እንግዲህ እኛ! 😊 ዛሬ እንዴት ኳስ በቀጥታ ለማየት ቻልን በጣም በተቀናጀ የሰው እና የቴክኖሎጂ ውጤቶች አልፎ ማየት እንዴት ቻልን ?
እስቲ ስለዚህ ቀለል ባለ መንገድ የተዘጋጀ መረጃ አለን፣ እናም በተለይ
በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የሚካሄዱ የቀጥታ ቪዲዮ ስርጭቶች እንዴት ወደ ተመልካች ይደርሳል በሚል ዙሪያ ቀለል ያለ መረጃ ልናካፍላቹ ወደድን።

👍1
⚽️ የቀጥታ ሊግ የኳስ ስርጭት እንዴት ይከናወናል በመጀመሪያ ለቀጥታ ስርጭት በተሳካ መልኩ ለተመልካች እንዲደርስ የሚረዱ ነገሮች:-
Control Room” እና “OB Truck (Outside Broadcast Truck)” (ተንቀሳቃሽ የስርጭት መቆጣጠሪያ መኪና) ሁለቱም በእግር ኳስ ጨዋታ ስርጭት ውስጥ በጣም አስፈላጊ ናቸው።
እንደ የቦታቸው እና ተግባራቸው ቢለያዩም ማለት ነው።
ምንድናቸው 👇
🎛️ 1. Control Room (የቁጥጥር ክፍል)
ይህ በቴሌቪዥን ኩባንያ ወይም የስርጭት ማዕከል ውስጥ የሚገኝ ክፍል ነው።
በውስጡም የቪዲዮ እና የድምፅ ቴክኒሽኖች ስርጭቱን በትክክል ይቆጣጠራሉ።
ዋና ተግባራቸው፦
የቪዲዮ መምረጫው የትኛው ካሜራ ይታይ ወይም Cam 12/15 እንደሚሆን ይወስናሉ
የድምፅ መቀነስ እና ማቀናበር
የተለያዩ ገጽታዎች (graphics፣ score boards፣ timer፣ logos እንዲገባ ፣
ቪዲዮን ለማቀነባበር እና ለመላክ ዝግጁ ሲሆን ማለት ነው።
ቀጥታ ስርጭቱም አየር ላይ ከዋለም በኋሏ ለ መከታተል ይረዳል።
በ መቆጣጠሪያ ክፍል ውስጥ የተለያዩ መሳሪያ ዎች አሉ ፣ Vision Mixer ፣ Audio Mixer ፣Monitors፣ Intercom System፣ Recording Replay systems
🚛 2. OB Truck (Outside Broadcast Truck)
ይህ እንደ ተንቀሳቃሽ የControl Room ተመሳሳይ ነው።
እንደ ታንስሚሽን መኪና (broadcast van) ይታወቃል።
በመስክ ዙሪያ (በስታዲየም በኩል) ይቆማል እና በዚያ ውስጥ ቪዲዮን በቀጥታ ተቀናብረው አየር ላይ ይውላሉ።
ዋና ተግባራቸው፦
ከመስክ ካሜራዎች ቪዲዮ በመቀበል
ዳይሬክተሩ ቪዲዮ እና ድምፅን በቀጥታ እንዲ ስተካከል በማዘዝ
ቪዲዮ ተቀነባብሮ በ
(Encoding)
ወደ Satellite / Fiber cables ይሰራጫሉ።
በ OB ውስጥ ልክ እንደ CR ሁሉ ተመሳሳይ መሳሪያዎች አሉ፦
12–20+ የካሜራ የሚገኙትን ተግባራትን ወደ Vision Mixer፣ ከድምፅ መሳሪያ የሚገኙትን ደግሞ ወደ
Audio Mixing እናም ሌሎች የ console
የReplay መሳሪያ EVS ፣ Slow motion systems
የPower Supply, Air Conditioning, Communication systems ይገኛሉ
📊 ስለዚህ በእግር ኳስ ጨዋታ ወቅት OB Truck በመስክ ዙሪያ በመቆም፣ ስርጭቱ በSatellite ወደ Control Room ይላካል።
የስርጭቱን ክንውን ምን ይመስላል ?
