያዘጋጅልናል።


🌟ማጠቃለያ : የAI አፕዎች እንደ የጠቀሜታቸው መድበናቸዋል:- 

📘 ለጽሁፍ ስራ
• ChatGPT
• Claude
• Gemini
• Grammarly

🎨 ለፎቶ ኤዲቲንግ
• Canva AI
• Lensa
• Remini AI
• Midjourney (Bot በDiscord ይሰራል)

🎬 ለቪዲዮ ኤዲቲንግ
• CapCut
• Runway ML
• Kaiber AI

💼 ለቢዝነስ ስራዎች
• Microsoft Copilot
• Notion AI
• Taskade AI

ከላይ የጠቀስናቸውን apps በፕለይ ስቶር የሚገኙ ሲሆን በተጨማሪም በአብዛኛዎቹ  በብራውዘር አድሬስ በማድረግ መጠቀም ያስቻላሉ።

#Ai #chatgpt #TechTips #aiapps #techinfo #ቴክኖሎጂ

CompuTech©
👍3
A.lilah 🥰
👏2
🥰🥰
👏2
👍2
ስልክ ከመግዛታችን በፊት ልናውቃቸው የሚገቡ ነገሮች 📱
ኦሪጅናል  ፣ ኮፒ / የታደሰ ወይም የተቀያየረ (Repack) እንዴት ማረጋገጥ ይቻላል?
ከዛ በፊት ግን📱የስልኮችን ባህሪ ለማወቅ ስለሚጠቅመን ኮፒ፣ ከፍተኛ ኮፒ(high copy) እና Repack ምን ማለት እንደሆነ እንይ:-
1️⃣ ኮፒ (Copy / Fake)
ብዙ ጊዜ ዝቅተኛ ጥራት አላቸው
የስልኩ ውስጥ ክፍሎች ዝቅተኛ ናቸው CPU፣ RAM፣ Screen፣ Camera ዝቅተኛ ናቸው።
IMEI የተሳሳተ / የማይታወቅ ይሆናል
ዋጋ እጅግ ዝቅተኛ ነው
ምሳሌ: Samsung M15 5G ይመስላል ነገር ግን CPU = MT6580 ነው → ኮፒ

2️⃣ ከፍተኛ ኮፒ /High Copy (Fake)
• የኦርጂናል ስልክ ተመሳሳይ ማለት ነው ፣ ነገር ግን በከፍተኛ ጥራት አለው ።
•   cpu ፣ ካሜራ፣ ስክሪን ከፍተኛ ጥራት አላቸው።
• ዋጋቸው በጣም መካከለኛ ነው ።
• IMEI ትክክል ሊሆን ይችላል የተሳሳተ ሊሆን ይችላል።
ለምሳሌ: “Samsung S21 Ultra ” ሞዴል ቼክ ስናደርግ CPU ከኦርጂናል ስልክ የተለየ ከሆነ → ኮፒ ነው።
3️⃣ Repack/ የታደሰ (Refurbished)
• ኦሪጅናል ስልክ ነው፣ ነገር ግን አንዳንድ የውስጣዊ እና የውጪዊ ክፍሎቹ  የተቀየሩ ናቸው።
• ዋጋ ዝቅተኛ ሳይሆን ከፍ ያለ ሊሆን ይችላል።
• IMEI ትክክል ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን በከፊል የስልኩ መረጃ የተጠቀሰ ሊሆን ይችላል።
ለምሳሌ: Samsung S21 Ultra ሞዴል ቼክ ስናደርግ ባትሪ የተቀየረ ከሆነ እና ስክሪን በሁለተኛው  የተቀየረ ከሆነ የቀየረ → Repack ነው ።
💡በአጠቃላይ:-
• ኮፒ = በጣም በዝቅተኛ አቅም ተመሳስለው (Fake) የተሰሩ ናቸው።
• ከፍተኛ ኮፒ = አርጂናል ይመስላል ወይም ለመለየት የሚዳግት ሊሆን ይችላል።
• Repack = የኦሪጅናል ክፍሎች  የተቀያየረለት / የታደሰ ነው።

