💯3❤2👍1
ምንም አትሆኑም
"የሕልውናችን መሠረት እግዚአብሔር ብቻ ነው። ሰው የሕይወታችንን መብራት፤ ለማብራትም ሆነ ለማጨለምም ድርሻ የለውም። የእኔ ሕይወትና የእኔ ጉዳይ በእግዚአብሔር እጅ ነው ብለን በእምነት መኖር ይገባናል።"
እምነት ከእውቀትና ፍርሃት በላይ ኃያል ነው። ለዚሁ ነው እግዚአብሔር ከምናውቀው ይልቅ እንድናምነው አጥብቆ የሚፈልገው። ስለ ህይወታችን ከሰው ይልቅ እግዚአብሔርን እንመነው።
@Christian_Insight

🔥3❤1👍1
እግዚአብሔር የተሻለ ሃሳብ አለው።
እኛ ለእኛ መልካም እንደሆንን ልናስብ እንችላለን ወይንም ደግሞ ሰዎች የተሻለ እንደሚያስቡልን እንገምት ይሆናል። ነገር ግን ሰዎች ምንም እንኳን መልካም ቢያስቡልንም ከእግዚአብሔር ሃሳብ አንፃር ካየነው መጥፎ ሊባል ይችላል።
ለዚህ ይመስላል ከአገልጋይነት ይልቅ ትምህርትን እንድናስቀድም የሚመክሩን። የሆነው ሆኖ እኛ ለእኛ ካለንም ሆነ ፣ ሰዎች ለእኛ ካላቸው ሃሳብ እግዚአብሔር ለእኛ ያለው ሃሳብ የላቀ ነው።
እወዳቸዋለሁ ❤

❤1👍1🥰1
"ያጠለቅነው ጫማ ባዶ እግራችንን፣ የለበስነው ልብስ ዕራቁት መወለዳችንን ካስረሳን ሞኝ ነን። በባዶነት ጀምረን በባዶነት በምንጨርስባት ዓለም ሁሉ የእኔ ካልሆነ ብለን አንታክት። በድብቅ እየወደቅን በገሀድ የወደቁት ላይ አንዘባበት። ትምህርታችን ያልተማሩትን ካልረዳ አለማወቅ ነው። የእኛን ትምህርት ዋጋ ያለው ያደረገው ያልተማሩት ናቸው። ጨለማን የማያስወግድ ብርሃን ራሱ ጨለማ ነው። ፍላጎታችንን ባለማወቅ የሰውን ድንበር አንግፋ። በክብር ለመኖር ልክን ማወቅ መሠረት ነው። ሐሰትን ከፈጠራት ያሰራጫት የከፋ ነውና የማናውቀውንም የምናውቀውንም ከመናገራችን በፊት እናስተውል።"
@Christian_Insight
@Christian_Insight
@Christian_Insight
@Christian_Insight
❤2🔥1🥰1
ተስፋ አታድርጉ.!
ተስፋ ሁሉ የመሆን ተስፋ የለውሞ። አንዳንድ ተስፋ ልክ እንደ ሎተሪ ነው ሊደርሳችሁ ይችላል ግን እርሱን ተማምነን ቤት አንቀልስም ምክንያቱም የተስፋው የመሆን ተስፋ ዝቅተኛ ነውና።
ልክ እንዲሁ ህይወት ላይም ያላችሁን ተስፋ ብዙም ከእውነታው አታርቁት። ተስፋ ጥሩ ቢሆንም ሲበዛ ግን እንደ አደንዛዥ መድሀኒት ነው። አቅማችንን እየበላ ይሄዳል። ሰዎች ላይ ያላችሁን ተስፋ ቀንሱ ፡ ነገሮች ላይ ያላችሁን ከልክ ያለፈ ተስፋ ቀንሱ ፡ ነገሩ ላይሆንም እንደሚችል ማሰብ ከፊት ካለው ህመም በቶሎ ለማገገም የሚረዳ ስንቅ ነው።
ሙሉ ተስፋ የሚደረገው እግዚአብሔር ብቻ ነው። ሌላው ግን ገደብና ክፍተት አለበት ስለሆነም በእግዚአብሔር ባላችሁ ተስፋ ፅኑ ፡ ለነገሮች መሳካት ከልብ እየሰራችሁ ከልክ በላይ ከሆነ ተስፋ ተቆጠቡ።