በቅድሚያ 🎥 ካሜራች
• ለምሳሌ በእያንዳንዱ የፕሪምየር ሊግ ጨዋታ በአማካይ ከ20 እስከ 30 እናም ከዛ በላይ cam ሊጠቀሙ ይችላሉ ።
የተወሰኑት cam አይነቶች:-
• 🎯 ዋና ካሜራ (Main Camera)
• 🕊️ ከላይ ያለ ካሜራ (Spider Cam)
• 🚀 የጎን ካሜራዎች (Touchline & Goal Cameras)
• 🧍♂️ የተጫዋች እና አሰልጣኞች ካሜራዎች
• 🎥 የVAR ካሜራዎች (በተለይ ለውሳኔ ማጣሪያ)
⚙️ እንዴት ከካሜራ ወደ OB Truck ይገናኛሉ ?
• እያንዳንዱ ካሜራ በ SMPTE Fiber Cable ወይም Triax Cable ወደ OB ይገናኛል።
• በ OB ትራክ ውስጥ ያለው CCU (Camera Control Unit) የካሜራውን ብርሃን፣ ቀለም እና መድረክ ይቆጣጠራል።
• የካሜራው ምስል በዚያ ትራክ ውስጥ በ Vision Mixer በኩል ዲስፕለይ ላይ ይደረደራል።
🎚️ በተጨማሪም በ OB Truck ውስጥ
• Director – የታየውን ካሜራ እንዲመርጥ ለኦፕሬተሩ ትዕዛዝ ይሰጣል። (“Camera 3, ready... take 3!”). ይቀይራል።
• Vision Mixer – በመጠቀም ኦፕሬተር ካሜራዎችን በቀጥታ ይቀያይራል።
• Sound Mixer – የደጋፊ ድምፅ፣ ሜዳ የኮሜንተሪዎችን ድምፅ ተግባር በተያያዘ ያዋህዳል።
• Graphics System – የስኮር /የቡድን ሚኑ፣ የተጫዋች ስም፣ ዲስፕለይ ላይ እንዲታይ ያደርጋል።
📡 ከ OB ትራክ ወደ አየር ላይ የሚውለውም
• የተዘጋጀው ዋና ፕሮግራም (PGM Feed) በ Satellite Uplink ወይም Fiber Connection ወደ የብሮድካስት ማዕከል ይላካል።
• ከዚያም አየር ላይ ይውላል።
• ለምሳሌ ያክል ወደ Sky Sports፣ BBC, SuperSport፣ የመሳሰሉ የኳስ ስርጭት አቅራቢዎች ይደርሳል።
• ወደ ተመልካችም በቴሌቪዥን ወይም በመስመር ላይ በቀጥታ ይደርሳል።
🧠 ማጠቃለያ
⚽️ ከካሜራ ወደ OB ትራክ → ከዚያ ወደ ሳተላይት → እና በመጨረሻ አየር ላይ ይውላል።📺🌍
CompuTech©

👏2
🌐 API ምንድ ነው?
API (Application Programming Interface) ማለት፣ ኮምፒውተሮች እርስ በእርሳቸው እንዲነጋገሩ የሚያስችል መንገድ ነው።
👉 API እንደ መልእክት ለመላክ የሚያግዝ ነው። አንድ መተግበሪያ ከሌላ መተግበሪያ ጋር ለመግባት ይጠቅማል።
💡 ለምሳሌ በቀላሉ
• አንተ በቴሌግራም ቻናል መልእክት መላክ ትፈልጋለህ እንበል፡ ነገር ግን ኮምፒውተሩ ትዕዛዝህን አያውቅም ስለዚህ API ገብቶ፤ እሱ እንደ ተርጓሚ ሆኖ — ትዕዛዝህን ይተርጉማል።
⚙️ተጨማሪ ምሳሌ – የTelegram API
በTelegram API:-
• መልዕክቶች በራስ /auto መልዕክት ለመላክ 🤖
• ተጠቃሚዎችን መቀበል 👥
• ፎቶ እና ፋይሎች ለመላክ 📷📁
• አዲስ “bot” አገልግሎት መፍጠር
🧠 በአጠቃላይ
API ማለት፣ ኮምፒውተሮች በመረጃ መንገድ በማገናኘት ስራ እንዲሰሩ የሚያስችል መተግበሪያ መንገድ ነው።
ልክ ሰዎች እርስ በእርሳቸው ለመግባባት ቋንቋ ግድ እንደሆነው ሁሉ ፣ ለኮምፒውተሮች ደግሞ API ያስፈልጋቸዋል።
እናም APIን በብዙ ቦታዎች ልንጠቀምበት እንችላለን።
#api #telegramapi #technews
#programming #ቴክኖሎጂ #TechEthiopia

👍2
የሳይበር ደህንነት (Cyber Security)
ማለት ምን ማለት እንደሆነ ቀለል ባለ መልኩ እና ጠለቅ ብለን ለመዳሰስ ሞክረናል።
🔐 ሳይበር ደህንነት ምንድን ነው?
