CompuTech©️
164 subscribers
360 photos
169 videos
28 files
208 links
Tech Update info
Computer and phones Security's
Computer Software Tips
Mobile Application Tips
Tutorial Point


Update " Yourself & Grow Knowledge also the Persons around you "
Download Telegram
TikTok Community Guideline Policy !!
የ ቲክቶክ ማህበራዊ በተዳደሪያ ደንብ ከ ቴክኖሎጂ አንፃር እንዴት ይሰራል ? 🤔
እንዴትስ ይተገበራል ?
👇
CompuTech©
👍2
TikTok Community Guide Line Policy ከ ቴክኖሎጂ አንፃር እንዴት ይሰራል?
TikTok  (Community Guidelines)  ማህበራዊ መመሪያ ሲሆን  TikTok ለተጠቃሚዎች ምን ማድረግ እንዳለባቸው  እና ምን እንደ ሚፈቀድ ወይም እንደማይፈቀድ የሚያሳይ መመሪያ ነው።  የተለያዩም መመሪያዎችን አካቷል።

እነዚህ መመሪያዎች ሁሉ በTikTok ላይ የተጠቃሚዎች ደህንነትን ለማስጠበቅ እና ጥሩ የማህበረሰብ ሁኔታ ለማስፈጸም  ተዘጋጅተዋል።

📡 TikTok  Community Guideline Policy ከ ቴክኖሎጂ አንፃር እንዴት ይሰራሉ?
🎥በ ቪዲዮ  (Upload)
• ቪዲዮ ከስልክ ወደ TikTok Server ይሄዳል።
• ይሄ CGP  እንዲሰራ   → API በPython, Java, Go ወዘተ.. የፕሮግራሚንግ አይነቶችን ይጠቀማል።
👉 ቪዲዮው ከመሰቀሉ በፊት:-
• AI ይመረምራል :-ምስል፣ ድምፅ፣ ጽሑፍ
• ከፖሊሲ መስፈርቶችን ይፈተሻል።
• ከተፈቀደ → በ CDN (Content Delivery Network) ተላልፎ በዓለም ዙሪያ ይታያል።
📡በ ላይቭ ስትሪም (Live Stream) ጊዜ
•  በRTMP Protocol (Real-Time Messaging Protocol) ቪዲዮ ይልካል።
• ይህ ቪዲዮ በ Streaming Server እንደ NGINX-RTMP፣ በTikTok ( የተሠራ ሲስተም) ይቀበላል።
• በስትሪም ላይ ላይቭ AI Filter ይሰራል
• የተከለከለ ንግግር፣  በምልክት ፣ ስለ አደንዛዥ ዕፆች  ወዘተ..
• ከተገኘ በቀጥታ ስትሪሙ ይቆራረጣል ።
• የተፈቀደ ስትሪም ከሆነ → በ CDN በምድር ዙሪያ ላሉት ተጠቃሚዎች Feed ላይ ይደርሳል ።

በTikTok Live Stream  ላይ የCommunity Guideline Policy እንዴት back end ላይ እንዴት እንደሚሰራ በቀላሉ ለመግለፅ እንሞክር:-

