Forwarded from የክርስቶስ ደቀመዝሙር ✞
"ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን፤ በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፤ አሰሮ ለሰይጣን፤ አግዐዞ ለአዳም፤ ሰላም እምይዕዜሰ፤ ኮነ፤ ፍስሐ ወሰላም።"
“ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ሥልጣን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ ዲያብሎስን አሰረው አዳምን ነጻ አወጣው ሠላም ከዛሬ ጀምሮ ሰላም ሆነ” ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲህ ፍጹም ሠላምና ደስታ ሆነ።
እንደተነገረው ተነስቷልና ከዚህ የለም ፣
ማቴ 28፣6
ጌታችን በአምስት ነገር በኩራችን መሆኑን መጻሕፍት ይነግሩናል
1. በጥንት ዓለም ሳይፈጠር ዘመን ሳይቆጠር ኖሮ እኛን ፈጥሮ ለማስገኘት በኩራችን ነው፡፡
2. በተቀድሶ/በመመስገን/ በኩራችን ነው፡፡ ቅዱሳን የጸጋ ምስጋና የሚመሰገኑት እርሱን በኩር አድርገው ነውና፡፡
3. በትንሣኤ በኩራችን ነው፡፡ እርሱን በኩር አድርገን እንነሣለንና “አሁንም ክርስቶስ ከሞቱ ሰዎች ሁሉ አስቀድሞ ተነሥቶአል በመጀመሪያው ሰው ሞት መጥቶአል በሁለተኛው ሰው ትንሣኤ ሙታን ሆነ” 1ቆሮ.15፥20፡፡
4. በዕርገት በኩራችን ነው፡፡ ቅዱሳን አረጉ መባሉ እርሱን በኩር አድርገው ነውና፡፡ “አርገ ከመ ያሌቡ ዕርገተ ጻድቃን ንፁሀን” የንፁሀን ጻድቃንን ዕርገት ያስረዳ ዘንድ አረገ ቅዳሴ ዩሐንስ ወልደ ነጎድጓድ”
5. ነፍሳትን ከሲዓል አውጥቶ ምርኮን ማርኮ ገነት መንግሥተ ሰማያት በመግባት በኩራችን ነው፡፡
እንኳን ለብርሀነ ትንሳዬው በሰላምና በጤና አደረሳችሁ @Christdisciples

❤3👍2🔥2
#ቀን_አንድ ፩/1 (የመጀመሪያ ቀን) ሰኞ
" #በነጻነት_ልንኖር_ክርስቶስ_ነጻነት_አወጣን፤ እንግዲህ ጸንታችሁ ቁሙ እንደ ገናም በባርነት ቀንበር አትያዙ።" (ወደ ገላትያ ሰዎች 5:1)
ክርስቶስ በሞቱና ትንሳኤዉ ከህግ ቁጥጥርና አድርግ አታድርግ ከሚል ስርአት ወደ ጸጋዉ ሕይወት ነጻ አዉጥቶናል ፡፡
በእርግጥ ሕጉ የሚታዘዙትን (የሚፈፅሙትን) ቢያጸድቃቸዉም የሰዉ ልጅ በሙሉ ግን በፍፅምና ሕጉን መጠበቅ ተስኖት የኃጢአት ባሪያ ሁኖ ሕይወቱን መርቷል ፡፡ ኢየሱስ ግን ራሱ በመስቀል የሁላችንን ኃጢያት ሁኖ ተሰቅሎልን በሕግ ከመጽደቅ ያለ ስራ በፀጋዉ ወደ መፅደቅ ነፃነት ወሰደን ፡፡
#ክርስቶስ_በሕግ_ሳይሆን_በጸጋዉ_አጽድቆናል ፡፡ ከዘላለም ሞትና ፍርድ ነፃ አዉጥቶናል @christdisciples

