CompuTech©️
167 subscribers
366 photos
169 videos
28 files
208 links
Tech Update info
Computer and phones Security's
Computer Software Tips
Mobile Application Tips
Tutorial Point


Update " Yourself & Grow Knowledge also the Persons around you "
Download Telegram
Microsoft Visio

ለምን አገልግሎት ይጠቅመናል ? 🤔


CompuTech©
Microsoft Visio ምንድን ነው?
በማይክሮሶፍት የተሰራ ፕሮፌሽናል ዲያግራም የምንሰራበት ሶፍትዌር ነው።  follow charts ፣ ድርጅታዊ Charts፣ የአውታረ መረብ ንድፎች፣ የወለል ፕላኖች፣ የምህንድስና ድሮዊንግ፣ እና ሌሎችም  የተለያዩ ምስላዊ ሰነዶችን ለመፍጠር ጥቅም ላይ ይውላል።  እንደ Word ወይም Excel ሳይሆን፣ Visio በተለየ መልኩ በመረጃ እና በስርዓቶች ምስላዊ መግለጫዎች ላይ ያተኩራል።

Visio ውስብስብ ንድፎችን ለመሰራት ቀላል ከሚያደርጉ በመቶዎች ከሚቆጠሩ አብሮ የተሰሩ ሞዴሎች እና shapes ወይም ቅርጾች  ተካተው እናገኛቸዋለን ። 
ስለዚህ ከ ዳታ ጋር ማገናኘት ይቻላል።  ሆኖም በቀላሉ ሊንቀሳቀሱ እና በተለዋዋጭ ሼፕ ልናደርገው እንችላለን። 
ለምሳሌ፣ ክሊክ ሊደረጉ የሚችሉ  የሰርቨር ግንኙነቶችን የሚያሳይ የአውታረ መረብ ዲያግራም ያለው Follow charts  ለመፍጠር ያስችለናል ።
እንዲሁም ተጠቃሚዎች እንደ ማይክሮሶፍት ኤክሴል፣ አክሰስ፣ SQL ሰርቨር ወይም SharePoint ካሉ ምንጮች እዛው ዲያግራሞቻቸውን እንዲያገናኙ ያስችላቸዋል።
ይህ ማለት ዳታ ሲቀየር ስዕላዊ መግለጫዎችዎ በራስ-ሰር ሊዘምኑ ይችላሉ።

Visio 3rd party toolችን/ትብብር ቱሎችን ይፈቅዳል ። ስለዚህ ብዙ ሰዎች በተመሳሳይ ዲያግራም ላይ በአንድ ጊዜ ሊሰሩ ይችላሉ፣ በተለይም Visio Onlineን ከ Microsoft 365 ጋር ከተጠቀሙ  በስራ ጊዜ አስተያየት መስጠት፣ መገምገም እና ሌላ ተጨማሪ ሶፍትዌሮችን ዲዛይን ውስጥ ይካተታሉ ።
በተጨማሪም Visio እንደ UML ለሶፍትዌር ሞዴሊንግ፣ BPMN ለንግድ ሂደት ሞዴሊንግ እና ERD ለዳታቤዝ ዲዛይን ያሉ ቴክኒካዊ ደረጃዎችን ይደግፋል፣ ይህም ለ developerች፣ ለንግድ ተንታኞች እና መሐንዲሶች ጠቃሚ ያደርገዋል።

የቪዚዮ ስሪቶች :-
✔️ Visio Standard :-ለመሠረታዊ ዲያግራም ለመስራት እና እንደ  follow charts እና ድርጅታዊ ሞዴል ቻርቶችን ቀዳሚ አድርጎ አካተዋል ።