1. AI እና Moderation Filter
TikTok ከመጀመሪያ በሁሉም Live ላይ በቀጥታ AI Filter ያስተናግዳል፦
• Computer Vision – ምስል መለያ  ለምሳሌ :- እርቃንን ማሳየት፣ ማጨስ ፣ ሽጉጥ ወዘተ ማሳየት።
• Speech-to-Text AI – ከድምጽ ቃል በማውጣት ግልጽ የሆኑ  ቃላትን ይመርምራል  ለምሳሌ:- የጥላቻ ንግግሮች ወዘተ..
• Behavior Analysis – ከህግ አንፃር ትንተና መስራት ለምሳሌ:- ማጭበርበር ፣ ትንኮሳ፣ የጥላቻ ንግግር ፣ ወዘተ ማጣራት።
2. Human Moderators:- በሰው ሀይል ይወሰናል
• በAI ችግር ካገኘ → ወደ Moderator Dashboard ይልካል።
• በሰው  ማዕከላዊ መቆጣጠሪያ ይመረመራል፣ ስለ ቀጣይ ውጤት ይወስናል።
• ከተጠቃሚ ሪፖርት (Report Button) ጋር ይቀላቀላል።
3. Policy Enforcement -ከህግ መስፈርት አንፃር
• Minor Violation → መልዕክት እና ጊዜያዊ እግድ
• Severe Violation → በቀጥታ Live ማቆም
• Repeated Violation → አካውንት መዘጋት / ማጥፋት
🖥  ሂደቱ ምን ይመስላል
    User → Start Live → Stream → TikTok Server
    AI → በቀጥታ ይመረመራል→  Alert → Moderator
   ችግር ከተገኘ:- 
   Enforcement → Community Guideline መሠረት በማድረግ ውሳኔ ይሰጣል።
ለምሳሌ:-
• የህግ መስፈርት: አይፈቀድም 👉 ስለ ወሲብ ይዘት፣ ጥቃት፣ ግፍ፣   ይዘት ያለው ነገር ማስተላለፍ ።
• ሲያገኝ → AI ይቀይረዋል → Moderator ይወስናል → Live ይቋረጣል ማለት ነው ።

ቲክቶክ ሊጠቀምባቸው የሚችሉ የ programming እና ዳታቤዝ ቴክ   አይነቶች

◍ Backend languages → Python, Java, Go, C++
◍ Database → MySQL, Redis, Cassandra
◍ Machine Learning → TensorFlow, PyTorch
◍ Content Moderation API → ቪዲዮ ወይም ላይቭ ከመታየታቸው በፊት ከፖሊሲው አንፃር ይመረምራል ።
◍ CDN → Akamai፣ የTikTok  መሆናቸው ይታወቃል።
"API "=Application Programming Interface ማለት ነው🤗::

በአጠቃላይ፦

በቪዲዮ post  ጊዜ= Server + AI + Policy Filter + CDN
በላይቭ ስትሪም = Streaming Server + AI በቀጥታ + CDN በመሆን በቀላሉ 😎 ይሰራል ማለት ነው።

#TechEthiopia #TikTok #tech #ቲክቶክ #ቴክኖሎጂ #programming #datacenters

CompuTech©
👍2
Name:- Shou Zi Chew
TikTok CEO
Born :- 1 January 1983 (age 42)
Singapore
Education:- University College London (BSc)
Harvard University (MBA)
Occupation Business:- executive Years active2006–present
Title:- Former CFO of Xiaomi (2015–2021) ,Former CFO of Byte Dance (2021)
CEO of TikTok (since 2021)