❤5👍2
#ቀን_ሁለት ፪/2 ማክሰኞ
" ... #የልጁም_የኢየሱስ_ክርስቶስ_ደም_ከኃጢአት_ሁሉ_ያነጻናል።"
(1ኛ የዮሐንስ መልእክት 1:7)
ከአዳም ጀምሮ የሰዉ ልጅን ባሪያ አርጎ ሲገዛ የነበረዉ ፣ ወደማይፈልግበት የሚነዳዉ ትልቁ የሰዉ ልጅ ጠላት ኃጢያት ነበር ፡፡ ኃጢያት ደግሞ የሚሰራ ብቻ ሳይሆን የሰዉ ማንነት ሆኖ ሰዉን ከአምላኩ አጣልቶ ከወንድሙ አባልቶ የሰዉ ልጆችን ሁሉ በምድር ያልተገባ ሕይወት እንዲኖሩ የሚያስገድድ ሀይል ነበር፡፡
የሰዉ ልጆች በዘመናቸዉ ከጥንት ጀምሮ ከዚህ ጨቋኝ ገዢ ለመላቀቅ ቢያስቡም የሚቻልና የሚዘለቅ አልነበረም ፡፡ አምላክም ፍጡሩን ስለሚወድ ከዚህ እንዲወጡ የተለያየ መንገድ ሲያዘጋጅላቸዉ እንደነበር መፀሀፍ ቅዱስ ይነግረናል ፡፡ ይሁን እንጂ የሰዉ ልጆች አምላክ የሰጣቸዉን ህግ ለመጠበቅ ሲጣጣሩ ነገር ግን ሳይችሉ ደግሞም መስዋት በማቅረብ ለኃጢአታቸዉ ስርየት ደም ሲያፈሱ እንደነበር ቅዱስ ቃሉ ይነግረናል፡፡
ይህም ሆኖ ዘላቂ መፍትሔ ማምጣት አልተቻለም ፡፡ ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በቀረበ ጊዜ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን ስለ ሰዋች ሁሉ ኃጢያት መስቀል ላይ ሰዋዉ ፡፡ ልጁም ኢየሱስ ስለኛ ታዞ በመስቀል ላይ ደሙን አፈሰሰልን ይህንንም ደም ይዞ ስለኛ ዘወትር ሊማልድ በአብ ቀኝ ተቀመጠ ፡፡ አሁን በእርሱ ለሚያምኑ ሁሉ ባፈሰሰዉ ደም ኃጢያታቸዉን ሊያነጻ ስለኛ በአብ ዘንድ ጠበቃ ሆኖ ተቀምጧል፡፡
የኢየሱስ ደም ከኃጢያት ሁሉ ያድናል ፡፡ ወንድሜ ፥ በኃጢያት ዉስጥ አለህ ፣ ማንነትህ ኃጢያት ነዉ ? እንግዲያዉስ ኃጢአትህን ሁሉ ሊያነፃ ወደሚችል ወደ ኢየሱስ ተመለስ፡፡
ማመሳከሪያ ጥቅስ ፦" ... ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።"
(ሮሜ 8:34) መልካም ቀን! @christdisciples