ሳይበር ደህንነት ማለት፣ ኮምፒዩተሮች ፣ ሰረቨሮች፣ ኔትዎርክ እና መረጃዎች ደህንነታቸውን ከመጠበቅ አንፃር የሚተግበር ነው።
እንዲሁም የኢንተርኔት ወንጀለኞች፣የመረጃ ቤዝ ጥፋቶችን፣ የመረጃ ቤዝ አጥፊዎች (hackers) የሚመጡ ጥቃቶችን ለመከላከል የሚተገበር ነው ማለት ነው።
በቀላሉ ፣ሳይበር ደህንነት ማለት የመረጃን እና ሌላ የቴክኖሎጂ አገልግሎትን ፣ ከ ቤዝ ጥቃት እና ከመረጃ መበላሸት ለመጠበቅ ይጠቅማል።
💻 ዋና ዋና የሳይበር ደህንነት ክፍሎች
1. 🌐 የኔትዎርክ ደህንነት (Network Security)
በኔትዎርክ ውስጥ ያለውን ፍሰት ለመመርመር ፣ከመሰረታዊ ጥፋት ይከላከላሉ።
ለምሳሌ:- Firewalls፣ VPNs፣ Antivirus እና ሌሎች የመከላከያ ሶፍትዌሮች።
2. 🧾 የመረጃ ደህንነት (Information Security / InfoSec)
የድርጅቶች መረጃ እንዳይታወቅ ወይም እንዳይቀየር ይጠብቃል።
ምሳሌ፡ አካውንት መከታተያ፣ ፓስወርድ መቆጣጠሪያ፣ እና መረጃ ኢንክሪፕሽን (Encryption)።
3. 💻 የመተግበሪያ ደህንነት (Application Security)
መተግበሪያዎች በመጠቀም ላይ እንዳይታሰሩ ይከላከላል።
ምሳሌ፡- የዲቫይስ ቁጥጥር ሶፍትዌሮች፣ የመረጃ መመርመሪያ (Vulnerability Testing)።
4. 🧠 ኢቲካል ሃኪንግ (Ethical Hacking)
ማለት ህጋዊ መንገድ ኮምፒዩተር ወይም የዳታሴንተር ሰርቨሮች ላይ ጉዳት ካለ አልያም ችግር ይደርሳል ወይም አይደርስም በማለት ይፈትሻል ።
በሰዓቱም ድንበሮች ላይ ችግር ካለ እንዲታወቅ ያግዛል።
5. 🕵️♂️ የተጠቃሚ ግላዊነት (User Privacy & Awareness)
ተጠቃሚዎች የግል መረጃዎቻቸውን እንዴት መጠበቅ እንዳለባቸው የሚያስተምር ነው።
ምሳሌ፡ በይለፍ ቃል ቁልፍ ቃላትን አትድገም፣ ምንነቱ ያልታወቀ ሊንክ አትጫኑ፣ ሁሉንም አካውንታቹ ላይ 2FA ማድረግ።
⚠️ የሳይበር አደጋዎች (Cyber Threats)
የሳይበር አደጋዎች ለምሳሌ የሶሻል ሚዲያ መረጃዎች እና በሌሎች ዌብ ስርዓት ላይ የሚፈጥሩ አደጋዎች ናቸው።
• Phishing (ፊሺንግ) – በሐሰት መልዕክት የመረጃ መመንተፍ እና አካውንት መጥለፍ።
• Malware ( ሜልዌር ቫይረስ) – የኮምፒውተር ስርዓቶች ውስጥ መረጃን እንዲያጠፋ የሚሰራ ቫይረስ ነው።
• Ransomware (ራንሰምዌር) – መረጃዎን እንዳይገኝ በመዝጋት ክፍያ የሚጠይቅ ቫይረስ ነው።
• Data Breach (የመረጃ ጥሰት) – የግል መረጃ-ይለፍቃል 🔑 መታወቅ።
• Social Engineering (ማታለያ ስራ) – ተጠቃሚዎችን በማታለል መረጃ እንዲሰጡ ማድረግ።
🛡️ መከላከያ መንገዶች
• የሶፍትዌር ስርዓቶችን እና መተግበሪያዎችን ማዘመን።
• እያንዳንዱ አካውንት የተለያየ ይለፍቃል(Password) መጠቀም።
• 2FA ይጠቀሙ።
• ከማያውቁት ሰው ሊንክ ከተላከ ሳይረጋገጥ አለመጫን። አንዳንዴ ከሚያውቁትም ሰው ሊላክ ይችላል ፣ ምክንያቱም የሚያውቁት ሰው አካውንቱ ተጠልፎ ሊሆን ስለሚችል ስለዚህ በቅድሚያ ማረጋገጥ።
• VPN መጠቀም በተለይ በህዝባዊ Wi-Fi ላይ።
• የመረጃ ቅጂ መያዝ (backup) ።