✔️ Visio Pro:-ሁሉንም ነገር በመደበኛ ውስጥ ያካትታል እና እንደ ዳታ link ወይም ማገናኘት፣ ተጨማሪ ሞዴል እና የተሻሉ ሶስተኛ ወገን ቱሎች የመሳሰሉ የተሻሉ ባህሪያትን ተካተዋል።
✔️ Visio Plan 1:- በ ብራውዘር  ውስጥ ቀላል ንድፎችን እንዲፈጥሩ የሚያስችል የ ዌብ ቨርዥን ነው።
✔️ Visio Plan 2:-ሁለቱንም የዴስክቶፕ እና የ ዌብ መተግበሪያዎችን፣ የላቁ አብነቶችን እና የድርጅት ደረጃ ባህሪያትን ያካትታል።
ቪዚዮ በብዙ ቦታዎች ልንጠቀመው እንችላለን።
የኔትወርክ መሠረተ ልማት ንድፎችን ለመስራት በ IT ባለሙያዎች ዘንድ ታዋቂ ነው። ዳታቤዝ  ሞዴሎችን ለመፍጠር የስርዓት አርክቴክቶች፣ የፕሮጀክት አስተዳዳሪዎች የጊዜ መስመሮች ፡ፋሎው ቻርት፣ እና የቦታ አቀማመጥ እቅድ አውጪዎች፣  እንዲሁም የስራ ፍሰቶችን ለማሳየት፣ በተደጋጋሚ በንግድ አካባቢዎች ውስጥ ጥቅም ላይ ይውላል።
📂  የ OS /የስርዓት መስፈርቶች
Visioን ኮምፒውተር ላይ ተጭኖ ለመጠቀም requirement ወይም መስፈርቶች አሉት።
ለምሳሌ:- Visio 2021 ለመጫን ከፈለግን መስፈርቶቹም
🔗 OS-  ዊንዶውስ 10 ወይም 11
🔗 Processor - ቢያንስ 1.6 GHz ባለሁለት ኮር
🔗  RAM- 4 ጂቢ ራም እና
🔗 HDD-  4 ጂቢ የሀርድ ዲስክ ክፍት ቦታ 
🔗 Display resolution - 1280 x 768 ወይም ከዚያ በላይ የምስል ጥራት ያስፈልገዋል።
 
ሌላው ሶፍትዌሩን በሽያጭ የሚቀርቡ ናቸው። አብዛኛዎቹም ሶፍትዌሮች በግዢ ለተጠቃሚ የሚቀርቡ እንደሆኑ የሚታወቅ ነው።
Visio የሚሸጠው የአንድ ጊዜ ግዢ Visio Standard or Professional ወይም እንደ ሞላነው ፎርም ይወሰናል ። ሆኖም Visio Plan 1 ወይም Plan 2) ነው።
የአንድ ጊዜ ፈቃዱን  ቀደም ብሎ ለማግኘት በጣም ውድ ነው ነገር ግን ወርሃዊ ክፍያዎችን አያስፈልገውም። 
የደንበኝነት ምዝገባው ሞዴል የበለጠ ተለዋዋጭ እና የክላውድ ባህሪያትን እና መደበኛ ዝመናዎችን ያካትታል።
የተወሰኑት ባህሪያቸው ነፃ ልናገኝ እንችላለን።ግን ሶፍትዌሮቹን ለመግዛት ካለንበት ሀገር አኳያ ሊከብደን ይችላል ስለዚህ እነዚህን የሶፍትዌሮች የተሟላ ባህሪያቸውን ለማግኘት በ ሌላ አማራጭ ማለትም ክራክ ሶፍትዌሮችን ተጠቅመን በክፍያ  የምናገኘውን ባህሪ እና ጥቅም በክራክ ሶፍትዌር ወይም ቱል በነፃ ማግኘት እንችላለን።
ክራክ ሶፍትዌሮች ልክ እንደ ሶፍትዌር በ developeroች ተዘጋጅተው ፡ለተጠቃሚ የሚቀርቡ ናቸው ። ስለ ክራክ ሶፍትዌሮች ከዚህ በፊት ማየታችን የማይረሳ ነው።
በሌላ ጊዜ ጠለቅ ባለ መልኩ ለማየት እንሞክራለን። 👍


