የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
826 subscribers
2.14K photos
47 videos
265 links
Download Telegram
በበጀት ዓመቱ የሴቶችና ወጣቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነትን በተመለከተ
የከተማዋን ሴቶች በማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ መስኮች ተሳትፎና ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ በተሰሩ ስራዎች

👉በኢኮኖሚው ዘርፍ ሴቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ በተስማሚ ቴክኖሎጂ እና በተለያዩ የገቢ ማስገኛ ዘርፎች 32,301 ሴቶች ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡

👉ለማህበራዊ ችግር ተጋላጭ የነበሩ 680 ሴቶች በሁለት ዙር በነገዋ የተሐድሶ እና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል ስልጠና አግኝተው የስራ ዕድል ተፈጥሮላቸዋል::

👉የምገባ ማዕከል ተጠቃሚ ከሆኑት በርካታ ሴቶችን በማሰልጠን፣የመስሪያ ቁሳቁስና ግብዓት ድጋፍ በማድረግ ከተረጂነት ወደ ስራ ፈጣሪነት ተሸጋግረዋል።
3
በተለያዩ ህገ-ወጥ ድርጊቶች ተሳታፊ የሆኑ ስደተኞችን በቁጥጥር ስር በማዋል የህግ የበላይነትን የማስከበር ስራ በትኩረት መሰራቱ ተገለፀ

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ እና የበጀት ዓመቱን ማጠቃለያ ጉባኤ እያካሄደ ይገኛል፡፡

አስፈጸሚ አካለትም ከምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት ላይ የሚገኙ ሲሆን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋዉ ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

አዲስ አበባ ከተማን ማዕከል አርገው የሚኖሩ ስደተኞች በግድያ፣ በዘረፋ፣በህገ ወጥ ገንዘብ ዝውውርና ህትመት ብሎም የማታለል ወንጀል ተሰማርተው የተገኙ ህገ ወጦችን ተከታትሎ የመያዝና ተጠያቂ የማድረግ እርምጃዎች ተወስደዋል ብለዋል።

የሀገር ህልውናን በሚጎዳ መልኩ ከፀረ-ሠላም ሀይሎች ጋር መረጃ የሚለዋወጡና ድጋፍ የሚሰጡ ህገ ወጥ ስደተኞችንም በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ ማካሄድና የተጠያቂነት ስራ መሰራቱን ጨምረው አብራርተዋል።

በየደረጃው ከሚገኙ የፀጥታ ሀይሎች እና ከህብረተሰቡ ጋር በቅንጅት በመስራት በከተማዋ ሠላምን ማስፈን እንደተቻለ ያነሱት ኮሚሽነሩ ለመዲናዋ ሠላምና መረጋጋት ሚናውን አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምን አስተማማኝ ደረጃ ማድረስ መቻሉን ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ገለፁ

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛና የበጀት አመቱን ማጠቃለያ ጉባኤ በማካሄድ ላይ ይገኛል።

በጉባኤው ከምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት የከተማዋ ሰላም እና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ፣ የመዲናዋን ሰላም አስተማማኝ ደረጃ ላይ ማድረስ መቻሉን ተናግረዋል፡፡

የምክር ቤት አባላት በተለይ ከፀጥታ ጋር በተያያዘ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች እንዲብራሩ በጠየቁት መሰረት ወ/ሮ ሊዲያ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ኃላፊዋ በሰላም እና ፀጥታ ዙሪያ ሕዝቡን ባለቤት ማድረጋችን ከፍተኛ ለውጥ አምጥቶልናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ሕብረተሰቡ በያለበት ተደራጅቶ የአካባቢውን ሰላም እንዲጠብቅ መደረጉ ትልቅ አጋዥ አቅም ሆኗል በማለት አብራርተዋል፡፡

በከተማዋ የተደራጀው የሰላም ሰራዊትም፣ ለሰላም እና ፀጥታው አስተዋፅኦ አበርክቷል ያሉት ወ/ሮ ሊዲያ፣ ከፀጥታ መዋቅሩ ጋር በሦስት ፈረቃ እንዲሰሩ ተደርጓልም ብለዋል፡፡