#ቀን_ሶስት ፫/3 ረቡዕ
" አሁን ግን እናንተ በፊት ርቃችሁ የነበራችሁ #በክርስቶስ_ኢየሱስ_ሆናችሁ_በክርስቶስ_ደም_ቀርባችኋል ።"
(ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2:13)
ሰዋች ሁላ በኃጢአታችን ምክንያት የቁጣ ልጆች የነበርን ሲሆን ከእግዚአብሔር ክብር ርቀን በመከራ በሀዘን እንኖር ነበር ፡፡ ነገር ግን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ስለ በደላችንና ስለ መተላለፋችን ባፈሰሰልን ደም ወደ እግዚአብሔር ክብር መቅረብ ሆነልን ይህም ሳይበቃ የእግዚአብሔር ወራሽ አደረገን ደግሞም እግዚአብሔርን እንመስል ዘንድ ከክብር ወደ ክብርም እየለወጠን ልጆቹ አደረገን፡፡
ድሮ ለእግዚአብሔርም ሆነ ለእርሱ ሕዝቦች ባዳ ሁነን እንኖር ነበር አሁን ግን ቤተኛ ብሎም ልጆች ሁነናል ፡፡
እዩት ኢየሱስን መስቀሉ ማማሩ
ለተመራመረዉ ብዙ ነዉ ሚስጥሩ !
በእዉነት ለሰዉ ልጆች በመስቀል ላይ የተሰራዉ ስራ ከመረዳት ያለፈና የሰዉ ልጅ ታሪክን ላንዴና ለመጨረሻ የቀየረ ስራ ነዉ ፡፡ በመስቀል ላይ በክርስቶስ ያየነዉ ፍቅር ለስፋቱ ድንበር ፣ ለጥልቀቱ መድረሻ የሌለዉ እጅግ በጣም ሰፊ የሆነ ነዉ ፡፡ መልካም ቀን! @christdisciples

❤4
#ቀን_አራት ፬/4 ሀሙስ
" የአዲስም ኪዳን መካከለኛ ወደሚሆን ወደ ኢየሱስ፥ #ከአቤልም_ደም_ይልቅ_የሚሻለውን_ወደሚናገር_ወደ_መርጨት_ደም_ደርሳችኋል ።"
(ወደ ዕብራውያን 12:24)
በመስቀል ላይ የፈሰሰልን ደም ተራ የአንድ ሰዉ ደም ብቻ አይደለም በመስቀል ላይ የፈሰሰዉ ደም አምላክ ሰዉ ሁኖ ስለኛ መተላለፍና በደል የከፈለዉ ዋጋ እንጂ ፡፡ ይህ ደም እንደ ዋዛ ፈሶም የቀረ ደም አይደለም ይልቁንስ ወደ እግዚአብሔር ዘወትር
ስለ ምህረት ፣ ይቅርታ ስለኛ የሚጮህ ነዉ ፡፡
" አለውም። ምን አደረግህ? የወንድምህ የደሙ ድምፅ ከምድር ወደ እኔ ይጮኻል። "
(ኦሪት ዘፍጥረት 4:10)
በእርግጥ ቃየን ወንድሙ አቤልን ሲገለዉ የአቤል ደም ስለ ራሱ ፍትህ ወደ እግዚአብሔር ይጮህ ነበር በመስቀል ላይ ስለኔና ስለናንተ የፈሰሰዉ የንጉሳችን ኢየሱስ ደም ግን ስለ ራሱ ሳይሆን ስለኛ ምህረትና ይቅርታ ዘወትር ይጮኸል ፡፡ በእርግጥ እግዚአብሔር ከአቤል ይልቅ ለሚጮኸዉ ደም እንዴት ምህረቱን በኢየሱስ በኩል ለህዝቡ አይሰጥ???!
መልካም ቀን!
@christdisciples

❤1
#ቀን_አምስት ፭/5 አርብ
" እንዲሁ ክርስቶስ ደግሞ፥ የብዙዎችን ኃጢአት ሊሸከም አንድ ጊዜ ከተሰዋ በኋላ፥ ያድናቸው ዘንድ ለሚጠባበቁት ሁለተኛ ጊዜ ያለ ኃጢአት ይታይላቸዋል። "
(ወደ ዕብራውያን 9:28)
በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት አምነን ለዳንን እኛ ፦ በአብ ዘንድ ሁልጊዜ የሚታይልን ዘራችን ፣ ቋንቋችን ፣ የትምህርት ደረጃችን ፣ የሀብት መጠናችን ፣ የጤና ሁኔታችን ሳይሆን ስለኛ እንደተሰቀለ ያመነዉ ክርስቶስ ነዉ ፡፡ እሱ ደግሞ በእግዚአብሔር አብ ፊት ቅዱስ መስዕዋትና ለእኛ ጠበቃ ነዉ ፡፡
መስቀሉን ስናስብ ፍቅሩን እናስታዉስ ፤
መስቀሉን ስናይ የተከፈለልንን አንርሳ ፤
ይህ ሁሉ ስቃይ ፣ ይህ ሁሉ መከራ በአምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ላይ የደረሰዉ እኛን ከዘላለም ፍርድ ለማዉጣት ስለኛም በአብ ፊት በፍፅምና ለመታየት ነዉ ፡፡