• የአንቲ-ቫይረስ ቱሎች መጠቀም።
🧭 ማጠቃለያ
በሳይበር ደህንነት የሚተገበሩ ነገሮች ፡
• የመረጃን አጠቃላይነት (Integrity) መጠበቅ፣
• የመረጃ መዳረሻን (Availability) ማረጋገጥ፣
• የግል መረጃን በመሰየም (Confidentiality) ማስቀመጥ ።
ሳይበር ደህንነት ማለት መረጃዎችን፣ የድረገፅ አገልግሎቶችን ተጠቃሚዎች ከዲጂታል ጥፋት እንዲጠበቁ የሚያገለግል የስራ ዘርፍ ነው።
#cybersecurity #technology #info
#መረጃአጠባበቅ #computer #telegram #ኢንተርኔት_ደህንነት #Privacy #TechTips

SQL Part 2
ቀደም ሲል ስለ SQL ማየታችን የሚታወስ ነው። 🥰
ዛሬም ከባለፈው የቀጠለ ቀደም ሲል ያየናቸውንም የ SQL ትዕዛዞችን ደግመን ለማየት ሞክረናል ። 👇

📚 SQL ትዕዛዞች
🖥️ የመረጃ ቤዝ (Database) ለመቆጣጠር የሚያገለግሉን ወሳኝ ትዕዛዞች 👇
🔹 SELECT — ዳታን፣ ለመመልከት
"SELECT * FROM Students; "
➡️ ከ "Student" ሁሉንም ተማሪዎች አሳይ ፣ የሚል ትዕዛዝ ነው።
🔹 INSERT — አዲስ ዳታ ለመጨመር
INSERT INTO Students (Name, Age) VALUES ('Jemi', 20);
🆕 አዲስ ተማሪ “Jemi” <--የሚባል Student Table ላይ ያስገባል።
🔹 UPDATE — ዳታን ለማስተካከል እና ለመቀየር ይጠቅመናል።
UPDATE Students SET Age = 21 WHERE Name = 'Jemi";
✏️ የ“Jemi” የሚባል ተማሪ ነባሩን ዕድሜ ወደ 21 ይቀይረዋል።
🔹 DELETE — ዳታ ለመሰረዝ የሚጠቅም ትዕዛዝ
DELETE FROM Students WHERE Name = 'Jemi;
🗑️ ተማሪ “Jemi”ን ከመረጃ ቋጥ ላይ ያጠፋዋል።
🔹 CREATE DATABASE — ይሄ ደግሞ አዲስ የዳታቤዝ ይፈጥርናል።
CREATE DATABASE SchoolDB;
በመረጃ ቋጥ ውስጥ "SchoolDB" የሚባል ይፈጥራል።
🔹 CREATE TABLE — አዲስ መረጃ table ዳታቤዝ ላይ ለመፍጠር ይጠቅማል።
USE SchoolDB;
CREATE TABLE Students (ID INT PRIMARY KEY, Name TEXT, Age INT);
📋 አዲስ "Student" የሚል "StudentDB" ዳታቤዝ ላይ Table ከሶስት Column ጋር ይፈጥራል።
Data type ያስገባል። ለምሳሌ:- IDን Integer አድርጎ Primary Key (Unique--የማይደገም ማለት ነው በአማርኛው)
Name :- Text
Age :-Integer ያደርገዋል ማለት ነው።
🔹 DROP TABLE — ዳታ ቤዝ ላይ የቴብሉን መረጃ ሙሉ በሙሉ ለመሰረዝ ያግዛል።
DROP TABLE Students;
⚠️ “Students” የሚለውን ዳታ አጥፋ።
💡 ለጥንቃቄ:
በSQL ላይ መረጃ እጅግ አስፈላጊ ነው።
ስለዚህ በDELETE ወይም UPDATE ትዕዛዞች ግዜ ሁሌ በጥንቃቄ ለተጠቀም ሞክሩ። ✅
🔥 #SQL #Database #Programming #ኮድን_ተማር #ቀላል_ኮድ #TechEthiopia #coding #አዲስ #TechTips

👍3
✈️ አይሮፕላን እንዴት ይበራል?