በሰላም እና ፀጥታ ዙሪያ የተሰሩ እነዚህ ስራዎች የከተማዋን የወንጀል ምጣኔ በ43 በመቶ እንዲቀንስ ማድረጉንም ገልፀዋል፡፡

አሁንም ህብረተሰቡ የተለመደ ተባባሪነቱን እና ተሳትፎውን ይቀጥል ያሉት ወ/ሮ ሊዲያ፣ ቤት አከራዮች የተከራይን ማንነት በሚገባ እንዲያጣሩም አሳስበዋል፡፡
👍3
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
በጀት ዓመቱ ከተማዋ በዘመናዊ የህክምና ታሪኳ የነበራትን አቅም እጥፍ የሚያደርግ ስራ የተሰራበት መሆኑን ዶክተር ዮሀንስ ጫላ ገለፁ

በጀት ዓመቱ በጤናው ዘርፍ የተከናወኑ የግንባታ ፕሮጀክቶች ከተማዋ በዘመናዊ የህክምና ታሪኳ የነበራትን አቅም እጥፍ ሊያደርግ የሚችል ስራ የተሰራበት ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዮሀንስ ጫላ ገለፁ።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ እና የበጀት ዓመቱን ማጠቃለያ ጉባኤ እያካሄደ ይገኛል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዮሀንስ ጫላ ጤናን በተመለከተ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ በጤናው ዘርፍ ትልልቅ ስራዎች ተሰርተዋል ያሉት ኃላፊው፣ በዘንድሮ በጀት ዓመት ፍትሃዊ ተደራሽነትን ከማስፈን አኳያ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የመሆን አቅም ያላቸው አዳዲስ ጤና ጣቢያዎችን ስራ ለማስጀመር የህክምና መሳሪያዎች በመሟላት ላይ ይገኛል ብለዋል።

በጤናው ዘርፍ የተከናወኑ የግንባታ ፕሮጀክቶች፣ ከተማዋ በዘመናዊ የህክምና ታሪኳ የነበራትን አቅም እጥፍ ሊያደርግ የሚችል ስራ የተሰራበት አመት እንደሆነም ነው የገለጹት።

ነባር ሆስፒታሎችም ያላቸውን አቅም እጥፍ የሚጨምር ግንባታ ተከናውኗል ያሉት ኃላፊው፣  በማሳያነትም በራስ ደስታ፣ በዘውዲቱ መታሰቢያ፣ በጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል እና በዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል የፎረንሲክ ህክምና ማዕከል የተገነባውን የማስፋፊያ ግንባታ ጠቅሰዋል።

የጤና ተቋማቱም በቅርብ ጊዜ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምሩ ተናግረዋል።

ከዚህ ቀደም ለህክምና ወደ ውጪ የሚሄዱ ታካሚዎችን በሀገር ውስጥ ህክምና ለመስጠት በሚያስችል መልኩ ወደ ስራ ለመግባት እየተሰራ መሆኑንም አንስተዋል፡፡

ከተማዋን የጤና ቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ የመንግስት የጤና ተቋማትም የበኩላቸውን አስተዋፅዎ ለማድረግ የሚያስችሉ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑንም ኃላፊው ተናግረዋል።
3
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአዲስ አበባ ፋይናነስ ቢሮ ኃለፊ አቶ አብዱልቃድር ሪድረዋን በ3ኛዉ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባዔ ላይ ለምክር ቤት አባላት የሰጡት ምላሽ፤-

👉የከተማችን ወጪ በየዓመቱ በዋናነት መነሻ የሚያደርገዉ ብድር እና እርዳታን በአማካይ ከወሰድን ከ2 በመቶ ያልበለጠ ሲሆን 98 በመቶ እና ከዚያ በላይ ከከተማችን በጀት ከዉስጥ የሚመነጭ እና ወጪዎቹም በዋናነት የመ፣ሸፍኑት ከዚሁ የዉስጥ ገቢ ግምት ዉስጥ ማድረግ ችለናል።

👉ከተማችን አገልግሎት ሰጪ በመሆኗ አገልግሎቱ በየዓመቱ ማደግ ስላለበት ከፍተኛ የሆነ የመደበኛ ወጪ ፍላጎት ያስከትላል፡፡ በተጨማሪም የተገልጋይ እርካታን ከማረጋገጥ አንፃር ተያይዞ የሪፎርም እና የዲጂታላይዝ ስራዎችን ለመስራት እና ተደራሽ ለማድረግም በቂ ግብዓት በማቅረብ የመደበኛ ወጪ ከፍ እንዲል የግድ ስለሁነ እየሰራን እንገኛለን፡፡