CompuTech©
👍1
Microsoft Word

👇

CompuTech©
👍3
ማይክሮሶፍት ኦፊስ ወርድ - Microsoft Word አጠቃቀም።
📘 መነሻ መምሪያ:-
🔹 Microsoft Word ምንድነው?
Microsoft Word የውል ወረቀት፣ የጽሁፍ ስራ፣ የመመዝገቢያ ወረቀት እና የማብራሪያ ሰነዶችን ለመዘጋጀት ፣ ለአጠቃላይ ጽሁፍ ስራ የሚጠቅመን የመተግበሪያ ሶፍርዌር ነው።
በተለያየም የስራ ዘርፎች ላይ እና ለግላዊ ነገሮች ላይ ልንጠቀምበት እንችላለን።
Microsoft Word ላይ ያሉት የMenu Tabs  የተለያየ ባህሪ አላቸው እነሱም ቀለል ባለ መልኩ እንይ :-
📝 Microsoft Word ዋና ሌብሎች Tabs
1. Home (መነሻ)
ጽሁፍ ለማስተካከል እና ለማስዋብ  ወዘተ.. toolችን አካቷል።
• Font → የፊደል አይነት፣ መጠን፣ ቀለም፣ (Bold/Italic/Underline)
• Paragraph → Alignment: ግራ/መሀከል/ቀኝ፣ የነጥብ ዝርዝር (Bullets, Numbers)፣ መለያ መስመር (Borders)
• Styles → አዘገጃጀት አማራጮች (Heading-  Title…)
2. Insert (ማስገቢያ) 
ከውጭ ወይም አዛው አንዳንድ ነገሮችን ለማስገባት ይጠቅማል።
• Pages → አዲስ ገጽ (Blank Page- Cover Page- Page Break)
• Tables → ሰንጠረዥ ማስገቢያ
• Pictures / Online Pictures → ምስል ማስገቢያ
• Shapes / Icons / SmartArt / Chart → ቅርጸ-ቅርጾች እና ግራፎች ለማስገባት
• Header & Footer → የራስጌ እና የግርጌ ጽሑፍ
• Page Number → የገጽ ቁጥር ለመስጠት ይጠቅመናል
3. Page Layout / Page Setup ለገጽ አቀማመጥ
የገጽ አቀማመጥን ለማስተካከል
• Margins → የገጽ ድንበር (Top፣ Bottom ፣ Left፣ Right)
• Orientation → አቀማመጥ (Portrait) – በቁመት እና (Landscape) – ወደ ጎን ስፋት
• Size → የወረቀት መጠን (A4፣ A3፣ Letter…)
• Columns → ጽሑፍን በአምድ ለመከፋፈል
• Breaks → የገጽ/አምድ ለመከፋፈል
4. Design (ዲዛይን / አዘገጃጀት)
የሰነድ ቅርጽና አዘገጃጀት ለማስዋብ ይረዳናል
• Themes → የሰነድ ቀለም እና ፊደል አቀማመጥ
• Colors & Fonts → የቀለም እና የፊደል አይነት ዝርዝር
• Page Background → የገጽ ቀለም (Page Color)፣ ከስር የሚገባ ጽሁፍ (Watermark)፣ የገጽ አይነት ድንበር  (Page Borders)
5. References (ማጣቀሻዎች)
ማጣቀሻ ዝርዝርና ቁጥር ከፈለጉ በእርግጥ እዚህ ውስጥ ይገኛል።
• Table of Contents → የይዘት ማውጫ
• Footnotes → የግርጌ ማስታወሻ
• Citations & Bibliography → ማጣቀሻ እና የምንጭ ዝርዝር
• Captions → ምስል ወይም ሰንጠረዥ ላይ ርዕስ መጨመር
• Index → ማውጫ /ማስገቢያ
6. Mailings (ደብዳቤዎች)
በተለይ የብዙ ሰዎችን ሰነድ እንዲቀበሉ ሲፈልጉ ፡ የኢሜይል/ደብዳቤ ስርጭት ከተፈለገ በዚህ ላይ አለ
• Envelopes → ፖስታ
• Labels → ለመለያ ቁጥር
• Mail Merge → ለብዙ ተቀባይ አንድ ሰነድ ለመላክ
7. Review (ግምገማ)
ሰነድን ለመፈትሽና ለማጥናት
• Spelling & Grammar → ቃላትና ሰዋሰውን ለማረም
• Thesaurus → ተመሳሳይ ቃላት መፈለጊያ
• Word Count → የቃላት ቁጥር
• Translate → ትርጉም ለመስራት
• Comments → ማስታወሻ ለመጨመር
• Track Changes → የተደረጉ ለውጦች ለመከታተል
8. View (እይታ)
የሰነድ እይታን ለመቀየር።
• Read Mode → ለንባብ ዕይታ ለማስተካከል
• Print Layout → ወረቀቱ ከመታተሙ በፊት እንዴት እንደሚታይ ለማየት
• Web Layout → በድህረገፅ እንደሚታይ
• Zoom → ማጉላት/መቀነስ
• Multiple Windows / Split → ሰነድን በክፍል ክፍል ለማሳየት