አይሮፕላን በ “አየር ላይ እንቅስቃሴ በማድረግ” ይበራል። እንዴት ?
ለአይሮፕላን መብረር አራት አስፈላጊ ነገሮች አሉ እነሱም :-
1️⃣ ግፊት (Thrust) – ግፊት በሞተሩ አማካኝነት ወደፊት የሚፈጠር እንቅስቃሴ ሲሆን፣ ኃይልን በመጨመር ግፊትን እንዲኖር ያደርጋል
ከፊት አየርን በመሳብ አየር ከኋላ ሲወጣ አይሮፕላኑን ወደ ፊት ይሄዳል።
2️⃣ መንሳፈፍ (Lift) – በፍጥነት ሲንቀሳቀስ አየር በክንፎቹ ላይ በላይና በታች በተለያዩ ፍጥነቶች ይፈሰሳል። የላይኛው አካል ላይ አየር ፈጣን ነው፣ ይህም ዝቅተኛ ግፊትን ያመነጫል። በታችኛው ግን በከፍተኛ ወደላይ ይገፋዋል ፣ይህም ግፊት አይሮፕላኑን ወደ ላይ በሚገፋበት ሰዓት እንዲሳፈፍ ያደርጋል።
3️⃣ ክብደት /ሚዛን ✈️ (Weight) – ክብደት ማመጣጠን፣ አይሮፕላኑን ወደ ታች የሚጎትት ሀይል ነው፣ብዙውን ግዜ ስበት(Gravity) እንለዋለን፣ ይህን ስበት ለማቆም ክብደትን በማስላት ሚዛን እንዲኖረው ይደረጋል።
🔹 4️⃣ መጎተት (Drag)
ይህም አይሮፕላኑ በአየር ውስጥ ወደፊት በሚሄድበት ጊዜ፣ አየሩ ተቃውሞ እንዳይፈጥር የሚያግዝ ነው።
ወደኋላ በመጎተት እንቅስቃሴውን በመቀነስ ከፊት ከአየር ጋር ግጭት እንዳይኖር ያደርጋል።
🛩 በቀላሉ ፣ መኪና በፍጥነት ወደፊት በሚጓዝበት ወቅት ፊለፊቱን አየር ሲመታው የሚፈጠረው ግፊት ማለት ነው ።
ይህ ነው Drag የምንለው።
አይሮፕላንም እንደዚህ ነው፤
አየሩ ፊለፊቱን በሚመታበት ጊዜ ወደኋላ ይጎተታል።
ይህ ከፊት የሚፈጠረው ኃይል አይሮፕላኑን ወደ ኋላ ይገፋዋል ማለት ነው ።
🧭 በአጠቃላይ :-
Lift-->ወደ ላይ አይሮፕላንን ያንሳፍፈዋል
Weight-->ወደ መሬት ወደ ታች ይጎትተዋል
Thrust-->ወደ ፊት አይሮፕላኑን ያንቀሳቀሳል
Drag-->ወደ ኋላ በመጎተት እንቅስቃሴውን ይቀንሳል
#technology #airplane #techinfo #TechTips #ቴክኖሎጂ #TechEthiopia

🏙 Smart City's
እንግዲ በዛሬው ፖስታችን ስለ ስማርት ከተማ (Smart City) ነው።
🌆 ስማርት ከተማ (Smart City) ማለት ምንድነው?
