የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
835 subscribers
2.14K photos
47 videos
265 links
Download Telegram
ማህበራዊ ችግር ያለባቸው የህብረተሰብ ክፍሎችን ከተረጂነት ባለፈ በቂ ስልጠና በመስጠት መስራት የሚችሉትን የማሸጋገር ስራ ሰርተናል።ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የኑሮ ውድነትና ጫናን ለማቃለል አለሜቀፋዊ ሁኔታን አገናዝበን ምላሽ ለመስጠት ሞክረናል።

* ኑሮ ውድነትን ለመቅረፍ አቅርቦትን ማሳደግ ላይ በትኩረት በመስራት በአምስቱም የከተማችን መግቢያ በሮች የግብርና ምርቶችን አቅርቦትን ተደራሽ ማድረግና የደላሎችን ሰንሰለት መበጣጠስ ችለናል።

* የኑሮ ውድነት ችግርን ማቃለል የምንችልበት መንገድ አምራችነትን በማሳደግ እንደመሆኑ መጠን የከተማችን ነዋሪ በተለያዩ አግባባች አምራችነቱ እንዲያድግ ስልጠና የመስጠትና የግብአት አቅርቦት እገዛ እያደረግን ነው።

* የገበያ ማረጋጋት ስራን በተመለከተ በቁጥጥር፣ በክትትልና፣ በድጎማ ህቦረተሰባችንን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ እየሰራን ነው።ውጤትም አግኝተንበታል።

* ለማህበራዊ ችግር የተጋለጡ የህብረተሰብ ክፍሎችና የእናቶችን የኑሮ ጫና ለማቃለል የሰራነው ስራ ሁሌም የምንኮራበት ነው።

* 26 የምገባ ማዕከላን በመክፈት ዝቅተኛ የህብረተሰብ ክፍሎችን በመመገብ ፍትሀዊ ተጠቃሚነታቸዉን ከማረጋገጥ ባሻገር ዜጎች አብሮ የማደግ ባህል እንዲጎለብት አድርገናል።
👍2
የኮሪደር ልማቱ ዙሪያ

👉በኮሪደር ልማት የመጣው ለውጥ "አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ አበባ እናደርጋታለን" ብለን ለህዝባችን ከገባነው ቃል የመነጨ ነው። ለአብነት የኮሪደር ስራችን ከመጀመራችን በፊት ባደረግነው ጥናት የአዲስ አበባ የመንገድ መሰረተ ልማት እና የአረንጓዴ ሽፋን እጅጎ ከፍ እንዲል ያስቻለን ሲሆን ይህም ለከተማችን ነዋሪዎች አጠቃላይ ጤና ያለው ፋይዳ የላቀ መሆኑን ሁሉም የሚገነዘበው ጉዳይ ነው።

👉በኮሪደር ልማት መኪና መንገድ ብቻ ሳይሆን 80% በላይ ተሽከርካሪ የሌለውን የከተማችን ነዋሪዎች በቀላሉ ሊጠቀሙበት የሚችሉትን የእግረኛ መንገዶችን አስፋፍተናል የሳይክል መንገዶችንም ማስፋፋት በመጀመራችን ህዝቡ ተጠቃሚ ሆኗል።

👉 በኮሪደር ልማትና መልሶ ማልማት ስራ የታየው ወሳኘ ጉዳይ የህዝባችን ያላሰለሰ ድጋፍና ትብብር የተረጋገጠበት መሆኑ ነው። በዚህ ስራ ውስጥ ወጣቶች እና ሴቶች በጉልበታቸው አግዘዋል፤ ባለሀብቶች ገንዘባቸውን አፍስሰዋል፤ የልማት ተነሺዎች አስደናቂ ትብብር አድርገዋል።

👉ኮሪደር ልማቱ የከተማችንን ገፅታ መቀየሩ እና ለህዝባችን ምቹ መኖሪያ እንድትሆን ከማድረጉ ጎንለጎን ለበርካታ ወጣቶችና ሴቶች የስራ ዕድል ፈጥሯል።

