CompuTech©️
163 subscribers
360 photos
169 videos
28 files
208 links
Tech Update info
Computer and phones Security's
Computer Software Tips
Mobile Application Tips
Tutorial Point


Update " Yourself & Grow Knowledge also the Persons around you "
Download Telegram
🖥 Server Computer 🖥
👍2
Server Computer
📌 ሰርቨር ኮምፒዩተር ምንድነው?
• ሰርቨር ኮምፒዩተር = ለኮምፒዩተሮች ወይም ለሎሎች ዲቫይሶች አገልግሎት የሚሰጥ ልዩ ኮምፒዩተር ነው።
ለተለያየ አገልግሎት ልንጠቀምበት እንችላለን።
በሌላ አባባል ሰርቨር = አገልጋይ ኮምፒዩተር ማለት ነው 🖥️
🔑 ባህሪው
• 24/7 ይሰራል
• ከመደበኛ ኮምፒዩተር የተለየ አቅም አለው ፣ፕሮሰሰር ፍጥነት፣ RAM፣ Storage።
• በኔትወርክ  ለብዙ ሰዎች አገልግሎት መስጠት ይችላል።
• ለሰርቨር አገልግሎት የሚሆን ስርዓት ወይም OS ነው የሚጫንበት ለምሳሌ:- Microsoft Server ፣ Oracle Database server ፣ ሌሎችም።
🖥️ የሰርቨር አይነቶች
1️⃣ 🌐 ዌብ ሰርቨር (Web Server)
• ዌብሳይት አገልግሎት ።
ምሳሌ፡ Apache, Nginx
2️⃣ 🗄️ ዳታቤዝ ሰርቨር (Database Server)
• መረጃን ያከማቻል እና ያቀርባል።
   ምሳሌ፡ MySQL, Oracle DB
3️⃣ 📂 ፋይል ሰርቨር (File Server)
• ፋይሎችን ለመጋራት የሚያገለግል።
4️⃣ 📧 ኢሜይል ሰርቨር (Mail Server)
• ኢሜይል ይቀበላል እና ይልካል።
   ምሳሌ፡ Microsoft Exchange, Postfix
5️⃣ 🎮 ጌም ሰርቨር (Game Server)
• ኦንላይን ጨዋታዎችን ለማካሄድ።
6️⃣ 🎥 ሚዲያ/ስትሪሚንግ ሰርቨር (Media/Streaming Server)
• ቪዲዮና ድምፅ በቀጥታ ለማስተላለፍ።
   ምሳሌ፡ YouTube, Netflix ፣ Tiktok servers
7️⃣ 🛠️ አፕሊኬሽን ሰርቨር (Application Server)
• ሶፍትዌር አፕሊኬሽኖችን እንዲሰሩ የሚያግዝ።
  ምሳሌ፡ Tomcat, JBoss
8️⃣ 🖨️ ፕሪንት ሰርቨር (Print Server)
• በኔትወርክ ላይ ያሉ ኮምፒዩተሮችን በአንድ ፕሪንተር አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ።
9️⃣ 🔒 ፕሮክሲ ሰርቨር (Proxy Server) " ምን እንደሆነ በሌላ ግዜ የምናየው ይሆናል" 👍
🔟 🌍 DNS ሰርቨር (Domain Name Server)
• የዌብሳይት ስም (example.com) ወደ IP አድራሻ የሚቀይር።
🔐 Authentication Server (የተጠቃሚ መለያ ማረጋገጫ)
• የመግቢያ መለያ (username/password) ማረጋገጥ።
📊 Analytics Server
• የተጠቃሚዎች እንቅስቃሴን መመዝገብ እና ትንታኔ ማድረግ።

🌍 በዕለት ተዕለት ህይወትህ ላይ የምትጠቀምበትን ማህበራዊ ሚዲያ ለምሳሌ ያክል ላሳይህ:)
• የፌስቡክ አካውንትህን ከፈትክ  መረጃ ስታይ በፌስቡክ ሰርቨር ነው።
• YouTube ላይ ቪዲዮ ከፍተህ ስታይ ከ ዩቲዩብ የሰርቨር አይነቶች ነው።

👉 በአጠቃላይ ሰርቨሮች ለልዩ ልዩ ስራ  የተሰሩ ኮምፒዩተሮች ናቸው።

CompuTech©
👍3
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🙏1
Technology news 👇