ስማርት ከተማ ማለት የቴክኖሎጂ መሰረተ-ልማት ፣ መረጀን Data center በመጠቀም፣ የከተማውን አገልግሎቶችን እንዲሻሻሉ፣ የነዋሪዎችን ሕይወት የተሻለ እንዲሆን፣ እና ከተማውን በመቆጣጠር በተሻለ መልኩ ማህበረሰቡን በ ቴክኖሎጂ በመታገዝ አገልግሎቶችን የሚሰጡ ከተሞች ናቸው ።
ለስማርት ከተሞች ዋና እስፈላጊ IoT ነው ።
IoT ማለት Internet of Things – ነገሮችን ሁሉ ከ ኢንተርኔት ጋር ማገናኘት ሲሆን ለስማርት ከተማ ግንኙነት IoT በጣም አስፈላጊ ነው።
🔹 የስማርት ሲቲ አገልግሎትቶች:-
1️⃣ ስማርት ትራንስፖርት – ትራፊክን በራሱ የሚቆጣጠር መብራት፣ ኤሌክትሪክ ባሶች እና የመኪኖች መቆጣጠሪያዎች፣ መቆለፊያ መተግበሪያዎች ፣ የIoT ሴንሰሮችን በመጠቀም።
2️⃣ ስማርት ኃይል – የስማርት የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት እና የSolar Energy ፣ የስማርት መለኪያዎች እና መቆጣጠሪያዎች ።
3️⃣ ስማርት መንግሥታዊ አገልግሎት – ኢ-አገልግሎቶች እንደ ኢ-ታክስ፣ ኢ-ፍቃድ፣ ኢ-ክፍያ ወዘተ።
4️⃣ ስማርት የውሃ ማጣሪያ - የስማርት የውሃ አቅርቦት
በቤት ውስጥ ቆሻሻ ካለው ራሱ የሚያሳውቅ፣ በ IoT ሴንሰር በመታገዝ የውሃ ፍሳሽ የሚጠብቅ የሚያሳውቅ።
5️⃣ ስማርት የህክምና አገልግሎት – ቴሌሜዲሲን የስማርት የጤና አገልግሎት በቴክኖሎጂ የታገዘ ህክምና መስጠት በጤና አገልግሎት ዘርፍ እገዛ ማድረግ።
6️⃣ ስማርት ደህንነት – በAI የሚተገበሩ CCTV ካሜራዎች፣ አደጋዎችን የሚያሳውቅ እና የድንገተኛ ጥሪ ስርዓት።
7️⃣ ስማርት ትምህርት – ዲጂታል ክፍሎች፣ የመማር መተግበሪያዎች ወዘተ።
🌍 በአለም ላይ የታወቁ የስማርት ከተሞች:
🏙️ 1. ሲንጋፖር (Singapore) – ትራፊክን በቀጥታ የሚቆጣጠር ስርዓት እና ንጹህ አካባቢ በአብዛኛው በቴክኖሎጂ የታገዘች ከተማ ነች ።
🏙️ 2. ዱባይ ፣ዩናይትድ አረብ ኤመረት ፡– በተለይ የመንግሥት አገልግሎቶች ሁሉ በሴንሰር እና በመተግበሪያ ቁጥጥር የሚደረግበት ከተማ።
🏙️ 3. ባርሴሎና ፣ ስፔን – የመንገድ መብራቶችን በሰው መንቀሳቀስ የሚቀነስ ሴንሰር እና ሌሎች የስማርት ቴክኖሎጂ አገልግሎቶች ።
🏙️ 4. ቶክዮ፣ ጃፓን – የድንገተኛ አደጋ አስተዳደር እና ከፍተኛ ቴክኖሎጂ ትራንስፖርት የተተገበረበት ከተማ።
🏙️ 5. ኒውዮርክ ፣ አሜሪካ – የስማርት መንግሥት ፕሮጀክቶችን በቴክኖሎጂ መሰረት የሚከታተል።
🇪🇹 በኢትዮጵያ – አዲስ አበባ ከተማ እንዴት የስማርት ከተማ ሊሆን ይችላል?
ያው ከተማችን ባለፉት ጊዜያቶች በተወሰነ ደረጃ ስማርት ለማድረግ
እየጣረች ትገኛለች እናም ከዚህ ቀጥሎ ያሉትን የስማርት ሲቲ አገልግሎቶች በከተማዋ እየተተገበረ ይገኛል።
የተሰሩ እና ወደፊት ልትሰራቸው የታቀዱ የቴክኖሎጂ ግልጋሎቶች አሉ።
እነሱም፡-
• በመንገዶች እና በመኪኖች ላይ የትራፊክ ሴንሰሮች
• የውሃ እና የኤሌክትሪክ ኃይልን የስማርት መለኪያ መቆጣጠሪያ
• የመንግሥት አገልግሎቶች online ማድረግ፣ (e-services)
• ኢ-ትራንስፖርት እና የኤሌክትሪክ ባሶች
• በAi የታገዘ የደህንነት ቁጥጥሮች
• በማዕከላዊ መንገዶች ላይ የ ኤሌክትሪክ መኪኖች ቻርጀር እና የነፃ Wi-Fi አገልግሎት
• የስማርት የውሃ እንቅስቃሴ አገልግሎት
እና ሌሎች አገልግሎቶች
🚀 “አዲስ አበባ የ 2030 Smart City” ዕቅድ
• ኤሌክትሪክ ባሶች
• የኤሌክትሮኒክ መንግስታዊ አገልግሎት
• የአየር ጥራት ክትትል
• ንጹህ ከተማ ወዘተ..
