የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
826 subscribers
2.14K photos
47 videos
265 links
Download Telegram
በበጀት ዓምእቱ የኑሮ ውድነት ቅነሳን በተመለከተ

👉በከተማዋ አምራቾች ምርታቸውን በቀጥታ በገበያ በማዕከላት እንዲያቀርቡ በተፈጠረው እደል 3.5 ሚሊዮን ኩንታል ምርት እንዲቀርብ ተደርጓል።

👉የቅዳሜና እሁድ የገበያ ቦታዎችን በማስፋት ከ193 ወደ 219 በማሳደግ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ እየቀረበ ይገኛል፡፡

👉በድጎማ ከሚቀርቡ ምርቶች የስኳር ምርት 305,295 ኩንታል፤ የምግብ ዘይት 4,382,179 ሊትር በትስስር ማሰራጨት ተችሏል።

👉በትራንስፖርት፣በጤና መድን፣ በዳቦ አቅርቦት፣ በምገባና በምርት አቅርቦት ከ14 ቢሊዬን ብር በላይ በመደጐም የነዋሪዎቻችን የኑሮ ጫናን የማቅለል ስራ ተሰርቷል፡፡

👉የዳቦ አቅርቦትን ለመጨመር በመንግስትና በግል ባለሀብቶች የጋራ ጥምረት በተሰራው ሥራ የሸገር ዳቦና ብረሃን ዳቦ ፋብሪካ ውደ ስራ በማስገባት፤በአጠቃላይ በ26 ዳቦ ፋብሪካዎች በሚሊዮኖች ዳቦ በማምረት የነዋሪውን ኑሮ ለመደገፍ ጥረት ተደርጓል።

👉በ26 የምገባ ማእከልላት በቀን አንድ ጊዜ ምግብ ማግኘት ችግር ላለባቸው 36ሺ ሰዎችን በምገባ ፕሮግራም ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡
በበጀት ዓመቱ አምራች ኢንዱስትሪውን በተመለከተ

👉የምርት ጥራት፣ ምርትና ምርታማነታቸውን ከማሳደግ አንፃር ለ566 አምራች ኢንዱስትሪዎች 4,235 ማሽነሪ መሳሪያ እና በብር ደግሞ 1,860,822,877 በማቅረብ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡
🥰2
ገቢን በተመለከተ
👉በመዲናዋ ከ241.46 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ ከ233 ቢሊዮን ብር በመሰብሰብ የእቅዱን 96.5% በመቶ መፈፀም የተቻለ ሲሆን ከባለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 83.3 ቢሊዮን ብር ወይም 57% እድገት አሳይቷል::

👉ባለፉት 11 ወራት ደረሰኝ ባለመስጠት በድምሩ 11,283 ያህል የተቀመጡ የግብይትና የታክስ ህጎችን ያላከበሩ ነጋዴዎች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዷል፡፡

👉በገቢ አሰባሰቡ ሂደት ላይ በሌብነትና ብልሹ አሰራር በተለዩ 247 ሰራተኞች ላይ ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዷል፡፡
2
የቤት ልማትና ማስተላለፍን በተመለከት

👉በግለሰብ አልሚ 11,260 ቤቶች ::
👉በሪል እስቴት አልሚዎች 30,507 ቤቶች፣
👉በበጎ ፈቃድ አገልግሎት የተገነቡ 8,786 ቤቶች፣
👉 በመንግስት ለልማት ተነሺ የተሰሩ 5,176 ቤቶች፣
👉በአጠቃላይ በ2017 በጀት አመት 55,729 ቤቶች ተገንብተዋል ማስተላለፍ ተችሏል::
👉በህገ -ወጦች የተያዙ 453 የመንግስት ቤቶች እና 212 የጋራ መኖሪያ ቤቶች በድምሩ 665 ቤቶችን በማስለቀቅ ለሚገባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ማስተላለፍ ተችሏል፡፡
🥰2
የሁለተኛው ዙር የኮሪደር ልማትን በተመለከተ፦