CompuTech©
👍2
History of Internet 📶📶

👇👇
CompuTech©
🔥2
🌐 Internet history
ኢንተርኔት አስገራሚ አፈጣጠር እና ዕድገት ከ 1960 እንደአውሮፓውያን የቀን አቆጣጠር ጀመሮ አስከ እስካሁኑ ሰዓት ድረስ 20s
የ ኢንተርኔት አፈጣጠር አስገራሚ ታሪክ እና በሌሎች ቴክኖሎጂዎች ውስጥ ተፅኖ አድራጊነት።
ኢንተርኔት ዛሬ ዓለምን እንደ መንገድ ማዕከል የሚያያዝ ቴክኖሎጂ ነው። ነገር ግን መነሻው በጦርነት ዘመን ላይ ነበር።
🌐 የኢንተርኔት ታሪክ  ከመጀመሪያ ጊዜዎች:-
የ ኢንተርኔት ሀሳብ መነሻ ምክንያቱ በጦርነት ምክንያት በ 1960s
በአሜሪካ የነበረው Advance Resarch Projects Agency (ARPA) የአሁኑ የ DARPA በመንግስት የተደገፈ ኢንተርኔት መስመር መፍጠር ጀመረ።
በ1969 ARPANET/Advance Resarch Projects Agency Network ተመሰረተ። የመጀመሪያው መረብ ነበር፣ 4 ዩኒቨርሲቲዎችን አገናኘ።
1ኛው መልዕክት የተላከው "LO" ነበር መላክ የታሰበው መልዕክት  "LOGIN"  ነበር። ነገር ግን መልዕክቱ  “LO” ን ከላከ በኋላ ልክ O እንዳስተላለፈ ስርዓቱ ተቋረጠ፡  የመጀመሪያ የኢንተርኔት መልዕክት ነበር።
🔗 በይነመረብ ዓለምን ማስተሳሰር  የተጀመረበት ጊዜዎች 1970s–1980s
1971 – የመጀመሪያ የኢሜይል መላኪያ ተሰራ።
Ray Tomlinson ፣ የ @ ምልክት መጀመሪያ ጊዜ ጥቅም ላይ  ዋለ።
TCP/IP Protocol (Transmission Control Protocols )በ 1983 አገልግሎት ጀመረ ዛሬም ይሄ ፕሮቶኮል ለ ኔትዎርክ እንቅስቃሴዎች የሚጠቀመን መሠረታዊ የበይነመረብ የጀርባ አጥንት ነው።
DNS (Domain Name System) – በ 1984 –  first name server በሰው የሚነበቡ ዶሜን ስሞችን ወደ አድራሻ ቁጥር ለመቀየር የታሰበ ሰርቨር ተዘጋጀ።
🌍 ኢንተርኔት በዓለም መስፋፋት የጀመረው – 1990s ነው።
በ1989 Tim Berners-Lee  የ World Wide Web (www) ን  ፈጠረ።
በ 1991 ደግሞ ለህዝብ ይፋ ሆነ።
የመጀመሪያ ዌብሳይት info.cern.ch
በ 1993 ደግሞ Mosaic Browser  ወይም ኢንተርኔት አሳሽ ሶፍትዌር ተፈጠረ።
ከ 1995–2000  የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች  በፈጣን ሁኔታ ጨመረ።
Yahoo፣ Amazon፣ eBay፣ Google በ 1998 እና ሌሎች ወደ ኢንተርኔቱ አለም ተቀላቀሉ።
ዘመናዊ ዓለም 2000s-2020s ድረስ ለውጥ የታየበት ጊዜ
በ 2004 Facebook ተመሰረተ ማኅበራዊ መድረኮች ወክሎ በይፋ ተጀመረ።
በ 2005 ደግሞ YouTube  ቀጠለ ፡ ቪዲዮች  ወደ ዓለም መተላለፍ ጀመሩ።
በ 2007 iPhone ስልክ ለመጀመሪያ ጊዜ  በ2G ለአለም ተዋወቀ።
በ 2010s እንደ WhatsApp፣ Instagram፣  Zoom ያሉ መተግበሪያዎች ቀጠሉ።
2020s ደግሞ አስገራሚ የኢንተርኔት እድገት ቀጠለ
📂2020s 5G፣Cloud Computing ፣ Artificial Intelligence (AI) እና ChatGPT ለተጠቃሚ ይፋ የሆኑበት ዘመን።
በይነመረብ በ2020-2025 አስገራሚ ለውጦች:-
  1. ግዙፍ የዲጂታል እድገት
በ2020 የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ትልቅ ለውጥ አስከትሏል ሰዎች ወደ online ወይም የመስመር ላይ ትምህርት፣ የርቀት ስራ እና ኢ-ኮሜርስ ተለመዱ።
እንደ Zoom፣ Google Meet እና Microsoft Teams ያሉ መተግበሪያዎች አስፈላጊ ሆነዋል።
በይነመረብ ለጤና፣ ለሥራ እና ለትምህርት የሕይወት መስመር ሆነ።
  2. የሞባይል ኔትዎርክ ለውጥ
የ5ጂ ኔትወርኮች በአለም ዙሪያ ተሰራጭተዋል።
የሞባይል ኢንተርኔት ፈጣን እና ጠንካራ ሆኗል፣ ይህም ቪዲዮ፣ ጨዋታ እና stream ወይማ ማሰራጨት እንዲቻል ተደርጎዋል።
የገጠር አካባቢዎች በሳተላይት ኢንተርኔት ለምሳሌ ስታርሊንክ መገናኘት ጀመሩ።
  3. የማህበራዊ ሚዲያ ትራንስፎርሜሽን
እንደ TikTok፣Instagram Reels እና YouTube Shorts ያሉ አጭር የቪዲዮ መተግበሪያዎች በታዋቂነት መዘዋወር ጀምረዋል።
ለ Creators በኦላይን ገቢ በማግኘት ዓለም አቀፍ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ሆኑ።
ይህም በማህበራዊ ህይወት ላይ ተፅኖ አድርጓል። የአዕምሮ ጤና፣ ግላዊነት እና ሱስ ስጋት ጨምሯል።