Home - Insert - Page Layout/Setup ሁሉም ለጽሁፍ ሰነድ ስራ የመጀመሪያ ዋነኛ የሆኑ ናቸው።
Designed – References – Mailings – Review – View ደግሞ የሰነዱን ጥራት፣ ዝርዝር፣ ማስተካከያና ማስተዳደሪያ የሚጠቅመን ነው ።

ይቀጥላል....
ማይክሮሶፍት ወርድ እንዴት ልጀምር ?
መጀመሪያ የማይክሮሶፍት ምርት የሆነው የ ኦፊስ ሶፍትዌርን በኮምፒውተራችን መጫን አለብን  በተለያየም አይነት እና ቨርዥን ይገኛል።  ከዛ
 1. የ Microsoft Word ፕሮግራም መክፈት
 2. አዲስ ሰነድ (Blank Document) ከHome ሜኑ ይምረጡ
3. ጽሁፍዎን ይፃፉ
 4. ፊደል አይነት (Font) እና መጠን ለመቀየር Home ታብ ይጠቀሙ
 5. ሰነዱን ለማስቀመጥ Ctrl + S ይጫኑ
📘  የፊደል እና ጽሁፍ አስተካከያ
🔹 ፊደል (Font) ለመቀየር:
• Home → Font box → ፊደል አይነት ምረጥ
🔹 መጠን (Size) ለመለወጥ:
• Font Size box → ቁጥር ምረጥ (እንደ 12, 14, 16…)
🔹 የጽሁፍ ቀለም:
• Home → Font Color 🎨
📘 የተለመዱ የኪቦርድ አቋራጭ መንገዶች (Shortcuts)
         Ctrl + C → ለ ኮፒ
         Ctrl + V → ለ ፔስት
         Ctrl + X → ቦታ ለመቀየር ( ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ለመቀየር ይረዳናል)
        Ctrl + Z → ያደረግነውን ድርጊት ለ መተው ለምሳሌ ፅሁፍ ፅፈን ከታች መስመር(underline) "አድርገን ካልተመቸን ወደነበረበት ለመመለስ ይረዳናል"
        Ctrl + P → Print (ወረቀት ለማተም)


CompuTech©
👍3
SQL (Structured Query Language)


CompuTech©
👍1
ዛሬ ስለ SQL ምንነት ለማየት እንሞክራለን።
ስለ ፕሮግራሚንግ  መሠረታዊ  የተግባር ትምህርቶችን ከዚህ በኋላ ለማየት እንሞክራለን።
ይህ ቻናል ለጀማሪዎች፣ መነሳሻ ይሆናቸዋል ብለን እናስባለን።
SQL ምንድነው ?
SQL (Structured Query Language) የዳታ መዝገቦችን ለመቆጣጠር፣ ለመፈለግ፣ ለመጨመር፣ ለማስተካከል እና ለማጥፋት የምንጠቀምበት ቋንቋ ነው።
በቀላሉ "SQL"  መረጃን ለመቆጣጠር እና ለማስተዳደር የምንጠቀምበት የቋንቋ አይነት ነው።
💡 ለምን አስፈላጊ ነው?
• የመረጃ መዝገቦችን በስርዓት ያያይዛል
• መረጃን በቀላሉ ለመፈለግ ያስችላል
• በድር መተግበሪያዎች፣ የኩባንያ ስራዎች እና ለዳታ ትንተና ስራዎች ሁሉ ውስጥ ይጠቀመናል።
🧠 መሠረታዊ  የቋንቋ ህጎች

👉 SELECT → መረጃ ለማንበብ
👉 INSERT → መረጃ ያስገባል
👉UPDATE → መረጃ ለማስተካከል
👉 DELETE → መረጃ ለማጥፋት

