የክርስቶስ ደቀመዝሙር ✞
1.07K subscribers
663 photos
9 videos
6 files
62 links
* ይህ channel ሰለ እውነተኛ የክርስቶስ ደቀመዝሙርነት ከቅዱሱ መፀሀፍ የሚታይበት ነዉ፡፡

" ማንም መስቀሉን ተሸክሞ በኋላዬ የማይመጣ፥ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።" ሉቃ 14 : 27
Download Telegram
#_______"ጮሃችሁ አሜን በሉ፣______#
ባትፀልዩም እግዚአብሔር የሚያስፈልጋችሁን ያውቃል"
⛪️⛪️⛪️እለቱ እሁድ በመሆኑ አዳራሹ በሰው ሙልት ብሎ ይታያል። የእለቱ የዝማሬ መሪዎች ከስድስት የማያንሱ ዝማሬዎችን ቀጣጥለው ከዘመሩ በኋላ የእለቱ ሰባኪ መድረክ ላይ ቆመ። በዚያ ቤተክርስቲያን ለማምለክ ከዚያ በፊት ተገኝቼ የማውቅ አይመስለኝም። በዚያን ዕለት ግን 'እግዚአብሔር ዛሬ ምን ይናገረኝ ይሆን?' በሚል ጥማት ጉባኤው መሃል ተቀምጬ እንደነበር አስታውሳለሁ።

ሰባኪው ሕዝቡን ለማነቃቃትና አሜን ለማስባል ይጠቅማል ብሎ የሚያስበውን ሁሉ እያደረገ ነው። ከሰባኪው መወራጨት በላይ እኔን የገረመኝ ግን የህዝቡ ስሜታዊነትና ያለማስተዋል አሜን ባይነት ነበር። ሰባኪው በቅጡ ያነበበው የመፅሃፍ ቅዱስ ክፍል አልነበረም። ወጥ የሆነ ሃሳቡ ግልፅ ባይሆንም አልፎ አልፎ እግዚአብሔር መልካምና ፍቅር እንደሆነ እየተናገረ ቀጠለ። ከዚያም "እኔ እኮ አንዳንዶቻችን ለምን ፆም ፀሎት፣ ደጅ መጥናት ምናምን እያልን እንደምንጨናነቅ አይገባኝም። እየው ወንድሜ ፀለይክም አልፀለይክም በረከቱ ያገኝሃል። እስኪ ጮሃችሁ አሜን በሉ፣ ባትፀልዩም እግዚአብሔር የሚያስፈልጋችሁን ያውቃል...።" ገና ንግግሩን ሳይጨርስ አዳራሹ በአሜንታ፣ በእልልታና በጭብጨባ ተናጋ። ሰባኪው ቀጥሏል.. በህዝቡ ድጋፍ የተደሰተ ይመስላል። "አስቡት እስኪ እናንተ ልጆቻችሁ ተርበው ምግብ እስኪጠይቁ ትጠብቃላችሁ? እግዚአብሔርም ለልጆቹ እንዲሁ ነው፣ አጠገባችሁ ያለውን ሰው ጨበጥ አድርጋችሁ አይን አይኑን እያያችሁ "አታካብድ፣ ባትፀልይም የሚያስፈልግህን የሚያውቅ አባት አለህ በሉት" አለ። እየሆነ የነበረውን ሁሉ እጆቼን አጣምሬ መሃል ተቀምጬ ስለነበረ የማየው ሁኔታዬ ያላማራቸው ከጎኔ የተቀመጡት ከሌሎች ጋር ተጨባበጡ።
በውስጤ የነበረው የእግዚአብሔርን ቃል የማድመጥ ጉጉት በሃዘንና በቁጭት እንዲሁም በብስጭት ተተካ። የሰባኪው ሲገርመኝ የህዝቡ ደግሞ እጅግ አስደነገጠኝ። ፀሎትን የማይደግፍ ሰባኪና መፀለይ የማይፈልግ ትውልድ እጅግ እየበዛ ያለበት ጊዜ ላይ ደርሰናል። በእውነት እነዚህ ሰዎች ሌላው ሁሉ ቢቀር 'የፃዲቅ ሰው ፀሎት በስራዋ እጅግ ታላቅ ነገርን ታደርጋለች' የሚለውን እና ጌታችን ኢየሱስ 'ወደፈተና እንዳትገቡ ትጉና ፀልዩ' ያለውን ብቻ እንኳን ስለማያውቁ ነው ወይስ መፀለይ አያስፈልጋችሁም መባሉ ለስጋቸው ስለተመቻቸው?
ፍርዱን ለሚመለከተው፣ ልብና ኩላሊትን ለሚመረምረው ትቼ መልእክቴን ላስተላልፍ።