4. ክላውድ፣ AI እና አውቶሜሽን
Cloud Storage /ማከማቻ እና ኮምፒውቲንግ እንደ Google Drive፣ iCloud፣ AWS መደበኛ ሆነዋል።
የተለያዩ AI ቱሎች ተሰርተዋል  እንደ ChatGPT፣  DALL·E፣ Midjourney ያሉ። ሰዎች መለወጥ ጀመሩ።
ለትምህርት፣ለስራ፣ለጥበብ እና ለ content ፈጣሪዎችም ጥሩ አጋዥ ሆኗል።
ስማርት ረዳቶች አሌክሳ፣ ጎግል ረዳት የተሻሉ እና የበለጠ አጋዥ ሆነዋል።
5. Web3፣ Blockchain እና በዲጂታል ክሪፕቶ ምንዛሬዎች እና ኤንኤፍቲዎች ታዋቂነትን አግኝተዋል እንደ Bitcoin፣ Ethereum፣ OpenSea።
Web3 ያልተማከለ፣ በተጠቃሚዎች ባለቤትነት መያዝ ጀመረ።
6. Virtual World/ምናባዊ ዓለማት እና Metaverse
እንደ ሜታ -ፌስቡክ ያሉ ኩባንያዎች በቪአር ምናባዊ እውነታ እና በሜታቨርስ ላይ ኢንቨስት አድርገዋል።
ቪአር/ኤአር መሳሪያዎች ወደ ትምህርት፣ ጤና እና ጨዋታ ገብተዋል። አሁንም በእድገት ላይ ይገኛል።

7. የሳይበር ደህንነት እና ደንብ
እንደ ጠለፋ፣ ማጭበርበር እና የውሸት ዜና ያሉ የመስመር ላይ ማስፈራሪያዎች ጨምረዋል።
የ አለም መንግስታት የቴክኖሎጂ ግዙፍ ድርጅቶችን መቆጣጠር ጀመሩ።
በዲጂታል መብቶች፣ የ መረጃ ጥበቃ እና በ  AI ህጎች ላይ አተኮሩ።

የኢንተርኔትን ቴክኖሎጂ ከዚህ በኋሏ በአስደናቂ ሆኔታ ለውጦች ያሳየናል ብለን እናምናለን፣ እነሱም:-
✔️ 6G እና ፍጥነት ያለው መገናኛ
✔️ ያልተለመዱ ወይም አብዛኛው ነገሮች ከ በይነመረብ የማገናኘት ወይም Internet of Things (IoT) ተጀምሮዋል ግን ከዚህ በኋላ ደግሞ በፈጣን ሁኔታ ዕድገት ያሳያል።
✔️  AI Powered Web  4.0
✔️ Metaverse  በኢንተርኔት ውስጥ አስደናቂ ምህዳሮች ውስጥ መኖር።
🏷 በአጠቃላይ ፈጣን፣ ስማርት፣ የበለጠ ፣ ግን ደግሞ የበለጠ ውስብስብ እና አደገኛ።


CompuTech©
🔥2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Website Developers (EX)

Junior and Senior

CompuTech©
👍2
Smart phone comparison

Samsung Galaxy A15 and A16
የተሻለውስ የቱ ነው ?