🧩 ለምሳሌ
SELECT name age FROM students WHERE age > 18;
ይህ ከstudents ዳታ ሰንጠረዥ ውስጥ እድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ የሆኑትን ተማሪዎች ያወጣል።
🧩 SQL ውስጥ መረጃ እንዴት እናስገባለን (INSERT)
በSQL ውስጥ አዲስ መረጃ ወደ ሰንጠረዥ (table) ለመጨመር የምንጠቀምበት ትዕዛዝ INSERT ተብሎ ይታወቃል።
ይህ ትዕዛዝ አዲስ መዝገብ (record) እንዲገባ ያደርግልናል።
💡አቀራረቡም
" INSERT INTO ሰንጠረዥ_ስም (column1, column2, column3) VALUES (value1, value2, value3); "
🧠 ለምሳሌ
INSERT INTO students (name, age, grade) VALUES ('Eleni', 20, 'A');
እዚህ እንደምናየው፣ እሌኒ የተባለች አዲስ ተማሪ   ዕድሜዋን "20" እና ደረጃዋን  “A”መረጃዎች ያስገባል።
🎯 በአንድ ጊዜ ብዙ ዳታ ለማስገባት
INSERT INTO students (name, age, grade)
VALUES
('Kebede', 22, 'B+'),
('Marta', 19, 'A-'),
('Tadesse', 21, 'B');
ብዙ ዳታ ስናስገባ እንደዚህ እናስገባለን ማለት ነው።
⚠️ ማስታወሻ
•  columns እና  values በትክክል አስገቡ ።
• የመነሻ መለያ (Primary Key) ያለው ኮሎመን ከሆነ፣ value ላይ የማይደገም (unique ) መሆኑን አረጋግጡ።
🚀 መደምደሚያ
SQL በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ለዓለም እጅግ አስፈላጊ ነው።
የዳታ መረጃን ለመቆጣጠር፣ ለማስተናገድ እና ለመተግበር የሚረዳን መሰረታዊ መሳሪያ ነው።
📍 በቀጣይ ደግሞ ፦
“SQL ሌላኛውን ትዕዛዝ የምናይ ይሆናል።
#SQL #programming #Database #እንማር_coding
#coding

CompuTech©
👍21
የደህንነት ምክሮች ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
***
የሳይበር ደህንነት ወርን ለ2ኛ ጊዜ “የታመነ የባንክ አገልግሎት በዜሮ ትረስት ደህንነት” (Zero Trust Security for Trusted Banking Services) በሚል መሪ ቃል እያከበረ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፣
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ያዘጋጀው ከላይ ያለውን የደህንነት ምክር ተግባራዊ በማድረግ የሂሳብዎን ደህንነት ይጠብቁ።
***