👉እንደ ከተማ አስተዳደር ባለፉት ዓመታት 50 እና 50 የነበረዉ በጀት በተወሰነ ደረጃ በመደበኛ ወጪም 50 በመቶ ደርሶ የነበረዉን በመቀልበስ ከተማ አስተዳደሩ በወሰደዉ ቁርጠበኛ አቋም በዚህ በጀት ዓመት ከ70 በመቶ በላይ የካፒታል በጀትን ማድረስ መቻላችን አንዱ ማሰያችን ነዉ፡፡

👉ከ2010 እስከ 2013 የከተማዉን በጀት እድገት በአማካይ ስናይ ትልቁ ያደገዉ በ15 ፐርሰንት ፤ትልቁንም ብር ከወሰድን 7.8 ቢሊዮን ብር እድገቱ ነዉ፡፡በዚህም ዝቅተኛዉ 3.9 ቢሊዮን ከፍተኛዉ በአንድ ዓመት 7.68ቢ ሲሆን ከ2014 እስከ 2017 ዝቅተኛ ዓመታዊ ገቢ ያደገዉ በ40 በመቶ ሲሆን ከፍተኛዉ ደግሞ ከበፊቱ በ53 በመቶ ገቢያችን ማሳደግ ችለናል፡፤

👉የ2017 በጀት ዓመት ከባለፈዉ ዓመት የ83 ቢሊ ብር እድገት ያለዉ ሲሆን ይህም ገቢን ለማሳደግ ከተማ አስተዳደሩ ግብረ ኃይል አቋቁሞ በትኩረት የሰራበትና ትልቁ ዉጤት ሊሆን ችሏል፡፡

👉ለገቢ እድገታችን ሌላዉ ምክንያት በፊት ከነበረዉ የትንበያ ልማዳዊ አሰራር በመላቀቅ ከተማዋ ያላትን ገቢ የማመንጨት አቅም በጥናት በመለየት፤በቁጠባ በጀትን በመጠቀም፤በአሰራርና አደረጃጀት በማዘመን ለሚነሱ የልማት ጥያቄዎች ተገቢዉን ምላሽ ከተማ አስተዳደሩ እየሰጠ ይገኛል፡፡
ህብረተሰቡ ጉቦ መስጠት የሚጸየፍና ለመብቱ የሚታገል መሆን አለበት፡፡ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ሌብነትና ብልሹ አሰራርን ከማስተካከል አንጻር ለውጡ ከህብረተሰባችን መጀመር አለበት፡፡

እንደ መንግስት ሲቪል ሰርቪሱን ሪፎርም ለማድረግና ተቋሞቻችን ለማጠናከር ከፍተኛ ጥረቶች እያደረግን ነው፡፡ ከዚህ አንጻር አገልግሎቶች መንግስት በተቀያየረ ቁጥር የሚቀያየር እንዳይሆንና አገልግሎት አሰጣጡ መሰረት እንዲይዝ ለማድረግና በሚሰራው ስራ ላይ በቂ እውቀት ያለው ሲቪል ሰርቫን ለመፍጠር በትኩረት እየሰራን ነው፡፡

ይሄን ለማሳካት ባደረግነው ጥረት ውስጥ የተለያዩ ተግዳሮቶች ማጋጠ ማቸውም የሚታወስ ነው፡፡አሁንም ቢሆን ህዝቡ በመታገልና የአፈጻጸም ችግር ያለባቸውን በማጋለጥ ለአገልግሎት መሻሻል የበኩሉን ድርሻ መወጣት ለውጡን ማፋጠን አለበት፡፡
ከ15960 በላይ ፕሮጀክትን አቅዶ የመፈፀም እና ፈጣን ምላሽ መስጠት የቻልንበት በጀት ዓመት ነው::ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አጠቃላይ ህብረተሰቡን አወያይተን ከረዥም እና አጭር ጊዜ አንጻር ፈጣን ምላሽ የሚያስፈልጋቸውን ለይተን ምላሽ ሰጥተናል፡፡

ከአጭር ጊዜ አንጻር ለጤና ባለሞያዎች ከዲውቲና ከትርፍ ሰአት ክፍያ እንዲሁም ከትራንስፖርትና ከተቋማቸው ውጪ የህክምና አገልግሎት ማግኘት ጋር ተያይዞ ያለውንና የመምህራንን ጥያቄዎችን በተመሳሳይ ችግር የሚፈታ ፈጣን ምላሽ ሰጥተናል፡፡