🌐 ቻይና የዓለም የመጀመሪያውን የ10G ኢንተርኔት መስመር አስጀመረች!
🇨🇳 በ2025 April ቻይና በሄቤይ ግዛት ውስጥ በ ሲዮንጋን (Xiong’an) ከተማ ከዓለም የመጀመሪያው የ10 ጊጋቢት ብሮድባንድ (10G Internet) መስመር መጀመሯን አስታወቀች።
ይህ የ 10ኛው ትውልድ ዋና ተግባራቱም
• የመውረድ (Download) ፍጥነት፡ እስከ 9.8 Gbps
• የመጫን (Upload)፡ እስከ 1 Gbps
• ዝግጅት (Latency)፡ እስከ 3 milliseconds
• ማለትም የ20GB ፊልም በአንድ ደቂቃ በታች 😱 ይወርዳል!
🎯 የተዘጋጀበት ዋና አላማውም
• ለ8K ቪዲዮ ስትሪሚንግ
• ምናብ/ምስል ቨርቹዋል ሪያሊቲ (AR/VR)
• ለቴሌ ሜዲሰን የርቀት ህክምና ግልጋሎት
• ለመማር ለማስተማር እና ለሰው አልባ መኪናዎች

ውዶቼ 🤗10G እንድትረዱት ያክል:-
• የ“10G” ማለት አስረኛው ትውልድ የኢንተርኔት ፍጥነትን ለማመላከት ነው ፡ፍጥነቱም  10 ጊጋቢት በሰከንድ ነው፣ እንጂ እንደ  5G የሚለው  (Generation) ለማመላከት  አይደለም።
• ማለትም የፋይበር broadband እንጂ ሞባይል ኔትዎርክ አይደለም ለማለት ያክል ነው።
👉 ቻይና በዓለም የበለጠ ፈጣን ኢንተርኔት ስርዓት በማምጣት ሌሎች አገሮች ተሞክሮ እያደረገች ለ አመታት ቆይታለች።

ይመቻት👍

CompuTech©
👍3
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ድል ለሀገሬ ኢትዮጵያ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹 💪
Title:- Facebook founder
Co-founder, chairman and CEO of Meta Platforms and Facebook
Co-founder and co-CEO of Chan Zuckerberg Initiative

Name :- Mark Elliot Zuckerberg
Born:- May 14, 1984 (age 41)
White Plains, New York, U.S.
Harvard University (dropped out)
Occupations :- Businessman
computer programmer
Years active :- 2004–present

CompuTech©
👍31
የ 12ኛ ክፍል የማትሪክ ውጤት ከታች ባሉት ፖርታል መመልከት ትችላላቹ:-

ፖርታል 👉 result.neaea.gov.et

በአጭር የፅሁፍ መልዕክት 👉 6284 "R" አስቀድመን የመለያ ቁጥር አስገብቶ በመላክ ውጤታችሁን ማወቅ ትችላላቹ።
👉 እንደ አማራጭ የቴሌግራም ቦት አዘጋጅተዋል በዚህም ማየት ትችላላቹ።
ተስፋ አለን ከ48ሺዎቹ አንዱ እንደምትሆኑ😎😂
CompuTech©
👍2
TikTok Data Center
TikTok Data Center
📌 TikTok ዳታ ማዕከል
ያው ዳታ ሴንተር ውስጥ ልናገኛቸው ከምንችላቸው አንዱ ሰርቨር ነው።
   TikTok ሰርቨር
• የTikTok ዳታ መዓከል ልክ እንደ ሌሎች ማህበራዊ መድረኮች እንደ Facebook, YouTube በመሳሰሉት እንዳላቸው ሁሉ የሚሰሩ ትልቅ አቅም ያላቸው ኮምፒዩተሮች (Servers) አሉት።
• እነዚህ ሰርቨሮች ቪዲዮ፣ ኮሜንት፣ ላይክ ወዘተ ሁሉንም የተጠቃሚ መረጃ ይቀበላሉ እና ይቆጣጠራሉ።
   ዳታ ማዕከል (Data Center)
• ዳታ ማዕከል ብዙ ሰርቨሮችን በአንድ ቦታ የሚያከማች ትልቅ ቦታ ላይ ያረፈ  ነው።
        TikTok በብዙ አገሮች ዳታ ማዕከል አለው
  ለምሳሌ:-
🇸🇬 ሲንጋፖር፣ 🇮🇪 አየርላንድ (Europe ዳታ ማዕከል)፣ 🇺🇸 አሜሪካ ፣ (Oracle ካምፓኒ ጋር)
• እነዚህ ዳታ ማዕከሎች የተጠቃሚዎች መረጃ በአገራቸው እንዲቀመጥ ያደርጋሉ።
  ለምን አስፈላጊ ሆኑ ?
• የፍጥነት ጥበቃ (Fast streaming & loading)
• ደህንነት ለማስከበር (User data privacy)
• የአገር ህግ እንዲከተል አውሮፓ የሚጠይቁት በተለይ  አሜሪካ።