ስልክ ከመግዛታችን በፊት ልናውቃቸው የሚገቡ ነገሮች:-

1. IMEI (International Mobile Equipment Identity) መለያ መፈተሽ
ይሄን  : *#06# መደወል
IMEI ቁጥሮቹን በ IMEI.info ላይ ማረጋገጥ።
• ትክክለኛ መረጃ ካላመጣ → Repack / ኮፒ
• IMEI ካልተገኘ → ከፍተኛ ኮፒ
2. ቦክስ ላይ ያለው እና በስልኩ ያለው IMEI ማመሳሰል
• ቁጥሮቹ ካልተመሳሰሉ → አንዳንድ ክፍሎች የተቀየረለት ስልክ (Repack) ነው
3. ሞዴሉን በSettings ውስጥ መፈተሽ
Settings → About Phone
ኦሪጅናል ሞዴል በትክክል ይታያል
ለምሳሌ:- የ Samsung A55 ሞዴል
ኮፒ ስልኮች እንዲህ ያሉ ስሞች ሊያሳይ ይችላል፦
• A55 Pro Max
• S23 Ultra+ Max
• Ultra Pro Max
እነዚህ ሁሉ ኮፒ ናቸው።
4. ስክሪኑን መፈተሽ
ውስብስብ ብርሀን/brightness ☀️፣ ዝቅተኛ ቀለም፣ እና በጣም ቀርፋፋ ስታክ የሚሆን ከሆነ→ ኮፒ ስልክ ነው።
5. Play Store Certification መፈተሽ
Play Store → Settings → About
• “Certified” ከሆነ → ኦሪጅናል
• Not certified → ኮፒ ወይም Repack
6. ካሜራ ጥራት መመርመር
ዝቅተኛ ቀለም፣ ድብዘዝ ያለ ከሆነ፣ በ እንቅስቃሴ ግዜ ዝግ የሚል ከሆነ → ኮፒ ነው።
7. የባትሪን መረጃ መፈተሽ
Device Info HW ወይም AIDA64 መተግበሪያ ጭነው ቼክ ማድረግ።
መረጃ ካልታየ → ከፍተኛ ኮፒ ወይም Repack
8. ዋጋ  ማነፃፀር
በጣም እርካሽ ሊሆን ይችላል።
ለምሳሌ፦ኦርጂናል የSamsung A55 → 20ሺ–30ሺ ብር ቢሆን
የኮፒ/ Repack ዋጋ ደግሞ 10ሺ–15ሺ → ሊሆን ይችላል።
9. ቻርጀርና አክሰሰሪ ማየት
ኦሪጅናል ቻርጀር ክብደት አለው፤
ያልሆኑት ቻርጀሮች ቀላል ናቸው።
10. CPU መፈተሽ
CPU-Z app በዚህ መተግበሪያ መፈተሽ
•  Exynos/Snapdragon /Media Tek Dimensity ከሆነ → ኦሪጅናል ነው
• MT6580/MT6735
የተለየ ሞዴል ቁጥር ካሳየ → ኮፒ

በቀጣይ የስልክ ሞዴል እንዴት መፈተሽ እንዳለብን እናያለን ፣በተጨማሪም ቪድዮ እናዘጋጃለን ውዶቼ🥰 🤙

#ቴክኖሎጂ #techinfo #TechTips #phonetips #technology #TechEthiopia

CompuTech©
👍3
🔥3
Cyber Tips of the Week - ሳምንታዊ የሳይበር ደህንነት ምክር

📊 የደህንነት ምክር

🔹 2FA (Two Factor Authentication) አብሩ
🔹 Strong Password ይጠቀሙ
🔹 Public WiFi ላይ Banking አትግቡ
🔹 Telegram Active Sessions በየሳምንቱ ይፈትሹ
🔹 በ VirusTotal በፋይል እና መተግበሪያዎችን መርመር። ✌️🥰 ውዶቼ


