COD-ET®
20.5K subscribers
598 photos
27 videos
122 files
519 links
#COD-ET 🇪🇹

💻 Code • Learn • Build
🚀 Ethiopia’s growing developer community

🎯 Tech tips | 💡 Learning | 🌐 Web & Apps | 🎨 Design | 💼 Online opportunities

We build. We learn. We grow. Together.

Smart Code. Smart Security. Ethiopian Soul
Download Telegram
የስታርትአፕ ዘርፍን በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ለማጎልበት ሲካሄድ የነበረው የ«Cursor AI Hackathon 2026» ውድድር በስኬት ተጠናቀቀ።
==================
በኢትዮጵያ የስታርትአፕ ሥነ-ምህዳርን ለማጎልበትና የወጣቶችን የፈጠራ አቅም በሰው ሰራሽ አስተዋፅኦ (AI) ቴክኖሎጂ ለማበልጸግ ያለመው «Cursor AI Hackathon Ethiopia 2026» ውድድር ከሐምሌ 18 እስከ 19 ቀን 2018 ዓ.ም. ሲካሄድ ቆይቶ በስኬት ተጠናቀቀ።

በውድድሩ ማጠቃለያ መርሃ ግብር ላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የኢኖቬሽን ልማት መሪ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሰላምይሁን አደፍርስ እንደገለጹት፣ መሰል የቴክኖሎጂ ውድድሮች የወጣቶችን የፈጠራ እውቀቶችን ወደ ተግባራዊ የፈጠራ መር ቢዝነሶች በመቀየር የሀገሪቱን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ እንደሚያፋጥኑ ገልጸዋል።

አክለውም ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ለዲጂታል ስታርትአፖች የሚያደርገውን ሁለገብ ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል በመጠቆም፣ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ሀገር በቀል ችግሮችን የሚፈቱ መፍትሔዎችን ማመንጨት የነገዋ ኢትዮጵያን እድገት የሚያረጋግጥ መሠረት መሆኑን አብራርተዋል።

በውድድሩ ላይ የላቀ የቴክኖሎጂ መፍትሔዎችን በማቅረብ ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ የወጡ አሸናፊ ቡድኖች የተለያዩ ማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

ይህ የሃካቶን ውድድር ወጣት የፈጠራ ባለቤቶች በጋራ በመሆን ሀሳቦቻቸውን በተግባር የሚፈትሹበትና ልምድ የሚለዋወጡበት ትልቅ መድረክ ሆኖ ማገልገሉ ተመልክቷል።

በመጨረሻም ውድድሩ በስኬት እንዲጠናቀቅ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አዘጋጆችና አጋር አካላት ምስጋና የቀረበ ሲሆን፣ በቀጣይም መሰል የፈጠራ መድረኮችን በስፋት በማዘጋጀት ለኢትዮጵያ የስታርትአፕ ዘርፍ እድገት በትኩረት እንደሚሠራ ተገልጿል።
1
Forwarded from Ethio telecom
የከርሰር (Cursor) ኢትዮጵያ AI Hackathon 2026 በታላቅ ስኬት ተጠናቀቀ!

በአድዋ ሙዚየም የተከናወነው ይህ መርሐ ግብር እጅግ ተስፋ ሰጪ የነበረ ሲሆን ከከርሰር ኢትዮጵያ እና ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር (MINT) ጋር በመተባበር 300+ ብቁ ገንቢዎችን፣ ተማሪዎችን እና ፈጣሪዎችን በማሰባሰብ መፍትሔዎችን የሚሰጡ የAI ሥራዎችን ፈጥረናል። ከአገልግሎት አሰጣጥ እስከ ጤና አጠባበቅ ሥራዎች ድረስ፣ ተሳታፊዎች አስደናቂ ችሎታቸውን አሳይተዋል።

እንደ ተባባሪ አዘጋጅ ኩባንያችን ኢትዮ ቴሌኮም የሀገራችንን የዲጂታል የወደፊት መፃኢ ዕድል እና የሥራ ፈጠራን በመደገፉ ኩራት ይሰማዋል።

ሙሉ ተሳታፊዎችን ከልብ እያመሰገንን ላሸነፉት ቡድኖች እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እንወዳለን!

#CursorAIHackathon #Ethiotelecom
#MINT #AIInnovation #TechEthiopia #DigitalEthiopia
#RealizingDigitalEthiopia
3
Forwarded from Birhan Nega
Presentation has some extra advantages😀
😁5
Forwarded from Self Taught Developers (✞Faith✞)
😁4
😂😂
Forwarded from Opportunity Hub
Job Title: SENIOR ሆያ ሆዬ ጨፋሪ😂
🤣61😁1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Robot breaking the human speed record and BREAKING an electrical box at the same time.

@cod_et
😁4🤣1🏆1
📚 ትምህርት ሚኒስቴር የ 2018ዓ.ም የ 12ኛ ክፍል Entrance ፈተናን በተመለከተ ከደቂቃዎች በሗላ መግለጫ ይሰጣል ፥ መግለጫውን በቀጥታ በቴሌግራም ለመከታተል ከታችን ያለውን ሊንክ በመንካት በ Tikvah Ethiopia በኩል በቀጥታ መከታተል ትችላላችሁ።

https://t.me/tikvahethiopia?livestream

©️@Cod_et
🫡1
#National_Exam_Result

በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች 12.8% ተማሪዎች ማለፋቸውን ትምህርት ሚኒስቴር አሳወቀ።

ለፈተና ከተቀመጡ 560,210 ተማሪዎች 70,544 ወይም 12.8% የሚሆኑት ማለፋቸውን የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ለጋዜጠኞች ገልፀዋል።

በመላ አገሪቱ የመልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ውስጥ 88 ትምህርት ቤቶች 100% ያስፈተኗቸውን ተማሪዎች ማሳለፋቸውን የገለፁ ሲሆን፣ 585 ትምህርት ቤቶች ደግሞ ምንም ተማሪ አለማሳለፋቸውን ገልፀዋል።

@cod_et