CompuTech©️
167 subscribers
366 photos
169 videos
28 files
208 links
Tech Update info
Computer and phones Security's
Computer Software Tips
Mobile Application Tips
Tutorial Point


Update " Yourself & Grow Knowledge also the Persons around you "
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Website Developers (EX)

Junior and Senior

CompuTech©
👍2
Smart phone comparison

Samsung Galaxy A15 and A16
የተሻለውስ የቱ ነው ?


CompuTech©
👍2
📱 Samsung Galaxy A15 vs Galaxy A16 — Full Comparison
ሁለቱን ስልኮች ለማነፃፀር እንሞክር፣
የተሻለውስ የትኛው ነው?
🗓️ Release & Software
ለ ተጠቃሚ የቀረበበት ቀን እና ሶፍትዌር ቨርዥን
• Galaxy A15: 📅 Dec 2023
• Android 14 (One UI 6.0)
📥 4 ዓመት updates(አንድሮይድ ማዘመን)
• Galaxy A16: 📅 Oct 2024
• Android 14 (One UI 6.1)
📥 6 ዓመት updates
🖥️ Display & Design(ምስል ጥራት )
• A15:- 6.5" Super AMOLED
• 1080×2340 resolution
• 90Hz refresh rate ~800 nits brightness
• A16: 6.7" Super AMOLED
• 1080×2340 resolution
• 90Hz refresh rate ~800 nits brightness
IP54 dust/splash resistant
⚙️ Performance( አፈፃፀም/ ብቃት (CPU/GPU)
• A15 (4G): MediaTek Helio G99
• AnTuTu ~380K
• Geekbench ~660 (single-core)
• A16 (5G):-
•  Exynos 1330 or Dimensity 6300
• AnTuTu ~410K
• Geekbench ~990 (single-core)
📈 ~30–50% የተሻለ performance!
💾 Memory & Storage
• ሁለቱም ተመሳሳይ:
• 4GB/6GB/8GB RAM
• 128GB or 256GB storage
• microSD slot:-
▫️ A15: up to 1TB
▫️ A16: up to 1.5TB
📸 Camera
ሁለቱም ተመሳሳይ
📷 Rear(የኋላ):-
• 50MP main
• 5MP ultrawide
• 2MP macro
🤳 Front(ፍለፊት): 13MP
🎥 Video: 1080p @ 30fps
🔁 ምስል ጥራት ሁለቱም ተመሳሳይ
🔋 Battery & Charging
Both:- ሁለቱም 👇
🔋 5000mAh battery
25W fast charging
🔌 Battery Life:የባትሪ ቆይታ
▫️ A15: Up to 15.5 hours(ሰዓታት)  
▫️ A16: ~12–13 hours
🔋 A15 is በጣም የተሻለ
📶 Connectivity & Features
• A15:-
• 4G only
• Wi-Fi 5, Bluetooth 5.3
• USB-C, NFC, 3.5mm jack
• Side fingerprint scanner
• A16:
5G connectivity
• Dolby Atmos sound
• IP54 rating
• Same ports + sensors
• Slightly better speakers
💵 ዋጋ ግምታዊ
• A15:-💲  18500 ETB–22500 ETB
• A16: 💲20000 ETB–24500 ETB
በመጨረሻም :-ቀጥሎ ባሉት መስፈርቶች Galaxy A16 ብቁ ሆኖ አገኘነው:-
✔️ 5G እና ከ A15 በኋሏ የተመረተ
✔️ በ performance(አፈፃፀም)
✔️ በ software ድጋፍ ለ 6 ዓመታት
✔️  display(ምስል) + Dolby Atmos
✔️ IP54 splash resistance
ቀጥሎ ባሉት መስፈርቶች ደግሞ Galaxy A15 የተሻለ ሆኖ አገኘነው
✔️ Better battery life
✔️ ቀለል ያለ size
✔️  camera ኳሊቲ ሁለቱም እኩል ጥራት አላቸው


Samsung Galaxy A16 5G ቢመረጥ የተሻለ ነው ብለን አሰብን። 👍


CompuTech©
🔥3
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከ RAT Tool ፈጣሪ ይጠብቃቹ 🙏🙏🙏