#ቀን_ስድስት ፮/6 ቅዳሜ
" ሙሴም በምድረ በዳ እባብን እንደ ሰቀለ እንዲሁ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ የሰው ልጅ ይሰቀል ይገባዋል።"
(የዮሐንስ ወንጌል 3:14-15)
እግዚአብሔር በብሉይ ኪዳን ጊዜ ህዝቡን ከስጋ ሞት ሊያድን ሙሴን የነሀሱን እባብ በመስቀል ላይ እንዲሰቅል አደረገ ፡፡ ያንን የተሰቀለ እባብ ያየ ሁላ ከስጋዉ ሞት ይድን ነበር ፡፡ በእርግጥ በመስቀል ላይ የተሰቀለዉ እባብ የሚወክለዉ እርግማንንን ሀጢያትን ክፋትን በደልን ነበር ፡፡
በሚሻለዉ በአዲሱ ኪዳን ግን እግዚአብሔር ህዝቡን ከስጋዊ ሞት ሳይሆን ከስጋ ሞት ከሚከፋዉ ዘላለማዊ ሞት ሊያድን አንድያ ልጁን በመስቀል ላይ እንዲሞት ወሰነ ፡፡ ኃጢያት የማያዉቀዉንም ቅዱስ ልጁን በመስቀል ላይ ስለሁላችን በደል ኃጢያት አርጎ ስለኛ ክፋት እኛን ለማዳን ሰቀለዉ ፡፡
ማጣቀሻ
(ኦሪት ዘኍልቍ ምዕራፍ 21)
6፤ እግዚአብሔርም በሕዝቡ ላይ እባቦችን ሰደደ፥ ሕዝቡንም ነደፉ፤ ከእስራኤልም ብዙ ሰዎች ሞቱ።
7፤ ሕዝቡም ወደ ሙሴ መጥተው። በእግዚአብሔርና በአንተ ላይ ስለ ተናገርን በድለናል፤ እባቦችን ከእኛ ያርቅልን ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጸልይልን አሉት።
8፤ ሙሴም ስለ ሕዝቡ ጸለየ። እግዚአብሔርም ሙሴን። እባብን ሠርተህ በዓላማ ላይ ስቀል፤ የተነደፈውም ሁሉ ሲያያት በሕይወት ይኖራል አለው።
9፤ ሙሴም የናሱን እባብ ሠርቶ በዓላማ ላይ ሰቀለ፤ እባብም የነደፈችው ሰው ሁሉ የናሱን እባብ ባየ ጊዜ ዳነ።
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ 5:21
እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንሆን ዘንድ ኃጢአት ያላወቀውን እርሱን ስለ እኛ ኃጢአት አደረገው።

#ቀን_እሑድ ፯/7 እሁድ
" በእኛ ላይ የነበረውን የሚቃወመንንም በትእዛዛት የተጻፈውን የዕዳ ጽሕፈት ደመሰሰው። እርሱንም በመስቀል ጠርቆ ከመንገድ አስወግዶታል።"
(ወደ ቆላስይስ ሰዎች 2:14)
ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሰዉ ልጆች ሁሉ በደል ሲሰቀል ከኛ ላይ ያልገፈፈልን ነገር አልነበረም ፡፡ የዘላለም ሞታችንን ፣ አበሳችንን መከራችንን ስቃያችንን እንዲሁም በበደላችን ምክንያት የነበረብንን የዕዳ ጽሕፈት አንድ ሳያስቀር በሱ በማመናችን ብቻ አስወገደልን ፡፡ ክብር ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ ይሁን፡፡
መልካም ሰንበት!