❤1🔥1🥰1
🌸 - ከህይወት ትዝብት - 🌸
🍀 ፍቅር ለማይገባው ፡ ፍቅርህን
ንግግርህ ለማይገባው ፡ ቃላትህን አትስጥ።
🍀 የምታደርገውን የትኛውንም ነገር ስታደርግ ከቁም ነገር ለሚቆጥርና ዋጋህን ተገንዝቦ value ለሚሰጥ ሰው አድርገው።
🍀 አየህ ለስጋ በሊታ እንስሳ ሳር አይሰጥም ፣ ሳር ለሚበላ እንስሳም ስጋ አይሰጥም ለሁሉም የራሱ ስርዓት አለው። ያንን ስርዓት ለመበጠስ መጣር ከተፈጥሮ ህግ ጋር መጣረስ ነው።
ፍቅርህንና ቃልህን ለሚገባው ብቻ ስጥ.!

❤4👍1💯1
🌸 ሥር የሰደዱ ዛፎች ነፋስን ይቋቋማሉ ፣ ወደ ታች የጠለቁ መሠረቶች ብዙ ፎቅ ይሸከማሉ ።
🌸 ሰውም በሳል ሲሆን በፈተና ይጸናል ፣ ፈተናና ነፋስ ያልፋሉና ። ነፋሱ ዘንበል ቢያደርግህም እንዲሰብርህ መፍቀድ የለብህም ።
🌸 ብዙ ጫናዎችን ለመሸከም እውቀትና ማስተዋልን ገንዘብ አድርግ ። ከአገሬ በቀር አገር የለም ፣ ከእናቴ በቀር እናት የለም ፣ ከእኔ በቀር ሰው የለም ፣ ከእገሌ በቀር አገልጋይ የለም አትበል።
🌸 ጨርሶ መናገር ለዚህ ዓለም ነዋሪ ትዝብት ያተርፍለታል ። በክረምት ለመዝራት ዝናቡን የተሰቀቁ የአጨዳ ዘመን የላቸውም ። ሌላው ሲያለቅስ የሳቁ በኀዘናቸው አጋር አያገኙም።
🌸 ካልገዛ በቀር ስጦታውን የሚያቃልል የእግዚአብሔርና የሰው ወዳጅ መሆን አይችልም ። ፍላጎት መልካም ነው ፣ ከልክ ያለፈ መሻት ግን በቀን ሰላም ፣ በሌሊት እንቅልፍ የሚነሣ ነው ።

❤3👍1🔥1
ቶሎ ቶሎ ውለዱ
🍀 ለሁሉም ነገር ጊዜ አለው። ለመሳቅ ፡ ለማልቀስ ፡ ለመውጣት ፡ ለመግባት እንዲሁም ለመውለድም ጊዜ አለው።
🍀 አንድ ነገር ጊዜ አለው ማለት ያንን ነገር ለማድረግ ምርጡ ጊዜ እሱ ነው ማለት ሲሆን ፡ ያ ጊዜ ሳይመጣም ሆነ ካለፈ በኋላ ያንን ነገር ማድረግ አንችልም።
🍀 ለምሳሌ ለመውለድ ጊዜ አለው ከሆነ እድሜ በላይ እና ከሆነ እድሜ በታች ነው መውለድ የሚቻለው። ከዚያ የጊዜ ማዕቀፍ ውጪ መውለድ አይቻለም።
🍀 በህይወት ላይም ጊዜ የሚባል ነገር አለ። ከእናት ማህፀን የሚወለደውን ልጅ ራዕይ ወይም አላማ ነው እንበለውና አጠር ያለ ነገር ልበላችሁ። የወጣትነት እድሜ ራዕይና አላማችንን መውለጃ ምርጡ ጊዜ ነው። እሄንን ጊዜ ተጠቅመን በውስጣችን የሚመላለሰውን ራዕይ መውለድ አለብን።
🍀 ይህ ባይሆን ግን መውለድ ፈልገን እንኳን መውለድ የማንችልበት ጊዜ ይመጣል። በተወለዱ ራዕዮች ስንቀና እንኖራለን። ስለዚህ ባላችሁ በዚህ ጊዜ ቶሎ ቶሎ ውለዱና ተገላገሉ። እኛም እንኳን ጌታ ረዳችሁ ለማለት ቸኩለናል።
የተወደዳችሁ ናችሁ ❤