CompuTech©
😱2
ትላልቅ ታዎቂ የሆኑ የቴክኖሎጂ ድርጅቶች እና አገሮቻቸው:-
1. Apple – United States 🇺🇸
የሚታወቅበት በ iPhones፣ Macs፣ እና iOS os ነው።
2. Microsoft – United States 🇺🇸
ታዎቂ የሆኑትን የ Windows ፣ Office፣ እና cloud services መስራች እና አስተዳዳሪ ነው።
3. Google (Alphabet) – United States 🇺🇸
የሁሉንም ነገር ማፋለጊያ / በ Search engine 🔎 ፣  በ Android os፣ YouTube እና ሌሎችም።
4. Dell Technologies – United States 🇺🇸
ኮምፒውተሮችን እና ሰርቨሮችን በማምረት ይታወቃል።
5. HP (Hewlett-Packard) – United States 🇺🇸
ይሄም በ ኮምፒውተር እና ፕሪንተሮችን በማምረት ብራንዱን ማግዘፍ የቻለ የቴክኖሎጂ ድርጅት ነው።
6. Cisco Systems – United States 🇺🇸
በ ኔትዎርኪንግ እና በ ኢንተርኔት መሰረተ ልማት ቀዳሚ ድርጅት።
7. IBM (International Business Machines) – United States 🇺🇸
ቀደሚው የ computer ድርጅት ነው በ AI እና በ cloud እንዲሁም  mainframe ችን በማዘጋጀት ይታወቃል።
8. Intel – United States 🇺🇸
ትልቁ የኮምፒውተር processors ወይም CPU አምራች ነው።
9. AMD (Advanced Micro Devices) – United States 🇺🇸
ይሄም በ CPU እና ለ ጌሚንግ የሚሆኑ GPUችን ወይም የግራፊክስ ፕሮሰሰሮችን በማምረት ይታወቃል። 
10. Amazon – United States 🇺🇸
በ E-commerce ወይም በ online የንግድ ፕላትፎርም እና ግዙፉ የ AWS cloud services አስተዳዳሪ።

ይቀጥላል 👍

CompuTech©
👍2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
Installation Python Programming by Termux

CompuTech©
🔥21
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Tor Browesr is a different.

Computech©
👍2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
Network Statistics Checking by
Netstat

CompuTech©
👍1
ቆይ ለምን ግን ለምን ? ....!
BYBIT
ባይቢት ከጁላይ 21 ቀን 2025 ጀምሮ በኢትዮጵያ ብር የሚደረገውን ግብይት እናቋርጣለን ብሎዋል ።
ETB ጋር የተያያዙ ሁሉም የ P2P ማስታወቂያዎች የሚያስወግዱ ይሆናል።