👉 የከተማችን ነዋሪዎች ልማቱ ወደ ሁሉም የከተማችን አካባቢዎች እንዲመጣ መጠየቃቸው አግባብነት ያለው ጥያቄ ቢሆንም ስራው ሰፊ ሀብት እና ጊዜ የሚፈልግ በመሆኑ በጥናት እና በቅደም ተከተል ወደ ሁሉም የከተማችን ክፍሎች በመምጣት የምናለማ ይሆናል::

ከንቲባ አዳነች አቤቤ
👍2
የአዲስ አበባ ከተማ ም/ቤት ባካሄደው 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤ ተጨማሪ በጀት አፀደቀ

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ለ2017 ዓ.ም የሚውል ከ11 ቢሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ በጀት አፅድቋል፡፡

ተጨማሪ በጀቱ በከተማዋ የተጀመሩ ዘርፈ ብዙ ልማቶችን ለማስቀጠል አስፈላጊ መሆኑ በምክር ቤቱ ተገልጿል፡፡
#followerseveryone
#viralreelschallenge
#highlighteveryone
#አዲስ_አበባ
👍1
አገልግሎት አሰጣጥ በተመለከተ

.አገልግሎትን ከማዘመን አንፃር ኮሪደር ልማቱ የፈጠረልንን ቴክኖሎጂ የማዘመን እድል በአግባቡ በመጠቀም 347 በቴክኖሎጂ የታገዙ አገልግሎቶችን ማዘመን ችለናል።

• የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ለማዘመን በትኩረት መስራት ይኖርብናል።

• የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን ለመቅረፍ በመንግሥት ተቋማት ካደረግነው ውጤታማ ሪፎርም ጎን ለጎን በብልሹ አሰራር ላይ የተሳተፉ 1726 ሠራተኞችና ከ90 በላይ አመራሮች ላይ እርምጃ በመውሰድ ሌብነትና ብልሹ አሰራርን መታገል በልዩ ትኩረት እየሰራን ነው።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ
👍1
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት በ4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤው ለ2017 ዓ.ም ከ11 ቢሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ በጀት እና ልዩ ልዩ ሹመቶችን በማፅደቅ ተጠናቅቋል:: በዚህም መሰረት:-

1. ወ/ሮ ቆንጆት ደበላ ዎላ - የአዲስ አበባከተማ አስተዳደር የሴቶች፣ ሕጻናትና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ(በሽግሽግ)
2. አቶ አወሌህ መሐመድ ኦመር - የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ
3. ወ/ሮ አይሻ መሐመድ አደን - የአዲስ አበባከተማ አስተዳደር የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር
4. ኢ/ር ሕይወት ሣሙኤል ጸጋዬ - የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር
5. ሲ/ር ሶፊያ አለሙ - የሴቶች፣ የወጣቶችና ህፃናት ቋሚ ኮሚቴ ሆነው ተሹመዋል::

በሌላ በኩል ተጨማሪ በጀቱ በከተማዋ የተጀመሩ ዘርፈ ብዙ ልማቶችን ለማስቀጠል አስፈላጊ መሆኑንም ምክር ቤቱ ተወያይቶ በሙሉ ድፅ አፅድቋል፡፡
ኑሮ ውድነት ከሰብል ምርት ጋር እጥረት እንዳይገጥም ህብረት ስራ ማህበራትን ያላቸውን ካፒታል የሰብል ምርቶችን በመግዛት ስቶክ እንዲኖራቸው ተደርገዋል:: ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ

• 216 የእሁድ ገበያዎች በአይነትና በጥራት ምርቶቻቸዉን በወጣላቸው ስታንዳርድ መሰረት እንደቀርቡ የማድረግ ስራን በከተማዋ የተቋቋመው የግብረ ሃይል አደረጃጀት ቁጥጥር እያደረገ እና ህጋዊ እርምጃ እየወሰደ በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡

• ኮሪደር ልማቱን በተመለከተ ዘለቄታዊነት ያላቸውን የከተማውን እድገት ሊያፋጥኑ የሚችሉ ሁሉን አቀፍ ስራዎችን ለመስራት አስተዳደሩ ያለውን ምቹ ሁኔታ በማየት የቀጣይ ስራዎችን ጨምሮ በቅድመ ዝግጀት ስራዎች የሚሰሩትን በትኩረት አቅደን እና ዲዛይን አድርገን ተወያይተን በቀጣይ የበለጠ የሚሰራ ይሆናል፡:

• የአዲስ አበባ ከተማ የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ የከተማ አስተዳደሩ የፐብሊክ ትራንስፖርት፤የቤት አቅርቦት፣የስራ እድል ፈጠራ ፣የትምህርት ቤት ምገባ እና ምገባ ማዕከላት ከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ በጀት በመደብ እየሰራ ይገኛል::

ከዚህም በተጨማሪ በከተማችን የሚገኙ 4 የገበያ ማዕከላት በቂ ምርት እንዲኖራቸው የማድረግ ስራ እተሰራ ሲሆን እነዚህም ስራዎች የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያላቸዉ መሆኑን ልንገነዘብ ይገባል::
👍5
የበጎ ፈቃድ ማኅበራት ጥምረት በበጎ ፈቃድ አገልግሎትና ማኅበራዊ ኃላፊነት ደንብ ዙሪያ ምክክር አካሄደ።

በአዲስ አበባ ከተማ የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን የቋቋመው የበጎ ፈቃድ ማኅበራት ጥምረት ከተማ አስተዳደሩ ባዘጋጀው የበጎ ፈቃድ አገልግሎትና ማኅበራዊ ኃላፊነት ደንብ ቁጥር 161/2017 ዙሪያ ውይይት አካሂዷል።

ውይይቱ የጥምረቱ አባል ማኅበራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተቋማዊ ቅርፅ እንዲይዝና ኢኮኖሚያዊ አስተዋፅዖው እንዲታወቅ፣ የመረዳዳትና የመተሳሰብ እሴት እንዲዳብር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ላወጣው ደንብ ተግባራዊነት የድርሻቸውን እንዲወጡ ለማድረግ እንደሚያግዝ በመድረኩ ተመላክቷል።

በሌላ በኩል ጥምረቱ በበጀት ዓመቱ ያለፉ ወራት ያከናወናቸው ዋና ዋና ተግባራት አፈፃጸም ቀርቦ ውይይት የተደረገ ሲሆን የጥምረቱን አባል ማህበራት የእርስ በርስ ግንኙነት በማጠናከረ የነዋሪዎችን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን መፍታት እንደሚጠበቅ ተገልጿል።

በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የበጎ ፈቃድ ማኅበራት ከአንድ ዓመት በፊት በጋራ መስራት የሚያስችላቸውንና የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡበት እንዲሁም እርስ በርስ ተሞክሯቸውን የሚለዋወጡበት ጥምረት መመስረታቸው ይታወሳል።

"በጎ ፈቃደኝነት ለማኅበረሰብ ለውጥ!"