⚙️ TikTok Back-End እንዴት ይሰራል?
1. Client → Server :-ግንኙነት
• እኛ Appን ተጠቀመን  ቪዲዮ ስንጭን (Upload) ወይም ስንመለከት (Watch)፣
• የአፕሊኬሽኑ መረጃ (Request) ወደ TikTok ሰርቨር ይሄዳል።
• ሰርቨሩ የምንፈልገውን ዳታ በመመልስ ወደ reels ያስገባል።
2. Main Components በ Back-End ላይ እንሆ:-
• API Gateway:- ለምሳሌ ተጠቃሚው ከስልክ የላከውን መልእክት ወደ ትክክለኛው ሰርቨር ይልካል።
• Application Servers:- የመረጃ ሂደትን ያከናውናሉ፣ ለምሳሌ ቪዲዮ ማስተካከል፣ ኮሜንት መጨመር፣ አልጎርይዝም እንዲሰራ ማዘጋጀት።
• Database (DB):-የተጠቃሚ መረጃ፣ የፎሎወር ዝርዝር፣ ኮሜንት፣ ወዘተ ይቀመጣሉ።
• Content Delivery Network (CDN):-ቪዲዮዎችን በቅርብ ዳታ ማዕከል እንዲጫኑ ይረዳል፣ ስለዚህ እጅግ ፈጣን ሂደቶች ነው ያሉት።
• Recommendation Engine (AI/ML):-በአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ ተመስርቶ የሚሰራ አልጎርይዝም፣ የምንመለከተውን ይታወቃል እና እንደ "For You Page" ይሰጠናል።
3. ሂደቱ ምን እንደሚመስል በተወሰነ መልኩ
• ቪዲዮ መጫን → API Gateway ይቀበላል
• Application Server ቪዲዮውን ያስተካክላል (compress, encode)
• Database ተጠቃሚ መረጃ እና ስም ይመዝገባል
• CDN ወደ ቅርብ አገር ያስቀመጣል
• AI እንደ ፍላጎትህ ቪዲዮውን ወደ "Feed" ይጨምራል
4. ቴክኖሎጂዎች
• Programming: Python, Go, Java etc
• Database: MySQL, Redis, Cassandra
• CDN: Akamai, TikTok Edge Servers
• AI/ML: Deep Learning Models
👉 እንዲህ 😂 በቀላሉ ነው TikTok Back-End የሚሰራው።

በሚቀጥለው ስለ Community Guide line policy የምናይ ይሆናል 👍

CompuTech©
👏2👍1
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እያንዳንዱ ሞባይል “የእስራኤል እጅ” አለበት  ሲሉ በቅርቡ ተናግረዋል።

ይህ መግለጫ የወጣው ፔጋሰስ ስፓይዌር ኩባንያ በአለም አቀፍ የክትትል ተቋም ሲደረግበት ሲሆን በሊባኖስ የቴል አቪቭ ፔጀር የስልክ ጥቃት እስራኤል በመገናኛ ቴክኖሎጂ ውስጥ ያላትን ጥልቅ ተሳትፎ ያሳየ እነደነበር አይረሴ ነው።

ማሳሰቢያ:-
ይህ ይዘት ለመረጃ እና ግንዛቤ ዓላማዎች ብቻ  ነው። የየትኛውንም የፖለቲካ አመለካከት ወይም ፓርቲ ድጋፍ አይወክልም።

#technology #tech #news #TechEthiopia

Computech©
🔥1
TikTok Community Guideline Policy !!
የ ቲክቶክ ማህበራዊ በተዳደሪያ ደንብ ከ ቴክኖሎጂ አንፃር እንዴት ይሰራል ? 🤔
እንዴትስ ይተገበራል ?
👇
CompuTech©
👍2