wtf!!!!😟

CompuTech©
😱2
Top fives secure 🔓 internet browsers


CompuTech©
Top 5 Secure 🔐 Browsers/ አምስት የኢንተርኔት አሳሾች
📌 በጣም አሪፍ ደህንነታቸው የተጠበቀ የኢንተርኔት አሳሾች /browsers
በ2025 ከፍተኛ ደህንነታቸው የተጠበቀ 5  አሳሾች /browsers ከታች ለመዘርዘር ሞክረናል።
እያንዳንዳቸውም ጠንካራ የግላዊነት እና የደህንነት ችሎታዎች አሏቸው።
የኢንተርኔት አሳሾች(Browsers):-
1. Brave
• ምርጥነቱም:- ፍጥነት እና አብሮገንቢነት ጥበቃ የሚፈልጉ በግላዊነት ላይ ያተኮሩ ለ ተጠቃሚዎች ትኩረት የሚሰጥ
• የደህንነት ባህሪያት-፡ማስታወቂያዎችን፣ መከታተያዎችን፣ የጣት አሻራዎችን እና የሶስተኛ ወገን ኩኪዎችን  ያግዳል።
• በሁሉም ቦታ በ HTTPS መስራቱ ።
• የግል አሰሳ በቶር(Tor) አማራጭ አለው።
•ለ ዊንዶውስ፣ ማክ፣ ሊኑክስ፣ አንድሮይድ፣ አይኦኤስ ስርዓቶች የሚሆን።
2. Mozilla Firefox with privacy tweaks/ ከግላዊነት ማስተካከያዎች ጋር
• ምርጥነቱም ፡-  ክፍት ምንጭ ደህንነት ለሚፈልጉ ተጠቃሚዎች ማስተካከል ማስቻሉሉ ።
• የደህንነት ባህሪያት፡- የተሻሻለ የመከታተያ ጥበቃ።
• DNS በ HTTPS (DoH) ላይ።
• ሙሉ በሙሉ ክፍት ምንጭ።
ጠቃሚ ምክር፡- ለጠንካራ ጥበቃ Firefox + uBlock Origin + Privacy Badgerን ይጠቀሙ።
• ለ ሁሉም ዋና ስርዓተ ክወናዎች የሚሆን።
3. Tor Browser
• ምርጥ ነገሩም፡ በ ከፍተኛ ደረጃ ማንነትን መደበቅ እና censorship ማለፍ መቻሉ ።
• "censorship": ፀያፍ ፣ ፖለቲካዊ ተቀባይነት የሌላቸው ወይም ለደህንነተ ጠንቅ እንደሆኑ ተደርገው የሚቆጠሩ ጽሁፎችን የሚያስወግድ ነው።
• የደህንነት ባህሪያቱም፡- ኔትወርክ ትራፊክን በቶር ኔትወርክ ውስጥ ያካሄዳል "onion routing" ያሰራጫል።
✔️onion ማለት የበይነመረብ ትራፊክዎ በብዙ layer የተመሰጠረ (encrypted )ነው።
• ስክሪፕቶችን ያግዳል እና የአሳሽ አሻራን ይከለክላል።
• ምንም የአሰሳ ታሪክ/history አያስቀምጥም።
• በትራፊክ ልውውጦች ምክንያት ቀርፋፋ አፈጻጸም ቢኖረውም ምርጥ ነገሮች አሉት።
• ለ ዊንዶውስ፣ ማክኦኤስ፣ ሊኑክስ፣ አንድሮይድ ስርዓቶች ላይ ይጫናል።
4. LibreWolf
• ምርጥነቱም:-  ሃርድኮር ግላዊነት ያለ ቴሌሜትሪ ወይም ክትትል ።
• የደህንነት ባህሪያቱ :-የፋየርፎክስ ፎርክ ከቴሌሜትሪ ጋር ተወግዷል።
• ጠንካራ የግላዊነት ቅንብሮች።
• uBlock መጀመሪያ ተጭኗል።
• ከሞዚላ ሰርቨሮች ጋር ምንም ራስ-ሰር(auto) ግንኙነት የለውም ።
• ለ ዊንዶውስ፣ ማክ፣ ሊኑክስ ስርዓት የሚሆን
5. DuckDuckGo Browser
• ጥሩ ነገሩም፡ ቀለል ባለ ሁኔታ፣ የግል አሰሳ በሞባይል ወይም lightweight ለሆኑ የዴስክቶፕ መጠቀም ማስቻሉ።
• የደህንነት ባህሪያት፡- መከታተያዎችን ያግዳል፣ HTTPSን ያስገድዳል።
• መረጃን በቅጽበት ለማጽዳት fireproofing  cookieችን በ "fire button " አንዴ በመንካት ያስወግዳል ።
• ለ አንድሮይድ፣ አይኦኤስ፣ ለ ዊንዶውስ ስርዓት ደግሞ ቤታ version ።

እያንዳንዳቸው በደህንነት፣ በግላዊነት፣ open-source code፣ በታማኝነታቸው
በመመስረት በጥልቀት አይተን  መርጠናቸዋል።

CompuTech©
World Technology Companies

11. Alibaba – China 🇨🇳
በጣም ታዋቂ  ትልቁ የ  e-commerce ወይም የኦላይን ንግድ መድረክ ነው ፡ ቻይና ውስጥ የcloud ድርጅት አለው ።
12. Meta (Facebook) – United States 🇺🇸
የ Facebook፣ የ Instagram፣ እና የ WhatsApp ባለቤት።
13. Tencent – China 🇨🇳
በ ጌም ጨዋታዎች (gaming) በ ማህበራዊ ሚዲያ  በሆነው በ WeChat ይታወቃል።
14. Tesla – United States 🇺🇸
የኤሌክትሪክ መኪና እና በኢነርጂ ቴክኖሎጂ ዘርፍ ላይ እየሰራ ያለ ትልቅ ድርጅት
15. Samsung – South Korea 🇰🇷
የሚታወቁበት  smartphones፣  በ TV ፣እና በchips።
16. Huawei – China 🇨🇳
እነዚህም የሚታወቁበት በ mobile phones እና በኔትወርክ መሰረተልማቶች በተለይ በ5G ቴክኖሎጂ ።
17. NVIDIA – United States 🇺🇸
GPU / ግራፊክስ ካርድ እና AI ሃርድዌር  በማምረት የሚታወቅ።
18. Oracle – United States 🇺🇸
ትልቁ የዳታቤዝ ፣ ክላውድ እንዲሁም ለ ትላልቅ enterprise /ለድርጅት እና ለተቋማት software ያመርታል ይሸጣል።

ይቀጥላል...!