📊 እነዚህ የስማርት ከተሞች ተመሳሳይ አገልግሎቶች እና ዓላማዎች አላቸው፦
🧷 የህዝብን ሕይወት መሻሻል
🧷 ትራፊክ እንቅስቃሴዎች መቀነስ
🧷 ንጹህ አካባቢ እና የኤነርጂ ተደራሽነት
🧷 የመንግሥት አገልግሎትን በቴክኖሎጂ ማቀናበር ወዘተ
💬 በአጠቃላይ ፦
“ስማርት ከተማን መፍጠር የመንግሥት ሥራ ብቻ አይደለም፣
የዜጎችም ተሳትፎ እና ተግባር አስፈላጊ ነው።”
#technology #smarycity #ቴክ
#ቴክኖሎጂ #TechEthiopia #TechTips

CompuTech©️️
Photo
🤖 AI — Artificial Intelligence-ሰው ሰራሽ አስተውሎት
የዛሬው አለም ላይ በቴክኖሎጂው በፍጥነት እየተሻሻለ ነው፣ ከቴክኖሎጂ ውስጥም አንዱ AI -አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እጅግ ትልቅ ሚና እያጫወተ ይገኛል።
AI ማለት መሣሪያዎች እንደ ሰው እንዲያስቡ፣ እንዲማሩ፣ እንዲገመቱ የሚያደርግ ብልህ ቴክኖሎጂ ነው።
ይህ ቴክኖሎጂ በተለያዩ ስራዎች ላይ በማበር ግንዛቤ በመጨመር ስራን እንዲቀላጠፍ እና ውጤት እንዲሻሻል በጣም ተጠቃሚ እየሆነ ይገኛል።
👉 በመቀጠልም የAI ምንነት ፣ አስተዋጽኦዎች፣ ዋና ጥቅሞችን እና ተግባራዊ ምሳሌዎችን እንመለከታለን።

Artificial Intelligence (Ai) 🤖
AI ምንድን ነው? — አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ
AI (Artificial Intelligence) ወይም አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ማለት፣
(AI) የሰው ልጅ የማሰብ ችሎታ በሚያስፈልጋቸው ተግባራቶች ላይ በመግባት የተለያዩ ስራዎችን ማከናወን እንዲችሉ እና ስርዓቶችን በመፍጠር ላይ ያተኮረ የኮምፒውተር ሳይንስ መስክ ነው።
AI ኮምፒዩተሮች እንደ ሰው እንዲያስቡ፣ እንዲማሩ እና ውሳኔ እንዲያወጡ የሚያደርገው ቴክኖሎጂ ነው።
አንዳንድ ጊዜ ለእያንዳንዱ እርምጃ በግልጽ ፕሮግራም ሳይደረግላቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እራሳቸውን እንዲያሻሽሉ ይደረጋሉ። በዛሬው ዓለም በስራ፣ በትምህርት እና በቢዝነስ ላይ ወሳኝ አዲስ ኃይል ሆኖዋል ።🚀
የAI የስራ ችሎታዎች የተወሰኑት፦
• ቋንቋን መረዳት
• ንድፎችን መለየት
• ውሳኔዎችን ወይም ትንበያዎችን ማድረግ
• ማስተካከያ ውጤት መስጠት
• ከዳታ መረጃ በመውሰድ መማር
ለምሳሌ:- Machine Learning
በቀላሉ ፣ AI = እንደ ሰው የሚያስተስተውል ብልህ መሣሪያ ነው።
🤖 AI የሚሰራቸው ዋና ስራዎች