❤2👍1🔥1🥰1
በኢየሱስ...
"ህይወት ትርጉም የሚያገኘው በእየሱስ ውስጥ ራሳችንን ማየት ስንጀምር ነው። የተፈጠርንለትን ዓላማ ማግኘት የምንችለው ወደ እየሱስ በመንፈስ ቅዱስ መቅረብ ስንጀምር ነው። ፀሎት እኛ ጋር ድርግት ሳይሆን ህይወት (life style) መሆን ሲጀምር ስጦታውን ትተን ሰጭውን ራሱን መፈለግ ስንጀምር ያኔ የህይወታችንን ዓላማ ማግኘት እንጀምራለን። መንፈስ ቅዱስ አባትሽ ነው የሩቅ ሰው አታድርጊው ይወድሻል ዕለት ዕለት ሊያወራሽ ይፈልጋል። እውነት ነው እሱ አብሮን እየኖረ ነው እሱ አብሮሽ እየኖረ ነው ማለት ግን አንቺ አብረሽው እየኖርሽ ነው ማለት አይደለም ቅረቢው አውሪው ይህንን ካደረግሽ እርግጠኛ ነኝ ዳግመኛ ህይወት ይደብራል የሚል ቃል ከአንደበትሽ አይወጣም ።"

ማንንም አልሰማም 💪 እናገራለሁ !
ህይወትህ የሚለወጠው አንተ ስትለወጥ ብቻ ነው! አመለካከትህ፣ በራስ መተማመንህ፣ የጊዜ አጠቃቀምህ፣ የገንዘብ አያያዝህ፣ ለራስህ የምትሰጠው ቦታ፣ አላማህን ማወቅህና በእቅድ መመራትህ...እነዚህ ነገሮች ሲቀየሩ እመነኝ መንፈሳዊ ህይወትህ ፣ አስተሳሰብህ ፣ የፀሎት ህይወትህ ፣ ከሰዎች ጋር ያለህ ግንኙነት እና በዙሪያህ ያሉ ነገሮች በሙሉ ይቀየራሉ!
ስለዚህ ነገሮቹን ከመቀየርህ በፊት እራስህን ቀይር። ምርጡን ማንነትህን ቀድመህ ገንባውና ጨርስ። ይህ ያልሆነ እንደሆነ የገነባኸውን ቤት በእጅህ ታፈርሰዋለህ።
መሰረቱ አንተ ነህ ሌላው በአንተ ላይ የሚታነፅ ነው። አንተ ካልጠነከርክ ፡ ካልበረታህ መቼም የምትፈልገውን ኑሮ አትኖርም። ያ የምትናፍቀው መንፈሳዊ ህይወት ምኞት ሆኖ ይቀራል። ስለዚህ ለራስህ ፅናትን ፡ ትግስትን ፡ ቆራጥነትን ፡ ታታሪነትን አስተምረው።
በፍቅር የተፃፈ ❤