#ቀን_ስምንት ፰/8 #ሰኞ
#ሞት_ጥፋት_እልቂት_ከሀገራችን_ይወገድ !
" ሙሴም የእስራኤልን ሽማግሌዎች ጠርቶ አላቸው። በየቤታችሁ ጠቦት ምረጡ፥ ወስዳችሁም ለፋሲካ እረዱት።"
(ኦሪት ዘጸአት 12:21)
በብሉይ ኪዳን የሞት መለአክን በር መቃን ላይ የጠቦት ደም በመቀባት አምልጠዋል ፤ እኛ የአዲስ ኪዳን ነዋሪዎች ግን በእኛ ላይ ያለዉ ከዘለአለም ሞት የሚያስመልጠን የክርስቶስ ደም በእኛ ላይ አለ፡፡
ደሙ በመቃኔ ላይ ስለተቀባ
ደሙ በጉበኔ ላይ ስለተቀባ
ሞት አለፈ ሄደ እራቀ ከእኔ ጋር
የጌታዬን ደም አይቶ
የኢየሱሴን ደም አይቶ (፪x)
ሞት አለፈ ፣ ሞት አለፈ
ሄደ ከእኔ ርቆ
መልካም ቀን !

#ቀን_ዘጠኝ ፱/9 #ማክሰኞ
" በታላቅም ድምፅ። የታረደው በግ ኃይልና ባለ ጠግነት ጥበብም ብርታትም ክብርም ምስጋናም በረከትም ሊቀበል ይገባዋል አሉ።"
(የዮሐንስ ራእይ 5:12)
ክብር
ክብር
ክብር
ክብር
መስዋዕት ሆኖ ላዳነን ለጌቶች ጌታ ለነገስታት ንጉስ ኢየሱስ ይሁን ፡፡
መልካም ቀን ! @christdisciples

#ቀን_አስር ፲/10 #ረቡዕ
" ከሂሶጵ ቅጠልም ጭብጥ ውሰዱ፥ በዕቃ ውስጥ ባለውም ደም ንከሩት፥ በዕቃውም ውስጥ ካለው ደም ሁለቱን መቃኖችና ጉበኑን እርጩ፤ ከእናንተም አንድ ሰው ከቤቱ ደጅ እስኪነጋ ድረስ አይውጣ።"
(ኦሪት ዘጸአት 12:22)
እስራኤላዊያን በግብፅ ሳሉ የበራቸው መቃን ላይ የጠቦት ደም በመቀባት የሞት መለአክን አምልጠዋል ፤ እኛ የአዲስ ኪዳን ነዋሪዎችን ግን ከከበበን የዘለአለም ሞት የሚያስመልጠን የክርስቶስ ደም ነዉ፡፡
#ምህረት_ኢተፋ
ደሙ በመቃኔ ላይ ስለተቀባ
ደሙ በጉበኔ ላይ ስለተቀባ
ሞት አለፈ ሄደ እራቀ ከእኔ ጋር
የጌታዬን ደም አይቶ
የኢየሱሴን ደም አይቶ (፪x)
ሞት አለፈ ፣ ሞት አለፈ ሄደ ከእኔ ርቆ
የሞት መልአክት አያስፈራኝ
ተሸፍኛለሁ አያገኘኝ (፪x)
ዙሪያዬ ከደሙ ታጥሯል
ያን ቅጥር አልፎ እንዴት ይገባል (፪x)
መልካም ቀን! @christdisciples