AI ዛሬ በብዙ መስኮች ውስጥ የሰውን ስራ በማጎልበት ስራዎች ላይ በመቀላጠፍ እየተሳተፈ ይገኛል።
እነሆ ዋና ተግባሮቹ ለመተንተን ሞክረናል፦
✔️ 1. መረጃ መተንተን
AI ብዙ መረጃ በጥቂት ሰዓት ይተንትናል፣
ትክክለኛ ውጤት ያወጣል።
✔️ 2. ስሜት እና ቋንቋ መረዳት
በቋንቋ ትርጉም፣ ድምጽ በመለየት፣
ተጠቃሚው ምን እንደሚል መረዳት ይችላል።
✔️ 3. ማስተላለፊያ ውሳኔ መውሰድ
AI ምሳሌዎች እየተመለከቱ እና እየተማሩ
የተሻለ ውሳኔ ይወስዳሉ።
✔️ 4. ተስማሚ የስራ ሚና
• ኢሜይል መጻፍ
• የጽሁፍ ማዘጋጀት
• ፎቶ ማቀናበር
• የተለያዩ የዝግጅቶችን ሂደቶችን በማቀላጠፍ ፣በፍጥነት ይፈጽማል።
✔️ 5. የአስተዳደር ስራዎች ማቀላጠፍ
AI ሰነዶችን ማዘጋጀት፣ በየስራ ቀኑ ስራዎችን
በማቀናበር፣ የማዕከላዊ መረጃ ቁጥጥር
ያቀላጥፋል።
🧠 እንግዲህ ለምን AI ጠቃሚ ነው እንደሆነ የተረዳን ይመስለኛል።
ትክክለኛ ፣ ፈጣን ፣ የተሻለ ውጤት ለማግኘት፣
ሰውንም ከከባድ ስራ ያግዛል ማለት ነው።
🤖 የAI ተግባሮች — ጠቃሚ ምሳሌዎች
AI በስራዎች ላይ እንዴት እንደሚረዱ በግልጽ ምሳሌዎች ለመመልከት እንሞክር፦
✔️ 1. ፈጠራዊ ይዘት(Content Creation)
AI ፈጣን ጽሁፍ፣ caption፣ blog፣ የንግድ መልዕክት ይፃፋል ያዘጋጃል።
🌟 ከዚህ በፊህ 10 ደቂቃ የሚፈጅብን ከሆነ Ai በ5 ሰከንድ ያዘጋጅልናል!
✔️ 2. የቋንቋ ትርጉም
ከአማርኛ ወደ እንግሊዝኛ፣ ከእንግሊዝኛ ወደ ሌሎች ቋንቋዎች
በፍጥነት ይተርጎማል።
✔️ 3. ፎቶ እና ዲዛይን ፈጠራ
የመግለጫ ፎቶ፣ ቫክቶር ዲዛይን፣ ሎጎ፣ poster ማቀናበር
በAI አስቸጋሪ አይሆንም።
✔️ 4. ትምህርት ማስተማር
AI ትምህርት ላይ ወሳኝ ነው። ትምህርታዊ የሆኑ ነገሮችን ማስረዳት፣ ቀለል ባለ መልኩ ትምህርቶችን ይሰጣል፣ እናም
የትምህርት ምድቦችን መግለጽ ይችላል።
✔️ 5. የንግድ ስራ ማቀላጠፍ
• የደንበኛ መልስ ማቀናበር
• የንግድ ዕቅዶችን ማዘጋጀት
• የሽያጭ ትንበያዎችን ማውጣት
AI በንግድ ክፍል በተሻለ ውጤት ይረዳል።
✔️ 6. የጤና መረጃ ትንተና
በAI ህመሞችን መለየት፣ የመድሀኒት መለኪያ፣
የህክምና ትንተና ለመስጠት በብዙ አገሮች ተጠቃሚ እየሆነ መጥቶዋል ።
✔️ 7. የኢንተርኔት ፍለጋ ና ማስረዳት
AI የትኛውም መረጃ በፈጣን ሁኔታ ፈልጎ ያስረዳናል፣
የምርምር ማጠቃለያ ማቅረብ ይችላል።
🌟 በአጠቃላይ
AI በመጠቀም ስራዎን በፍጥነት፣ በትክክል እና በቀላሉ ለማከናወን ያስችላል።
AI = ለምርታማ ስራ + የተሻለ ውጤት ነው!
በቀጣይ ተወዳጅ የሆኑ AI የሆኑ የመጠቀሚያ አፕልኬሽኖችን የምናይ ይሆናል።👍
#Ai #tech #ቴክኖሎጂ #technology #TechTips #techinfo