CompuTech©
#ደህንነት #news
#Cybersecurity #Cybersecurity #ቴክኖሎጂ #technews #Cybersecurityawarenessmonth #zero_trust
እንግዲህ እኛ! 😊 ዛሬ እንዴት ኳስ በቀጥታ ለማየት ቻልን በጣም በተቀናጀ የሰው እና የቴክኖሎጂ ውጤቶች አልፎ ማየት እንዴት ቻልን ?
እስቲ ስለዚህ ቀለል ባለ መንገድ የተዘጋጀ መረጃ አለን፣ እናም በተለይ
በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የሚካሄዱ የቀጥታ ቪዲዮ ስርጭቶች እንዴት ወደ ተመልካች ይደርሳል በሚል ዙሪያ ቀለል ያለ መረጃ  ልናካፍላቹ ወደድን።
👍1
⚽️  የቀጥታ ሊግ የኳስ ስርጭት እንዴት ይከናወናል በመጀመሪያ  ለቀጥታ ስርጭት በተሳካ መልኩ ለተመልካች እንዲደርስ የሚረዱ ነገሮች:-
Control Room” እና “OB Truck (Outside Broadcast Truck)” (ተንቀሳቃሽ የስርጭት መቆጣጠሪያ መኪና) ሁለቱም በእግር ኳስ ጨዋታ ስርጭት ውስጥ በጣም አስፈላጊ  ናቸው።
እንደ  የቦታቸው እና ተግባራቸው ቢለያዩም ማለት ነው።
ምንድናቸው 👇
🎛️ 1. Control Room (የቁጥጥር ክፍል)
ይህ በቴሌቪዥን ኩባንያ ወይም የስርጭት ማዕከል ውስጥ የሚገኝ ክፍል ነው።
በውስጡም የቪዲዮ እና የድምፅ ቴክኒሽኖች ስርጭቱን በትክክል ይቆጣጠራሉ።
ዋና ተግባራቸው፦
የቪዲዮ መምረጫው የትኛው ካሜራ ይታይ ወይም Cam 12/15  እንደሚሆን ይወስናሉ
የድምፅ መቀነስ እና ማቀናበር
የተለያዩ ገጽታዎች (graphics፣ score boards፣ timer፣ logos እንዲገባ ፣
ቪዲዮን ለማቀነባበር እና ለመላክ ዝግጁ ሲሆን ማለት ነው።
ቀጥታ ስርጭቱም አየር ላይ ከዋለም በኋሏ ለ መከታተል ይረዳል።
በ መቆጣጠሪያ ክፍል ውስጥ የተለያዩ መሳሪያ ዎች አሉ ፣ Vision Mixer ፣ Audio Mixer ፣Monitors፣ Intercom System፣ Recording Replay systems
🚛 2. OB Truck (Outside Broadcast Truck)
ይህ እንደ ተንቀሳቃሽ የControl Room ተመሳሳይ ነው።
እንደ ታንስሚሽን መኪና (broadcast van) ይታወቃል።
በመስክ ዙሪያ (በስታዲየም በኩል) ይቆማል እና በዚያ ውስጥ ቪዲዮን በቀጥታ ተቀናብረው አየር ላይ ይውላሉ።
ዋና ተግባራቸው፦
ከመስክ ካሜራዎች ቪዲዮ በመቀበል
ዳይሬክተሩ  ቪዲዮ እና ድምፅን በቀጥታ እንዲ ስተካከል በማዘዝ
ቪዲዮ ተቀነባብሮ በ
(Encoding)
ወደ Satellite / Fiber cables ይሰራጫሉ።
በ OB ውስጥ ልክ እንደ CR ሁሉ ተመሳሳይ መሳሪያዎች አሉ፦
12–20+ የካሜራ የሚገኙትን ተግባራትን ወደ Vision Mixer፣ ከድምፅ መሳሪያ የሚገኙትን ደግሞ ወደ
Audio Mixing እናም ሌሎች የ console
የReplay መሳሪያ EVS ፣ Slow motion systems
የPower Supply, Air Conditioning, Communication systems ይገኛሉ
📊 ስለዚህ በእግር ኳስ ጨዋታ ወቅት OB Truck በመስክ ዙሪያ በመቆም፣ ስርጭቱ በSatellite ወደ Control Room ይላካል።
የስርጭቱን ክንውን ምን ይመስላል ?
በቅድሚያ 🎥  ካሜራች
• ለምሳሌ በእያንዳንዱ የፕሪምየር ሊግ ጨዋታ በአማካይ ከ20 እስከ 30 እናም ከዛ በላይ cam ሊጠቀሙ ይችላሉ
የተወሰኑት cam አይነቶች:-
🎯 ዋና ካሜራ (Main Camera)
🕊️ ከላይ ያለ ካሜራ (Spider Cam)
🚀 የጎን ካሜራዎች (Touchline & Goal Cameras)
🧍‍♂️ የተጫዋች እና አሰልጣኞች ካሜራዎች
🎥 የVAR ካሜራዎች (በተለይ ለውሳኔ ማጣሪያ)
⚙️ እንዴት ከካሜራ ወደ OB Truck ይገናኛሉ ?
• እያንዳንዱ ካሜራ በ SMPTE Fiber Cable ወይም Triax Cable ወደ OB  ይገናኛል።
• በ OB ትራክ ውስጥ ያለው CCU (Camera Control Unit) የካሜራውን ብርሃን፣ ቀለም እና መድረክ ይቆጣጠራል።
• የካሜራው ምስል በዚያ ትራክ ውስጥ በ Vision Mixer በኩል ዲስፕለይ ላይ ይደረደራል።
🎚️ በተጨማሪም በ OB Truck ውስጥ
• Director –  የታየውን ካሜራ እንዲመርጥ ለኦፕሬተሩ  ትዕዛዝ ይሰጣል። (“Camera 3, ready... take 3!”). ይቀይራል።
• Vision Mixer –  በመጠቀም ኦፕሬተር ካሜራዎችን በቀጥታ  ይቀያይራል።
• Sound Mixer – የደጋፊ ድምፅ፣ ሜዳ   የኮሜንተሪዎችን ድምፅ ተግባር በተያያዘ ያዋህዳል።
• Graphics System – የስኮር /የቡድን ሚኑ፣ የተጫዋች ስም፣ ዲስፕለይ ላይ  እንዲታይ ያደርጋል።
📡 ከ OB ትራክ ወደ አየር ላይ የሚውለውም
• የተዘጋጀው ዋና ፕሮግራም (PGM Feed) በ Satellite Uplink ወይም Fiber Connection ወደ የብሮድካስት ማዕከል ይላካል።
• ከዚያም አየር ላይ ይውላል።
•  ለምሳሌ ያክል ወደ Sky Sports፣ BBC, SuperSport፣ የመሳሰሉ የኳስ ስርጭት አቅራቢዎች ይደርሳል።
• ወደ ተመልካችም  በቴሌቪዥን ወይም በመስመር ላይ በቀጥታ ይደርሳል።
🧠  ማጠቃለያ
⚽️ ከካሜራ ወደ OB ትራክ → ከዚያ ወደ ሳተላይት → እና በመጨረሻ አየር ላይ ይውላል።📺🌍