ሚያዚያ 29/2017 ዓ.ም (አዲስ አበባ)
የማኀበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን፥
‎ፌስቡክ - https://www.facebook.com/cpvcc.2015
‎ቴሌግራም - https://t.me/CommunityPVC
‎ቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@aacpvcc
‎ዩቱዩብ - https://youtube.com/@communityparticipationvolu8714
‎ዌብሳይት - www.aacpvcc.gov.et
የ2017/18 በጀት ዓመት የክረምት በጎ ፈቃድ ፕሮግራሞች ውጤታማ ለማድረግ በጎ ፈቃደኞችን ለአገልግሎት የማብቃት ስራ እየተከናወነ ነው።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን የ2017/18 በጀት ዓመት የክረምት በጎ ፈቃድ ፕሮግራሞች ለማሳካት በጎ ፈቃደኞችን ለአገልግሎት ብቁ የማድረግ የቅድመ ዝግጅት ስራ እያከናወነ ይገኛል።

የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በራስ ተነሳሽነት ጊዜን፣ ጉልበትንና ገንዘብን ለማህበረሰብ ሁለንተናዊ ለውጥ በነፃ የማዋል ተግባር ሲሆን ይህንን ዓለም አቀፍና ወሰን የሌለው አገልግሎት በጥሩ ስብዕናና በመልካም ሥነ-ምግባር መተግበር ይገባል።

በከተማ ደረጃ አንድ ሺህ በጎ ፈቃደኞች በበጎ ፈቃድ ጽንሰ ሀሳብና በአገልግሎት ሥነ-ምግባር ዙሪያ በተለያዩ ዙሮች ስልጠና የወሰዱ ሲሆን ለመጭው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት እስከ ወረዳ ድረስ ከ11 ሺህ በላይ በጎ ፈቃደኞች የሥነ-ምግባር ስልጠና ይወስዳሉ።

የ2017/18 የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የከተማዋን ነዋሪዎች ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት በሚያረጋግጥ መልኩ እየተዘጋጀ ሲሆን ከግንቦት 30 በፊት በተለያዩ ፕሮግራሞችና መርሀ ግብሮች ይፋ ይደረጋል።

"በጎ ፈቃደኝነት ለማኅበረሰብ ለውጥ!"
ሚያዚያ 29/2017 ዓ.ም (አዲስ አበባ)
የማኀበራዊ ሚዲያ አማራጮቻችን፥
‎ፌስቡክ - https://www.facebook.com/cpvcc.2015
‎ቴሌግራም - https://t.me/CommunityPVC
‎ቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@aacpvcc
‎ዩቱዩብ - https://youtube.com/@communityparticipationvolu8714
‎ዌብሳይት - www.aacpvcc.gov.et
👍3
ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የተለያዩ የሰው ተኮር ስራዎች መሰራታቸዉን እና እየተሰሩ መሆናቸዉን ከኢቲቪ ጋር በነበራቸዉ ቆይታ ገልፀዋል፡፡

ከንቲባዋ እንደገለፁት ምንም ገቢ የሌላቸዉ የከተማችን ነዋሪዎች በቀን 1 ጊዜ እንኳን መመገብ የሚቸገሩ የከተማችን ነዋሪዎች አሁን 36 ሺ የሚሆኑ ወገኖቻችን ትኩስ እና ንፁህ ምግብ በቀን 1 ጊዜ መመገብ የቻሉበት እና በዚህም ምግብ ብቻ ሳይሆን ክብርም፤ፍቅርም ያገኙበት ፕሮግራም መሆኑን ገልጸዋል::

በተጨማሪም ትዉልድ ላይ ትኩረት በማድረግ በተማሪዎች ምገባ በየትቤ/ቱ 1 ሚሊዮን የሚጠጉ ተማሪዎች በቀን 2 ጊዜ እንዲመገቡ ማድረግ የተቻለበትና የትምህርት ቁሳቁስ ግብዓት በሟሟላት የወላጆችን ጫናን ለማቃለል መንግስት ሃላፊነት ወስዶ እየሰራበት መሆኑንም አብራርተዋል፡፤

ከንቲባዋ አክለዉም በሰዉ ተኮር ስራወች ሰፋፊ እና በሚሊዮን የሚቆጠር የስራ እድል መፍጠር የተቻለበት እና በመሰረታዊነት የሰዉ ህይወት የተቀየረበት መሆኑን ገልፀዉ በሴፍቲኔት ብቻ ወደ 100ሺ የሚሆኑ የከተማችን ነዋሪዎች ባለፉት ዓመታት ወደ ተሻለ ህይወት በተጨባጭ ማሻገር የተቻለበት ነዉ ብለዋል፡፡