❤2
Forwarded from የክርስቶስ ደቀመዝሙር ✞
#ቀን_አስራአንድ ፲፩/11 #ሀሙስ
(የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 20)
27፤ ከዚያም በኋላ ቶማስን። ጣትህን ወደዚህ አምጣና እጆቼን እይ፤ እጅህንም አምጣና በጎኔ አግባው፤ ያመንህ እንጂ ያላመንህ አትሁን አለው።
28፤ ቶማስም። ጌታዬ አምላኬም ብሎ መለሰለት።
መልካም ቀን!
@christdisciples
(የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 20)
27፤ ከዚያም በኋላ ቶማስን። ጣትህን ወደዚህ አምጣና እጆቼን እይ፤ እጅህንም አምጣና በጎኔ አግባው፤ ያመንህ እንጂ ያላመንህ አትሁን አለው።
28፤ ቶማስም። ጌታዬ አምላኬም ብሎ መለሰለት።
መልካም ቀን!
@christdisciples
#ቀን_አስራሁለት ፲፪/12 #አርብ
" የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት፥ ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና።"
(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1:18)
ዳንኤል አምደሚካኤል
🎵🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎶🎵
ሞኝነት ሆኖ አይደለም ፍቅሩን ቀምሼ ነው
ና ሲለኝ የተከተልኩት ነፍሴ ተማርካ ነው
ጠቢባን ያላዩት ዕውቀት ለእኔ ተገልጦ ነው
የጌታን የማዳን ሚስጢር ነፍሴ ተረድታው ነው
ከወርቅ ከዕንቁ በልጦብኝ ነው
ከማንም በላይ ተመችቶኝ ነው
የቱ ነው ታዲያ ሞኝነቱ
ለእኔ ጥበብ ነው ጌታን ማወቄ ኤሄሄ (፪x)
አምላኬን ማወቄ
አምላኬን ማወቄ አሃሃ/ኦሆሆ
አምላኬን ማወቄ (፪x)
እኔስ መድኃኒቴን ተስፋ አደርገዋለሁ
እኔስ ኢየሱሴን ተስፋ አደርገዋለሁ
ቢጐድልም ቢሞላው በእርሱ እታመናለሁ
እርሱ አይለየኝም ይህንን አውቃለሁ
ድንቁን አይቻለሁ በሕይወት ዘመኔ
ከኢየሱሴ በቀር ጌታ አላውቅም እኔ
ሞት ያላሸነፈው አምላክ እርሱ ብቻ
ዘመን የማይሽረው ነው የሌለው አቻ

#ቀን_አስራሶስት ፲፫/13 #ቅዳሜ
" እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን፤ ይህም ለአይሁድ ማሰናከያ ለአሕዛብም ሞኝነት ነው፥" (1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1:23)
ያለ ክርስቶስ ፣ ያለ መስቀል ድነት የለም ! የምናመልከዉ #የተሰቀለዉን_ክርስቶስን ነዉ !
የምንኖረዉ #ለተሰቀለዉ_ክርስቶስ ነዉ!
ዳግም መቶ የሚወስደን #የተሰቀለዉ_ክርስቶስ ነዉ!
ትክክለኛ ክርስቲያን ስብከቱ የተሰቀለዉ ክርስቶስ ነዉ !
#ተስፋዬ_ጋቢሶ
አይሁድ ምልክት ይለምናሉ
ግሪኮች ጥበብ ይሻሉ
ጌታን ጥለው ይቅበዘበዛሉ
አዝ፦ እኛ ግን የሞተልንን
በደሙም የተቤዥንን
አዳኝነቱን ንጉሥነቱን
ለፍጥረት ሁሉ እንሰብካለን
አዎን እንሰብካለን (፪x)
ያልገባቸው ያላወቁት በድንቅ
እንደ ሞኝነት ቢቆጥሩትም
በመስቀሉ ቃል አናፍርበትም

#ቀን_አስራ አራት ፲፬/14 #እሑድ
" መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።"
(የሐዋርያት ሥራ 4:12)
በተሰቀለው... እግዚአብሔርም ከሙታን ባስነሣው ...በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ብቻ!
መልካም ቀን !
@CHRISTDISCIPLES