CompuTech©
👍2
📱 Samsung Galaxy A15 vs Galaxy A16 — Full Comparison
ሁለቱን ስልኮች ለማነፃፀር እንሞክር፣
የተሻለውስ የትኛው ነው?
🗓️ Release & Software
ለ ተጠቃሚ የቀረበበት ቀን እና ሶፍትዌር ቨርዥን
• Galaxy A15: 📅 Dec 2023
• Android 14 (One UI 6.0)
📥 4 ዓመት updates(አንድሮይድ ማዘመን)
• Galaxy A16: 📅 Oct 2024
• Android 14 (One UI 6.1)
📥 6 ዓመት updates
🖥️ Display & Design(ምስል ጥራት )
• A15:- 6.5" Super AMOLED
• 1080×2340 resolution
• 90Hz refresh rate ~800 nits brightness
• A16: 6.7" Super AMOLED
• 1080×2340 resolution
• 90Hz refresh rate ~800 nits brightness
IP54 dust/splash resistant
⚙️ Performance( አፈፃፀም/ ብቃት (CPU/GPU)
• A15 (4G): MediaTek Helio G99
• AnTuTu ~380K
• Geekbench ~660 (single-core)
• A16 (5G):-
•  Exynos 1330 or Dimensity 6300
• AnTuTu ~410K
• Geekbench ~990 (single-core)
📈 ~30–50% የተሻለ performance!
💾 Memory & Storage
• ሁለቱም ተመሳሳይ:
• 4GB/6GB/8GB RAM
• 128GB or 256GB storage
• microSD slot:-
▫️ A15: up to 1TB
▫️ A16: up to 1.5TB
📸 Camera
ሁለቱም ተመሳሳይ
📷 Rear(የኋላ):-
• 50MP main
• 5MP ultrawide
• 2MP macro
🤳 Front(ፍለፊት): 13MP
🎥 Video: 1080p @ 30fps
🔁 ምስል ጥራት ሁለቱም ተመሳሳይ
🔋 Battery & Charging
Both:- ሁለቱም 👇
🔋 5000mAh battery
25W fast charging
🔌 Battery Life:የባትሪ ቆይታ
▫️ A15: Up to 15.5 hours(ሰዓታት)  
▫️ A16: ~12–13 hours
🔋 A15 is በጣም የተሻለ
📶 Connectivity & Features
• A15:-
• 4G only
• Wi-Fi 5, Bluetooth 5.3
• USB-C, NFC, 3.5mm jack
• Side fingerprint scanner
• A16:
5G connectivity
• Dolby Atmos sound
• IP54 rating
• Same ports + sensors
• Slightly better speakers
💵 ዋጋ ግምታዊ
• A15:-💲  18500 ETB–22500 ETB
• A16: 💲20000 ETB–24500 ETB
በመጨረሻም :-ቀጥሎ ባሉት መስፈርቶች Galaxy A16 ብቁ ሆኖ አገኘነው:-
✔️ 5G እና ከ A15 በኋሏ የተመረተ
✔️ በ performance(አፈፃፀም)
✔️ በ software ድጋፍ ለ 6 ዓመታት
✔️  display(ምስል) + Dolby Atmos
✔️ IP54 splash resistance
ቀጥሎ ባሉት መስፈርቶች ደግሞ Galaxy A15 የተሻለ ሆኖ አገኘነው
✔️ Better battery life
✔️ ቀለል ያለ size
✔️  camera ኳሊቲ ሁለቱም እኩል ጥራት አላቸው


Samsung Galaxy A16 5G ቢመረጥ የተሻለ ነው ብለን አሰብን። 👍


CompuTech©
🔥3
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከ RAT Tool ፈጣሪ ይጠብቃቹ 🙏🙏🙏