ኑሮ ውድነትን ከማረጋጋት አንጻር ምርትን ለማቅረብና ምርታማነትን ለማሳደግ ገበያ ማእከላትን ለማስፋፋት እስከ 14 ቢሊየን የሚጠጋ በጀት በመመደብ ዝቅተኛ ገቢ ያለውን ህብረተሰብ ድጎማ አድርገናል፡፡

ከዚህም ሌላ ብዙዎችን ከተረጂነት አላቀን ራሳቸውን እንዲችሉና ስራ እንዲፈጥሩ ማድረግ ችለናል፡፡
"የወጣቶች ግንዘቤና ተሳትፎን በማሳደግ 2,230,995 ወጣቶች በተለያዩ የበጎ ፈቃድ ተግባራት እንዲሳተፉ ለማድረግ ታቅዶ በድግግሞሽ 2,368,228 (ከ100% በላይ) ማሳተፍ ተችሏል።"

ከንቲባ አዳነች አቤቤ
👍1
3ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉበዔውን 2ኛ ቀን ውሎ በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

ምክር ቤቱ በሁለተኛ ቀን ውሎው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍርድ ቤቶች የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት በማድረግ በሙሉ ድምፅ
አፅድቋል
👍2
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
በአዲስ አበባ ምክር ቤት 2 ኛ ቀን ውሎ በ 2017 በጀት ዓመቱ ፍርድ ቤቶች ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት በመስጠት ረገድ የተሻለ የፍትህ ሥርዓት አፈፃፀም እንደነበራቸው ተገልጿል ።

የአዲስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች 2017 ዕቅድ አፈፃፀም ለምክር ቤቱ ያቀረቡት የአዲስ አበባ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቶች ፕሬዝዳንት አቶ ተስፋዬ መለሰ ቀልጣፋ ፣ውጤታማና ተደራሽት ያለው አገልግሎትን መስጠት የፍርድ ቤቶች ተቀዳሚ ተግባር መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ መዛግብት የማጥራት ዕቅድ 97 በመቶ ለመፈጸም ታቅዶ 98 በመቶ መከናወኑንም አስታውቀዋል፡፡

የቅልጥፍና መለኪያ በተቀመጠው ጊዜ መሠረት ለጉዳች ውሳኔ መስጠት ነው፤ በዚህ መሠረትም በስታንዳርድ መሠረት 89 በመቶ የፍትሀብሔር ጉዳዮች ውሳኔ አግኝተዋል ብለዋል፡፡

በ2017 በጀት ዓመት ውሳኔ ሳያገኙ ወደ ቀጣይ በጀት ዓመት የተላለፉት በይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት እና በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት 3ሺ 32 ጉዳዮች መኖራቸውንም ገልጸዋል፡፡

18 ዓለም አቀፍ የአገልግሎት እርካታ ደረጃ ምዘና መስፈርት መሠረት ከ85 በመቶ በላይ አፈፃፀፀም ማስመዝገብ ከፍተኛ መሆኑን ያስገነዘቡት ፕሬዝዳንቱ በበጀት ዓመቱ የተሻ ውጤት የተገኘባቸውን ክንውኖችም በሪፖርታቸው አመላክተዋል፡፡

ባለጉዳይን ያለ ምንን ልዩነት በትህት እና አክብሮት ማገልገል፣ የዳኞች እና ሰራተኞች ያለ ጉቦ ማገልገል፣ የፍርድ ቤቶች ኃላፊዎች ሙስናና ብልሹ አሠራርን ለመካላከል ያላቸው ተነሳሽነት ፣ የሥነ ምግብር ጉድለት ያሳዩትን ተጠያቂ ለማድረግ ያለው ቄርጠኝነት እና በመሳሰሉት መስፈርቶች ከፍተኛ ውጤት ተመዝግቧል ብለዋል፡፡

በአንፃሩ ግልፅ ችሎት አለመኖር፣ የቀረቡ ክርክሮችና ማስረጃዎችን በአግባቡ አለመመዘን፣ በቴክኖሎጂ የታገዘ አገልግሎት ውስንነት፣ ተደጋጋሚ ቀጠሮ መስጠት፣የቋንቋ አስተርጓሚ አለመኖር፣ ነፃ የህግ አገልግሎት አለመኖር እንዲሁም ጉዳዮች በእርቅ እንዲያልቁ በፍርድ ቤት ተገቢው እድል አለመስጠት በሚሉት መመዘኛዎች ደግሞ ፍርድ ቤቱ ከዓለም አቀፍ ምዘና በታች መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