1⃣ፀሎት ጉዳይ ማስፈፀሚያ ሳይሆን ከእግዚአብሔር ጋር ጊዜ ማሳለፍ(ጌታን ማዳመጥና ለጌታ የውስጥን መንገር) ነው። ከእግዚአብሔር ጋር መሆን ጥያቄ ባይኖረን እንኳን ማንነቱን በመናፈቅ በፊቱ መደፋትንም ያካትታል። አሳ ከውሃ ውጪ እንደማይኖር እኛም ከህልውናውና ከድምፁ ርቀን መኖር ስለማንችል ፀሎት ለእውነተኛ የክርስቶስ ተከታዮች የመኖርና ያለመኖር ጉዳይ ነው።
2⃣ፀልዩ ብሎ ጌታ ካዘዘን ካልፀለይን ብዙ የምንጎዳበት ምክንያት ስላለ ነው። ያልተመለሱ ጥያቄዎች፣ ችግሮቻችን ከኛም አልፈን ለትውልድ፣ ለቤተክርስቲያን ለአለማችን ሁሉ የመፍትሔ ቁልፍ ያለው እግዚአብሔር እንዲሰራና ክንዱን እንዲገልጥ መፀለይ እጅግ ወሳኝ ነው። ባለመፀለያችን እኛ እንጂ እግዚአብሔር አይጎዳም ።
3⃣ፀሎት በእግዚአብሔር ላይ ያለንን እምነት በተግባር የምንገልፅበት መንገድ ነው። ወደ እግዚአብሔር ካልጮህን በሱ መታመናችን ምኑ ላይ ነው?
4⃣ፀሎት ሰይጣንን የምንዋጋበትና የምናሸንፍበት መሳሪያም ነው። በዚህ አጭር ፅሁፍ የፀሎትን ጥቅም መዘርዘር ባልችልም....ትውልዳችን አንዱ የተጎዳው የፀሎት መሰዊያው ስለፈረሰ ይመስለኛል።

🙏 እለት እለት በጌታ እግር ስር በመሆን ጌታ ይባርከን።
#ምንጭ_FB
👍👍👍
@christdisciples
#የክርስቶስ_ደቀመዝሙር
#የክርስቶስ_ደቀመዝሙር
#በኤልሻዳይ_ቴሌቪዥን_ኔትወርክ
#ቅዳሜ 5:30-6:00
በድጋሜ #አርብ 9:30-10:00

ስለ ክርስቶስና ስለ መስቀሉ የሚወራበት ለክርስቶስ እንዴት መኖር እንዳለብን የምንማርበት ወጣቶች ላይ ያተኮረ ልዩ ፕሮግራም ነዉ፡፡

በyoutube ቻናላችንን subscribe በማረግ ወይም የ Face book ፔጃችንን Like/Follo በማድረግ ትምህርቶቹን መከታተል ይቻላል፡፡

Watch "Christ Disciple : የክርስቶስ ደቀመዝሙር" on YouTube
https://youtu.be/89HfMIhBACU
#ጸሎት የደቀመዝሙር ሕይወት ትልቁ መገለጫና መለኪያ ነዉ ፡፡
በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 12 ደቀመዛሙርቱ ኢየሱስን ጸሎት እንዲያስለምራቸዉ እንደጠየቁት እንመለከታለን፡፡
" እርሱም በአንድ ስፍራ ይጸልይ ነበር፥ በጨረሰም ጊዜ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ። ጌታ ሆይ፥ ዮሐንስ ደቀ መዛሙርቱን እንዳስተማረ እንጸልይ ዘንድ አስተምረን አለው።" (የሉቃስ ወንጌል 11:1)

ስለዚህ በዚህ ሳምንት ስለ ጸሎት ጌታ ኢየሱስ ያስተማረዉን ትምህርት እንመለከታለን ፡፡ ደግሞም በደንብ ስለ ራሳችን( ስራ ፣ ትምህርት ፣ "አገልግሎት" ...) እንዲሁም ስለ ቤተሰባችን ፣ ሀገራችን እንጸልያለን ፡፡
መልካም ሳምንት፡፡
@christdisciples
#ጸሎት
በእርግጥ ጸሎት አብዛኛዉን ሀይማኖቶች የሚያመሳስል ድርጊት/ስርአት ነዉ ነዉ ፡፡ እንደየሀይማኖቱ ስርአቱና ሁኔታዉ ቢለያይም የማይፀልይ ሀይማኖት ተከታይ አለ ብሎ ማሰብ ግን ያስቸግራል፡፡ ወደ ክርስትና ስንመጣ ደግሞ ጸሎት የአንድ ክርስቲያን ዋንኛ መገለጫ መሆኑን እናያለን ፡፡