❤1👍1🔥1
ልካችንን እንወቅ
በእጃቸው እንዲገባ የሚፈልጉትን ነገር ከአላማቸው አንፃር የቃኙና ልካቸውን የሚያውቁ ሰዎች በዚህ ምድር ላይ ያላቸውን ዓላማና ግብ በሚገባ አውቀውና አገናዝበው ለዚያ አላማቸውም ምን እንደሚያስፈልጋቸው ለይተው የተደላደሉ የተመቻቹ ሰዎች ናቸው።
ልክህን ስታውቅ ተለክተህ እንደተፋለህ ልብስ ሁሉ አስተሳሰብህም ሆነ ምኞትህ በአንተ አቅም መመጠኑን ያሳይሃል።
ልክህን እወቅ ሲባል ቀላል ንግግር አይደለም። በልክህ መኖር፣ በልክህ መመላለስ ፣ በልክህ ማሰብ፣ በልክህ መብላት፣ በልክህ ማውራት የመጠንህንና የአቅምህን ልኬት ያሳይሃል።
በልክህ ባሰብክ ቁጥር ጭንቀትን መቀነስ ትችላለህ ከአቅምህ በላይ ባማይመለከትህ፣ በማያገባህ ነገረ ያሰብክ እንደሆነ ግን ማሰቡን ትተህ ወደ ጭንቀት ጉድጓድ ሰተት ብለህ ገባህ ማለት ነው።
ሁሉም ነገር በልክና በአቅም መጠን ሲሆን ውብ ነው፤ ደስም ይላል። ልክህ የህይወትህ ጠዓም መለኪያ ነው። በልክህ እየኖሮክ እንደሆነ የህይወት መልካም ገፀበረከት ያለማንም ከልካይነት ወደ ቤትህ ይገባል። ስለዚህ በልክህ መኖርን አዘውትር፣ በልክህ ማሰቡንም እንዲሁ። በልክህ አውራ ፣ በልክህ እየወጣህ ግባ። ያለ አቅምህ እየተንጠራራህ እንዳትሰበር ተጠንቀቅ።😎😎
love you .!

❤2👍1🔥1
"ቍጣው ለዐጭር ጊዜ ነው፤ ቸርነቱ ግን እስከ ዕድሜ ልክ ነውና፤ ሌሊቱን በልቅሶ ቢታደርም፣ በማለዳ ደስታ ይመጣል።"
(መዝሙር 30:5)
🍀 እግዚአብሔር የመጽናናት ሁሉ አምላክ ነው በመሆኑ ከማንም በላይ የሚያፅናናን እርሱ ነው።
🍀 ኀጢአታችንና ዐመፃችንን በከባድ ሁኔታ ቢቀጣም ይህንን የሚያደርገው ለመልካም ነው። ቁጣው ለዐጭር ጊዜ ቢሆንም ከዚያ ተከትሎ ደስታ ይመጣል። እግዚአብሔር እየገሠጻችሁ ከሆነና የኀጢአትን መዘዝ እየተቀበላችሁ ከሆነ ተስፋ አትቁረጡ።
🍀 ማለዳ ይመጣል፣ ጎህ ሲቀድም የእግዚአብሔር ጸጋ ይመጣል። ይህ ልንጠብቀው የሚገባው ተስፋ ነው።
🍀 አባት የሚወደውን ልጅ ስለሚወደው ይቀጣል እግዚአብሔርም እንዱሁ ያደርጋልና ቅጣቱንም የሚቀበል ልብ ይኑራችሁ።
🍀 ጨለማ ሲያልቅ ብርሃን እንደሚመጣ ሁሉ ከቁጣው በኋላ ደስታና መልካም ስጦታው እንደ ወገግታ ሆኖ ይወጣል።
Love you ❤

🍀 ይህ ይህወት እግዚአብሔር በቸርነቱ የሰጠን ነው።
🍀 የሕይወት ዋጋዋ ስንት ነው ?
ዋጋው ያኖረን ቸርነቱ ነው። እስትንፋሳችን በአፍንጫችን ላይ የተንጠለጠለች ፣ ለመሄድ የተዘጋጀች ናት። እስትንፋሳችንን በአፍንጫችን ያሳደረልን ፣ ያዋለልን ጌታ ቸር ነው። ይህን ቸርነቱን ማጣጣም ፣ ማመስገን ፣ መመስከር ይገባል።
🍀 በእግዚአብሔር የሚታመን ሰው ምስጉን ነው።