#viralreelschallenge
#followerseveryone
#addisababa
#Ethiopia
#etv@CommunityPVC
ከተቋማት ጋር በአጋርነት በተሰሩ የኅብረተሰብ ተሳትፎና የበጎ ፈቃድ ተግባራት ተጨባጭ ለውጦች መጥተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ባለፉት አስር ወራት ከተቋማት ጋር በአጋርነት በተሰሩ ተግባራት ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር አካሂዷል።

በአጋርነት በተሰሩ ተግባራትም የኅብረተሰቡን ተሳትፎ እና እርስ በርስ የመደጋገፍ እሴት በማጎልበት ተጨባጭ ውጤት መመዝገቡ ተጠቁሟል።

ተቋማት የኅብረተሰቡን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ይበልጥ በማሳደግ የአካባቢ መሠረተ ልማት ስራዎችንና የበጎ ፈቃድ ፕሮግራሞችን ስኬታማ በማድረግ ረገድ የነበራቸው ሚና እድገት ማሳየቱን የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ይመር ከበደ ገልፀዋል።

በኅብረተሰቡ ውስጥ በራስ እቅም ችግሮችን ለይቶ የመፍታት ባህል መጎልበቱ የተገለፀ ሲሆን የከተማ አስተዳደሩ ተቋማት ከኮሚሽኑ ጋር ተቀናጅተው የሰሯቸው ተግባራት ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉድለቶችን በመሙላት ለከተማዋ ፈጣን እድገት ከፍተኛ አስተዋፅዖ እያበረከቱ በመሆኑ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ኮሚሽነሩ አሳስበዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በከተማዋ ለሰው ተኮርና ለህዝብ ተሳትፎ ተግባራት ውጤታማነት የአጋርነት ሚናቸውን እንደሚያስቀጥሉና በበጀት ዓመቱ በትሥስር ያቀዷቸውን ግቦች ለማሳካት እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 30/2017 ዓ.ም
በሌሎች የማኅበራዊ ሚዲያ አማራጮች ለመከታተል ቀጣዩን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ፣
https://linktr.ee/cpvcc
1👍1👎1
የኀብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን - አዲስ አበባ
Photo
"የኮሙኒኬሽንና የህዝብ ግንኙነት ስራዎችን ለማሳለጥ ብቃት ያለዉ ባለሙያ መኖር እና የተቀናጀና የተናበበ ወጥነት ያለዉ አዳጊ የተግባር እንቅስቃሴ ማስፈን ወሳኝ ሚና ያለዉ በመሆኑ ምንግዜም መርህ አድርገን ልንተገብረዉ የሚገባ ጉዳይ ነዉ"አቶ ሁሴን ዝናብ

ይህ የተገለፀዉ የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ በስሩ የሚገኙ የሴክተር ተቋማት የኮሙኒኬሽን ዘርፍ የ 9 ወራት እቅድ አፈፃፀም እና የ6 ወራት የክትትልና ድጋፍ ምልከታ ምዘና ዉጤት ላይ መሠረት አድርጎ በገመገመበት ወቅት ነዉ፡፤።

በግምገማዉ ላይ የበጀት ዓመቱ የሴክተር ተቋማት የ9 ወራት አበይት ቁልፍ ተግባራት እቅድ አፈፃፀም ያለበት ደረጃ ፣በኮሙኒኬሽን የተግባቦት ስራዎች መረጃን በመሸጥና ተደራሽ በማድረግ የሀሳብ የበላይነት ከማረጋገጥ አኳያ እንዲሁም የንቅናቄ ስራዎች ያሉበት ሁኔታ እና በግማሽ ዓመት በጥንካሬና በክፍተት የታዩ የሴክተሮች የምዘና ዉጤት ትኩረት የተደረገባቸዉ አጀንዳዎች ናቸዉ።