ዛሬ ስለ ጸሎት ማሰባችንን እንቀጥላለን ።
በዉኑ ጸሎት ጉዳይ ማስፀጸሚያ ነዉን?
ኢየሱስ ፣ ሐዋሪያት እንዲሁም የብሉይ ነቢያት ሲጸልዩ ለምንድን ነበር የጸለዩት? የምር ኑሮአቸዉ እንዲስተካከል ፣ እንዲሳካላቸዉ ፣ ችግር እንዲነሳ ለማረግ ብቻ ነበርን የጸለዩት ?

መልሱን ሁላችን እናስብበት ፤ ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ ይህን ፀሎት አስተምሮአቸዋል ፡፡ ይህስ ጸሎት ምን ምን ያካትታል?
@christdisciples
Forwarded from Deleted Account
የክርስቶስ ደቀመዝሙር ✞
Voice message
Temesgen Tadesse
(ውዴ እንደ አንተ ያለ)
Original mezmur Zerfe Kebede
የክርስቶስ ደቀመዝሙር ✞
Photo
#የምስራች_ይህ_ፅሁፍ_ለምታነቡ_በሙሉ ፡፡
በእግዚአብሔር እርዳታ የክርስቶስ ደቀመዝሙር አገልግሎት አስተባባሪዎች ጸሎት ለሚፈልጉ ሁሉ ለመጸለይ ስላሰቡ ማንኛዉንም አይነት የጸሎት ርዕስ (እንዲጸለይላችሁ የምትፈልጉትን) በfacebook አድራሻችን
fb.com/christdiscipless
✔️Send Message✔️ የሚለዉን በመጫን እንድታረጉልን እንጠይቃለን፡፡ በእርግጥ ዳግም የተወለደ ሁሉ የእግዚአብሔር ልጅና በእግዚአብሔር እኩል የሚሰማ ነዉ ይሁን እንጂ መጸሀፍ ቅዱስ ደግሞ አንዱ ለሌላዉ እንዲጸልይ ያሳስበናል ፡፡

" ወንድሞች ሆይ፥ ስለ እኛ ጸልዩ።"
(1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 5:25)

ስለዚህ ማንኛዉንም የጸሎት ርዕስ በዉስጥ መስመር እንድትልኩ እናበረታታለን ፡፡ የተላከዉ ርዕስ ሚስጢራዊነቱ እንደተጠበቀ ነዉ እናም የጸሎት ርዕሱን በዉስጥ መስመር profile ( facebook.com/christdiscipless ) ዉስጥ
✔️Send Message✔️ የሚለዉን በመጫን ይላኩ ፡፡

ጸሎት ለተቸገረ ሰዉ ወደ ጌታ የሚደረግ ጥሪ ብቻ አይደለም ይልቁንስ ጠንክሬአለሁ ብሎ ለሚያስብም ሰዉ መንፈሳዊ ልምምድና ተግባር ነዉ ፡፡

አንድ ክርስቲያን የበለጠ አምላክን ሲጠጋዉና ወደሱ ሲቀርብ የበለጠ የአምላክ እርዳታ እንደሚያስፈልገዉ ይረዳል ፡፡ ስለዚህ የጸሎት ሕይወቱን እየጨመረ ይሄዳል ማለት ነዉ ፡፡
የክርስቶስ ደቀመዝሙር ✞
Photo
ለክርስቶስ ደቀመዝሙር ፔጅ ቤተሰቦች ፡፡ በዚህ ሳምንት ስለ ጸሎት ጥሩ ነገር እንዳገኛችሁ እናምናለን ፡፡

ዋናዉ ግን ስለ ጸሎት ማወቅ ሳይሆን ጸሎትን ማወቅና መጸለይ ነዉ ፡፡ ጌታ እግዚአብሔር ግዜያችንን ሰተነዉ እንድናወራዉ ይፈልጋል ፡፡ አንድ የምንወዳትን ልጅ ወይም የምንወደዉን ልጅ ለማዉራት እንዴት እንደምንመኝ ፣ የምንወደዉም ሰዉ ጊዜዉን ሰቶ ሲያዋራን ምን ያህል ደስ እንደሚለን አስቡት?