CompuTech©
😱2
ትላልቅ ታዎቂ የሆኑ የቴክኖሎጂ ድርጅቶች እና አገሮቻቸው:-
1. Apple – United States 🇺🇸
የሚታወቅበት በ iPhones፣ Macs፣ እና iOS os ነው።
2. Microsoft – United States 🇺🇸
ታዎቂ የሆኑትን የ Windows ፣ Office፣ እና cloud services መስራች እና አስተዳዳሪ ነው።
3. Google (Alphabet) – United States 🇺🇸
የሁሉንም ነገር ማፋለጊያ / በ Search engine 🔎 ፣  በ Android os፣ YouTube እና ሌሎችም።
4. Dell Technologies – United States 🇺🇸
ኮምፒውተሮችን እና ሰርቨሮችን በማምረት ይታወቃል።
5. HP (Hewlett-Packard) – United States 🇺🇸
ይሄም በ ኮምፒውተር እና ፕሪንተሮችን በማምረት ብራንዱን ማግዘፍ የቻለ የቴክኖሎጂ ድርጅት ነው።
6. Cisco Systems – United States 🇺🇸
በ ኔትዎርኪንግ እና በ ኢንተርኔት መሰረተ ልማት ቀዳሚ ድርጅት።
7. IBM (International Business Machines) – United States 🇺🇸
ቀደሚው የ computer ድርጅት ነው በ AI እና በ cloud እንዲሁም  mainframe ችን በማዘጋጀት ይታወቃል።
8. Intel – United States 🇺🇸
ትልቁ የኮምፒውተር processors ወይም CPU አምራች ነው።
9. AMD (Advanced Micro Devices) – United States 🇺🇸
ይሄም በ CPU እና ለ ጌሚንግ የሚሆኑ GPUችን ወይም የግራፊክስ ፕሮሰሰሮችን በማምረት ይታወቃል። 
10. Amazon – United States 🇺🇸
በ E-commerce ወይም በ online የንግድ ፕላትፎርም እና ግዙፉ የ AWS cloud services አስተዳዳሪ።

ይቀጥላል 👍

CompuTech©
👍2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
Installation Python Programming by Termux

CompuTech©
🔥21
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Tor Browesr is a different.

Computech©
👍2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
Network Statistics Checking by
Netstat

CompuTech©
👍1
ቆይ ለምን ግን ለምን ? ....!
BYBIT
ባይቢት ከጁላይ 21 ቀን 2025 ጀምሮ በኢትዮጵያ ብር የሚደረገውን ግብይት እናቋርጣለን ብሎዋል ።
ETB ጋር የተያያዙ ሁሉም የ P2P ማስታወቂያዎች የሚያስወግዱ ይሆናል።