የከተማ ፍርድ ቤቶች የሪፎርም ሥራዎች በትግበራ ላይ እንደሚገኙ ያነሱት ፕሬዝዳንቱ በዓመቱ በጥንካሬ የተመዘገቡ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል እና በክፍተት የተለዩትን ደግሞ በበማረም ለተሻለ ውጤት እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡

የፍርድ ቤቶችን ሥራ በተለይም በቴክኖሎጂ ማስደገፍ ላይ የታየውን ውስንነት ለማሻሻል በሪፎርሙ በስፋት እየተሰራበት ይገኛልም ብለዋል፡፡

የበጀት አመቱን የፍርድ ቤቶች የአፈፃፀም ሪፖርት ያዳመጠው ምክር ቤቱ በቀረበዉ ሪፖርት ላይ የተሰጡትን የአባላቱን ሀሳብ እና አስተያየት ካዳመጠ በኋላ ሪፖርቱን በሙሉ ድምፅ አፅድቋል፡፡
ምክር ቤቱ የከተማው ካቢኔ የአራት ተቋማትን አወቃቀር አፅድቆ በላከው የውሳኔ ሃሳብ መሰረት ተወያይቶ በሙሉ ድምፅ አፀድቋል፡፡

የቱሪዝም ኮሚሽን ለብቻው ወጥቶ መደራጀትን አስመልክቶ አስፈላጊነቱ ላይ በአፅንኦት ተወያይቷል::
በዚህም መሠረት
1-ቱሪዝም ዘርፍ ራሱን ችሎ በኮሚሽን እንዲቋቋም፤
2-የዲዛይን እና ግንባታ ሥራዎች ቢሮ እና የትላልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ ፅ/ቤት ጋር እንዲወሀድ::

3 ማህበራዊ ትረስት ፈንድ ፅ/ቤት ከህብረተሰብ ተሳትፎ እና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ጋር እንዲወሃድ::

4-የከተማ ውበትና አረንጋዴ ልማት ቢሮ የህዝብ መፀዳጃ ቤቶችን የማልማት ተግባር ለውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ማስተላለፍን ያከተተ ማሻሻያዎች ላይ ምክርቤቱ ተወያይቶ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል፡፡

በ3ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ በአራት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ምክር ቤቱ ተወያይቶ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል::
👍2
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 በጀት 350.13 ቢሊየን ብር ሆኖ ፀደቀ።

ረቂቅ በጀቱ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የፋይናንስ ቢሮ ሃላፊ አቶ አብዱልቃድር ሬድዋን አማካኝነት ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡

በቀረበው ረቂቅ ላይ አጠቃላይ 350.13 ቢሊየን ብር በምን መልኩ ለማግኘት እንደታሰበ ተዘርዝሯል፡፡

ከዚህ ውስጥ ከታክስ ገቢ 238 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ እንደታቀደ አቶ አብዱልቃድር አብራርተዋል፡፡

የምክር ቤቱ አባላት በረቂቅ በጀቱ ላይ ሃሳብ እና አስተያየት እንዲሁም ጥያቄዎች አንስተዋል፡፡

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የፋይናንስ ቢሮ ሃላፊ አቶ አብዱልቃድር ሬድዋን በተነሱት ጥያቄዎች ላይ ምላሽና ማብራሪያ ከሰጡ በኋላ የ2018 በጀት 350.13 ቢሊየን ብር ሆኖ በሙሉ ድምፅ ፀድቋል፡፡

#AMN
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የተለያዩ ሹመቶችን በመስጠት ተጠናቋል።

በ3ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ያቀረቡትን የተለያዩ ሹመቶች አፅድቋል።

በዚህም መሰረት
1-አቶ አብዱልቃድር ሬድዋን :-በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ፍይናስ ቢሮ ሃላፊ መሆናቸውን ለምክር ቤቱ እንዲያውቀው ተደርጓል::

2. አቶ ኦልያድ ስዮም :-የከተማ ቦታ ማስለቀቅ ጉዳዮች እና ይግባኝ ሰሚጉባኤ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ሆነው ተሹመዋል ።

3-አቶ መኮንን ያኢ :-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማት ቢሮ ሀላፊ ሆነው ተሹመዋል ።
👍31