ጸሎትም ደግሞ ከዚህም የባሰ ነዉ ፡፡ እግዚአብሔር በጣም ስለሚወደን ሁልጊዜ እንድናዋራዉ ይፈልጋል ፡፡ የምወደዉ ልጄ መቼ ነዉ የሚያዋራኝ ብሎ ያስባል ፡፡ ይሄ ሁሉ ግን ለኛ ጥቅም እንጂ እሱ ምንም ጎሎበት አይደለም ፡፡ ስለዚህ እባካችሁ የጌታ መልዕክትኛ ሁኜ ልጠይቃችሁ ፡፡ ፀሎት የሚጀመረዉ ለ 3 ሰአት ወይም ከዛ በላይ በመጸለይ አይደለም ፡፡ ይልቁንም ጠዋት በሰላም አዉለኝ ፣ ማታ በሰላም አሳድረኝ ብለን ነዉ ፡፡ በእርግጥ በነጋታዉ ደግሞ በሰላም ስላሳደርከኝ አመሰግንሀለዉ በሰላም ደግሞ አዉለኝ እያልን ከአምላክ ጋር ያለንን ንግግር እየጨመርን እንሄዳለን ፡፡
ጸሎት
ጸሎት
ጸሎት ... አምላክን የበለጠ እንድንወደዉ ይረዳናል ፡፡

ምድራዊ ሕይወታችንም በተስፉ በደስታ በፍቅር የተሞላ ያረገዋል ፡፡
@christdisciples
#እስከ አርብ ምሳ ሰአት የቀሩ የጸሎት ርዕሶቻችሁን እንድትልኩ እንጠይቃለን ?

#58 ሰዋች የፀሎት ርዕስ ስለላካችሁልን እናመሰግናለን ፡፡ እግዚአብሔር ደግሞ የሁላችሁንም ጥያቄ እንደሚመልስ በማመን ወደ ጌታ ስለናንተ #የካቲት ወር በሙሉ እንጸልያለን ፡፡
ነገር ግን ነገ የካቲት 1 (አርብ ለሊትም) ለሁላችሁም በአጠቃላይ የሚፀለይ ይሆናል ፡፡ ስለዚህ የጸሎት ርዕስ ያላካችሁና እንዲጸለይላችሁ የምትፈልጉ ሰዋች አርብ (ነገ) ምሳ ሰአት ድረስ በክርስቶስ ደቀመዝሙር profile ዉስጥ Send Message የሚለዉ በመጫን መላክ ትችላላችሁ ፡፡ fb.com/christdiscipless

አንዳንዱ የጸሎት ርዕስ ደግሞ በመነጋገር (በዉይይት ) ስለሚመለስ በጥቂት ቀን በዉስጥ መስመር ፈቃደኛ ከሆናችሁ እናናግራችኀለን ደግሞም በጋራ እንመካከራለን እንጸልያለን፡፡

ጌታ እግዚአብሔር ይባርካችሁ ፡፡
ነገ #ቅዳሜ ከ 5:30 - 6:00
#በኤልሻዳይ_ቴሌቪዥን_ኔትወርክ
ስለ #ሐዋሪያዉ_ጴጥሮስ ታሪክ ይቀርባል።

በፕሮግራሙ ፦
#ጴጥሮስ ምን አይነት ባህሪ ነበረዉ
#ጴጥሮስ በምን አይነት ሁኔታ ዉስጥ ሁኖ በኢየሱስ ተጠራ እናም ማን ወደ ኢየሱስ መራዉ
#የጴጥሮስ ደቀመዝሙራዊ ሕይወት ምን ይመስል ነበር?
#ጴጥሮስ እንዴት ሞተ?
#ከጴጥሮስ የደቀመዝሙርነት ሕይወት ምን እንማራለን?
#ጴጥሮስ ከሌሎቹ ሀዋሪያት ይልቅ ከኢየሱስ ምን ተማረ ?