CompuTech©
👍2
Microsoft Windows 10 64 bit OS Deadline Date

CompuTech©
Windows 10 version 22H2 end of support on October 2025
  የዊንዶውስ 10 የመጨረሻው ዕትም     የድጋፍ ማብቂያ እየተቃረበ ነው።
   ከላይ የምታዩት ፅሁፍ ምስል የማይክሮሶፍት ፅሁፍ ሲሆን የተፃፈውም በኦፊሻል ድህረገፃቸው በ  04/27/2023 እንደ አውሮፓውያን የቀን አቆጣጠር ሲሆን የ Windows 10ን የምርት ላይፍ ታይም ማብቂያ ይናገራል
የድጋፍ ማብቂያ ቀን እና ከዛ ቀን በላይ ማሻሻያዎችን ስለሚያገኙ የተለያዩ እትሞች አብራርተዋል።
የ ዊንዶውስ 10 የመጀመሪያው ቨርዥን  ጥቅም ላይ የዋለው በ ፈረንጆች የቀን አቆጣጠር በ ጁላይ 29 2015 ነበር። የመጨረሻውም የዊንዶውስ ቨርዥን 22H2 ሲሆን በ ኦክቶበር 2022 ለተጠቃሚ ይፋ ተደርጎ እንደነበረ የማይረሳ ነው ። 
  ድጋፍ የሚያበቃበት ቀን በ ኦክቶበር 14  2025 ነው። ይህ ማለት ከዚህ ቀን በኋላ አምራቹ ማይክሮሶፍት ለዊንዶውስ 10 22H2 ይፋዊ ድጋፍ ወይም ዝመናዎችን አያቀርብም ማለት ነው።
ዊንዶውስ 10 ከድጋፍ ማብቂያ ቀን ድረስ ማሻሻያዎችን ማግኘቱን ግን ይቀጥላል።
ድጋፍ የሚያበቃባቸው  ዕትሞችም :-
✔️ Home
✔️ Pro
✔️ Pro Education
✔️ Education
✔️ Pro for Workstations
✔️ Enterprise
✔️ Enterprise multi-session
ያካትታል።  እነዚህ ዕትሞች እስከ መጨረሻው የድጋፍ ቀን ድረስ ወርሃዊ የደህንነት ዝመናዎችን ማግኘታቸውን ይቀጥላሉ።
ነገር ግን  ቀደም ሲል የነበሩው የረጅም ጊዜ አገልግሎት ላይ ያለው ዕትም LTSC (Long-Term Servicig Channel )LTSC ሲብራራ ለዲቫይሶች በተረጋጋ ሁኔታ ስቴብል ሆኖ ለረጅም ጊዜ እንዲያገለግል ታስቦ የተሰራ ሌላኛው የ ዊንዶውስ ቨርዥን ኦኤስ ቤተሰብ ነው። ይሄም ዕትም ላይፍ ታይም ውስጥ በመመርኮዝ ከ ዊንዶውስ  10 ጊዜ ማብቂያ  በላይ  ዝመናዎችን እና ድጋፎችን ይቀጥላሉ ማለት ነው።
ለዊንዶውስ 10 መጫን ሂደቶች አስፈላጊ የሆኑ ዝመናዎችን እና ድጋፎችን ማግኘታቸውን ለማረጋገጥ ተጠቃሚዎች ይህን  መረጃ አይተው የኮምፒውተራችውን ስርዓት ወደ ዊንዶውስ 11 እንዲያዘምኑት እንመክራለን።

እንዴት ድጋፍ ላማግኘት እችላላለሁ ብለው ከጠየቁ መጀመሪያ የኮምፒውተር አቅም ማየት አስፈላጊ ነው። ምክንያቱም የ ዊንዶውስ 11 መጫን ከመጀመሪያችን በፊት መስፈርት ስላለው ማለት ነው።

ዊንዶውስ 11 Requirements /መስፈርቶች እና እንዴት አድርጌ የኮምፒውተሬን መረጃ ማግኘት እችላለሁ  ? ለሚለው ጥያቄ ለመመለስ
  በቀጣይ ጊዜ በቪዲዮ የታገዘ መረጃ የምናቀርብ ይሆናል።

CompuTech©
👍3
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
In 1994 and startup windows 3.11 💿💿💿💿


CompuTech©
👍2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
How to create QR Code for URL

CompuTech©
👍1💯1