👉የመንገድ መሠረተ ልማት፡- 135 ኪ.ሜ የተሽከርካሪ መንገድ፣ 246 ኪሎ ሜትር የእግረኛ መንገድ፣141 ኪ.ሜ የብስክሌት መንገድ፣ 43 ኪ.ሜ የመሮጫ ትራክ፣ 53 የተሽከርካሪ እና እግረኛ መሻገሪያ ድልድዮች፤190 ኪ.ሜ የጎርፍ ማስወገጃ ሥርዓት ዝርጋታና፣ 83 ኪ.ሜ የድጋፍ ግንብ ሥራ ተሰርቷል።

👉 የትራንስፖርት ሥርዓት ለማሳደግ ፦ 153 ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያዎች፣ በአንድ ጊዜ 35,000 ተሸከርካሪዎችን የማስተናገድ አቅም ያላቸውና 33 የባስ እና ታክሲ ዘመናዊ ተርሚናሎች፣

👉 የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ፦ 1,122 ስማርት እና 1708 ኖርማል በአጠቃላይ 2830 የመብራት ምሰሶዎች ተተክሏል፤ 179.6 ኪ.ሜ የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ፤ 5,048 የኤሌክትሪክ ምሰሶ ማዛወር፤ 22.41 የመሬት ውስጥ መካከለኛ የኤሌክትሪክ መስመር መቅበር፤ 324 የዲስትሪቢዩሽን ትራንስፎርመሮችና 7.9 ኪ.ሜትር ፒቪሲ ዝርጋታ ሥራ ተሰርቷል።

👉የሕዝብ መዝናኛዎችና ማረፊያዎችን ማስፋፋት፦ የአረንጓዴ ልማት ፤ የህዝብ መዝናኛ ፕላዛዎች ፤ ዘመናዊ የመንገድ ዳር የሕዝብ መፀዳጃ ቤቶች (Public toilets)፣ ስፍራዎች ተገንብተዋል።
በበጀት ዓመቱ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎተ በተመለከተ፦

👉የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎተ ለማሻሻል 1ዐዐ የኤሌክትሪክ አውቶቡሶችና 15ዐ የኤሌክትሪክ ሚኒባሶች ተገስተዉ የትራንስፖርት ተደራሽነትን ማሻሻል ተችሏል፡፡

👉የብዙሃን ትራንስፖርት በቀን በአማካኝ በህዝብ ትራንስፖርት የሚጓጓዝ ህዝብ 3.79 ሚልየን ለማድረስ ታቅዶ ለ4.025 ሚሊየን አገልግሎት ተሰጥቷል፡፡

👉የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል በሪፎርም በበጀት ዓመቱ ባለስልጣን መ/ቤቱ ካሉት 45 ዋና ዋና አገልግሎቶች መካከል 35ቱን በቴክሎጂ በሲስተም አገልግሎት መስጠት የተቻለ ሲሆን ከ1.8 ሚሊዮን በላይ የተገልጋዮችን ፋይል በቴክኖሎጂ በመታገዝ በአዲስ መልክ በማደራጀት በቴክኖሎጂ የተደገፈ አገልግሎት በመስጠት የተገልጋይ ውጣ ውረዶችን በማስቀረትና የሚፈለጉ መረጃዎችን በቀላሉ እንዲያገኙ አስችሏል፡፡

👉ለዓመታት ቁጥጥርና ምዘና ሳይደረግባቸው የቆዩ የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ እና የተሸከርካሪ ቴክኒክ ምርመራ ተቋማት ላይ በበጀት ዓመቱ ቁጥጥርና ምዘና በማድረግ ጉድለት የተገኘባቸው ላይ የእርምት እርምጃ ተወስዷል፡፡