❤4👍1🔥1
ሰው ካከበረው እግዚአብሔር ያከበረው እጅጉን ይበልጣል፤ ሰዎች በሁኔታዎች ይቀየራሉ፣ እንዳስቀመጥክ ላታገኛቸው ትችላለህ። የሰው ልጅ ሸምበቆ ነው ተደግፈኸው የሆነ ቀን ሊቀነጠስ ይችላል። ሙሉ እምነትህን እግዚአብሔር ላይ ብቻ አድርገው!
እግዚአብሔር አያሳፍርህም። ሞገስና ጌጥ ፡ ክብርና ዝና ፡ መካሪና ወዳጅ ፡ አጋዥና መሪ ፡ እናትና አባት ፡ ጓደኛና አድማጭ ይሆንልሃል ❤
@Christian_Insight
@Christian_Insight
እግዚአብሔር አያሳፍርህም። ሞገስና ጌጥ ፡ ክብርና ዝና ፡ መካሪና ወዳጅ ፡ አጋዥና መሪ ፡ እናትና አባት ፡ ጓደኛና አድማጭ ይሆንልሃል ❤
@Christian_Insight
@Christian_Insight
👍3🥰2❤1
በእግዚአብሔር የታመነችን ፣ ስንፍናን የናቀች አይኖቿን ከሁኔታዎች እና ከከበቧት ችግሮቿ አንስታ ወደ አምላኳ ያደረገችን ሴት ማንም እንደፈለገ አይሰብራትም እንዳሻዉም አያታልላትም ምክንያቱም እግዚአብሔር ለመንገዷ መሪ ለእግሮቿ መብራት ለልቧም ብልሀት እና ሞገስ ነዉ።
@Christian_Insight
@Christian_Insight
@Christian_Insight
@Christian_Insight
❤4🔥2👍1
ከገበያው ውጡ
ያላችሁበት ገበያ ምን የሚሸጥበት እንደሆነ ስለማታውቁ አብዛኞቻችሁ ያላችሁበት ገበያ ለእናንተ የሚመጥን አይደለም።
አያችሁ ይሁዳ መገኘት በሌለበት ገበያ ተገኝቶ ነው ክርስቶስን ሽጦ የወጣው። መሸጡ የማይገባ እንደሆነ ተረድቶ ለመመለስ እና ክርስቶስን ለማስመለስ ቢመለስም እሺ ብለው አልመለሱለትም ነበር።
እናንተስ የትኛው ገበያ ውስጥ ነው ያላችሁት ? ምናልባት ክርስቶስ የሚሸጥበት ገበያ ቢሆንስ ? አሁን አንድ ነገር አድርጉ ያላችሁበትን ገበያ ተመልከቱ። ምድር ክርስቶስን ለሚሸጥ ትልቅ ጥቅምና ቦታ ትሰጣለች። ምናልባት የተሰጠን ትልቅ ቦታ የተሰጠን ክርስቶስን በዚያ ቦታ ላይ አስጥሎን ቢሆንስ ?
ክርስቶስ የሚሸጥበት ገበያ በተለምዶ የሚሞቅና የሚደራ ነው። ለመሳተፍም መነሳሳትን ይፈጥራል።
ገበያው ምናልባት የምንሰራው ስራ ፡ የምንውላቸው ሰዎች ፡ የምንገባበት ቤት ፡ የምንውልበት ቦታ ፡ የምንወዳቸው ሰዎች even ቤተሰቦቻችን ሊሆኑ ይችላሉና በደንብ ተመልከቱአቸው።
ክርስቶስ የሚሸጥበት ገበያ መገኘትና በግብይቱ መሳተፍ የሚቀበሩበትን ጉድጓድ እንደ መቆፈር ነው።

❤4🥰2👍1