wtf!!!!😟

CompuTech©
😱2
Top fives secure 🔓 internet browsers


CompuTech©
Top 5 Secure 🔐 Browsers/ አምስት የኢንተርኔት አሳሾች
📌 በጣም አሪፍ ደህንነታቸው የተጠበቀ የኢንተርኔት አሳሾች /browsers
በ2025 ከፍተኛ ደህንነታቸው የተጠበቀ 5  አሳሾች /browsers ከታች ለመዘርዘር ሞክረናል።
እያንዳንዳቸውም ጠንካራ የግላዊነት እና የደህንነት ችሎታዎች አሏቸው።
የኢንተርኔት አሳሾች(Browsers):-
1. Brave
• ምርጥነቱም:- ፍጥነት እና አብሮገንቢነት ጥበቃ የሚፈልጉ በግላዊነት ላይ ያተኮሩ ለ ተጠቃሚዎች ትኩረት የሚሰጥ
• የደህንነት ባህሪያት-፡ማስታወቂያዎችን፣ መከታተያዎችን፣ የጣት አሻራዎችን እና የሶስተኛ ወገን ኩኪዎችን  ያግዳል።
• በሁሉም ቦታ በ HTTPS መስራቱ ።
• የግል አሰሳ በቶር(Tor) አማራጭ አለው።
•ለ ዊንዶውስ፣ ማክ፣ ሊኑክስ፣ አንድሮይድ፣ አይኦኤስ ስርዓቶች የሚሆን።
2. Mozilla Firefox with privacy tweaks/ ከግላዊነት ማስተካከያዎች ጋር
• ምርጥነቱም ፡-  ክፍት ምንጭ ደህንነት ለሚፈልጉ ተጠቃሚዎች ማስተካከል ማስቻሉሉ ።
• የደህንነት ባህሪያት፡- የተሻሻለ የመከታተያ ጥበቃ።
• DNS በ HTTPS (DoH) ላይ።
• ሙሉ በሙሉ ክፍት ምንጭ።
ጠቃሚ ምክር፡- ለጠንካራ ጥበቃ Firefox + uBlock Origin + Privacy Badgerን ይጠቀሙ።
• ለ ሁሉም ዋና ስርዓተ ክወናዎች የሚሆን።
3. Tor Browser
• ምርጥ ነገሩም፡ በ ከፍተኛ ደረጃ ማንነትን መደበቅ እና censorship ማለፍ መቻሉ ።
• "censorship": ፀያፍ ፣ ፖለቲካዊ ተቀባይነት የሌላቸው ወይም ለደህንነተ ጠንቅ እንደሆኑ ተደርገው የሚቆጠሩ ጽሁፎችን የሚያስወግድ ነው።
• የደህንነት ባህሪያቱም፡- ኔትወርክ ትራፊክን በቶር ኔትወርክ ውስጥ ያካሄዳል "onion routing" ያሰራጫል።
✔️onion ማለት የበይነመረብ ትራፊክዎ በብዙ layer የተመሰጠረ (encrypted )ነው።
• ስክሪፕቶችን ያግዳል እና የአሳሽ አሻራን ይከለክላል።
• ምንም የአሰሳ ታሪክ/history አያስቀምጥም።
• በትራፊክ ልውውጦች ምክንያት ቀርፋፋ አፈጻጸም ቢኖረውም ምርጥ ነገሮች አሉት።
• ለ ዊንዶውስ፣ ማክኦኤስ፣ ሊኑክስ፣ አንድሮይድ ስርዓቶች ላይ ይጫናል።
4. LibreWolf
• ምርጥነቱም:-  ሃርድኮር ግላዊነት ያለ ቴሌሜትሪ ወይም ክትትል ።
• የደህንነት ባህሪያቱ :-የፋየርፎክስ ፎርክ ከቴሌሜትሪ ጋር ተወግዷል።
• ጠንካራ የግላዊነት ቅንብሮች።
• uBlock መጀመሪያ ተጭኗል።
• ከሞዚላ ሰርቨሮች ጋር ምንም ራስ-ሰር(auto) ግንኙነት የለውም ።
• ለ ዊንዶውስ፣ ማክ፣ ሊኑክስ ስርዓት የሚሆን
5. DuckDuckGo Browser
• ጥሩ ነገሩም፡ ቀለል ባለ ሁኔታ፣ የግል አሰሳ በሞባይል ወይም lightweight ለሆኑ የዴስክቶፕ መጠቀም ማስቻሉ።
• የደህንነት ባህሪያት፡- መከታተያዎችን ያግዳል፣ HTTPSን ያስገድዳል።
• መረጃን በቅጽበት ለማጽዳት fireproofing  cookieችን በ "fire button " አንዴ በመንካት ያስወግዳል ።
• ለ አንድሮይድ፣ አይኦኤስ፣ ለ ዊንዶውስ ስርዓት ደግሞ ቤታ version ።

እያንዳንዳቸው በደህንነት፣ በግላዊነት፣ open-source code፣ በታማኝነታቸው
በመመስረት በጥልቀት አይተን  መርጠናቸዋል።

CompuTech©
World Technology Companies

11. Alibaba – China 🇨🇳
በጣም ታዋቂ  ትልቁ የ  e-commerce ወይም የኦላይን ንግድ መድረክ ነው ፡ ቻይና ውስጥ የcloud ድርጅት አለው ።
12. Meta (Facebook) – United States 🇺🇸
የ Facebook፣ የ Instagram፣ እና የ WhatsApp ባለቤት።
13. Tencent – China 🇨🇳
በ ጌም ጨዋታዎች (gaming) በ ማህበራዊ ሚዲያ  በሆነው በ WeChat ይታወቃል።
14. Tesla – United States 🇺🇸
የኤሌክትሪክ መኪና እና በኢነርጂ ቴክኖሎጂ ዘርፍ ላይ እየሰራ ያለ ትልቅ ድርጅት
15. Samsung – South Korea 🇰🇷
የሚታወቁበት  smartphones፣  በ TV ፣እና በchips።
16. Huawei – China 🇨🇳
እነዚህም የሚታወቁበት በ mobile phones እና በኔትወርክ መሰረተልማቶች በተለይ በ5G ቴክኖሎጂ ።
17. NVIDIA – United States 🇺🇸
GPU / ግራፊክስ ካርድ እና AI ሃርድዌር  በማምረት የሚታወቅ።
18. Oracle – United States 🇺🇸
ትልቁ የዳታቤዝ ፣ ክላውድ እንዲሁም ለ ትላልቅ enterprise /ለድርጅት እና ለተቋማት software ያመርታል ይሸጣል።

ይቀጥላል...!

CompuTech©
👍2