CompuTech©
👏2
🌐 API ምንድ ነው?
API (Application Programming Interface) ማለት፣ ኮምፒውተሮች እርስ በእርሳቸው እንዲነጋገሩ የሚያስችል መንገድ ነው።
👉 API እንደ መልእክት ለመላክ የሚያግዝ ነው።  አንድ መተግበሪያ ከሌላ መተግበሪያ ጋር ለመግባት ይጠቅማል።
💡 ለምሳሌ በቀላሉ

• አንተ በቴሌግራም ቻናል መልእክት መላክ ትፈልጋለህ እንበል፡ ነገር ግን ኮምፒውተሩ ትዕዛዝህን  አያውቅም ስለዚህ API ገብቶ፤ እሱ እንደ ተርጓሚ ሆኖ — ትዕዛዝህን ይተርጉማል።

⚙️ተጨማሪ ምሳሌ – የTelegram API
በTelegram API:-
• መልዕክቶች በራስ /auto መልዕክት  ለመላክ  🤖
• ተጠቃሚዎችን መቀበል  👥
• ፎቶ እና ፋይሎች ለመላክ 📷📁
• አዲስ  “bot” አገልግሎት መፍጠር

🧠 በአጠቃላይ
API ማለት፣ ኮምፒውተሮች በመረጃ መንገድ በማገናኘት ስራ እንዲሰሩ የሚያስችል መተግበሪያ መንገድ ነው።
ልክ ሰዎች እርስ በእርሳቸው ለመግባባት   ቋንቋ ግድ እንደሆነው ሁሉ ፣ ለኮምፒውተሮች ደግሞ API  ያስፈልጋቸዋል።
እናም APIን በብዙ ቦታዎች ልንጠቀምበት እንችላለን።

#api #telegramapi #technews
#programming #ቴክኖሎጂ #TechEthiopia

CompuTech©
👍2