የሚሉትን ጥያቄዋች ከነመልሳቸዉ እንመለከታለን፡፡
@Christdisciples
#የፀሎት_ርዕስ ለላካችሁ ወንድሞቼና እህቶቼ ፡፡ ጌታ ይባርካችሁ ፡፡ የሁላችሁም የፀሎት ርዕስ በዚህ ወረቀት ላይ ሰፎሯል ፡፡

እስከ አርብ ማታ ከራሴ የፀሎት ርዕስ ጋር የ 93 ሰዉ ርዕሶች ደርሰዉኛል ፡፡ እናም ትናንት አርብ ለሊት በጌታ እርዳታ ለሁላችሁም በሕብረት ተፀልዮል ፡፡ ስለዚህ ጌታ ፀሎታችሁን ይመልሳል ብዬ አምናለሁ ፡፡ በቀረዉ ግን በዚህ የካቲት ወር ሙሉ ለሁላችሁም ዛሬ የላካችሁትን ጨምሬ ለየብቻ ጌታ በረዳኝ መጠን እፀልያለሁ ፡፡
እንዲሁም በ Telegram የፀሎት ርዕስ መላክ የምትፈልጉ @cdimage መላክ ትችላላችሁ፡፡
ጸሎት
ጸሎት
" ወዲያውም የደምዋ ምንጭ ደረቀ ከሥቃይዋም እንደዳነች በሰውነትዋ አወቀች።"
(የማርቆስ ወንጌል 5:29)

በኢየሱስ ስም ችግራችሁ ብቻ ሳይሆን የችግራችሁ ምንጭ የደረቀ ይሁን፡፡ 12 አመት ስትሰቃይ የነበረችዉን ሴት ብዙ ሰዋችና ባለመዳኒቶች ጋር ሂዳለች ፡፡ በእርግጥም ብዙዋቹ ደሟን አድርቀዉላት ይሆናል ፡፡ ነገር ግን ምንጩ ስላልተነካ ለ12 አመት ሙሉ ስትንከራተት ነበር፡፡ ኢየሱስን ግን ስታየዉ ደሟን አልነበረም ያደረቀላት ፡፡ የደሟን ምንጭ ነበር ፡፡
የችግራችሁ ምንጭ ድጋሜ ላይነሳና ላይረብሻችሁ በኢየሱስ ስም ለዘላለም ይድረቅ፡፡
አሁን አንድ ወዳጄ ሰርግ ላይ ነኝ ፡፡ በሰርጉ ቦታ በጊዜም ሆነ አርፍዶ የደረሰዉ ሁሉ በጉጉት የሙሽሮችን መምጣት እየተጠባበቁ ነዉ ፡፡ ግን ለምን ነዉ የሚጠብቁት ብዬ ሳስብ ? የመጣልኝ መልሶች ፡፡

1. አንዳንዱ ሙሽሮች ካልመጡ ምግብ ወፍ እንደሆነ (ብፌ መነሳት እንደማይጀምር ) ስለሚያዉቅ 😂
2.አንዳንዱ የሙሽሮችን ዉበት ለማድነቅና ሰርጋቸዉን ለማድመቅ
3.አንዳንዱ ቀረ ላለመባል ሰርጉን ቶሎ ጨርሶ ወደ ሌላ ስራዉ ሊሄድ
4.እና በጣም ብዙ ምክንያት ...

#የፅሁፋ_ቁምነገር_ግን_ይኼ_ነዉ፡፡ ዉዱ ወንድሜ ፣ ዉዷ እህቴ ማራናታ ፣ ጌታ ሆይ ቶሎ ና የምንለዉና የሱን መምጣት የምንጠባበቀዉ ለምንድነዉ???

አሁንም በዚህ ሀሳብ ሁኜ ሙሽራን እየጠበኩ ነዉ ፡፡ እኔስ ለምን ምክንያት ይሆን የምጠብቀዉ ??
" እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።"
(የማቴዎስ ወንጌል 11:28)

ወንድሜ ፥ ሕይወት ከብዶሀል? ሁሉ ነገር ሰልችቶሀል ?
#ወደ ኢየሱስ ና???

እህቴ ፥ እረፍት አጣሽ ? ደስታሽ አለቀ ?
#ወደ ኢየሱስ ነይ ?

እኔ ወደ ኢየሱስ እሄዳለሁ ፡፡ ከነ ጉድለቴ ፣ ከነ ችግሬ ፣ ከነ መጥፎ ፀባዬ ፡፡
ኢየሱስ አንተ ታሳርፈኛለህ ፡፡
አንተ ከእስራቴ ትፈታኛለህ ፡፡
አንተ ቀንበሬን ትሰብራለህ ፡፡

Graphics ©Biruk
የአደጋ ጊዜ መዉጫ!
@Christdisciples
ስለ ጸሎት ይህን ያዉቁ ኗሯል?