#cybersecurity #TechEthiopia #technology #ደህንነት

CompuTech©
👍2
Online Access Checking scam sites - በኦላይን ከመጭበርበረዎ በፊት ቆም ብለው ይፈትሹ!
🖥️ ኦላይን ላይ ስንገኝ ብዙ መጭበርበሮች ሊኖሩ ይችላሉ።

በብዙ ዌብሳይቶች ላይ የተበላሸ SSL ምልክት ማለትም ደህንነቱ ያልተረጋገጠ (Not Secure) ይኖራል

የFake Websites ብዛት እበዙ ነው።
በተለይ የJob Offer፣ Scholarship፣ Investment ፣ የሚባሉ መሳቢያ አማራጮች የተጠቃሚዎች መጭበርበር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ይገኛል።

መፍትሔውም:-

https://”ውን በደንብ ይፈትሹ ይመርምሩ

በተለይ ማስፈንጠሪያ ከሆነ Websiteን ሳይነኩት በደንብ ያረጋግጡ። አጠራጣሪ ከሆነ ማጥፋት።


CompuTech©
👍3
📺 ይተዋወቁት ውዶቼ🥰 ከቴክኖሎጂው መዝገብ ላይ 📖
ስሙ Pavel Valeryevich Durov ይባላል ፣የተወለደው October 10 1984 እንደ አውሮፓውያን የቀን አቆጣጠር ሲሆን፣ ሩሲያዊ የቴክኖሎጂ ሥራ ፈጣሪ ነው።
በተጨመራም የቴሌግራም ዋና ሥራ አስፈፃሚ (CEO) እና ፈጣሪ ነው ።
🧷 Title
CEO of VK (2006–2014)
CEO of Telegram (2013–present)

CompuTech©
👏2
ቴሌግራም ፣ቴሌግራም ሜሴንጀር በመባልም የሚታወቅ ሲሆን በክላውድ ላይ መሰረት በማድረግ፣ የማህበራዊ መድረክ ግልጋሎት የሚሰጥ ሲሆን ፣ የማህበራዊ ሚዲያ የፈጣን መልዕክት (IM) አገልግሎት ሲኖረው፣ በኦገስት 14-2013 - ኦክቶበር 20፣ 201፣ 12 ዓመት ሆኖታል፣ ለ iOS እና ለአንድሮይድ ስርዓቶች አገልግሎት መስጠት ጀመረ።
ተጠቃሚዎች መልዕክቶችን እንዲለዋወጡ፣ ሚዲያዎችን እና ፋይሎችን እንዲያጋሩ፣ የግል እና የቡድን የድምጽ ወይም የቪዲዮ ጥሪዎችን እንዲሁም የህዝብ የቀጥታ ስርጭቶችን እንዲመሰርቱ ያስችላቸዋል። ለአንድሮይድ፣ ለ iOS፣ ለዊንዶውስ፣ ለማክሮስ፣ ላይኑክስ እና ዌብ ማፋለጊያ ላይ መጠቀም ያስችለናል። ቴሌግራም በድምጽ እና በቪዲዮ ጥሪዎች፣ በሁለት ተጠቃሚዎች ፣መካከል ተንቀሳቃሽ መሳሪያ የሚጠቀሙ ከሆነ በግል ውይይቶች ላይ end to end ምስጥር (encryption) ይጠቀማል።
የቴሌግራም  የፕሮግራሚንግ አይነት ደግሞ -
written in Desktop:- C++፣ C፣ Java፣ Python
Android: -Java
iOS:- Swift

Latest update - 12.2.10
Update on - Dec 05- 2025

#TechEthiopia #TechTips #ቴክኖሎጂ #ቴክ #phonetips

CompuTech©
👍2
👏2
👍2
1👍1