የከተማዋን ሁለተናዊ አዳጊ የተለያዩ የልማት እንቅስቃሴዎችንና የከተማዋ ነዋሪዎች የመረጃ ፍላጎት እርካታ ሊመጥኑ የሚችሉ የመረጃ ጥራትና ተደራሽነትን በኮሙኒኬሽን ተግባቦት የማስፋት፤ዘመናዊ የመረጃ ፍሰትን የማሳለጥ እና የተናበበና የተቀናጀ ወጥነት ያለዉ የክትትልና ድጋፍ መኖሩ ከባለፈዉ አፈፃፀማችን ተሻሽሎና ጎልቶ የታየበት ዉጤት መሆኑ በቀረቡት ሪፖርቶችና በተደረገዉ ግምገማዊ ዉይይት ተመላክቷል፡፡

የቢሮዉ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ሁሴን ዝናብ ከዚህ ጋር ተያይዞ እንደገለፁት በሁሉም አደረጃጀቶች ባደረግነዉ የተቀናጀ የክትትልና ድጋፍ አግባብ የከተማዋን የተለያዩ አጀንዳዎች በመልዕክት በመምራት በከተማዋ የሃሳብ የበላይነት እንዲሰፍን ማድረግ የተቻለበትና ይህም በጋራ የመጣ ትልቅ ስኬት መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የቢሮው ም/ኃላፊና የዲጂታልና ሞኒተሪንግ ዘርፍ ኃላፊ አቶ በትግሉ ዲባባም ሁለንተናዊ የመረጃ ተደራሽነትን በማስፋትና ለማህበረሰባችን ወቅታዊና ታዕማኒነትን ያማከለ የመረጃ ምንጭ መሆን እንዳለባቸውና የኮሙኒኬሽንና የህዝብ ግንኙነት ስራዎችን ለማሳለጥ እና የተቀራረበ አፈፃፀም በሴክተሮች መካከል ለማምጣት ብቃት ያለዉ ባለሙያ መኖር እና የተቀናጀና የተናበበ ወጥነት ያለዉ አዳጊ የተግባር እንቅስቃሴ ማስፈን ወሳኝ ሚና ያለዉ በመሆኑ ምንግዜም መርህ አድርገን ልንተገብረዉ የሚገባ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

በመጨረሻም በ9 ወራት ያልተፈፀሙ ስራዎችን ለይቶ ማቀድ እና መስራት፤ ሁሉም ሴክተሮች የማህበራዊ ፕላት ፎርሞችን አማራጭ ማስፋትና መጠቀም እንዲሁም የተከታይ ቁጥርን ማሳደግ ላይ በንቃት መሳተፍ፤ ልምድና ተሞክሮን ማስፋት፤ ሴክተሮች የመረጃ ምንጭ እንዲሆኑ ማድረግ፤ የክትትልና ድጋፍ እንዲሁም ስልጠናዎችን ማጠናከር እና የበጀት፤ የሰዉ ሃይል እና የግብዓት ችግሮችን መፍታት በበጀት ዓመቱ ቀሪ ጊዜያት ሊተኮርባቸዉ የሚገቡ የቀጣይ አቅጣጫ መሆናቸዉንም አመላክተዋል፡፤

ተሳታፊዎችም የመጣዉ የጋራ ዉጤት በሁለተናዊ መልኩ ቢሮዉ ያደረገዉ የክትትልና ድጋፍ አግባብ ወሳኝ ሚና እንደነበረዉ ገልፀዉ በቀጣይም ይህን የበለጠ አጠናክሮ በማስቀጠል ሁላችንም ወደ ተቀራረበ አፈፃፀም እንድንመጣ በትጋት መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡
👍52