#ቀን_አስራአምስት ፲፭/15 #ሰኞ
" ገና ደካሞች ሳለን ክርስቶስ ዘመኑ ሲደርስ ስለ ኃጢአተኞች ሞቶአልና።"
(ወደ ሮሜ ሰዎች 5:6)
ክርስቶስ ሞቶልናል፡፡ የኛ ሕይወት የሚመዘነዉ ባለን ሀብት መጠን ፣ በእዉቀታችን ልክ ፣... ሳይሆን በወደደን ደግሞ ኃጢያተኛ ሁነን በሞተልን በጌታችን ፍቅር ነዉ ፡፡
በእርግጥ ክርስቶስ እጅግ በጣም ይወደናል ፡፡ ለዚህም ሞቶልናል !
#መስቀሉን ሳስብ እንበረታለን
#መስቀሉን ሳስብ እኅፅናናለን
#መስቀሉን ሳስብ እንታደሳለን
#መስቀሉን ሳስብ ሀሴት አናደርጋለን
ኢየሱስ ኃጢያተኛ ሁነን ወዶናል ደግሞም ሞቶልናል ፡፡ እንዴት ያለ ፍቅር ነዉ ?!
#መልካም ቀን

#ቀን_አስራስድስት ፲፮/16 #ማክሰኞ
" ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ #ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ #ፍቅር ለማንም የለውም።"
(የዮሐንስ ወንጌል 15:13)
ፍቅር ! ፍቅር ! ፍቅር !
አለም ከተፈጠረች ትልቁ ፍቅር የተገለጠዉ መስቀል ላይ ነዉ ፡፡
ሰዋዊ ፍቅርን
ከ - ፍቅር እስከመቃብር ፣ ከ ሮሚዬና ጁሊየት አልያም ከ ታይታኒክ ፊልም
አይተን ተገርመን ፣ አልቅሰን ፣ ተማርከን ይሆናል ፡፡
ግን በቃ #ትልቁ_ፍቅር የተገለጠዉ በነዚህ ታሪኮች ላይ አይደለም ፡፡
በቃ ትልቁ ፍቅር
....
....
....
.... የተገለጠዉ
.... ከ 2000 አመት በፊት
.... አዳኛችንና ወዳጃችን ኢየሱስ ስለ እኛ ኃጢያት መስቀል ላይ ሞቶ ያሳየን #ፍቅር ነዉ ፡፡
ለእዚህ ፍቅር ምላሻችን ምን ይኾን ?
#መልካም ቀን !

#ቀን_አስራሰባት ፲፯/17 #ረቡዕ
" ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ፤ እኔም አሁን ሕያው ሆኜ አልኖርም ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል፤ አሁንም በሥጋ የምኖርበት ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው።"
(ወደ ገላትያ ሰዎች 2:20)
ክርስቲያን ክርስቲያን የሆነዉ ከክርስቶስ ጋር አብሮ ሲሰቀል ብቻ ነዉ !
ክርስትና መከራ መቀበል ጭምር ነዉ !
ክርስትና ለወንጌል ዋጋ መክፈል ጭምር ነዉ !
አልጋ በአልጋ የሆነ ክርስትና የለም !
ክርስቲያን በመሆናችን ዋጋ እየከፈልን ካልሆነ እራሳችንን እንጠይቅ? ምክንያቱም የምንኖርበት አለም የኃጢያት አለም ስለሆነ ከኛ ሕይወት ጋር የሚቃረንና እንደ ጌታችን ኢየሱስ የሚያሳድደን በመሆኑ ነዉ ፡፡
ክርስቲያን የራሴ የሚለዉ ሕይወት የለዉም ! ምክንያቱም በመስቀል ላይ ከክርስቶስ ጋር ሞቶ የተነሳዉ ክርስቶስን ለብሶ ነዉ ፡፡ ሲነሳ ደግሞ የተነሳዉ ለክርስቶስ ነዉ ፣ የተነሳዉ በክርስቶስ ነዉ ፡፡