👉ለትራፊክ አደጋ የሚያጋልጡ (risk factors) የትራፊክ ደንብ ጥሰቶች ቁጥጥር በማጠናከር፤ የቁጥጥር ስርዓቱን በማዘመን አዲስ ሲስተም በማልማት በድምሩ 2.5 ሚሊየን የሚሆኑ ደንብ ተላላፊዎች ላይ የትራፊክ ቅጣት ተፈጽሟል፡፡

👉ከፓርኪንግ ስራ ጋር በተያያዘ ተቋሙ ያለማውን አዲስ ፓርኪንግ ማኔጅመንት ሲስተም ተግባራዊ በማድረግ 144 ማህበራት ወደ ስርዓት በማስገባት 310,000 በላይ ተሸክርካሪዎች በተዘረጋው ሲስተም እንዲያለፉ ተደርጓል፡፡

👉በአጠቃላይ በኮሪደር የለሙ የተሸከረካሪ ማቆሚያ ቦታዎች የካ ቁጥር 2 ጨምሮ ወደ አግልግሎት እንዲገቡ ተደርጓል፡፡
የከተማችንን የእህትማማች ግንኙነት ከማጠናከር አንፃር ፦

👉የጀርመኗ በላይብዚሽ ከተማ በአዲስ አበባ ከተማ ስም የአደባባይ ወካይ ሀዉልት ወይም መገለጫ ተሰርቷል፡፡

👉 በደቡብ በኮሪያ የሴኡል ከተማ ስማርት ሲቲ 2024 115 አቻ ከተሞች መካከል በከተማ ለዉጥ ዘርፍ ቀዳሚ በመሆን በማሸነፍ ተሸላሚ መሆን ችላለች

👉 አዲስ አበባ የአፍሪካ ስማርት ከተሞች ኢንቨስትመንት ፎረም (Best Africa Smart Cities Award) አሸናፊ ከተማ ሆናለች፡፡

👉 ከናሚቢያዋ ዋና ከተማ ዊንድሆክ (Windhock) እና ከቻይናዋ ሪጃው (Rizhao) ከተማ ጋር በዘላቂ ልማት፣ በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ፣ በባህል፣ በንግድ፣በትምህርት እና ጤና መስኮች በትብብር ለመስራት ተችሎል ፡፡

👉በኮሪደር ልማት ስራችን ከልማቱ ማንም ወደ ኋላ ሳይቀር ሁሉም ተጠቃሚ እንዲሆን የተደረገበት የከተማችንን ደረጃ መሻሻል እና የተወዳዳሪነት አቅም የተፈጠርበት፣ የሥራ ባህል መሻሻል (24/7) ፣ የይቻላል አስተሳሰብ የዳበረበት ነዉ ፡፡

👉የከተማዋን ገጽታ መቀየር የተቻለበት ፣ የፕሮጀክት አመራርና የኮንትራት አስተዳደር አቅም ያገበት ፣ የባለድርሻ አካላት አቅም እየጎለበተ የመጣበት፣ የመሰረተ ልማት ተቋማት የቅንጀት እና ትብብር ደረጃ በእጅጉ የተሻሻለበት ነዉ ፡፡
የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶችን በተመለከተ

👉በደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር ረገድ ከተማዋ ከ983,944.9 ቶን በላይ ደረቅ ቆሻሻን በመሰብሰብና በማስወገድ፣ ከ11 በመቶ ወደ 12.2 በመቶ በማሳደግ በመልሶ መጠቀም ወደ ሀብትነት መለወጥ ተችሏል።

👉በሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት በኩል ከተማዋ 377,624 የወሳኝ ኩነት ምዝገባዎች ተከናውኗል።

👉በ2017 የበጀት አመት ወደ ዲጂታል ምዝገባ ያልተቀላቀሉ 671,019 ነዋሪዎች በዲጂታል አገልግሎት አግኝተዋል ።
🥰2
በበጀት ዓመቱ ኢንቨስትመንት በተመለከተ

👉 ለ3,207 ባለሀብቶች አዲስ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ተሰጥቷል
👉 በተመሳሳይ ለ2,025 ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ዕድሳት ተሰጥቷል።